No summary available.
ሚያዝያ 22 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ኂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ታፈሰ ይርጋ አብደራሂም አህመድ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡-
በዚህ መዝገብ የቀረበው የጉዱፈቻ ውል ይፍረስልኝ ጥያቄን የሚመለከት ጉዲይ ነው። አመልካቾች ለፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታ በጉዱፈቻ የተወሰደው ልጅ ከውሳኔ በኋላ ሲመረመር የአእምሮ እድገት ዝግመት ያለበት መሆኑ ስለተረጋገጠ የጉዱፈቻ አድራጊዎቹ በዚህ ምክንያት ልጁን ሉቀበለ ስላልቻለ ውሳኔው ይሰረዝልን ሲለ ጠይቀዋል። ፍ/ቤቱም ጉዲዩን አይቶ የጉዱፈቻ ውል በመርህ ደረጃ ሉፈርስ እንደማይችል በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 195/1/ ስር የተቀመጠ ሲሆን በንኡስ አንቀጽ 2 ስር ደግሞ የጉዱፈቻ ውል ሉፈርስ የሚችልበት ልዩ ሁኔታ መስፈሩን፣በዚህ መሰረት ውለ ሉፈርስ የሚችለው የጉዱፈቻ ውል ተቀባዩ የጉዱፈቻ ልጅን እንደልጁ በማሳደግ ፊንታ የልጁን የወደፉት ህይወት በሚጏዲ አኳኋን ሲይዘው እንደሆነ፣በተያዘው ጉዲይ ግን ውል እንዱፈረስ የቀረበው ምክንያት ውለን ለማፍረስ የሚያስችል አለመሆኑን ተችቶ ጥያቄውን ውድቅ አድርጏታል። በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካቾች ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ ይግባኙን ሰርዞ መዝገቡን ዘግቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካቾች በቅሬታቸው ጉዱፈቻ የተደረገው ልጅ በሽታ ያለበት መሆኑ የተረጋገጠው ስምምነቱ ከፀደቀ በኋላ ስለሆነና ጉዱፈቻ አድራጊዎቹ የዚህ አይነት ችግር መኖሩን ቢያውቁ ህፃኑን መረከብ እንደማይችለ፣ልጁን እንዱረከቡ ቢገደደ የልጁን ጤንነት የሚጠይቀውን ወጪ ለማውጣት አቅማቸው የማይፈቅድ በመሆኑ የልጁ የወደፉት ህይወት ባያላው የሚጏዲ መሆኑን ገልፀው የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ የቤተሰብ ሕጉን አንቀጽ 195/2/ በአግባቡ ያላገናዘቡ ስለሆነ ውለ እንዱፈርስ እንዱወሰንላቸው ጠይቀዋል። ይህ ሰበር ችልትም የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 36/1/ ስር ከተደነገገው የህፃናትን ጥቅም ማስጠበቅ (best interest of the child) መርህ አኳያ ተገቢነቱን ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ አድርጓል። መዝገቡንም እንደሚከተለው መርምሯል።
በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 195/1/ በመርህ ደረጃ የጉዱፈቻ ውል ሉፈርስ እንደማይችል ያስቀምጥና በንኡስ ቁጥር 2 ስር ደግሞ ውለ ሉፈርስ የሚችልባቸውን ልዩ ሁኔታዎች ይደነግጋል። በዚህ መሰረት ውለ እንዱፈርስ የሚደረገው ጉዲፈቻ አድራጊው በጉዱፈቻ የተቀበለውን ልጅ እንደ ልጁ በማሳደግ ፊንታ በባርነት ወይም ባርነት በሚመስል ሁኔታ ወይም ከግብረ-ገብ ውጪ በሆኑ ተግባሮች እንዱሰማሩ በማድረግ መጠቀሚያ ያደረገው እንደሆነ ወይም በማናቸውም ላላ መንገድ የልጁን የወደፉት ሕይወት ክፈኛ በሚጏዲ አኳኋን የያዘው መሆኑን የተረዲን እንደሆነ ነው። በመሆኑም ውለ በተለይ “በማንኛውም ላላ መንገድ የልጁን የወደፉት ሕይወት ክፈኛ በሚጏዲው አኳኋን የያዘው” የሚለው ትርጉም የሚያስፈልገው ሲሆን ይህ ችልት ድንጋጌው እንዳት መተርጏም እንዲለበት በመ/ቁ. 44101 ትርጉም ሰጥቶበታል። በዚህም መሰረትም ይህ ድንጋጌ የተቀመጠውም ጉዱፈቻ አድራጊው ልጅን በዓለም አቀፍ የሕፃናት እና ሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን በሚፃረርና የልጁን ጥቅምና ደህንነት በሚጏዲ አኳኋን መያዙን ማረጋገጥ የሚያስችለ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ የጉዱፈቻ ውለ እንዱቀጥል ማድረጉ የሚያስገኘው ፊይዲ ባለመኖሩ ጉዲዩ በሚመለከተው ማንኛውም አመልካች ጠያቂነት መሰረዝ እንዱችል ታምኖበት መሆኑን የተሻሻው የቤተሰብ ሕግ ሃተታዘምክንያት ማመልከቱን፣ጉዱፈቻ እንዱደረግና የሕግ ጥበቃ እንዱደረግለት ያስፈለገው በዋናነት የሕፃኑን ጥቅም ለመጠበቅ ሲባል እንደሆነ፣የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ-መንግስትም ሆነ ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው አለም ዓቀፍ ስምምነቶች ህፃናትን የሚመለከቱ ጉዲዮች ለሕፃናት ጥቅም ደህንነት (best interest of the child) ቅድሚያ መስጠት አስፈላጊ መሆኑ በመርህ ደረጃ ማስቀመጣቸውን፣በሕገመንግስቱ አንቀጽ 36/5/ ስር መንግስት ለእጓለማውታን ልዩ ጥበቃ እንደሚያደርግላቸው፣በጉዱፈቻ የሚያድጉበትን ስርአት የሚያመቻቹና የሚያስፊፈ እንዱሁም ደህንነታቸውንና ትምህርታቸውን የሚያራምደ ተቋማች እንዱመሰረቱ እንደሚያበረታታ መደንገጉን፣ከፍ ሲል የተመለቱት ድንጋጌዎች ሁለ የጉዱፈቻ ጉዲይ በጥንቃቄ መታየት ያለበት መሆኑንና በድንጋጌ አተረጓጏም ላይ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ፣በዚህም መሰረት የጉዱፈቻ ስምምነት እንዱሰረዝ ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው በልጁ አኗኗርና አያያዝ እንዱሁም ወደፉት ሕይወቱ ላይ በተጨባጭ የደረሰ ጉዲት በመኖሩ ብቻ ሳይሆን ወደፉት ሉደርስ የሚችል ጉዲት ስለመኖሩም ማርጋገጥ ሲቻል እንደሆነ የሕግ ትርጉም ተሰጥቶበታል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካቾች የጉዱፈቻ ስምምነቱ እንዱሰረዝ ጥያቄ ያቀረቡት ስምምነቱ ከተደረገና በፍ/ቤት ከፀደቀ በኋላ ልጁ ሲመረመር የአእምሮ እድገት ዝግመት ያለበት መሆኑ በሃኪም በመረጋገጡ ነው። አመልካቾች በአቤቱታቸው በጉዱፈቻ ለመቀበል የሚችለት ጤነኛ ልጅ መሆኑና በጉዱፈቻ የተቀበለት ልጅ ካለበት የጤና ችግር አኳያ ለአስተዲደጉና ለጤንነቱ የሚያስፈልጉ ተጨማሪ ወጪዎችን ለመሸፈን የገንዘብ አቅም የላላቸው መሆኑን ገልፀዋል። ከዚህም የአመልካቾች አቤቱታ መረዲት የሚቻለው ጉዱፈቻ አድራጊዎቹ በጉዱፈቻ የተቀበለት ልጅ ካለበት የአእምሮ ዝግመት ችግር አኳያ ልዩ እንክብካቤ እና አያያዝ እንዱሁም ክትትል የሚያስፈልገው ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ የጉዱፈቻ አድራጊዎቹ አቅም ያላቸው ለመሆኑና ወጪውንም ለማውጣት ፈቅደው ስምምነቱን ያደረጉ መሆኑ አልተረጋገጠም። በተቃራኒው ጉዱፈቻ አድራጊዎቹ ልጁን እንዱወስደ ቢገደደ በልጁ የወደፉት ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዲት ሉደርስ እንደሚችል እየገለፁ ነው። ከፍ ሲል እንደተገለፀው ደግሞ ጉዱፈቻ እንዱደረግ የሚፈቅደውና የሕግ ጥበቃ የሚደረግለት ዋነኛ አላማ የህፃናቱን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ነው። የጉዱፈቻ ውለ እንዱቀጥል ማድረጉ የሕፃኑን የወደፉት ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑ ከወዱሁ ከተረጋገጠ ውለ ሉሰረዝ ይገባል። ሕጉም ውለ እንዱፈርስ የሚፈቅደው ወደፉት ልጁ ላይ በተጨባጭ ጉዲት መድረሱ ሲረጋገጥ ብቻ አይደለም። ጉዱፈቻ አድራጊዎቹ ልጁን ወስደው ለማሳደግ የማይችለ መሆኑንና እንዱወስደ ቢገደደ እንኳን ወደፉት ህይወቱ ላይ ከፍተኛ ችግር እንደሚከተል መግለፃቸው ሲታይ ውለ እንዱቀጥል ማድረጉ የልጁን ጥቅም ከማስጠበቅ ይልቅ ህይወቱን አደጋ ላይ መጣል መሆኑን መገንዘብ ስለሚቻል ውለ አይፈርስም ተብል በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ከፍ ሲል የተመለከቱት የሕግ ድንጋጌዎች ያላገናዘበና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው።
የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ ግንቦት 3 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 82881 ጥቅምት 12 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ፀንቷል።
ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ህፃን ፈጠነን በጉዱፈቻ ልጅነት ለመቀበል ታህሣሥ 28 ቀን 2001 ዓ.ም ያደረጉትና በፍ/ቤት መጋቢት 16 ቀን 2001 ዓ.ም የፀደቀው የጉዱፈቻ ውል ተሰርዟል።
ይህንኑ አውቆ ተገቢውን እንዱፈጽም የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍ/ቤት ይተላለፍ።
No topics extracted.