No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 24 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሃይ ታደሰ ሂሩት መለሰ አለማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ገነት በቀለ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ትዕግስት አሰፊ - ቀረቡ
ለክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ የጀመረው በአድአ ወረዲ ፍ/ቤት ነው። አመልካች በሁለት ግለሰቦች ላይ በመሰረቱት ክስ ተከሳሾች ሞግዚት ለሆኑላቸው ልጃቸው በውርስ ከአባታቸው ሉተላለፍላቸው የሚገባውን ቤት ስለያዙ እንዱመልሱላቸው ጠይቀው ፍ/ቤቱ ተከሳሾቹ ቤቱን እንዱመልሱ ወስኗል። ከዚህ በኋላ ተጠሪ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 መሰረት መቃወሚያ በማቅረብ ቤቱን ከስር ተከሳሾች ገዝተው የባለቤትነት ስሙ በስማቸው ያዛወሩ በመሆኑ ውሳኔው እንዱሰረዝላቸው አመልክተዋል። ፍ/ቤቱም ሁለንም ወገኖች አስቀርቦ ክርክራቸውን ከሰማ በኋላ ቀደም ሲል የተሰጠው ውሳኔ የሚሰረዝበት ምክንያት የለም በማለት ተጠሪን መቃወሚያ ውድቅ አድርጓል። በዚህ ውሳኔ ላይ ተጠሪ በምስ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ ተጠሪን ቤቱን ያገኙት በህጋዊ መንገድ ገዝተው በመሆኑ ሉያስረክቡ አይገባም በማለት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ሽሯል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ላይ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ቀጥልም ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ቢያቀርቡም ቅሬታቸው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ሲሆን ቅሬታው በአጭሩ ተጠሪ ቤቱን የገዙት መብት ከላላቸው ሰዎች በመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሳኔ ሉሻር ይገባል የሚል ነው። ይህ ችልትም የአመልካች አቤቱታ ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ የግራ ቀኙ የቃል ክርክር ተሰምቷል። ችልቱም መዝገቡን መርምሯል።
ከፍ ሲል እንደተመለከትነው አመልካች ክስ ያቀረቡት ከአባታቸው በውርስ ሉተላለፍላቸው የሚገባውን ንብረት ለመረከብ ሲሆን ክስ የመሰረቱት ወራሽ ነን በሚለ ግለሰቦች ላይ ነው። ከመዝገቡ የስር ተከሳሾች ክርክር የተነሳበትን ቤት የባለቤትነት ስም በስማቸው በማዛወር በ1993 ዓ.ም ቤቱን ለተጠሪ መሸጣቸውን ተረድተናል።
የስር ተከሳሾች ቤቱን በሚሸጡበት ወቅት የባለቤትነት ምስክር ወረቀት በስማቸው አግኝተው የቤቱ ባለቤት ሆነዋል። በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1195 የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብትን በማወቅ በአስተዲደር ክፍል የባለሃብትነት ምስክር ወረቀት በተሰጠ ጊዜ ምስክር ወረቀቱን ያገኘው ሰው የማይንቀሳቀሰው ንብረት ባለንብረት ሆኖ እንደሚቆጠር ተመልክቷል። በመሆኑም ሽያጩ በተከናወነበት ጊዜ ቤቱ የሻጮቹ የግል ንብረት ሲሆን ተጠሪም ቤቱን የገዙት የሻጮቹን የባለቤትነት ምስክር ወረቀት በማየት ነው። በልላ በኩል ደግሞ የቤቱም ሽያጭ ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው የውልና ማስረጃ ጽ/ቤት መደረጉንና ስሙም ወደ ገዢዋ መዛወሩን መገንዘብ ችለናል። በአጠቃላይ ተጠሪ ቤቱን በገዙበት ወቅት ቤቱ በሻጮች ስም የነበረ በመሆኑ ሽያጩን ህጉ በሚጠይቀው የአፃፃፍ ስርዓት መሰረት ማከናወናቸው ተጠሪዋ ቤቱን የገዙት በቅን ልቦና መሆኑን ያመለክታል። በመሆኑም ምናልባት አመልካች በንብረቱ ላይ ድርሻ አለን የሚለ ከሆነ ስር ተከሳሾችን ከሚጠይቁ በቀር ተጠሪ በህጋዊ መንገድ የገዙትን ቤት እንዱያስረክቡ የሚደረግበት የህግ አግባብ ስለላለ ውሳኔው መሰረታዊ ህግ ስህተት ተፈፅሞበታል ማለት አልተቻለም። ስለሆነም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የምስ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ መጋቢት 30 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፣ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ ጥር 8 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ፣ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ መጋቢት 09 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ፀንቷል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.