No summary available.
የካቲት 24 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሐይ ታደሰ ኂሩት መለሰ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ዓለማየሁ ከተማ - ጠበቃ ኃይለማሪያም ኢትቻ ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የጋራ ውርስ ሃብት ሽያጭ ውል ይፍረስ ጥያቄን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁኑ ተጠሪዎች በአሁኑ አመልካች እና በወ/ሮ አበበች ጫካ ላይ ሕዲር 27 ቀን 1999 ዓ.ም በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም በአዱስ አበባ ከተማ በቀድሞው አጠራር ወረዲ 13 ቀበላ 21 በአሁኑ አጠራር የካ ክፍለ ከተማ ቀበላ 07 ውስጥ የሚገኘውን ቁጥሩ 266/2/ የሆነውን ቤትና ይዞታ ከእናታቸው ከወ/ሮ ጥሩነሽ ወልደየስ ከወ/ሮ አበበች ጫካ ጋር በውርስ የተላለፈላቸው መሆኑን፣ቤቱ ለሰባት ወራሾች ለማከፍፈል አመቺ ካለመሆኑ በላይ ከእናታቸው መታሰቢያነት እንዱሆንና ወራሾችንም በቤቱ ላይ ለመገናኘት ይችለ ዘንድ ከሚሸጥ ይልቅ ቤት ያልነበራት ወ/ሮ አበበች ቤቱ ውስጥ እንድትኖርበትና ማንኛውም ወራሽ በቤቱ መኖር ከፈለገ መኖር እንደሚችል በቤተ ዘመድ ጉባኤ ውሳኔ መሰጠቱን፣ይህ ሆኖ እያለ ወ/ሮ አበበች ጫካ የሟች ወ/ሮ ጥሩነሽ ወልደየስ ብቸኛ ወራሽ በማስመሰል የወራሽነት ማስረጃ አውጥተው ቤቱን በስሟ ካዛወረች በኋላ ቤቱን ለአሁኑ አመልካች በብር 450,000(አራት መቶ አምሳ ሺህ ብር) በመሸጥ ስመ ሐብቱ ሁለ በገዥው ስም እንዱዛወር ማድረጓን በመግለጽ በውርስ ንብረታችን ላይ የተደረገው የሽያጭ ውል እንዱፈርስ ይወሰንልን በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካችም ለክሱ በሰጡት መልስ፡- የሽያጭ ውል ይፍረስልን ጥያቄ በይርጋ የታገደ መሆኑን፣ሽያጩን በሕጉ አግባብ ያደረጉት በመሆኑ ሉፈርስ እንደማይገባ ገልፀው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ ቤቱ የውርስ ሃብት መሆኑን በማረጋገጥ እና ቤቱ የተሸጠው ከሁለ ወራሾች ፈቃድ ውጪ በመሆኑ ሽያጩ በሕግ ፉት ሉፀና የሚችልበት ምክንያት አለመኖሩን በመግለጽ ውለ ፈራሽ ነው በማለት ተዋዋይ ወገኖች ወደ ነበሩበት እንዱመለሱ፣አመልካች የሽያጭ ገንዘቡን ብር 270,000(ሁለት መቶ ሰባ ሺህ ብር) ከወ/ሮ አበበች ወልደየስ እንዱቀበለ፣ቤቱን አመልካች ለወራሾች እንዱመልሱ ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ጠበቃ ሐምል 07 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ሦስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት አመልካች እጃቸው ውስጥ ያስገቡት ሕጋዊ በሆነ መንገድ መሆኑ በግልጽ ተረጋግጦ እያለ ሽያጩ ፈራሽ ነው መባለ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም ይገባዋል በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በስር አንደኛ ተከሳሽ በነበሩት በወ/ሮ አበበች ወልደየስ ስም ተመዝግቦ የሚታወቀውን አከራካሪውን ቤት ውል ማዋዋል ሥልጣን ባለው አካል ፉት በመቅረብ አመልካች መግዛታቸው ተረጋግጦ እያለ ውለ ፈራሽ ነው ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጏ አንደኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ጥቅምት 11 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገጽ ማመልከቻ፣የሁለተኛ ተጠሪ ወራሾች ደግሞ ታህሣሥ 27 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ አምስት ገጽ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። የመልሳቸው ይዘትም ባጭሩ፡- ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የጋራ ውርስ ንብረት ላይ በተጭበረበረ መንገድ በውልና ማስረጃ የተደረገ የሽያጭ ውል ሕጋዊ ላሆን የሚችልበት ምክንያት ስለላለ የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም ተብል ሉፀና ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። የአመልካች ጠበቃም በተጠሪዎች መልስ ላይ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
No topics extracted.
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አከራካሪው ቤት ተጠሪዎች ከወ/ሮ አበበች ጫካ ጋር ከሟች ወ/ሮ ጥሩነሽ ወልደየስ በውርስ የተላለፈላቸው መሆኑን፣ይህንን ቤት በስር ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሳሽ የነበሩት ወ/ሮ አበበች ጫካ ሲያስተዲድሩትና ሲጠቀሙት ቆይተው የቤቱን ስመ ሐብት ወደ ራሳቸው በማዞር ለአሁኑ አመልካች በውልና ማስረጃ ፉት በተደረገ የሽያጭ ውል በብር 450,000(አራት መቶ ሃምሳ ሺህ) መሸጣቸውን፣ከዚህም በኋላ አመልካች የስመ ሃብቱን ወደ ራሳቸው አዙረው እየተጠቀሙበት የሚገኙ መሆኑ በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጡ ፍሬ ጉዲዮች መሆናቸውን ነው። የተጠሪዎች ክርክር መሰረቱም የወራሾች የጋራ የሆነው ንብረት የሁለም የጋራ ባሃብቶች ስምምነት ሉኖር ሲገባ ወ/ሮ አበበች ጫካ በተጭበረበረ መንገድ ወራሽነት አሳውጀው እና የቤቱን ስመሃብት በማዞር መሸጣቸውን ሽያጩን ሕጋዊ አያደርገውም በሚል ምክንያት ስለመሆኑም ተገንዝበናል። እኛም በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች ከሕጉ ጋር በሚከተለው መልኩ በማዛመድ ተመልክተናል።
በመሰረቱ የውርስ ሃብት አከፊፈለ እስኪፈፀም ድረስ በወራሾቹ መካከል ሳይነጣጠል እንደሚቆይ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1060/1/ ስር የተመለከተ ሲሆን የጋራ የሆነውን ንብረት ለመሸጥ፣ለማስተላለፍ ወይም በዋስትና ለማስያዝ ወይም የተመደበበትን አገልግልት ለመለወጥ የጋራ ባለሃብቶቹ ሁለ ስምምነት አስፈላጊ ስለመሆኑ ደግሞ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1266 ድንጋጌ ያሳያል።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም የስር አንደኛ ተከሳሽ የነበሩት ወ/ሮ አበበች ጫካ አከራካሪውን ቤት የሸጡት የተጠሪዎችን ስምምነት አግኝተው ባይሆንም የቤቱን ስመ-ሐብት ከሽያጩ በፉት ከተገቢው የአስተዲደር አካል ከአገኙ በኋላ ሲሆን ሽያጩም ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፉት ስለመሆኑ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው።
በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1195 ድንጋጌ መሰረት ደግሞ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነትን በማወቅ በአስተዲደር ክፍል የምስክር ወረቅት ሲሰጥ የምስከር ወረቀቱን ያገኘው ሰው የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብት ሆኖ ሉቆጠር እንደሚገባ ተመልክቷል። ይህን ማስረጃ የያዘ ሰው ደግሞ ሃብቱን በሕጉ አግባብ ከሸጠ ተግባሩ ሕገ ወጥ የሚባልበት ምክንያት የለውም። አንድ ሰው በሕግ ጥበቃ የተደረገለትን መብት በሕጋዊ መንገድች ለላላ ለማስተላለፍ መብት አለውና። በስር ፍ/ቤት አንደኛ ተከሳሽ የነበሩት ወ/ሮ አበበች ጫካ አከራካሪውን ቤት በስማቸው የባለሃብትነት ምስክር ወረቀት መያዛቸው ንብረቱ የግል ሃብት እንደሆነ የሚያስቆጥር ሲሆን ይህን ማስረጃ በመመልከት ንብረቱን ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፉት የሚገዛ ሰው ሽያጩን ያከናወነው ከሕግ ውጪ ነው ልባል የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም። በቤቱ ላይ ሕጋዊ መብት የላለው ሰው ሽያጩን አከናውኖ ሲገኝም ትክክለኛው ባለሃብት ሉጠይቅ የሚችለው ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጏ የገዛውን ገዥ ሳይሆን ሻጩን ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 997፣እና 2882 እስከ 2884 ድረስ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መንፈስ እና ይዘት የምንገነዘበው ነጥብ ነው። በአጠቃላይ አመልካች አከራካሪውን ቤት የገዙት በሕግ ፉት ተቀባይነት ያለውን ማስረጃ ከያዙት ግለሰብ ሆኖ ሽያጩንም ያከናወኑት ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፉት በመሆኑ ውለ የሚፈርስበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። ተጠሪዎች በቤቱ ላይ የጋራ ወራሽነት መብት ያላቸው መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ያላቸው መፍትሄ የሽያጩን ዋጋ ከስር ፍ/ቤት አንደኛ ተከሳሽ ከነበሩት ከወ/ሮ አበበች ጫካ መቀበል ነው።
በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስለአገኘነው ተከታዩን ወስነናል።
348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በአከራካሪው ቤት ላይ የተደረገው ሽያጭ ውል ሉፈረስ አይገባም፣አመልካች ቤቱን ሉያስረክቡ አይገባም ብለናል።
ተጠሪዎች በቤቱ ላይ ባላቸው ድርሻ መሰረት የሽያጩን ገንዘብ ከወ/ሮ አበበች ጫካ በልላ ክስ የመቀበል መብታቸውን ይህ ውሣኔ አያስቀርም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።