No summary available.
መጋቢት 06 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሐይ ታደሰ ኂሩት መለሰ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ዮሐንስ ጡእማይ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ምህረት ገብሩ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ባልና ሚስት በትዲር ወቅት እያለ አንደኛው ተጋቢ ከላላው ተጋቢ እውቅና ውጪ ብድር ተበድሮ ሲገኝ ብድር የጋራ የሚሆንበትን አግባብ የሚመለከት ነው። ክርክር የተጀመረው በትግራይ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት በውቅሮ በደደቢት ጣቢያ ማህበራዊ ፍርድ ቤት የአመልካች የካቲት 01 ቀን 2000 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ነው። የአቤቱታቸው ይዘትም ባጭሩ፡- ከተጠሪ ጋር የነበረኝ ጋብቻ በፍቺ እንዱፈርስ የጋራ ንብረት ክፍፍልም በፍ/ቤት ውሳኔ እንዱፈፀምልኝ የሚል ነው። የአሁኗ ተጠሪም ለክሱ በሰጡት መልስ ጋብቻው በፍቺ በፍርድ ቤት ቢፈርስ ተቃውሞ የላላቸው መሆኑን፣በጋራ ንብረት ክፍፍልም ተገቢ ነው ያለትን ክርክር አቅርበዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመመረመረ በኋላ በአመልካችና በተጠሪ በፈፀሙት የጋብቻ ውል መሰረት እኩል በእኩል እንዱካፈለ፣በጋብቻ ወቅት የተወለደት ሦስት ልጆች ከተጠሪ ጋር እንዱያድጉ ሆኖ ቀለብን በተመለከተ ግን ለእያንደንዲቸው በወር ብር 70.00(ሰባ ብር) አመልካች እንዱከፍለ ሲል ወስኗል። ከዚህም ተጨማሪ አመልካች ለአሁኑ ክርክር መሰረት የሆነው ማረት ከተባለ ድርጅትና ከዲሽን ባንክ የተወሰነውን የብድር እዲ በተመለከተ ተጠሪና አመልካች በጋራ የከፈለት ተቀንሶ ቀሪውን በጋራ እንዱከፍለት፣እዲው ከተቀነሰ በኋላ የንብረት ክፍፍልም እንዱፈፀም ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ተጠሪ ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለውቅሮ ወረዲ ፍርድ ቤት አቅርበው ተቀባይነት አላገኙም። ከዚህ በኋላም ተጠሪ የሰበር አቤቱታቸውን ለትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ሰበር ሰሚው ችልት የንብረት ክፍፍልን በሚመለከት የስር ፍ/ቤቶች የሰጡትን ውሣኔ ሙለ በሙለ ሲያፀና በስር ፍርድ ቤቶች የጋራ ነው ተብል የተሰጠውን ውሳኔ ግን አመልካች የተበደሩትን ብር በሚመለከት ተጠሪን ሳያሳየው የተበደሩት፣የተበደሩትም ብር በጋራ ጥቅም መዋለን ያላስረደ እና እንዱሁም የአመልካችና የተጠሪ የጋራ ቤት የሆነውን አመልካች ከዲሽን ባንክ ለተበደሩት ብድር አከፍፈል ለዋስትና ሲያስይዙ የተጠሪን ፈቃድ አልጠየቀም የሚለትን ምክንያቶች በመያዝ አመልካች ከዲሽን ባንክ የተበደሩትን ብር 65,000.00(ስልሳ ስምንት ሽህ ብር) የአመልካች የግል እዲ ነው በማለት ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
አመልካች ታህሣሥ 19 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት ሦስት ገጽ የሰበር አቤቱታ የክልለ ሰበር ችልት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት በተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- ተጠሪ ብድሩ መኖሩን አውቀው ከስምንት ወራት ያህል እዲውን ከአመልካች ጋር ሲመልሱ የነበሩ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ እና አመልካች ነጋዳ በመሆናቸው የተጠሪን ፈቃድ ሳይጠይቁ ብድር መበደርና የጋራ ንብረትን በዋስትና ማስያዝ የሚችለ መሆኑን ሕጉ የሚፈቅድ ሆኖ እያለ የተጠሪ ፈቃድ ያልተጠየቀበት እና እዲው ለትዲር ጥቅም የዋለ መሆኑ አልተረጋገጠም ተብል እዲው ተጠሪን አይመለከታቸውም መባለ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በአንድ በኩል የአመልካች በንግድ ስራ ከመሰማራታቸውና በልላ በኩል ደግሞ የባንክ ብድሩ የተወሰደው ግራ ቀኙ በጋብቻ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ከመሆኑ አንፃር ብድሩ ለጋራ ጥቅም አልዋለም ተብል ተጠሪ ከእዲው ነፃ እንዱሆኑ መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጏአል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካችና ተጠሪ በትዲር ፀንተው በነበሩበት ወቅት አመልካች በንግድ ስራ ተሰማርተው የነበሩ መሆኑን፣በዚህም ወቅት አከራካሪውን ብድር ተጠሪን ሳያሳውቁ የማይንቀሳቀስ የጋራ ንብረት በዋስትና አስይዘው መውሰዲቸውን፣ከትዲር ላይ እያለም የተወሰነውን የብድሩን ገንዘብ መመለሳቸውን ነው።
አመልካች በንግድ ስራ የተሰማሩ ነጋዳ ከሆኑ ብድሩን በሚበደሩበት ወቅት የተጠሪን ፈቃድ ማግኘት ነበረባቸው ሉባለ የማይችለ መሆኑን የንግድ ሕግ ቁጥር 16 ድንጋጌን ይዘትና መንፈስ በምንመለከትበት ጊዜ የምንረዲው ነጥብ ነው። ተጠሪ እዲው መኖሩን ያውቁ የነበረ ስለመሆኑም በወቅቱ የብድሩን ገንዘብ በጋራ መመለሳቸው የሚያረጋግጠው ነገር ነው። በመሆኑም ብድሩ አመልካች ነጋዳ ሆነው በትዲር ወቅት ወስደው በጋራ ሲከፈል የነበረ በመሆኑ የተጠሪ ፈቃድ የለበትም ልባል የሚችል አይደለም። በእርግጥ የባልና ሚስት የጋራ ሐብት የሆነ አንድ የማይነቀሳቀስ ንብረት ሐብትነትን ወይም ላላ መብት ለ3ኛ ሰው ለማስተላለፍ የሁለቱም ተጋቢዎች ስምምነት ማስፈለጉ በቤተሰብ ሕጉ የተመለከተ ሲሆን ስምምነቱን ያልሰጠው ተጋቢም ውለ እንዱፈርስ ለፍርድ ቤት ጥያቄ ማቅረብ ውለ እንዱፈርስ ማድረግ የሚችል መሆኑን የቤተሰብ ሕጉ ደንግጏ እናገኘዋለን። የሕጉ መንፈስ ውለ የአንደኛው ተጋቢ ስምምነት ሳይኖር በመደረጉ ብቻ ከጅምሩ ውጤት አልባ ነው ወደሚለው ድምዲሜ የማይወስድ ነው። ይልቁንም ስምምነቱን ያልሰጠው ተጋቢ በሕጉ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ውለ እንዱፈርስ እስካላደረገው ድረስ ውለ ውጤት ይኖርዋል። በተያዘው ጉዲይም አመልካች ነጋዳ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ብድሩን ተጠሪ እያወቁ ለተወሰነ ጊዜ አብሮ ሲከፍለ የነበረ፣ውለን እንዱፈርስ ያላደረጉት መሆኑ በሚገባ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው።
No topics extracted.
ብድሩ በትዲር ወቅት የተወሰደ ከሆነ ደግሞ ለትዲር ጥቅም እንደዋለ ሕግ ግምት የሚወስድበት ሲሆን ለትዲር ጥቅም አለመዋለን የማስረዲት ሸክም ያለባቸው ተጠሪ እንጂ አመልካች ሉሆኑ አይችለም። ስለሆነም የትግራይ ክልል ሰበር ሰሚ ችልት የበታች ፍርድ ቤቱ የብድር እዲው የጋራ ነው ሲለ የሰጡትን ውሳኔ መሻሩ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች ባግባቡ ከንግድ ሕጉ እና ከቤተሰብ ሕጉ መንፈስ ሳያገናዝብ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ጥቅምት 26 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሻሸሎል።
አመልካች ከዲሽን ባንክ እና ከማረት ማህበር የወሰደት ብድር የጋራ እዲ ነው በማለት ወስነናል።
በዚህ ችልት በተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።