No summary available.
መጋቢት 22 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጏስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ አደፍርስ በቀለ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ይቁም በቀለ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በስጦታ የተገኘ ቤት ልረከብ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ ጥር 21 ቀን 1999 ዓ.ም በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው።
የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- በቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 15 (በቀድሞው አጠራር ወረዲ 28 ቀበላ 15) ክልል ውስጥ የሚገኘውን ቁጥር 321 የሆነውን ቤት ከሟች ወ/ሮ አለሚቱ በላይነህ በስጦታ የተላለፈላቸው መሆኑን፣አመልካች ወንድማቸው በመሆኑ በጊዜው ሲቸግራቸው ቤቱን እንዱጠቀሙበት ተጠሪ ፈቅደውላቸው ይዘው ሲጠቀሙት ከቆዩ በኋላ ቤቱን እንዱለቁላቸው ሲጠየቁ አመልካች ፈቃኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን ገልፀው አመልካች ቤቱን ለቀው እንዱያስረክቡ እንዱወሰንላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካችም ለክሱ በሰጡት መልስ፤ተጠሪ ያቀረቡት የስጦታ ማስረጃ አለመኖሩን፣ግብር መክፈል የቤት ባለቤት እንደማያደርግ እና ተጠሪ ክስ ለመመስረት የሚያስችላቸው መብት የላላቸው መሆኑ፣የቤቱ ግምትም የተጋነነ መሆኑን፣በቤቱ ውስጥ ከ1981 ዓ.ም ጀምሮ መኖር የጀመሩ በመሆኑ ጉዲዩ በይርጋ እንደሚታገድ፣ቤቱ የወ/ሮ አለሚቱ በላይነህ ሆኖ አመልካችም የወ/ሮ አለሚቱ በላይነህ ወራሽ በመሆናቸው ቤቱን ሉለቁ እንደማይገባ ገልፀው ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከመመረመረ በኋላ አከራካሪውን ቤት በተመለከተ ተጠሪ በስጦታ ውል መሰረት ያገኙት በመሆኑ አመልካች ለተጠሪ ሉያስረክቡ ይገባል ሲል ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ጸንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
አመልካች ጥር 04 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- በስር ፍርድ ቤት የተነሳው የይርጋ ክርክር የታለፈው ያላግባብ ነው፣የቤቱ ባለቤት መሆኔን የሚያሳይ ማስረጃ ስላለኝ ይቅረብልኝ የሚል ጥያቄ የታለፈው ያላግባብ ነው በማለት ውሳኔ እንዱሻር ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታቸው ተመርምሮም አመልካች ያነሱት የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ የተደረገው ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ ቀርበው ሰኔ 24 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገጽ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። አመልካችም ሐምል 16 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ አንድ ገጽ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ይህ ችልት ግራ ቀኙን ታህሣሥ 20 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት በቃል አከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አከራካሪው ቤት የሟች ወ/ሮ አለሚቱ በላይነህ መሆኑን፣ተጠሪ ቤቱን አግኝቼአለሁ የሚለት ሐምል 26 ቀን 1972 ዓ.ም በተደረገው ስጦታ ሆኖ ስጦታው አግባብነት ባላቸው አካላት የተቀመጠ እና የተመዘገበ ስለመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ማረጋገጡን፣የቤቱ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ አለሚቱ በላይነህ ከዚህ አለም በሞት እስከተለዩበት ጥር 11 ቀን 1995 ዓ.ም ድረስ በአከራካሪው ቤት ውስጥ ይኖሩበት እንደነበር፣አመልካች በቤቱ ውስጥ ከ1981 ዓ.ም ጀምሮ አስካሁን ድረስ መኖራቸውን፣የቤቱ ስመ ሃብት ከሟች ወደ አመልካችም ሆነ ተጠሪ ያልተዛወረ መሆኑን ነው።
ተጠሪ ለክርክሩ መሰረት ያደረጉት የስጦታ ውል ሐምል 26 ቀን 1972 ዓ.ም የተደረገ ሆኖ ክሱ እስከተመሰረተበት ጊዜ ድረስ ለአፈፃፀም ያልቀረበ መሆኑን ክርክሩ በግልጽ ያሳያል። ስጦታ በምን ያህል ጊዜ መፈፀም አለበት የሚለውን ጥያቄ በዚህ ረገድ የተመለከቱት ልዩ ድንጋጌዎች በግልጽ ያስቀመጡት የጊዜ ገደብ የለም። ይሁን እንጂ የስጦታ ውል ድንጋጌዎች በዚህ ረገድ ያስቀመጡት የጊዜ ገደብ የለም ተብል የስጦታ ውል ይፈፀም ጥያቄ በማናቸውም ጊዜ ላቀርብ ይችላል ልባል አይችልም። በሕጉ በግልጽ ካልተቀመጠ በስተቀር ማንኛቸውም ግዳታ ሉፈፀም የሚገባበት የጊዜ ገደብ ሉኖር ይገባል። የስጦታ ውልን የሚገዙ ድንጋጌዎች ግልጽ የሆነ ጊዜ ገደብ ባያስቀምጡም ስጦታ ውል እንደመሆኑ መጠን ሉፈፀም የሚገባው በአስር አመት የጊዜ ገደብ መሆኑን ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 1676/1/ እና 1845 ድንጋጌዎች ይዘት እና መንፈስ መገንዘብ ይቻላል። ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመጣ ተጠሪ የስጦታ ውለ ሐምል 26 ቀን 1972 ዓ.ም ተደርጏልኛል እያለ ስጦታ አድራጊያቸው በሕይወት እያለ አከራካሪውን ቤት በስጦታ ውለ መሰረት እንዱፈጸምላቸው ያቀረቡት ጥያቄ የለም። የስጦታ ውለ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ክሱ እስከተመሰረተበት ጊዜ እስከ ጥር 21 ቀን 1999 ዓ.ም ድረስ ደግሞ በሕጉ የተመለከተው የአስር አመት ጊዜ ገደብ አልፎል። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካችን የይርጋ ክርክር ውድቅ ያደረጉት ያላግባብ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህ ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 34508 ሐምል 02 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 69852 ግንቦት 06 ቀን 2001 ዓ.ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ ስጦታውን መሰረት አድርገው የአቀረቡት የቤት ይለቀቅልኝ ጥያቄ በይርጋ የታገደ ነው፣አመልካች ቤቱን ሉያስረክቡ አይገባም ብለናል።
ለክርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።