No summary available.
መጋቢት 20 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ሙለሸዋ ቦጋለ - በራሳቸውን እና ወኪል ለሆኑላቸው
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ የሰበር መዝገብ የቀረበው ክርክር በውርስ ሕጉ ውስጥ የተመለከቱትን ይርጋ ድንጋጌዎችን አተረጓጏም እና አፈፃፀማቸውን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካቾች መጋቢት 29 ቀን 2000 ዓ.ም በአሁኑ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ፤የአመልካቾች ወላጆች የሆኑት አቶ ቦጋለ ባሩዳ ሰኔ 06 ቀን 1989 ዓ.ም ፣እና ወ/ሮ ኢትዮጵያ ናዳ ደግሞ መስከረም 17 ቀን 1997 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ወራሽነታቸውን ማረጋገጣቸውን፣ሟቾች በሕይወት እያለ ያፈሩትን ንብረት የአሁኑ ተጠሪ እንዱያካፍሎቸው ቢጥይቋቸውም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ለብቻቸው ይዘው እየተጠቀሙ እንደሚገኙ ገልፀው የውርስ ሃብቱን የሚያጣራ የውርስ አጣሪ በፍርድ ቤት እንዱሾምቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪም ለክሱ በሰጡት መልስ የአመልካቾች የውርስ ይጣራልን ጥያቄ አውራሾቻቸው በሞት ከተለዩ በኋላ ከሦስት አመታት በኋላ የቀረበ በመሆኑ በይርጋ ውድቅ ነው ሲለ ተከራክረዋል። የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር በመመርመር የአመልካቾች የውርስ ይጣራልኝ ጥያቄ አውራሾቻቸው ከሞቱ በአንድ ጊዜ ውስጥ ያልቀረበ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም፣ሆኖም አመልካቾች የውርስ ንብረቱን በተመለከተ ገምተው ክስ ማቅረብ ይችላለ የሚል ምክንያት በመስጠት የአመልካቾችን አቤቱታ (ጥያቄ) ውድቅ አድርጏል። በዚህ ውሳኔ አመልካቾች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ይኸው ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት ይርጋን አስመልክቶ የያዘውን ምክንያት በመቀየር የውርስ ይጣራልኝ ጥያቄ በሦስት አመት ያልቀረበ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ምክንያቱን ለውጦ አጽንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
አመልካቾች መጋቢት 07 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ሦስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡አመልካቾች ወራሽነታቸውን በጊዜው አረጋግጠው የውርስ ንብረት ይጣራልኝ የሚለውን ጥያቄ ማቅረባቸውንና ተጠሪም የሰጠው መልስ አመልካቾች ለቤቱ ጥበቃ የወጣውን ሂሳብ ለተጠሪ ከፍለው ውርሱ ቢጣራ ተቃውሞ የለኝም የሚል ሆኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች ጉዲዩ በይርጋ የታገደ ነው በማለት መወሰናቸው ያላግባብ ነው ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል ተጠሪ ቀርበው የካቲት 12 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገጽ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። የመልሳቸው ይዘትም ጉዲዩ በይርጋ የታገደ ነው ተብል መወሰኑ ባግባቡ ስለሆነ የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የአመልካቾች የውርስ ይጣራልን ጥያቄ በሦስት ዓመት ይርጋ የታገደ ነው ተብል መወሰኑ ባግባቡ ነው አይደለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ መገንዘብ የተቻለው አከራካሪውን ንብረት ሟች ወ/ሮ ኢትዮጵያ ናዳ እስከእለት ሞታቸው ድረስ ይዘው ሲጠቀሙት የነበረ መሆኑ፣ወ/ሮ ኢትዮጵያ ናዳ መስከረም 17 ቀን 1997 ዓ.ም መሞታቸውን፣አመልካቾች የወ/ሮ ኢትዮጵያ ናዳ መጀመሪያ ደረጃ ወራሽነታቸውን በመ/ቁ. 612/98 የካቲት 30 ቀን 1998 ዓ.ም፣ተጠሪ በበኩላቸው የወ/ሮ ኢትዮጵያ ናዳ መጀመሪያ ደረጃ ወራሽነታቸውን በመ/ቁጥር 56/98 ታህሣሥ 25 ቀን 1998 ዓ.ም ማረጋገጣቸውን፣አሁን እየተከራከሩ ያለት የውርስ ንብረት ድርሻቸውን አመልካቾች እንዱያካፍሎቸው መሆኑን ነው።
የፍ/ብ/ሕ/ቁ .1000 የወራሽነት ጥያቄ የማቅረቢያ የጊዜ ገደብ ነው። ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 996 እስከ 1002 ድረስ ከተደነገጉት ድንጋጌዎች መገንዝብ የሚቻለውም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 999 ስር በተመለከተው መሰረት የሚቀርበው የወራሽነት ጥያቄ(petition hereditists) በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 996 እና ተከታዮቹ ቁጥሮች ከተገለፀው የወራሽነት የምስክር ወረቀት ጋር የተያያዘ መሆኑን ነው። በመሆኑም የወራሽነት ጥያቄ አንድ ወራሽ በልላ በወራሽነት የውርስ ሐብት በያዘ ሰው ላይ ክስ ሲያቀርብ ተፈፃሚነት ባላቸው የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1000/1/ እና /2/ ድንጋጌዎች ስር በተመለከቱት ደንቦች መሰረት የሚገደብ ነው።
No topics extracted.
በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ የሟች ወ/ሮ ኢትዮጵያ ናዳ ወራሽነታቸውን ታሕሣሥ 25 ቀን 1998 ዓ.ም ብቻቸውን፣አመልካቾች ደግሞ የካቲት 30 ቀን 1998 ዓ.ም በመሆን በፍርድ ቤት ውሳኔ አረጋግጠዋል፣የክፍፍለ ጥያቄ በቀረበበት ንብረት ደግሞ በሟች ወ/ሮ ኢትዮጵያ ናዳ ተይዞ የቆየ መሆኑ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። ከዚህም የምንገነዘበው የሟቿ ወራሾች በሕጉ በተመለከተው ጊዜ ገደብ ውስጥ ተለይተው መታወቃቸውን ነው።
የአመልካቾች ጥያቄ ደግሞ የውርስ ክፍያ ነው። የውርስ ክፍያ ደግሞ ራሱን የቻለ የውርስ ሕግ ሆኖ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ.
1060 እስከ 1113 ድረስ ባለት ድንጋጌዎች ስር የተሸፈነ ጉዲይ ነው። የውርስ ክፍያ ጊዜን በተመለከተ የፍ/ብ/ሕጉ በአንቀጽ 1062 ስር የደነገገ ሲሆን የድንጋጌው ይዘትም ውርሱ በተጣራ ጊዜ በማናቸውም ጊዜ ቢሆን እያንዲንደ የጋራ ወራሾች ውርሱን እንከፊፈል ብለው ለመጠየቅ እንደሚችለ መደንገጉን የሚያሳይ ነው። በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1060 ድንጋጌ ስር ደግሞ የውርስ አከፊፈል እስካልተፈፀመ ድረስ ውርሱ በወራሾች መካከል ሳይነጣጠል እንደሚቆይ ተመልክቷል። በመሆኑም አመልካቾች የሟች ወራሽነታቸውን በሕጉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ አረጋግጠው ከቆዩ በኋላ የውርስ ንብረቱን የክፍፍል ጥያቄ ማቅረባቸው በፍ/ብ/ሕ/ቁ .1000/1/ እና /2/ ስር በተመለከተው የይርጋ ድንጋጌ የሚታገድ ሳይሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1062 ድንጋጌ መሰረት በማናቸውም ጊዜ የሚቀርብ በመሆኑ ፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሆነ የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የያዙት ምክንያትም ሆነ የደረሱበት መደምደሚያ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 57313 በሐምል 30 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጠቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 71948 ጥር 27 ቀን 2000 ዓ.ም ምክንያቱ ተለውጦ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የአመልካቾች የዲኝነት ጥያቄ የውርስ ክፍፍል በመሆኑ በይርጋ ሉታገድ አይገባም ብለናል።
የአመልካቾችን የውርስ ንብረት ክፍፍል ጥያቄያቸውን የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተገቢውን እንዱያሟለ አድርጏ እንዱያስተናግደው በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341/1/ መሰረት መልሰንለታል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።