No summary available.
ሰኔ 24 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ኑኑ ሸህሞል - ቀረበ ጠ/ሰለሞን ታደሰ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ አሰገድች ጫኔ - ጠ/መስፍን ጌታቸው ቀረቡ።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ የጀመረው በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ነው። አመልካችና አቶ አለም ባሕታ በሚከራከሩበት ጉዲይ ለክርክር ምክንያት የሆነው ቤት ታግድ እንዱቆይ ትዕዛዝ በመሰጠቱ ተጠሪ እግደ እንዱነሳላቸው አመልክተዋል። በማመልከቻቸውም ከሥር ተከሣሽ ጋር ባልና ሚስት እንዲልሆኑና ተከሣሹ የተጠሪን ፈቃድ ሳያገኙ የቤቱን ካርታ አስይዘው በመበደራቸው ቤቱ የታገደ በመሆኑ እግደ እንዱያነሳላቸው ፍ/ቤቱን ጠይቀዋል። አመልካች ለቀረበው አቤቱታ በሰጡት መልስ ተጠሪና የስር ተከሣሽ እንደ ባልና ሚስት አብረው በሚኖሩበት ጊዜ የተፈራ ንብረት በመሆኑ የጋራ ንብረት ስለሆነ እግደ ሉነሳ አይገባም በማለት ተከራክረዋል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ በሁለቱ መሃከል እንደ ደባልና ሚስት አብሮ የመኖር ሁኔታ ስላለ እና ንብረቱም በግንኙነቱ ውስጥ የተፈራ ስለሆነ እግድ እንዱነሳ የቀረበውን ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል። ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ በተሻሻለው ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 1ዐ6/3/ መሰረት በሁለት ሰዎች መሃከል እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖርን ሁኔታ የሚረጋጠው በግንኙነቱ ውስጥ ያለት ሰዎች ጠያቂነት ብቻ እንጂ በልላ ሶስተኛ ወገን ጥያቄ አይደለም፣ ቤቱን በሥር ተከሣሽ ስም ባለመሆኑና የመያዣ ውለም ስላልተመዘገበ ውለ ፈራሽ ነው በማለት የሥር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር በቤቱ ላይ የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ እንዱነሳ ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ላይ ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ የቀረበውን ይግባኝ ሰርዞታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። አመልካች በቅሬታቸው ከጋብቻ ውጪ እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር ሁኔታ ስለመኖሩ ማስረዲት የሚችል በግንኙቱ ውስጥ ያለት ብቻ ናቸው መባለ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ብለዋል። ችልቱም ይህንኑ ነጥብ ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ተጠሪ ክርክራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል። ችልቱም መዝገቡን እንደሚከተለው መርምሯል።
ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ማመልከቻ ከሥር ተከሣሽ ጋር ከጓደኝነት የዘለለ ግንኙነት የላላቸው መሆኑን ገልፀው ተከሣሹ ያለ እሳቸው ፈቃድ ካርታቸውን አስይዞ በመበደሩ ምክንያት ቤታቸው መታገደ አግባብ አለመሆኑን ተከራክረዋል። አመልካች በበኩላቸው በስር ተከሣሽና በተጠሪ መሃከል እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር ሁኔታ መኖሩን ተከራክረዋል። ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር ሁኔታ ማስረዲት የሚችለት በግንኙቱ ውስጥ ያለት ሰዎች ብቻ ናቸው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። ይሁን እንጂ የተሻሻለው ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 98፣ 99 እና 1ዐ6 በአንድ ወንድና በአንዱት ሴት መሃከል እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር ሁኔታ አለ የሚባለው መቼ እንደሆነና የግንኙነቱ መኖር በምን አይነት መንገድ ማስረዲት እንደሚቻል ከሚያመለክቱ በቀር ግንኙነት ስለመኖሩ ለማስረዲት መጠየቅ የሚችለት በግንኙቱ ውስጥ ያለት ሰዎች ብቻ እንዱሆኑ ገድቦ ያስቀመጠው ነገር የለም። በአንቀጽ 1ዐ6/3/ ግንኙነት መኖሩን “አንደኛው ወገን ለማስረዲት የቻለ እንደሆነ” በማለት የተቀመጠው በግንኙቱ ውስጥ ያለት ሰዎች መሃከል የሚነሳውን ክርክር ታሳቢ በማድረግ እንጂ ላላ 3ኛ ወገን ግንኙነቱን ማስረዲት እንዲይችል ለመከልከል አይደለም። በመሆኑም የግንኙነቱ መኖር አለመኖር በሶስተኛ ወገኖች መብት ላይ የሚያስከትለው ውጤት ካለ ይኸው ሶስተኛ ወገን ግንኙነቱን ከማስረዲት የሚከለክለው የሕግ መሰረት ስለላለ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት መኖሩን ማስረዲት የሚችለት በግንኙነቱ ውስጥ ያለት ሰዎች ብቻ ናቸው በማለት የደረሰበት መደምደሚያ የሕግ ስህተት ያለበት ነው።
በልላ በኩል ግን በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ ማመልከቻ ያቀረቡት ንብረቴ ነው በሚለት ቤት ላይ የተሰጠው እግድ እንዱነሳቸው ነው። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 158 መሰረት በተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ቅሬታ የተሰማው ወይም ያለአግባብ ነው የሚለው ወገን ለፍ/ቤት ጥያቄ ሲያቀርብ ፍ/ቤቱ በቂ ምክንያት መኖሩን ያመነ ከሆነ የሰጠውን የእግድ ትዕዛዝ ማሻሻል፣ ማንሣት ወይም ጨርሶ መሰረዝ ይችላል። ተጠሪ እግደ ይነሳልኝ የሚለት ቤቱ የግል ንብረቴ ነው በማለት ነው። አመልካች በበኩላቸው በተጠሪና በሥር ከሣሸ መሃከል እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር ሁኔታ ያለና ንብረቱም የተፈራው በዚህ ግንኙነት ውስጥ በመሆኑ የተጠሪ ጥያቄ ውድቅ እንዱሆን አመልክተዋል። ፍ/ቤቱም በዚህ ጉዲይ በዋናነት ሉያስተናግድ የሚገባው የእግድ ትዕዛዝ ሉነሳ ይገባል? አይገባም?
የሚለው ቢሆንም ከዚህ አልፍ በተጠሪና በሥር ተከሣሽ መሃከል በሕግ የታወቀ ግንኙነት መኖር አለመኖሩ እንዱሁም የንብረቱን ባለቤት አስመልክቶ ውሣኔ አሳርፎል። ከመዝገቡም መረዲት እንደሚቻለው እነዚህ ጉዲዮች በዋና ጭብጥነት ተይዘው በመደበኛ የሙግት ስርዓት ተገቢው ክርክርና ማስረጃ ቀርቦባቸው የተወሰኑ አይደለም።
የተሰሙት ምስክሮች የሰጡት ምስክርነትም ቢሆን የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 1ዐ6 የሚያስቀምጠውን ሁኔታ የሚያሟላ መሆን አለመሆኑ ሳይመዝን እንዱሁም ቤቱ የተሰራው መቼ እንደሆነ ሳይረጋገጥ የተሰጠው ውሣኔ የተጠሪን መብት በእጅጉ የሚጎዲ መሆኑን መረዲት ችለናል። ፍ/ቤቱ እግድ የተሰጠበት ንብረት የተጠሪ የግል ንብረት ለመሆኑ በቂ ማስረጃ ያልቀረበለት ከሆነ የተጠሪን የእግድ ይነሳልኝ ጥያቄ ውድቅ ማድረግ እንጂ በጭፍጫፉ ጉዲይ መደበኛ ክርክርና ማስረጃ ሳይቀርብና ጉዲዩ በአግባቡ ሳይመረመር ተጠሪ ከሥር ተከሣሽ ጋር ያላቸውን ግንኙነትና የንብረት ባለቤትነት መብት በማረጋገጥ የሰጠው ውሣኔ የሙግት ስርዓትን ያልተከተለና ስነ ሥርዓታዊ ግድፈት የተፈፀመበት ነው። በልላ በኩል ግን ምንም እንኳን ተጠሪ በንብረቱ ላይ ያላቸውን መብት በልላ መንገድ የማረጋገጥ መብታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በሥር ፍ/ቤት ዕግድ የተሰጠበት ንብረት የተጠሪ የግል ሃብት መሆን አለመሆኑ በበቂ ሁኔታ ስላልተረጋገጠ በንብረቱ ላይ የተሰጠው እግድ እንዲይነሳ የሥር ፍ/ቤት የሰጠው ትእዛዝ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም ተከታዩ ውሣኔ ተሰጥቷል።
ው ሣ ኔ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 69894 ታህሣሥ 25 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ እና የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ መጋቢት 25 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. ዐ8135 ሐምል 7 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በሰጠው ብይን በተጠሪና በሥር ተከሣሽ መሃከል እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር ሁኔታ አለ እንዱሁም የእግድ ትዕዛዝ የተሰጠበት ቤት በዚህ ግንኙት መሃል የተፈራ ነው በማለት የሰጠው ትችት ውድቅ ተደርጓል። የእግድ ትዕዛዙ ሉነሳ አይገባም ሲል የሰጠውን ብይን ግን ፀንቷል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ነ/ዓ
ሐምል 02 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፣ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች፣ ወ/ሮ ደጅይጥኑ አለማየሁ - ቀረቡተጠሪ፣ ወ/ሮ አዛለች ደበብ - ጠበቃ ደርበው ተመስገን ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር የጋብቻ ማስረጃን መስጠት በመቃወም የተጀመረ ነው። የጉዲዩ አጀማመር ለተጠሪ የተሰጠ የጋብቻ ማስረጃ አለአግባብ ነው፤ ሉሰረዝ ይገባል በማለት አመልካች መቃወሚያ በማቅረባቸው የአ/አ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቀደም ሲል ለተጠሪ የሰጠው ማስረጃ በመሰረዝ ውሣኔ ሰጥቷል። በዚህ ቅር በመሰኘት ተጠሪ ለአ/አ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራቀኙን ካከራከረ በኃላ አመልካች ያቀረቡት መቃወሚያ በተጠሪ እና በሟች መካከል ጋብቻ መኖሩን አምነው ጋብቻው ፈርሷል የሚል መከራከሪያ ያቀረቡ ስለሆነ ጋብቻው ፈርሷል? አልፈረሰም? የሚለውን ማጣራት ይገባው ነበር ካለ በኃላ በዚህ ምክንያት የሥር ፍ/ቤት ውሣኔን ሸሯል። አመልካች ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ ያቀረቡት በዚሁ ላይ ሲሆን ይዘቱም በተጠሪ እና በሟች ጫኔ በዛብህ መካከል ጋብቻ አልነበረም አለ ከተባለም በሕይወት እያለ ተፊትተው የተለያዩ በመሆኑ ይህ ሳይጣራ የተሰጠው ውሣኔ አለአግባብ ነው ሲለ እንዱሻር ጠይቀዋል። ይህ ሰበር ሰሚ ችልትም ጉዲዩን መርምሮ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ጋብቻ ፈርሷል ወይስ አልፈረሰም? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ በራሱ ሳያጣራ ወይም በሥር ፍ/ቤት ተጣርቶ እንዱወሰን ሳያደርግ በደፈናው የሰጠው ውሣኔ በአግባቡ ስለመሆኑ ለመመርመር ተጠሪን አስቀርቧል የተጠሪ ጠበቃ ሚያዚያ 18 ቀን 2002 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል በይዘቱም የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለውም ተብል እንዱፀና ያመለከቱበት ነው።
እኛም የክርክሩን አመጣጥ አስመልክቶ በዚህ ሰበር ችልት እንዱመረመረ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ጉዲዩን መርምረናል። ከሥር መዝገብ መረዲት የተቻለው አመልካች ለተጠሪ የተሰጠው የጋብቻ ማስረጃ እንዱሰረዝ አቤቱታ ሲያቀርቡ በተጠሪ እና በሟች መካከል የነበረው ጋብቻ ቀድሞ ፈርሷል በሚል መነሻ ምክንያት ነው።
የሥር ፍ/ቤት በሟች እና በተጠሪ መካከል ጋብቻ ነበር ወይስ አልነበረም? ጋብቻ ነበር ከተባለ ቀድሞ በፍቺ የፈረሰ ወይንስ በሟች ሞት ምክንያት? የሚለት ነጥቦች በአግባቡ ሳያጣራ የተወሰነ መሆኑን ከመዝገቡ ተረድተናል የአ/አ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤትም በውሣኔው በግልፅ እንዲመለከተው በተጠሪ እና በሟች መካከል የነበረው ጋብቻ ፈርሷል? ወይስ አልፈረሰም? የሚለው ነጥብ ያልተጣራ መሆኑ ሲረዲ ይህ ነጥብ እንዱጣራ ማድረግ አሉያም ሥር ፍ/ቤት ጉዲዩ እንዱጣራ ማድረግ ይገባው ነበር ይህ ሳይጣራ በደፈናው የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ በመሻር ብቻ ጉዲዩ የመጨረሻ እልባት አግኝቷል ለማለት አያስችልም ምክንያቱም የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ በተመለከተ በግልፅ በመቀበል ወይም ባለመቀበል የተሰጠ ውሣኔ ባለመኖሩ ነው። ስለሆነም የአ/አ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ የሙግት አመራር እና ጭብጥ አያያዝ ስህተት ያለው መሆኑን ከተረዲ ማረም ሲገባው ማለፈ እና የአመልካችን ጥያቄ ግልፅ ዲኝነት ያልሰጠበት ከመሆኑም አንፃር በክርክሩ አመራር ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን ተገንዝበናል። የአ/አ ከተማ ፍርድ ቤቶች ሰበር ችልትም ይህንን ማረም ሲገባው ማለፈ ተገቢ አይደለም።
ስለሆነም ይኸው ሉታረም ይገባል ብለናል። ስለዚህም ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የአ/አ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዲ ምድብ በመ/ቁ 1234/99 በ3/01/02 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ እና የአ/አ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ/ በ9/03/02 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ እና የአ.አ ከተማ ፍ/ቤቶች ሰበር ችልት በመ/ የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በሟች እና በተጠሪ መካከል ጋብቻ ነበር በአመልካች ስላልተካደ፤ ጋብቻ ነበር ከተባለስ ጋብቻው በፍቺ ፈርሷል? አልፈረሰም? የሚለው የአመልካች መቃወሚያ ነጥቦች ላይ ግራቀኙን አከራክሮ የመሰለውን ውሣኔ እንዱሰጥ ብለን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 343/1/ መሰረት መዝገቡን ለአ/አ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዲ ምድብ እንዱመለስ አዝዘናል። ይፃፍ።
የዚህ ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ። መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
ም.አ
ሐምል 8 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፣ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች፣ እንዲልካቸው ዘለቀ ጠ/ቴዎድሮስ ተስፊዬ ቀረቡተጠሪ፣ ወ/ሮ ብዙዓለም መንግሥቱ ጠ/ዩሴፍ ደስታ ቀረቡ
በዚህ መዝገብ የቀረበው የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ነው። በአመልካች እና በተጠሪ መሃከል የነበረው ጋብቻ ከፈረሰ በኃላ ተጠሪ የጋራ ንብረት ለመካፈል የንብረት ዝርዝር አቅርበዋል። ባቀረቡት የንብረት ዝርዝር ውስጥም ለክርክር ምክንያት ሆነው ቤት የጋራ በመሆኑ አመልካች እንዱያካፍሎቸው ጠይቀዋል።
አመልካች በበኩላቸው የኮንድሚኒየም ቤት እጣ የተመዘገቡት ከጋብቻ በፉት መሆኑንና ሐምል 4 ቀን 1999 ዓ.ም ከአ/አ ከተማ አስተዲደር የኮ/ቀ/ክ/ከ/ የቤት ማስተላለፉያ ጽ/ቤት ጋር የቤት ሽያጭ ውል የፈረሙ አመልካች ብቻ እንጂ ተጠሪ አለመፈረማቸውን ገንዘቡንም አመልካች ከመ/ቤት ካገኙት ብድር እና ወደፉትም ከደሞዛቸው የሚከፈል በመሆኑ ቤቱ አመልካች የግል ንብረት ልባል እንደማይችል ተከራክረዋል። ፍ/ቤቱም የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ግራቀኙ ጋብቻ የመሰረቱት ሚያዚያ 22 ቀን 1998 ዓ.ም ሲሆን ፍቺ የተፈፀመው መስከረም 30 ቀን 2000 ዓ.ም ነው አከሪካሪ የሆነው ኮንድሚኒየም ቤት እጣ የወጣውና ሽያጭ ውለ ከአ/አ መስተዲድር ጋር የተፈረመው በጋብቻ ወቅት ሐምል 4 ቀን 1999 ዓ.ም በመሆኑ ቤቱ የጋራ ንብረት ነው በሚል ከተቻለ በአይነት ካልተቻለ በሃራጅ ተሽጦ እንዱካፈለ ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ላይ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው የይግባኝ ቅሬታቸው ተሰርዞባቸዋል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። አመልካች በቅሬታቸው የኮንድሚኒየም ቤት ምዝገባ የተከናወነው ከጋብቻ በፉት በመሆኑ የቤቱ ግዥ የተፈፀመው አመልካች ከአ/አበባ መስተዲድር የኮ/ቀ/ክ/ከ የቤት ማስተዲደር መምሪያ ጋር በፈረሙት ውል መሆኑ የቅድሚያ ክፍያ የተከፈለው ከአመልካች ደሞዝ በተወሰደ ብድር መሆኑ ለቀሪው ክፍያ ከባንክ ጋር የብድር ውል የፈረሙት አመልካች ብቻ በመሆናቸው እንዱሁም የቤቱ ርክክብ በጋብቻ ጊዜም ሆነ በፍቺ ወቅት ያልተፈፀመ በመሆኑ ቤቱ የአመልካች የግል ሃብት ነው በማለት ስር ፍ/ቤት ቤቱን አስመልክቶ የሰጠው ውሣኔ እንዱሻርላቸው ጠይቀዋል።
ይህ የሰበር ችልትም ምንም እንኳን የኮንደሚኒየሙ እጣ በጋብቻ ወቅት የወጣ ቢሆንም አመልካች ምዝገባ ያደረጉት ከጋብቻ በፉት መሆኑና ከባንክ የተወሰደው ብድር ጋብቻው ከፈረሰ በኃላ ከአመልካች የሚከፈል ከመሆኑ አንፃር ተጠሪ ያላቸው መብት ምንድነው? የሚለውን ነጥብ ለመመርመር ሲባል አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባለ ብሎል። በዚህም መሰረት ግራቀኙ ቀርበው የቃል ክርክራቸው ተሰምቷል። ችልቱም መዝገቡን መርምሯል።
በዚህ መዝገብ አከራካሪ የሆነው ጉዲይ ለክርክር ምክንያት የሆነው ቤት የግራቀኙ የጋራ ንብረት ነው ወይስ የአመልካች የግል ንብረት ነው የሚለው ነው ስለ ባልና ሚስት የጋራ ንብረት የሚደነግገው የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 62 በንዐስ ቁጥር ሁለት ስር በጋብቻ ወቅት በግብይት የተገኙ ንብረቶች የጋራ ንብረቶች እንደሆኑ ተመልክቷል በተያዘው ጉዲይ አከራካሪውን ቤት አመልካች የተመዘገቡት ከጋብቻ በፉት ስለመሆኑና ዕጣው የደረሰው ግን የሁለቱ ጋብቻ ፀንቶ በነበረበት ወቅት ስለመሆኑ ክርክር አላስነሳም ይህም ብቻ ሳይሆን አመልካች ከአ/አበባ አስተዲደር የቤት ማስተዲደር መምሪያ ጋር የቤቱን የሽያጭ ውል ያደረጉት ከተጠሪ ጋር በጋብቻ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ነው። አመልካች ለኮንድሚንየሙ ቤት የተመዘገቡት ከጋብቻ በፉት ቢሆንም የቤቱ ባለቤት የሚያደርጋቸውን የሽያጭ ውል ያደረጉት ግን በጋብቻ ወቅት በመሆኑ ቤቱ በግብይት ተገኘ ልባል የሚችለው የሁለቱ ጋብቻ ፀንቶ ባለበት ወቅት ነው አመልካች ውለን ለብቻቸው መፈረማቸው ብቻውን ቤቱን የግል ንብረታቸው አያደርገውም የሽያጩን ውል ለብቻቸው ማድረጋቸው ቀርቶ በጋብቻ ወቅት የተገኘው ቤት በስማቸው መመዝገቡ እንኳን ንብረቱን የግል ንብረት እንደማያደርገው የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 63/1/ ያመለክታል። በመሆኑም የሽያጩን ውል አመልካች ብቻ መፈረማቸው ቤቱ የአመልካች የግል ንብረት ነው አያሰኘውም ላላው አመልካች ቤቱ የግል ላሆን ይገባል በማለት የሚከራከሩት ለቤቱ የቅድሚያ ክፍያ የተከፈለው ከአመልካች ደመወዝ በብደር የተገኘ ገንዘብ መሆኑ እንዱሁም ቀሪውን ዕዲ ለመክፈል አመልካች ለብቻቸው ከባንክ ብድር መውሰዲቸውን ነው ይሁን እንጂ አመልካች ለቤቱ ግዥ ከደሞዛቸውም ሆነ ከባንክ ለወሰደት ብድር ተጠሪም የጋራ ባለእዲ ከሚሆኑ በቀር ንብረቱን የአመልካች የግል ንብረት አያደርገውም በአጠቃላይ ምንም እንኳን አመልካች ለቤቱ የተመዘገቡት ከጋብቻ በፉት ቢሆንም እጣው የወጣው በጋብቻ ጊዜ ስለመሆኑና የቤቱ ባለቤት የሚያደርጋቸው የሽያጭ ውልም የተፈረመው በጋብቻ ውስጥ በመሆኑ ቤቱ የግል ነው መባለ ከተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 62/2/ አኳያ ሲታይ ተገቢ በመሆኑ ቤቱን ከተቻለ በአይነት እንዱካፈለ ካልተቻለ አንፊ ለላላኛው የቤቱን ግምት ከፍል እንዱያስቀር በዚህም ካልተስማሙ ቤቱ በሃራጅ ተሽጦ የሚገኘውን ገንዘብ ግራቀኙ እንዱካፈለ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ማለት አይቻልም።
በልላ በኩል ግን ግራቀኙ ክርክር የቤቱን ዋጋ ለመክፈል ብድር ስለመወሰደና ወደፉትም የቤቱ ቀሪ እዲ መከፈል ያለበት መሆኑን መረዲት ችለናል ተጠሪ የቤቱ የጋራ ባለሃብት ናቸው የተባለ በመሆኑ ቤቱ ለተገዛበት የብድር ገንዘብ እንዱሁም ቀሪ ክፍያም ካለ የጋራ ባለእዲ ሉሆኑ ይገባል በመሆኑም ለቤቱ መግዣ አመልካች ከደሞዛቸውም ሆነ ከባንክ ለወሰደት እዲ እንዱሁም የቤቱ ቀሪ ክፍያ ካለም ግራቀኙ ለእዲው በጋራ ሃላፉ ሉሆኑ ስለሚገባ የስር ፍ/ቤት ይህን በተመለከተ ሳይወሰን ማለፈ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው ብለናል።
ው ሣ ኔ
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ የካቲት 29 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ የሰጠው ትዕዛዝ ተሻሽሎል።
አከራካሪው የኮንደሚኒየም ቤት የባልና ሚስቱ የጋራ ንብረት ነው ተብል እንዱካፈለ መወሰኑ ተገቢ ቢሆንም ቤቱን ለመግዛት አመልካች የወሰደት ብድር እና እንዱሁም ከቤቱ ለሚፈለገው ቀሪ እዲ አመልካችና ተጠሪ በጋራ ባለእዲ ናቸው ብለናል። በመሆኑንም የሚፈለገውን እዲ ግማሽ ተጠሪ ሉከፍለ ይገባል ብለናል፣፣
ወጨና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.