No summary available.
መጋቢት 21 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሑሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡-
ጉዲዩ ሐሰተኛ የወራሽነት ማስረጃ መሰረት ተደርጎ የተከናወነ የውርስ ሃብት ሽያጭ ውል ይፍረስልን ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የሐረሪ ክልል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካቾች በአሁኑ ተጠሪዎች ላይ መጋቢት 18 ቀን 2000 ዓ.ም አሻሽለው በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም የአመልካቾች አውራሽ ወ/ሮ ታደለች ወ/ገብርኤል በጥር 21 ቀን 1987 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን፣ የሟች ሕጋዊ ወራሾች አመልካቾች እና በክስ ውስጥ ያልገቡ ሁለት ወራሾች መኖራቸውን፣ አንደኛ ተጠሪ ከሟች ወ/ሮ ታደለች ወ/ገብርኤል ጋር ምንም አይነት ለወራሽነት የሚያበቃ ዝምድና ሳይኖራቸው፣ በአንድ በኩል በ1968 ዓ.ም ስጦታ አድርገውልኛል የሚል ሰነድ ለፍርድ አቅርበው ተቀባይነት ሲያጡ ከሟች ጋር የአንድ እናት ልጆች፤
እህትማማቾች ናቸው፣ ላላ ወራሽ የላቸውም በማለት በሐሰት የሚመሰክሩ ምስክሮችን አዘጋጅተው በፍርድ ቤት የወራሽነት ማስረጃ ማግኘታቸውን፣ ይህንኑ ማስረጃ ይዘውም የሟች ወ/ሮ ታደለች ንብረት የሆነውን ቤት ለሁለተኛ ተጠሪ መሸጣቸውን፣ የአንደኛ ተጠሪ ወራሽነት ማስረጃም ሐሰተኛ መሆኑን ዘርዝረው አንደኛ ተጠሪ ከሁለተኛ ተጠሪ ጋር ያደረጉት የሽያጭ ውል እንዱፈርስላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪዎችም ለክሱ በሰጡት መልስ የቤቱ ስመ ሐብት በአንደኛ ተጠሪ ስም የሚታወቅ በመሆኑ አመለካቾች ክስ ለመመስረት መብት (ጥቅም) የላላቸው መሆኑን፣ የሽያጭ ውል ይፍረስልን ጥያቄ በይርጋ የታገደ መሆኑን፣ ሽያጩን በሕጉ አግባብ ያደረጉት በመሆኑ ሉፈርስ እንደማይገባ ገልፀው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ ቤቱ ስመ ንብረቱ የሚታወቀው በአንደኛ ተጠሪ መሆኑን፣ ንብረቱን አንደኛ ተጠሪ ወደ እጃቸው ያስገቡትም በአደራ ሉጠብቁ ተብል ስለመሆኑ አመልካቾች ገልፀው መከራከራቸውን፣ አንደኛ ተጠሪ የሟች ወ/ሮ ታደለች ወ/ገብርኤል ወራሽ መሆናቸውን የሚያሳይ የወራሽነት ማስረጃ ይዘው ባለበት ጊዜ የቤት ሽያጩን ስልጣን ባለው አካል ፉት ቀርበው ያደረጉ ቢሆንም የወራሽነት ማስረጃው ሐሰተኛ መሆኑ መረጋገጡን በመግለፅ አመልካቾች አንደኛ ተጠሪን ከሚጠይቁ በስተቀር የቤት ሽያጭ ውለ ሉፈርስ አይገባም ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካቾች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለሐረሪ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሙለ በሙለ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
አመልካቾች ሚያዚያ 12 ቀን 2001 ዓ.ም በተጻፈ ሦስት ገጽ አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ቤት ላይ ተጠሪዎች የሽያጭ ውለ የፈፀሙት ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ መሆኑ በግልፅ ተረጋግጦ እያለ ሽያጩ ሉፈርስ አይገባም መባለ ያላገባብ ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮ የሽያጩ ውል ሉፈርስ አይገባም መባለ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎ አንደኛ ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ሁለተኛ ተጠሪ በጠበቃቸው አማካኝነት ነሐሴ 18 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ አምስት ገጽ ማመልከቻ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። አመልካቾች በበኩላቸው መስከረም 15 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ሶስት ገፅ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን አጠናክረው ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አከራካሪውን ቤት አንደኛ ተጠሪ የወራሽነት ማስረጃ በመያዝና ስመ ሃብቱን በማዞር ለሁለተኛ ተጠሪ ስልጣን ባለው አካል ፉት ቀርበው የሸጡ መሆኑን፣ በውለ ላይም ለገዥ መድህን ስለመሆናቸው በመግለፅ ግዳታ የገቡ መሆኑን፣ አንደኛ ተጠሪ የያዙት የወራሽነት ማስረጃ ከሽያጩ በኋላ ሐሰተኛ መሆኑ መረጋገጡን፣ የተሸጠው ቤትም የአመልካቾች አውራሽ የሆኑት የወ/ሮ ታደለች ወ/ገብርኤል መሆኑ መረጋገጡን፣ ከሽያጩ በኋላ ሁለተኛ ተጠሪ የስመ ሃብቱን ወደ ራሳቸው አዙረው እየተጠቀሙበት የሚገኙ መሆኑ በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጡ ፍሬ ጉዲዮች መሆናቸውን ነው። የአመልካቾች ክርክር መሰረቱም የአውራሻቸው የግል ንብረት የሆነውን ምንም መብት የላላት አንደኛ ተጠሪ በተጭበረበረ መንገድ ወራሽነት አሳውጀው እና የቤቱን ስመ ሃብት በማዞር መሸጣቸው ሽያጩን ሕጋዊ አያደርገውም በሚል ምክንያት ስለመሆኑም ተገንዝበናል። እኛም በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች ከሕጉ ጋር በሚከተለው መልኩ በማዛመድ ተመልክተናል።
No topics extracted.
በመሰረቱ አንድ ሰው አንድ ንብረት ለላላ ሰው በሕጋዊ መንገድ ሉያስተላልፍ የሚችለው በንብረቱ ላይ መብት ሲኖረው መሆኑ የሚታወቅ ነው። በልላ አገላለፅ በጥበቃ የማይደረግለት ወይም የላለ መብት ወደ ሰው ሉተላለፍ አይችልም። ይህ ተቀባይነት ያለው የሕግ መርሕ ነው። የላላ ሰው ንብረት ለመሸጥ፣ ለማስተላለፍ ወይም በዋስትና ለማስያዝ ወይም የተመደበበትን አገልግልት ለመለወጥ ሕጋዊ የሆነ ስልጣን ሉኖር ይገባል።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አንደኛ ተጠሪ አከራካሪውን ቤት የሸጡት የአመልካቾችን ወይም የአውራሻቸውን ሕጋዊ ስምምነት ወይም ወራሽነት አግኝተው ባይሆንም የሟች ወራሽ መሆናቸውን በፍርድ ቤት አረጋግጠው፣ የቤቱን ስመ ሃብት ከሽያጩ በፉት ከተገቢው የአስተዲደር አካል ከአገኙ በኋላ ሲሆን ሽያጩም ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፉት ስለመሆኑ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195 ድንጋጌ መሰረት ደግሞ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብትነትን በማወቅ በአስተደደር ክፍል የምስክር ወረቀት ሲሰጥ የምስክር ወረቀቱን ያገኘው ሰው የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ባለሃብት ሆኖ ሉቆጠር እንደሚገባ ተመልክቷል። ይህን ማስረጃ የያዘ ሰው ደግሞ ሃብቱን በሕጉ አግባብ ከሸጠ ተግባሩ ሕገ ወጥ የሚባልበት ምክንያት የለውም። አንድ ሰው በሕግ ጥበቃ የተደረገለትን መብት በሕጋዊ መንገድች በልላ ለማስተላለፍ መብት አለውና። በስር ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሳሽ የነበሩት የአሁኗ አንደኛ ተጠሪ ወ/ሮ ሙለ ወልደየስ አከራካሪውን ቤት በስማቸው የባለሃብትነት ምስክር ወረቀት መያዛቸው ንብረቱ የግል ሃብት እንደሆነ የሚያሰቆጥር ሲሆን ይህን ማስረጃ በመመልከት ንብረቱን ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፉት የሚገዛ ሰው ሽያጩን ያከናወነው ከሕግ ውጪ ነው ልባል የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም። በቤቱ ላይ ሕጋዊ መብት የላለው ሰው በውለ ለገዥው መድህን ለመሆን ግዳታ ገብቶ ሽያጩን አከናውኖ ሲገኝም ትክክለኛው ባለሃብት ሉጠይቅ የሚችለው ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጎ የገዛውን ገዥ ሳይሆን ሻጩን ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2882 እስከ 2884 ድረስ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች እንዱሁም ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 997 ድንጋጌ መንፈስ እና ይዘት የምንገነዘበው ነጥብ ነው። በአጠቃላይ ሁለተኛ ተጠሪ አከራካሪውን ቤት የገዙት በሕግ ፉት ተቀባይነት ያለውን ማስረጃ ከያዙት ግለሰብ ሁኖ ሽያጩንም ያከናወኑት ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፉት በመሆኑ ውለ የሚፈርስበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። አመልካቾች በቤቱ ላይ የወራሽነት መብት ያላቸው መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ያላቸው መፍትሓ የሽያጩን ዋጋ ከስር ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሳሽ ከነበሩት ከወ/ሮ ሙለ ወልደየስ መቀበል ነው። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላላገኘነው ተከታዩን ወስነናል።
የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
በአከራካሪው ቤት ላይ የተደረገው ሽያጭ ውል ሉፈርስ አይገባም፣ ሁለተኛ ተጠሪ ቤቱን ሉያስረክቡ አይገባም ብለናል።
አመልካቾች የቤቱን ሸያጭን ገንዘብ .00 (ስልሳ ሺህ) ከወ/ሮ ሙለ ወልደየስ እንዱቀበለ ብለናል። በዚሁ ውሳኔ መሰረት እንዱያስፈፅም ለስር ፍርድ ቤት ግልባጩ ይድረሰው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።