No summary available.
ሰኔ 08 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ትዕግስት ግርማ የእነ አቤል ወርቁ ሞግዚት - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ኤፍሬም መንግስቱ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የኑዛዜ ወራሽነት ይረጋገጥልኝን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክር የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ነው። የተጠሪ የስር አቤቱታ ይዘት ሲታይም መስከረም 14 ቀን 1997 ዓ.ም በተፃፈ ሆኖ ሟች ወ/ሮ ውዳ ሙለጌታ መስከረም 18 ቀን 1995 ዓ.ም ኑዛዜ ለምዕራፍ ሰለሞን ያደረጉት ስለሆነ ልጅቱ የሟች ኑዛዜ ወራሽ መሆኗና የእኔም ሞግዚትነት ተረጋግጦ ማስረጃ እንዱሰጠኝ የሚል ነው። ምስክሮቻቸውን አቅርበውም እንደአቤቱታቸው ይዘት አስመስክረዋል። ከዚህም በኋላ የአሁኗ አመልካች በተቃዋሚነት ቀርበው ሟች ወ/ሮ ውዳ ሙለጌታ የአሁኗ አመልካች ሞግዚት የሆኑላቸው እናት መሆናቸውን አድርገውታል የተባለው ኑዛዜም ሟች ማንበብና መፃፍ የሚችለ በብዕር መፈረም የሚችለ ሆነው እያለ በጣት የተፈረመ መሆኑ ሐሰተኛ መሆኑን እንደሚያሳይ በኑዛዜው ላይ ያለው ፊርማ የሟች አለመሆኑን ሟች በጣም ታመው መናገርና መንቀሳቀስ የማይችለ በመሆኑ ከመሞታቸው አንድ ቀን በፉት አድርገውታል የተባለው ኑዛዜ የሟች ላሆን እንደማይችል ኑዛዜው በሕጉ መሰረት ስለመነበቡም የሚገልፀው ነገር ስለላለ መሆኑን ገልፀው ኑዛዜ ፈራሽ ነው በማለት ተከራክረዋል። የስር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ በመመርመር በኑዛዜው ላይ ያለው ፊርማ የሟች መሆኑን የማስረዲት ግዳታ ያለባቸው ተጠሪ ሲሆኑ ሟች በጣታቸው የፈረሟቸውን ላልች ተመሳሳይ ፊርማዎችን አቅርበው በባለሙያ ሉረጋገጥ አልተቻለም በተጨማሪም ሟች በብዕር ይፈርሙ እንደነበርና ኑዛዜውንም ያደረጉት ከመመታቸው በፉት አንድ ቀን ሲቀራቸው ነው የሚለትን ምክንያትቶችን በመያዝ ኑዛዜው ሟች ያደረጉት ነው ለማለት አሰቸጋሪ ነው ብል ኑዛዜው ውድቅ ነው ሲል ወስኗል። ከዚህም በኋላ የአሁኑ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ኑዛዜው ትክክል አይደለም የሚለው ወገን ይህንኑ ማስረዲት ግዳታ አለበት የአሁኗ አመልካች ግን ይህንኑ አልተወጡም የሚል ምክንያት በመያዝ የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ሙለ በሙለ ሽሮ ኑዛዜው ህጋዊ ነው በማለት ወስኗል። ከዚህም በኋላ አመልካች የሰበር አቤቱታቸውን ለከተማው ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ በድምጽ ብልጫ ፀንቷል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች የካቲት 22 ቀን 2002ዓ.ም በፃፈት ሶስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ በኑዛዜው ላይ የሰፈረው ፊርማ የሟች ስለመሆኑ የማስረዲት ሸክም የኑዛዜው ተጠቃሚ የሆነ ሰው ሆኖ እያለ ይህው ታልፍ ኑዛዜው ሕጋዊ ነው ተብል መወሰኑ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም አከራካሪው የጣት አሻራ የሟች /የተናዛዥ/ መሆኑን በተመለከተ የማስረዲት ሽክሙ ላይ ያለውን ክርክር ለማየት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎ ተጠሪ ቀርበው ሰኔ 07 ቀን 2002ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገጽ ማመልከቻ የአመልካችን የሰበር አቤቱታ በመንቀፍና በጉዲዩ ላይ የተሰጠውን ውሳኔ ተገቢነት በመግለጽ ተከራክረዋል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ሟች ማንበብና መፃፍ የሚችለ ቢሆንም በኑዛዜው ላይ የጣት ፊርማ ማስቀመጣቸውን ነው።
በመሰረቱ የኑዛዜውን ቃልና ይዘት አስመልክቶ ማን ማስረዲት እንዲለበትና ምን አይነት ማስረጃዎች ማቅረብ እንደሚገባው በውርስ ሕግ ውስጥ ልዩ ድንጋጌዎች ተቀምጠው እናገኛለን። በዚህም መሰረት አንድ የኑዛዜ ተጠቃሚ የሆነ ሰው ሟች በሕይወት ዘመኑ ለእሱ ጥቅም ያደረገው ኑዛዜ መኖሩንና የኑዛዜው ቃልና ይዘትምን እንደሆነ የማስረዲት ሽክም ያለበት መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 896 በግልጽ ያሳያል ይህ ድንጋጌ በግልጽ የሚያሳየው በኑዛዜው ሰነድ ላይ የሰፈረው ቃል እና ኑዛዜ መኖሩን ማስረዲት ያለበት የኑዛዜው ተጠቃሚ ነኝ የሚለው ሰው መሆኑን ነው። በመሆኑም የሟች የኑዛዜ ወራሽ እና ተጠቃሚ ነኝ የሚል ሰው ሟች በህግ ፉት ውጤት ያለውን ኑዛዜ የፈፀመ መሆኑን የኑዛዜውን ቃልና ይዘት እንደዚሁም እሱ እራሱ በሟች ኑዛዜ መሰረት ተጠቃሚ መሆኑን የማስረዲት ሸክም አለበት። ህጉ ለምን አይነት ኑዛዜ ምን አይነት ማስረጃ መቅረብ እንዲለበትም በግልጽ ማስቀመጡ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 897 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ያሳያለ።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች ሞግዚት የሆኑላቸው ልጆች የሟች ወራሾች ሲሆኑ ተጠሪ ሞግዚት ለሆኑላት ልጅ የተደረገው ኑዛዜ የተቃወሙት ሟች በብዕር የሚፈርሙ እንጂ በጣት አሻራ የሚፈርሙ አይደለም በማለት ነው። የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ተጠሪ ሞግዚት የሆኑላት ልጅ የኑዛዜው ተጠቃሚና የኑዛዜው ወራሽ ነኝ የምትል በመሆኑ ሟች የጣት አሻራ በላልች ጉዲዩች ይፈርሙ የነበረ ስለመሆኑ እንዱያስረደ ትዕዛዝ ሰጥቶ ይህንኑ ሉፈጽሙ ባለመቻላቸው ኑዛዜው አይፀናም ሲል ወስኗል። ተጠሪ በዚህ ችልት በሰጡት መልስም የጣት አሻራው የተፈረመው በአራት ሽማግላዎች ፉት ስለመሆኑ ተረጋግጧል። የጣት አሻራው የሟች ስለመሆኑ የማስረዲት ሸክም የአመልካች ነው ከሚለ በስተቀር ሟች በላልች ጉዲዮች በጣት አሻራ ይፈርሙ የነበረ መሆኑን ወይም ማንበብና መፃፍ የሚችለ ሆነው እያለ በጣት አሻራ ሉፈርሙ የቻለበትን አሳማኝ ምክንያት በስር ፍ/ቤት ያረጋገጡ መሆኑን ገልፀው አልተከራከሩም። አመልካች በስር ፍ/ቤት ባቀረቧቸው ማስረጃዎች ሟች በብዕር ሲፈርሙ የነበሩ ማንበብና መፃፍ ይችለ የነበሩ መሆኑን በሚገባ ያስረደ ስለመሆኑ የበታች ፍ/ቤቶች የውሳኔ ግልባጭ በግልጽ ያሳያል። እንግዱህ አመልካች ሟች በብዕር መፈረም ይችለ የነበሩ መሆኑን ከማስረዲት እና በኑዛዜው ሰነድ ላይ የሰፈረው የጣት አሻራ የሟች አይደለም በማለት መከራከር ብቻ በቂ ሲሆን ይህንኑ የማስተባበል ግዳታ ያለባቸው የኑዛዜው ተጠቃሚ የሆኑት ተጠሪ ሞግዚት የሆኑላት ልጅ ነች።
ተጠሪ ደግሞ የኑዛዜ ተጠቃሚ የሆኑትን ልጅ ወክለው ባቀረቡት ክርክር በኑዛዜው ሰነድ ላይ ያለውን የጣት ፊርማ የሟች ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 896 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ በሚያስገነዝበው ሁኔታ አላስረደም።
በመሆኑም የስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሻረውም ሆነ የከተማው ሰበር ሰሚ ችልት በአብላጫ ድምጽ ያፀናው ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 896 ድንጋጌ መንፈስ ውጭ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተዋል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በመ/ ሰጥቶ በከተማው ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ጥር 07 ቀን 2002ዓ.ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 350/97 ጥቅምት 08 ቀን 1999ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ሰበር ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.