No summary available.
የካቲት 3 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- አቶ ፍሬዘውድ ተካ ጏጂ - ቀረቡ ወ/ሮ ትርሲት ተካ ጏጂ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ ሰለሞን ኃ/ማሪያም - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የውርስ ንብረት የሚመለከት ነው። የአሁኑ አመልካቾች በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ ነበር። የክሱ ምክንያትም ከአያታቸው በኑዛዜ የተላለፈላቸውን የቤት ቁ. 1133 በንፊስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ቀበላ 03 ክልል የሚገኝ ቤት ተጠሪ አላአግባብ ይዞ እየተጠቀመ በመሆኑ እንዱለቅ እንዱወሰን የሚል ነው። ተጠሪም በሰጠው መልስ አመልካቾች በኑዛዜ ተሰጠን የሚለት ቤት የተናዛዧ ባለመሆኑ ለመክሰስ መብት የላቸውም እንዱሁም ቤቱን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ክስ ያልቀረበ በመሆኑ በይርጋ ሉታገድ ይገባል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል። በፍሬ ነገር ረገድም ቤቱን የሰሩት የእሱ አባት እና እናት መሆናቸውን እና ቤቱ በስጦታ ለእህቱ የተሰጠ ስለመሆኑ እሱም እህቱ በሰጠችው ውክልና ይዞ እየተጠቀመ መሆኑን ጠቅሶ ክሱ ውድቅ እንዱደረግ አመልክቷል።
ጉዲዩ የቀረበለት የፋ/የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰጠው ፍርድ አመልካቾች ክስ ያቀረቡበት የቤት ቁ.
1133 የሟች ወ/ሮ ጌጤ ሸኔ ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ የለም በማለት አመልካቾች በተጠቀሰው ቤት ላይ ባለመብት ስለመሆናቸው አላረጋገጡም በሚል ክስ ለማቅረብ የላቸውም ሲል የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33/2/ እና 244/2/መ በመመርኮዝ ክሱን ውድቅ አድርጓል። ይግባኝ የቀረበለት ከፍተኛ ፍ/ቤትም የሥር ፍ/ቤት ፍርድን አጽንቷል። የአመልካቾች ጠበቃ ታህሣሥ 20/2001 ዓ.ም ጽፍ ያቀረቡት አቤቱታ ይዘት ባጭሩ ሟች ወ/ሮ ጌጤ ሸኔ ጥቅምት 24/1989 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ በመ/ቁ. 265 ላይ መቃወሚያ ቀርቦ ተቀባይነት ሳያገኝ ኑዛዜው በፍርድ ቤት የፀደቀ ስለሆነ ይህንን ወደ ጏን በመተው የባለቤትነት ማስረጃ አልቀረበም በሚል የሥር ፍ/ቤት ክሱን ወድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ነው ተብል እንጂሻር እና እንደክሳቸው እንዱወሰን የሚል ነው።
ይህ ሰበር ሰሚ ችልትም የቀረበውን የሰበር አቤቱታ መርምሮ የአመልካቾች የኑዛዜ ወራሽነት በመ/ቁ.
265 ተረጋግጦ እያለ እና ቀደም ሲል የቀረበው መቃመሚያ ውድቅ ተደርጏ አመልካቾች የኑዛዜ ወራሽ ናቸው ተብል ከተወሰነ በኋላ ይህንኑ ቤት ለማስለቀቅ ያቀረቡት ክስ ውድቅ መደረጉ በግባቡ ስለመሆኑ ለመመርመር ተጠሪን አስቀርቧል። ተጠሪ መስከረም 15/2002 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርቧል። ይዘቱም ባጭሩ ሲታይ ኑዛዜ ለማጽደቅ የቀረበው አቤቱታ ላይ ተከራካሪ የነበሩት ተጠሪ እና ወ/ሮ ጉድ ጏጂ የነበሩ መሆኑንና ኑዛዜው መጽደቁ በሐብቱ ላይ የሚቀርበውን ክርክር የሚያግድ ላሆን እንደማይችል በማለት የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ እንዱፀና አመልክቷል።
ይህ ሰበር ሰሚ ችልትም የግራ ቀኙን መልስ እና የመልስ መልስ ከመረመረ በኋላ ታህሣሥ 22/2002 ዓ.ም በዋለው ችልት ቤቱ ያለበትን ይዞታ እና ቤቱ በማን እንደተሰራ ግራ ቀኙን በቃል በማነጋገር ጉዲዩን በማጣራት ግንዛቤ አግኝቷል። የግራ ቀኙ ክርክር እና የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተው ሲሆን በዚሁም መዝገቡን መርምረናል። እንደመረመርነውም ምላሽ የሚሻው ነጥብ ኑዛዜ በፍ/ቤት በመጽደቁ አመልካቾች በንብረቱ ላይ ባለመብት መሆናቸውን ማረጋገጫ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነው።
በመሰረቱ ኑዛዜ ሕጉ ያስቀመጠውን ሥርአት እና መስፈርቶች አሟልቶ ከተገኘ በራሱ በሕግ ረገድ ውጤት የሚሰጠው ሰነድ እንጂ በፍርድ ቤት ቀርቦ ማፀደቅ አስፈላጊ እንዲልሆነ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ.
17058 በተሰጠ ውሳኔ የተሰጠ የሕግ ትርጉም መረዲት ይቻላል ከዚህም አልፍ ኑዛዜው በፍ/ቤት ቀርቦ መጽደቅ ላልች ባለመብቶች ክርክር ወይም መቃመሚያ እንዲያቀርቡ ሉገድባቸው እንደማይችል በዚሁ ተጠቃሽ መዝገብ ውሳኔ ተሰጥቶበታል።
ከዚህ አንፃር አመልካቾች በመ/ቁ. 265 ኑዛዜ ለፍ/ቤት ማፀደቃቸው በራሱ በኑዛዜ በተሰጠው ቤት ላይ ባለሐብት ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ነው ተብል ሉወሰድ የሚችል ብቸኛ ማስረጃ አይደለም። ከዚህም ላላ ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት ቤት የተናዛዧ ስለመሆኑም በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1195 በተደነገገው መሰረት ከአስተዲደር ክፍል የተሰጠ ማረጋገጫ አልቀረበም ይልቁንም ከሥር ፍ/ቤት መዝገብ ለመረዲት እንደተቻለው የቤት ቁ. 1133 የሟች ወ/ሮ ጌጤ ሸኔ ስለመሆኑ ለማጣራት ሥር ፍ/ቤት ከክፍለ አስተዲደር ማህደር አስቀርቦ እንደተመለከተ እና ቤቱ የሟች ስለመሆኑ አስረጅ ሰነድ እንዲልቀረበ ተገልጿል።
No topics extracted.
ይህ በሆነበት ሁኔታ ደግሞ ኑዛዜ አጸድቀናል በሚል ምክንያት ብቻ አመልካቾች ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት ማጣቱ የሕግ ስህተት ነው ልባል የሚቻልበት ምክንያት አላገኘንም።
ስለሆነም የሥር ፍ/ቤቶች የአመልካቾችን የዲኝነት ጥያቄ ውድቅ ለማድረግ የሰጡት ምክንያትና ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል ለማለት ስላልተቻለ ባለበት ሁኔታ አጽንተናል።
የፋ/የመ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 09779 የሰጠው ፍርድ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 64033 የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
ግራ ቀኙ የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።