No summary available.
መጋቢት 21 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- እነ ወ/ሮ ቦጋለች ደባልቄ(4 ሰዎች) - አልቀረቡም ተጠሪ፡- ወ/ሮ መሰረት በለጠ - አልቀረቡም
አመልካቾች ለአዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪ የስር ሁለተኛ ተከሳሽ ከነበሩት ግለሰብ ጋር ያደረጉት የሽያጭ ውል እንዱፈርስ ያቀረቡት ክስ ፍ/ቤቱ ተቀብል ውለ እንዱፈርስ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ይግባኝ ሰሚው የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሳኔውን ስለሻረውና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልትም የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለውም በማለቱ የቀረበ አቤቱታ ነው።
አመልካቾች በአዋሳ ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ተጠሪዋ ከአቶ ፍሬው ለማ ጋር በጋብቻ በነበሩበት ጊዜ ቤት መስራታቸውንና ሁለት ልጆችም መውለዲቸውን ገልፀው አቶ ፍሬው ለማ ከዚህ አለም በሞት ሲለዩ ግን ተጠሪዋ የጋራ ንብረት የሆነውን ቤት በስማቸው አዛውረው ለስር ሁለተኛ ተከሳሽ ስለሸጡና ይህም የህፃናቱን መብት ስለሚጏዲ የሽያጩ ውል እንዱፈርስ ጠይቀዋል። ተጠሪም የሽያጩ ውል በሕጉ አግባብ የተከናወነ በመሆኑ ሉፈርስ አይገባም በማለት ተከራክረዋል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ተጠሪ በቤቱ ላይ ያላቸው ድርሻ ግማሽ ሲሆን ቀሪው ድርሻ ለህፃናቱ ከአባታቸው የተላለፈላቸው በመሆኑ የህፃናቱን ድርሻ አጠቃለው ቤቱን መሸጣቸው የህፃናቱን መብት የሚጏዲ በመሆኑ የሽያጩ ውል ሉፈርስ ይገባል ማለት በተጠሪ ስም ተሰጥቶ የነበረው የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እንዱሰረዝና በሟች ስም ተመዝግቦ ቤቱ የተጠሪና የህፃናቱ የጋራ ሃብት ሆኖ እንዱቆይ ወስኗል።
ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ላይ ቅር በመሰኘት ለደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ ሁለቱን ወገኖች አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ሽሯል። የሰበር አቤቱታ የቀረበለት የክልለ ሰበር ሰሚ ችልትም የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለውም በማለት አቤቱታውን ውድቅ አድርጓል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። ይህ ችልትም የሽያጭ ውለ ሉፈርስ አይገባም በማለት የተሰጠው ውሳኔ ከህፃናት መብትና ከሞግዚት ሥልጣን ወሰን አኳያ ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በፁሁፍ አቅርበዋል።
ከፍ ሲል እንደተመለከተው አመልካቾች የሚጠይቁት ተጠሪ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት የሆነውን ቤት በመሸጣቸው ውለ እንዱፈርስላቸው ነው። ውለ ሉፈርስ ይገባል የሚለትንም ቤቱ የተጠሪ የግል ሃብት ሳይሆን የተጠሪና የሕፃናቱ የጋራ ሃብት በመሆኑ የህፃናቱን ድርሻ አጠቃለው መሸጣቸው የህፃናቱን መብት ይጏዲል በማለት ነው። አካለ መጠን ያላደረሰ ልጅ የአሳዲሪነትና የሞግዚትነት ስልጣን የሚሰጠው ለልጁ እናትና አባት ሲሆን ከወላጆቹ አንደኛው የሞተ ከሆነ ይህንን ስልጣን ይዞ የሚቆየው በህይወት ያለው ወላጅ ነው። በዚህም መሰረት ተጠሪ የልጆቹ አሳዲሪና ሞግዚት ሆነዋል። የልጆቹ አስተዲዲሪና ሞግዚት በመሆናቸውም የልጆቹን መኖሪያ፣ጤና አጠባበቅ፣አስተዲደግ፣ትምህርት ማህበራዊ ግንኙነቱን በተመለከተ እንዱማሩና እንዱሁም ንብረትን በተመለከተ እንዱያስተዲድሩ ህጉ ለተጠሪ ሥልጣን ሰጥቷቸዋል። በመሆኑም ለልጆቹ መልካም አስተዲደግ ይረዲ ዘንድ የልጆቹን ሃብት እንዳት መጠቀም እንዲለባቸው የመወሰን ስልጣን ስላላቸው የልጆቹን ግማሽ ድርሻ በተመለከተ ለልጆቹ መልካም አስተዲደግ አስፈላጊ ከሆነ ድርሻቸውን መሸጣቸው ብቻውን የልጆቹን መብት ይነካል ለማለት የሚያስችል አይሆንም። በእርግጥ በተሻሻለው የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 292 ስር ሞግዚቱ እንዱሸጥ በግልጽ የተፈቀደለት የሚንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶችን፣አክስዮኖችንና የገንዘብ ሰነድችን ነው።
የማይንቀሳቀስ ንብረትን በመለከተ በህጉ መሸጥ የሚቻል መሆን አለመሆኑ በግልጽ የተቀመጠ ነገር የለም። ከፍ ሲል የተጠቀሰው ድንጋጌ ሞግዚቱ ሉሸጥ የሚችለውን የንብረት አይነቶች በግልጽ ለይቶ ማስቀመጡ ከዚህ ውጭ ያለትን ንብረቶች እንዲይሸጥ መከልከለን ያሳያል የሚባል ቢሆን እንኳን ሞግዚቱ የሕግ ድንጋጌዎች በመተላለፍ ለፈፀማቸው ድርጊቶች ወኪል የሆነ ሰው ከተሰጠው ስልጣን በላይ በሚሰራበት ጊዜ አግባብነት ያላቸው የውክልና ሕግ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ እንደሚሆኑ የክልለ ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 321 ያመለክታል። ውክልናን በሚመለከቱ የፍ/ህጉ ድንጋጌዎች ስንመለከት ደግሞ ወኪለ የስልጣን ወሰኑን በማለፍ በስራ ጊዜ ሿሚው ተግባሩን ለማጽደቅ ወይም ለማፍረስ የሚችል ቢሆንም እንኳን ተወካዩ በውክልና ከተሰጠው ስልጣን ውጭ በማለፍ ሰርቶ የተገኘ ስራ በቅን ልቦና የሰራው ከሆነ ወካዩ ስራውን ለማጽደቅ የሚገደድ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2207/1/ ያመለክታል።
ተጠሪም ቤቱን የሸጡት ለልጆቻቸ4ው መልካም አስተዲደግ በተለይ ለትምህርታቸው ስለሚጠቅም ያለባቸውን የሞግዚትነት ስልጣን በአግባቡ ለመወጣት እንደሆነ ተከራክረዋል። አመልካቾች ግን ተጠሪዋ ላላ ባል ስላገቡ ንብረቱን አዱስ ከመሰረቱት ጋብቻ ንብረት ጋር ይቀላቅላለ ከማለት ባለፈ አመልካች በልጆቹ አስተዲደግና አጠባበቅ ላይ ጉዲት አድርሰዋል ወይም ንብረታቸውን ያለአግባብ አባክነዋል በማለት በማስረጃ የተደገፈ ተጨባጭ ክርክር አላቀረቡም። በእርግጥ ተጠሪ ሞግዚት በመሆናቸው ብቻ የልጆቹን ሃብት እንደፈለጉ ማባከን ስልጣን የላቸውም።
አመልካቾችም ማስረዲት ያለባቸው ተጠሪ ቤቱን መሸጣቸውን ብቻ ሳይሆን ቤቱ በመሸጡ ምክንያት በልጆቹ ላይ የደረሰው ጉዲት ጭርም ነው። ለልጆቹ መልካም አስተዲደግ አስከሆነ ድረስ ተጠሪ የራሳቸውንና የልጆቻቸውን የጋራ ሃብት የሆነውን የማይንቀሳቀስ ንብረት መሸጣቸው በራሱ የሽያጩ ውል ለማፍረስ የሚያስችል በቂ ምክንያት ላሆን አይችልም። በመሆኑም የስር ፍ/ቤቱ የተሸጠው የልጆቹ መልካም አስተዲደግ መሆን አለመሆኑን ሳይመረምር ተጠሪ የራሳቸውንና የልጆቻቸው የጋራ ንብረት የሆነውን ቤት መሸጣቸውን ብቻ በምክንያትነት በመውሰድ የሽያጩ ውል ሉፈረስ ይገባል በማለት የደረሰበት መደምደሚያ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሳኔውን መሻሩ በአግባቡ ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 23385 ጥር 1 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 26392 መጋቢት 29 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.