No summary available.
መጋቢት 08 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ድንቁ ወርድፊ ተጠሪ፡- ወ/ሪት ኤደን ድንቁ ወርድፊ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የብድር እዲን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኗ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች እና የአመልካች ባለቤት በሆኑት በወ/ሮ ፀጋዬ ተክላ ላይ ሐምል 23 ቀን 1999 ዓ.ም በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- ተጠሪ በአረብ አገር ሰርተው ከሚያገኙት ደመወዝ ለአመልካችና ለባለቤታቸው ገንዘብ በሐዋላ ልከው ወላጅ እናታቸው ገንዘቡን ተቀብለው ለሚፈልጉት ጉዲይ ማዋላቸውን ገልፀው ክሱን ያስነሳውን ገንዘብ ብር 70,500.00(ሰባ ሺህ አምስት መቶ ብር) ከነሕጋዊ ወለድ እንዱከፍለ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስ ከተጠሪ ላይ የተበደሩት ገንዘብ የላለ መሆኑን፣ለማስረጃነት በቀረበው ሰነድ ላይም ያልፈረሙ በመሆኑ የሚከሰሱበት ሕጋዊ ምክንያት የለም ሲለ ገልፀው ተከራክረዋል። የስር ሁለተኛ ተከሳሽ የነበሩትና የአመልካች ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ፀጋዬ ተክላ ደግሞ የተጠሪን ክስ በማመን መልሳቸውን ሰጥተዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ የአመልካችን መከራከሪያ ነጥቦችን ውድቅ አድርጏ አመልካች እና ወ/ሮ ፀጋዬ ተክላን ለክሱ ኃላፉ በማድረግ ለክሱ ምክንያት የሆነው ገንዘብ በአንድነትና በነጠላ ክሱ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍለ ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ እና ተገቢው ማጣራት ከተደረገ በኋላ በዚህ ፍርድ ቤትም የአመልካች ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ፀጋዬ ተክላ ቀርበው ገንዘቡን ከተጠሪ ወስደው ለጋራ ጥቅማቸው ማዋላቸውን በድጋሚ በማረጋገጣቸው የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ መለ በሙለ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ለማስቀየር ነው።
አመልካች በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ሚያዝያ 14 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሦስት ገጽ የሰበር አቤቱታ ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታቸው ተመርምሮም አመልካች እዲውን ከወ/ሮ ፀጋዬ ተክላ(ከባለቤታቸው) ጋር በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጏ ተጠሪ የካቲት 12 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት ማመልከቻ የበታች ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ተገቢነት በመግለጽ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም ተብል ሉፀና ይገባል ሲለ መልሳቸውን ሰጥተዋል። አመልካች በበኩላቸው የካቲት 22 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት የመልስ መልስ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካችና ወ/ሮ ፀጋዬ ተክላ በትዲር ፀንተው በነበሩበት ወቅት ተጠሪ ገንዘብ ያደበሯቸው ስለመሆኑ መረጋገጡን፣በዚህም ወቅት አከራካሪውን ብርድ አመልካች በሰነደ ላይ ባይፈርሙም ባለቤታቸው የሆኑት ወ/ሮ ፀጋዬ ተክላ መፈረማቸውንና ገንዘቡን ለጋራ ጥቅም ያዋለ መሆኑን ነው።
ብድሩ አመልካች ሳይፈርሙበት በትዲር ወቅት ወ/ሮ ፀጋዬ ተክላ ወስደው በጋራ ጥቅም የዋለ መሆኑ ተረጋግጧል። በእርግጥ ከብር 500.00(አምስት መቶ) በላይ የሆነ ብድር ለማበደር ወይም ለመበደር የሁለቱም ተጋቢዎች ስምምነት ማስፈለጉ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 68/መ/ ስር የተመለከተ ሲሆን ስምምነቱን ያልሰጠው ተጋቢም ውለ እንዱፈርስ ለፍርድ ቤት ጥያቄ በማቅረብ ውለ እንዱፈርስ ማድረግ የሚችል መሆኑን የቤተሰብ ሕጉ ደንግጏ እናገኘዋለን። የሕጉ መንፈስ ውለ የአንደኛው ተጋቢ ስምምነት ሳይኖር በመደረጉ ብቻ ከጅምሩ ውጤት አልባ ነው ወደሚለው ድምዲሜ የማይወስድ ነው። ይልቁንም ስምምነቱን ያልሰጠው ተጋቢ በሕጉ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ውለ እንዱፈርስ እስካላደረገው ድረስ ውለ ውጤት ይኖረዋል። በተያዘው ጉዲይም አመልካች ሳያውቁ የተደረገ ነው ቢባል እንኳ ብድሩ ለጋራ ጥቅም የዋለ መሆኑ እና ፣ውለን እንዱፈርስ ያላደረጉት መሆኑ በሚገባ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው።
ብድሩ በትዲር ወቅት የተወሰደ ከሆነ ደግሞ ለትዲር ጥቅም እንደዋለ ሕግ ግምት የሚወስድበት ሲሆን ለትዲር ጥቅም አለመዋለን የማስረዲት ሸክም ያለባቸው አመልካች እንጂ ላላ ወገን ላሆን አይችልም። ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች የብድር እዲው የጋራ ነው ሲለ የሰጡትን ውሳኔ ከቤተሰብ ሕጉ መንፈስ አንፃር ሲታይ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት አልተቻለም።
በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት በአብላጫ ድምጽ ፀንቷል።
በዚህ ችልት በተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ። ብለናል።
No topics extracted.