No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዝያ 6 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ አማረ ረታ - ወ/መላኩ ረታ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሰለሞን ካሣዬ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር የኑዛዜ ወራሽ እና ያለኑዛዜ ወራሽ የሟች ንብረት ይካፈለ ሲል የሥር ፍ/ቤት የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የህግ ትርጉም ስሕተት የተፈፀመበት ነው ሲል አመልካች አቤቱታ በማቅረቡ ነው።
የአሁን አመልካች ሟች አቶ ካሣዬ ክፈተው ግንቦት 23 ቀን 1992 ዓ.ም ያደረጉትን የኑዛዜ ስጦታ መሰረት በማድረግ በአቃቂ ክ/ከተማ ቀበላ 01 የሚገኝ መኖሪያ ቤት ይዞ ያለ ሲሆን ተጠሪ በሥር ፍ/ቤት የሟች ወራሽ መሆናቸውን ጠቅሰው አመልካች ቤቱን እንዱለቅላቸው ዲኝነት ጠይቀው ነበር። የሥር ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ሟች ተወላጅ እያላቸው ከውርስ የነቀለ ስለመሆኑም በቂ ምክንያት ሳይሰጡ ያላቸውን ንብረት ለአመልካች በኑዛዜ ማስተላለፊቸውን ጠቅሶ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 939/3/ መሰረት በኑዛዜ ወራሽ እና ያለኑዛዜ ወራሾች ንብረቱን እኩል ይካፈለ ሲል ወስኗል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ቀርቦለት የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ አፅንቷል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል በማለት ታህሳስ 9/2001 ዓ.ም የተፃፈ አቤቱታ አቅርቧል። የሰበር አቤቱታው ይዘት ባጭሩ ለአመልካች በኑዛዜ የተሰጠው የሟች ጠቅላላ ንብረት ሳይሆን አንድ መኖሪያ ቤት ብቻ ነው በሚል የሥር ፍ/ቤት የጠቅላላ የውርስ ስጦታ ነው በሚል የፍ/ብ/ህግ ቁ 939/3/ ያለአግባብ ትርጉም ሰጥቷል በማለት እንዱታረም ጠይቋል።
ይህ ሰበር ችልትም አቤቱታውን ከመረመረ በኋላ በሟች የተሰጠውን ኑዛዜ የሥር ፍ/ቤቶች በማለፍ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሕግ ድንጋጌ ቁ. 939 እና 852 መሰረት መወሰናቸው በአግባቡ ሰለመሆኑ ለመመርመር ተጠሪን አስቀርቧል። ተጠሪም ነሐሴ 15 ቀን 2001 ዓ.ም ጽፍ ባቀረቡት መልስ ያለኑዛዜ ወራሾች በሕጉ አግባብ ከውርስ ያልተነቀለ ስለመሆኑና ሟችም ከተጠቀሰው ቤት ላላ ንብረት የላላቸው መሆኑን ጠቅሶ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱፀና ጠይቋል።
እኛም ይህንኑ የግራ ቀኙን ክርክር መሰረት አድርገን ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ከሕጉ አገናዝበን መርምረናል። ከፍ ሲል እንደተመለከተው አመልካች በኑዛዜ የተሰጠውን ቤት ለብቻው ለመውሰድ የሚከራከር ሲሆን ተጠሪ በበኩለ የሟች ያለኑዛዜ ወራሽ መሆኑን ጠቅሶ ከኑዛዜው ተጠቃሚ ጋር በሥር ፍ/ቤት በተወሰነው አግባብ ለመካፈል እንዱወሰን ጠይቋል።
በዚህ ፍ/ቤት ውሳኔ የሚያሻው ጉዲይ ሟች ለአመልካች ያደረጉት የኑዛዜ ስጦታ የጠቅላላ ውርስ(ስጦታ) ወይንስ ተለይቶ የታወቀ ንብረት ስጦታ ተብል ሉወሰድ ይገባል የሚለው መሰረታዊ ጉዲይ ነው። በዚህ ረገድ አመልካች አንድ መኖሪያ ቤት ብቻ ነው በኑዛዜ የተሰጠኝ ሲል ተጠሪ ደግሞ ሟች ከዚህ ቤት ላላ ንብረትም የላቸውም በማለት ተከራክሯል።
ይህንን መሰረታዊ ጉዲይ ለመፍታት የኑዛዜ ሰነደን አጠቃላይ ይዘት ማየት ተገቢ ሆኖ አግኝተናል።
ሟች ካሣዬ ክፈተው ግንቦት 23 ቀን 1992 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ እንደሚያመለክተው የወለዶቸው ልጆች እንዲልጠየቋቸው ጠቅሰው ያላቸውን ቤት ከነጣሪያው ከነግድግዲው ከነአፈሩ ለክርስትና ልጃቸው ለአማረ ረታ የተናዘዙ መሆኑን ነው። ከዚህም ላላ ቤት ውስጥ ያለ እቃ የኔነው ያለችውን ሚስት እንድትወስድ እንዱሁም በመንግሥት ተወርሷል የተባለ አንድ ክፍል ቤት ለሚስት ወ/ሮ እናት መንግሥቱ መስጠታቸውን ነው። ሚስት በሕይወት እስካለች ተጠቅማ በኋላ ለአቶ አማረ ረታ እንድታስረክብ የሚል ሀሳብ ተጨምሮ ይገኛል።
እንግዱህ ከዚህ የኑዛዜ ሰነድ ይዘት መረዲት የሚቻለው ሟች አለኝ ያለትን ንብረት ጠቅሰው የተናዘዙ ስለመሆኑ ነው። በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 911(1) እንደተደነገገው የሟች ተወላጆች እንዲያገኙ በማሰብ ያለውን ንብረት አጠቃል ለኑዛዜ ተጠቃሚ ስጦታ ያደረገ መሆኑ ሲታይ ሟች ያለውን ንብረት አጠቃላይ ያስተላለፈ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። በዚህ መልክ ያለውን ንብረት ዘርዝሮ ጠቅላላ በኑዛዜ ስጦታ ያስተላለፈ እንደሆነ ደግሞ ኑዛዜው ጠቅላላ ኑዛዜ ልባል እንደሚችል ከፍ/ብ/ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 912(1) መረዲት ይቻላል።
ስለሆነም አመልካች የጠቅላላ ኑዛዜ ተጠቃሚ ነው በሚል በሥር ፍ/ቤት የተደረሰው ድምዲሜ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት አለው ልባል የሚችልበት ምክንያት አላገኘንም።
አመልካች የሟች ተወላጅ (ያለኑዛዜ ወራሽ) አለመሆኑ አላከራከረም። አመልካች በጠቅላላ ኑዛዜ የሟች ሀብት በስጦታ የተላለፈለት መሆኑ ከተረጋገጠ በልላ በኩል ሟች ተወላጆቹን (ያለኑዛዜ) ወራሾችን ከውርስ የነቀለበት ሕጋዊ ምክንያት የላለ ስለመሆኑ በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠ መሆኑ ሲገናዘብ በዚህ ንብረት ላይ በኑዛዜ ወራሽ እና ያለ ኑዛዜ ወራሾች መካከል የሚኖረው መብት ምን ላሆን ይገባል የሚለው ጥያቄ አስመልክቶ የሥር ፍ/ቤቶች በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 939/3/ መሰረት መወሰናቸው ከመዝገቡ ተመልክተናል። ወደዚህ ድምዲሜ ለመድረስ የሚቻለው በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 915/1/ የተመለከተው ሁኔታ ተሟልቶ ሲገኝ እንደሆነ ነው። ከፍ ሲል እንደተመለከትነው አመልካች በኑዛዜ ጠቅላላ ስጦታ የተሰጠው ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ያለኑዛዜ የመጀመሪያ ደረጃ የሟች ወራሽ ነው። ይህ ከተሟላ ስለክፍፍለ ሥርዓት የሚወሰነው ደግሞ መርሁ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 939/3/ ይሆናል።
ስለሆነም የሥር ፍ/ቤቶች ይህንኑ የህጉን ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ተከትል የሰጡት ፍርድ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ሉያሰኝ የሚያስችል ምክንያት የለውም።
ስለሆነም የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ባለበት ሉፀና ይገባል ብለናል።
የፋዳራል የመ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ሚያዝያ 10 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ የሰጠው ፍርድ ፀንቷል።
ግራቀኙ በዚህ ፍ/ቤት ለተደረገው ክርክር የየራሳቸውን ወጪና ኪሣራ ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.