No summary available.
ሚያዝያ 4 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ታሪኳ አበበ የህፃን ሮቤል ንጉሤ ሞግዚት ተጠሪ፡- የለም መዝገቡን መርምርን የሚከተለውን ፍርድ ስጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የአዱስ አበባ ከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ይግባኝ ሰሚ ችልትና ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ጥቅምት 16 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ስለጠየቁ ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት አመልካች የህፃን ሮቤል ንጉሤ ሞላ አያት የነበሩት ወ/ሮ ተስፊነሽ አምባነሽ ደስታ መስከረም 27 ቀን 2001 ዓ.ም ውልና ማስረጃ ቀርበው ሁለት ምስክሮች ባለበትና በውልና ማስረጃ አግባብ ባለው ባለሥልጣን ፉት በአዱስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበላ 01 የቤት ቁጥር 872 የሆነውን መኖሪያ ቤትና ላልች ንብረቶች በሙለ በኑዛዜ መስጠታቸውን በመናዘዝ ህፃን ሮቤል ንጉሤ የኑዛዜ ወራሻቸው መሆኑን በማረጋገጥ ፈርመውበት ምስክሮችም ፈርመውበትና ባለሥልጣኑም ይህንን አረጋግጦ ኑዛዜውን መዝግቦ አንድ ኮፒ አስቀምጧል። አንድ ኮፒ በኑዛዜ ተጠቃሚ ተሰጥቷል ስለዚህ ህፃን ሮቤል ንጉሤ የሟች ወ/ሮ ተስፊነሽ አምባዬ ወራሽ መሆኑ ተረጋግጦ ማስረጃ ይሰጠኝ በማለት አመልክተዋል። የሥር ፍ/ቤት ሁለት ምስክሮች በማስቅረብ ሰምቷል። ሟች ውልና ማስረጃ ኑዛዜ ማድረጋቸውን መስክሯል።
የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የኑዛዜ ሰነደንና የምስክር ቃል ከመረመረ በኋላ ኑዛዜው በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 881 የተደነገገውን ፍርም አላሟላም። ከዚህ በተጨማሪ የውልና ማስረጃ ባለሥልጣን በምስክርነት ስሙ ያልተጠቀሰና ያልተፈረመ በመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 882 የተደነገገውን መስፈርት አያሟላም። አመልካች ሟች ወ/ሮ ተስፊነሽ አምባዬ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ፍትህ ሚኒስትር የሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት አዱስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ መስከረም 27 ቀን 2001 ዓ.ም በቁጥር 044/7/2001 ኑዛዜ ያደረጉ መሆናቸው በክፍለ ባለሥልጣን ተረጋግጦና ተፈርሞ የተሰጠን ማስረጃ አለ። ኑዛዜው ውል ክፍል ውስጥ በሥራ ቀን ሁለት ምስክሮች ባለበት የተደረገና ሟችና ምስክሮች የፈረሙበትና በውል ክፍል የሚመለከተው ባለሥልጣን ባለበት የተደረገ መሆኑ የተረጋገጠ ሆኖ እያለ ለፍትሐሓር ሕግ ቁጥር 882 የተዛባ የሕግ ትርጉም በመስጠት ኑዛዜው ዋጋ የለውም ተብል መወሰኑ የሟችን የኑዛዜ ቃል ዋጋ የሚያሣጣና የህፃኑን መብት ሚጏዲ በመሆኑ የሕግ ትርጉም ስህተቱ በሰበር ታርሞ ኑዛዜው ዋጋ አለው ተብል ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል በሥርም ሆነ በሰበር ደረጃ ተከራካሪ የሆነ ተጠሪ የለም።
አመልካች ለሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ፍርድ ቤቶቹ የሰጡት ውሣኔና አመልካች ያቀረበችው የሰበር አቤቱታ ይዘት ከላይ የተገለፀው ሲሆን መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው ሟች ወ/ሮ ተስፊነሽ አምባነሽ መስከረም 27 ቀን 2001 ውልና ማስረጃ ጽ/ቤት ቀርበው ያደረጉት ኑዛዜ በሁለት ምስክሮች እና በውልና ማስረጃ ሰራተኛ ፉት የተደረገና ወዱያውኑ ሟችና ምስክሮች የፈረሙበትና የውልና ማስረጃ አግባብ ባለው ባለሥልጣን ትክክለኛነትን በማረጋገጥ በጽ/ቤቱ ማህተም በማተምና በፊርማው በማረጋገጥ ያደረጉት መሆኑን በሥር ከቀረበው ክርክር ለመረዲት ይቻላል። ይህንን ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 882 ድንጋጌ አንፃር መመዘን ያስፈልጋል የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 882 “በግልጽ የሚደረገው ኑዛዜ ከምስክሮቹ መካከል አንደ ዲኛ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን የተሰጠው ሰው ሆኖ ኑዛዜውም የተደረገው ይህ ዲኛ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን የተሰጠው ሰው ሥራቸውን በሚያካሄድበት ክፍል ውስጥ የሆነ እንደሆነ ለኑዛዜው ዋጋ ለማግኘት ሁለት ምስክሮች ብቻ በቂ ናቸው” የአዱስ አበባ ከተማ ነክ ፍርድ ቤት ይህ ድንጋጌ ውል አዋዋይ ባለሥልጣኑ ስሙ በምስክርነት መገለጽ ያለበት መሆኑን እንደሚያስገድድ ኑዛዜው የተደረገው በውል አዋዋይ ባለሥልጣን ፉት ቢሆንም ባለሥልጣኑ በምስክሮች ስም ዝርዝር ስሙ ካልተገለፀ የሕጉን ፍርም ኑዛዜው አያሟላም ኑዛዜው ህጋዊ ውጤት አይኖረውም የሚል ትርጉም ሰጥቷል። ይህ አተረጓጏም የህጉን መንስፈና አላማ የሚያሣካ ውጤታማ አተረጓጏም አይደለም።
በቀረበው የኑዛዜ ማስረጃ ውል ለማዋዋል ሥልጣን ያለው ባለሥልጣን ፉት የተደረገ፣ኑዛዜው ከተነበበ በኋላ ሁለቱ ምስክሮችና ሟች እንደፈረሙበት ይህ ሁለ ተግባር በፉቱ ሲከናወን ጠቅላላ ሂደቱን የተከታተለው ውል ለማዋዋል ሥልጣን ያለው ባለሥልጣን ሂደቱ በአግባቡ የተፈፀመ መሆኑን በፊርማው በማረጋገጥና ማህተም በመምታትና ቁጥር በመስጠት አንድ ኮፒ ውልና ማስረጃ ጽ/ቤት በማስቀረት ቀሪውን ለሟች እንደሰጠ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ቀርቧል። ይህ መስፈርት በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 882 የተደነገገውን ፍርም የሚያሟላና ህጉ ኑዛዜው የሟች እርግጠኛ የመጨረሻ ቃል መሆኑን ለማረጋገጥ የደነገገውን መስፈርት የሚያሟላ ነው።
No topics extracted.
ስለዚህ አጠቃላይ ኑዛዜው የተደረገው ውል ለማዋዋል ሥልጣን ባለው ባለሥልጣን ፉት መደረጉን በማረጋገጥ በመሥሪያ ቤቱ ማህተምና ፊርማ የተረጋገጠ ከሆነ የባለሥልጣኑ ስም በምስክሮች ፉት ስም ዝርዝር ውስጥ መጠቀሱ የግድ አስፈላጊ አይደለም። የባለሥልጣኑ ስም መገለጽ የሚያስፈልገው ከእሱ ውጭ ላላ አንድ ምስክር ብቻ ከኖረ ነው። በያዝነው ጉዲይ ውል አዋዋይ ባለሥልጣኑ ውጭ ላልች ሁለት ምስክሮች ያለ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት ለፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 882 የሰጠው ትርጉም የሕጉን መንፈስና አጠቃላይ ግብ መሰረት ያላደረገና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት፣ ይግባኝ ችልትና ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
ሟች ወ/ሮ ተስፊነሽ አምባዬ ደስታ መስከረም 27 ቀን 2001 ዓ.ም በህፃን ሮቤል ንጉሤ ሞላ ያደረጉት ኑዛዜ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 882 የተደነገገውን መስፈርት የሚያሟላና ሕጋዊ ውጤት ያለው ኑዛዜ ነው ብለናል።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።