No summary available.
የካቲት 12 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- አቶ ካሳ ፊንታ - ጠበቃ ታደሰ መርእድ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ እስካዲር ግጨው - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የልጅ ቀለብን በተመለከተ ለአከፊፈለ ዋስትና ይሆን ዘንድ የአመልካች የግል መኪና ቀለብ ጠያቂዎቹ አስራ ስምንት ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ እንዲይሸጥ፣እንዲይለወጥ ተከብሮ እንዱቆይ የሚል ትእዛዝ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በመጽናቱ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ተብል የቀረበውን አቤቱታ የሚመለከት ነው።
የአመልካች ጠበቃ ግንቦት 11 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሦስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ትእዛዝ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል ተጠሪ ቀርበው ታህሳስ 28 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገጽ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። የአመልካች ጠበቃ በበኩላቸው ጥር 17 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገጽ ማመልከቻ የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል። ከዚህም በኋላ ይህ ችልት ግራ ቀኙን በቃል ሰምቷል።
ጉዲዩንም አቤቱታው ከቀረበበት ትእዛዝ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል።
እንደመረመረውም አመልካች የቀለብ ጥያቄው የሚመለከታቸው መሆኑን ሳይክደ የግል ንብረታቸው የሆነው ሕፃናቱ አስራ ስምንት ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ ሉከበር አይገባም የሚለት ለላላ እዲ አከፊፈል መኪናውን ለመሸጥ ካሰቡ ችግር የሚፈጥር ነው በሚል ምክንያት ነው። ይህ ችልትም መኪናው ላይ የተላለፈው እግድ እንዱነሳላቸው ከፈለጉ ጥሬ ገንዘቡን ሙለ በሙለ በአደራ ሉያስቀምጡ የሚችለበት መንገድ ካለ በችልት የአመልካችን ጠበቃ ጠይቆ ከሶስት እስከ አራት ወራት ድረስ ያለውን የቀለብ ገንዘብ ካልሆነ ሕፃናቱ እስከ አስራ ስምንት ዓመት ድረስ ሉከፈላቸው የሚችለውን የቀለብ ገንዘብ ሙለ በሙለ በአደራ ሉያስቀምጡ የማይችለ መሆኑን አረጋግጠዋል። ከዚህም በላይ ለሁለቱ ህፃናት በአሁኑ ጊዜ የተቆረጠው የቀለብ ገንዘብ ብር 450.00(አራት መቶ ሃምሳ) ሲሆን ይህ ገንዘብ ሕፃናቱ አካለ መጠን እኪሞላቸው ድረስ ይህ የገንዘብ መጠን ብቻ ለቀለብ ይበቃል ተብል ሉታሰብ የማይችል መሆኑን ከነባራዊው ዓለም እውነታ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። ስለሆነም የአመልካች የግል ንብረት ለህፃናቱ የቀለብ ጥያቄ አከፊፈል ዋስትና ይሆን ዘንድ መከበሩ ስለቀለብ የተደነገጉትን የቤተሰብ ሕግ ድንጋጌዎችንና በሕገ መንግስቱ የተመለከተቱትን የህፃናቱን መብት የሚያስከበር ነው ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.