No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 13 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ቅድስት ተካ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ የኔነሽ ተካ - ቀረቡ
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የወራሽነት ማስረጃን የሚመለከት ነው። አመልካች በአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታ በሟች ወ/ሮ መሰረት በሪ መጋቢት 7 ቀን 1995 ዓ.ም ኑዛዜ መሰረት የኑዛዜ ወራሽነታቸው ተረጋግጦ ማስረጃ እንዱሰጣቸው ጠይቀዋል። ፍ/ቤቱም ኑዛዜውን በማጽደቅ አመልካች የኑዛዜ ወራሽ መሆናቸውን በማረጋገጥ ውሳኔ ሰጥቷል። ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ተጠሪ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሰረት አመልካች የኑዛዜ ወራሽ ናቸው ተብል የተሰጠው ውሳኔ እንዱሰረዝ መቃወሚያ አቅርበዋል። በመቃወሚያቸውም ኑዛዜው በህጉ የተመለከተውን መስፈርት አያሟላም ሟች ኑዛዜው ያደረጉበት የራሳቸው ባልሆነ ንብረት ላይ ነው የሟች ኑዛዜ ተጠሪን ነቅሎል ንብረቱም በተጠሪ የተሰራ ነው የሚለ ክርክሮችን አንስተዋል። ፍ/ቤቱም ጉዲዩን መርምሮ የተጠሪን መከራከሪያዎች በሙለ ውድቅ በማድረግ ቀደም ሲል የሰጠውን ውሳኔ አጽንቷል። ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ላይ ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ ይግባኙን ሰርዞባቸዋል። በመቀጠልም ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርበው ችልቱ ጉዲዩን መርምሮ የወራሽነት ምስክር ወረቀት እንዱሰጥ ማመልከቻ ሲቀርብ ፍ/ቤቱ ወራሽነትንና የውርስ ሃብቱን ድርሻ በማረጋገጥ ማስረጃ መስጠት ስላለበት በቅድሚያ የውርስ ሃብት ሉጣራ ይገባል።
በመሆኑም የስር ፍ/ቤት የውርስ ሃብት ተጣርቶ ባልቀረበበት ሁኔታ የሰጠው ውሳኔ የህግ ስህተት አለበት በማለት ወራሾች የውርስ ሃብት አጣርተው ሲቀርቡ መሆኑን የማንቀሳቀስ መብታቸው ተጠብቆ ውሳኔውን ሽሮታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። የአመልካች ዋነኛ ቅሬታ በግራ ቀኙ መሃከል ያለው ክርክር ሟች ወ/ሮ መሰረት በሪ ያደጉት ኑዛዜ ሉፀና ይገባል አይገባም? የሚል ሆኖ ሳለ ተከራካሪዎቹ ያላነሱትን ክርክር መሰረት አድርጏ ውሳኔ መስጠቱ የህግ ስህተት ስለሆነ መታረም ይገባዋል የሚል ነው። ይህ ችልትም የግራ ቀኙ ክርክር ኑዛዜው ይሰረዝልኝ የሚል ሆኖ ሳለ በቅድሚያ የውርስ ሃብት እንዱጣራ የተሰጠው ውሳኔ አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል ብሎል። ተጠሪም ቀርበው በፁሁፍ በሰጡት መልስ ፍ/ቤት የሚሰጠው ማስረጃ ወራሽነትን የማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን የሚደርሰው የውርስ ሃብት ድርሻም የሚያረጋግጥ መሆን ስላለበት ህጉ በአግባቡ ተተርጉሟል በማለት ውሳኔው እንዱፀናላቸው ጠይቀዋል። ችልቱም መዝገቡን መርምሯል።
በስር ፍ/ቤት አመልካች የኑዛዜ ወራሽነታቸው ተረጋግጦ የወራሽነት ምስክር ወረቀት እንዱሰጣቸው አመልክተው ፍ/ቤቱ በዚሁ መሰረት አመልካች ኑዛዜ ወራሽ መሆናቸው ተገልጾ ማስረጃ ሰጠቷቸዋል። ተጠሪ ኑዛዜው በህጉ የተመለከተውን የአፃፃፍ መስፈርት ስላላሟላ ሟች ኑዛዜውን ያደረጉት የራሳቸው ሃብት ባልሆነ ንብረት ስለሆነና እንዱሁም ኑዛዜው ተጠሪን የነቀለ በመሆኑ አመልካች የኑዛዜው ወራሽ ሉባለ አይችለም በሚል መቃወሚያ አቅርበዋል። ጉዲዩ በመጀመሪያ የቀረበለት ፍ/ቤት መቃወሚያውን መርምሮ ተጠሪ ያቀረቡት መከራከሪያዎች ተቀባይነት የላቸውም ሲል የቀድሞውን ውሳኔ አጽንቷል። የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ግን የወራሽነት ምስክር ወረቀት የሚሰጠው ወራሽነትን በማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን የወራሹን የውርስ ሃብት ድርሻም በማረጋገጥ ስለሆነ በቅድሚያ የውርስ ሃብት ሉጣራ ይገባል በማለት አመልካች የኑዛዜ ወራሽ ናቸው ተብል የተሰጠውን ውሳኔ ሽሯል።
የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41(1)(ሸ) መሰረት የወራሽነት ምስክር ወረቀት የመስጠት ስልጣን ተሰጥቷቸዋል። በዚህም መሰረት ለአመልካች የኑዛዜ ወራሽነት ማስረጃ ወይም ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል። የተሰጠው የወራሽነት ምስክር ወረቀት እንዱሰረዝ ጥያቄ ሲቀርብም ፍ/ቤቶች በቂ ምክንያት ሲኖር የሰጡትን ምስክር ወረቀት ሉሰርዙ እንደሚችለ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 998(1) ስር የተመለከተ ጉዲይ ነው።
በተያዘው ጉዲይ ከፍ ሲል እንደተመለከተው ተጠሪ ተቃውሞ ያቀረቡት አመልካች የውርስ ተጠቃሚ የሆኑበት ኑዛዜ ህጋዊነት ላይ ነው። በመሆኑም ፍ/ቤቶቹ ሉመረምሩ የሚገባው የአመልካችን የውርሱ ተጠቃሚ ያደረጋቸው ኑዛዜ በህግ ፉት ተቀባይነት ያለው መሆን አለመሆኑን ነው። የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ግን ኑዛዜው በህግ ፉት ተቀባይነት አለው የለውም የሚለውን መመርመር ሲገባው በግራ ቀኙ ክርክር ያልተነሳበትን ነጥብ መሰረት አድርጏ በቅድሚያ የውርስ ማጣራት ሳይደረግ የወራሽነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ላሰጥ አይገባም ብሎል። ይሁን እንጂ ተጠሪ በኑዛዜ ለአመልካች የተሰጠውን ንብረት አመልካች ሉወስደ አይገባም የሚለ ሲሆን በንብረት ክፍፍል ጊዜ ተቃውሞ ከሚያቀርቡ በቀር የውርስ ሃብቱ ባለመጣራቱ ብቻ የአመልካች የኑዛዜ ወራሽነት ሉሰረዝ የሚችልበት ምክንያት አይኖርም። የአዱስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም ኑዛዜው ፈራሽ ላሆን የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት መኖር አለመኖሩን በመመርመር ተገቢውን ውሳኔ መስጠት ሲገባው በግራ ቀኙ ክርክር ያልተነሳውን የውርስ ሃብት ማጣራት ጉዲይ አንስቶ ውሳኔውን መሻሩ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው።
No topics extracted.
የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ መስከረም 22 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
ችልቱ የስር ፍ/ቤቶች የኑዛዜው ህጋዊነት አስመልክቶ የሰጡት ውሳኔ አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር አገናዝቦ በመመርመር ተገቢ ውሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(1) መሰረት ጉዲዩን መልሰናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።