No summary available.
የካቲት 24 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሐይ ታደሰ ሑሩት መለሰ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ሚስስ ፍራንሱዊስ ፖስተር - ጠበቃ ፈቃደ ሞላ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የጉዱፈቻ ስምምነት የሚፈርስበትን የሕግ አግባብ የሚመለከት ሲሆን ክርክር የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ብርሃነ ሕይወት የሕጻናት እና ቤተሰብ መርጃ ድርጅት የተባለው ባሁኑ ተጠሪዎች ላይ በመሰረተው ክሰ መነሻ ነው። ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለውም የአሁኑ ተጠሪዎች ሕፃን ቱለን በጉዱፈቻ ለመውሰድ በመጠየቃቸው የአሁኑ አመልካች በኃላፉነት የሚመሩት ድርጅት ሕፃኑን በስር ፍርድ ቤት አመልካች ከነበረው ብርሃነ ሕይወት የሕፃናትና ቤተሰብ መርጃ ድርጅት ተቀብል የፍርድ ቤት ስርዓቱን በማከናወን ላይ እያለ ተጠሪዎች ሕጻኑን የመውሰድ ሃሳባቸውን በመቀየራቸው የጉዱፈቻ ስምምነት እንዲይጸድቅ ከውሳኔ በፉት ግልጽ ደብዲቤ በመጻፍ ቢያሳውቁም ይህ ደብዲቤ በወቅቱ ለፍርድ ቤቱ ባለመድረሱ የጉዱፈቻ ስምምነቱ መጽደቁን ለተጠሪዎች ፍርድ ቤቱ የወሰነ ስለመሆኑ የነገራቸው ቢሆንም ሕጻኑን ላለመውሰድ በወሰደት ውሣኔ በመጽናታቸው ሕፃን ቱለ የአሁኑ አመልካች በሚያስተዲድሩት ድርጅት ጊዜያዊ ማቆያ ውስጥ ለመቆየት በመገደደ ማቆያው ለወደፉት የጉዱፈቻ ወላጅ የሆኑትን የአሁኑን ተጠሪዎች ድርጊት የሕፃኑን የወደፉት ሕይወት እና እድገት በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሰጋ በመሆኑ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ መሰረት እንዱሰረዝ ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ ማቅረቡን፣ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተጠሪዎች አድራጏት የሕፃኑን ሕይወት በአደጋ ላይ የሚጥል ስለመሆኑ አልተረጋገጠም በሚል ምክንያት ሳይቀበለው መቅረቱን ነው። በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሙለ በሙለ አጽንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ጠበቃ የካቲት 27 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታው ተመርምሮም በይግባኝ በነበረው የክርክሩ ሂደት የተጠሪዎች ወኪል ቀርበው የጉዱፈቻ ውለ ቢፈርስ ተቋውሞ የለኝም እያለ ፍርድ ቤቱ ውለ ሉፈርስ አይገባም በማለት መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጏ ለተጠሪዎች በጋዜጣ ጥሪ ቢደረግላቸውም የቃል ክርክሩ በሚሰማበት ወቅት ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ተደርጎአል።
የክርክሩ አመጣጥ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ጉዲዩን ለስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ግልባጭ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር መርምሮታል።
በላለበት የሚታይ ነው የጉዱፈቻ ስምምነት ከፀደቀ በኋላ በማናቸውም ምክንያት ሉፈርስ የማይችል ስለመሆኑ በፀንሰ ሃሳብ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ የተሻሻለው የፋዳራለ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 195(1) የሚያሳይ ቢሆንም የዚሁ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ ሁለት የጉዱፈቻ ስምምነት የሚፈርስባቸውን ምክንያቶችን ደንግጓል። የዚህ ድንጋጌ መንፈስ ሲታይም በጉዱፈቻ አድራጊው ልጁን በዓለም አቀፍ የሕጻናት እና ሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን በሚፃረርና የልጁን ጥቅምና ደህንነት በሚጎዲ አኳኋን መያዙን ማረጋገጥ የሚያስችለ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ የጉዱፈቻ ስምምነቱ እንዱቀጥል ማድረግ የሚያስገኘው ፊይዲ ባለመኖሩ ጉዲዩን በሚመለከተው ማንኛውም አመልካች ጠያቂነት መሰረዝ እንደሚቻል ታመኖበት ድንጋጌው መቀመጡን የተሻሻለው የፋዳራለ የቤተሰብ ሕግ ሐተታ ምክንያት ያስገነዝባል።
ሕጉ ጉዱፈቻ በሚወሰደት ልጆች ላይ በተጨባጭ እና በተግባር የሚያጋጥሙ ችግሮችን ማገናዘብ የሚጠበቅበት በመሆኑ የድንጋጌው መካተት የሕፃናትን ጥቅምና ደህንነት ከመጠበቅ አኳያ ጠቀሜታው የጎላ ስለመሆኑም የሚታመን ነው። ድንጋጌው በአተረጓጏም ላይ ጥንቃቄ ካልተደረገ የጉዱፈቻ ስምምነት እንዱሰረዝ ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው በልጁ አኗኗርና አያያዝ እንዱሁም በወደፉት ሕይወቱ ላይ በተጨባጭ የደረሰ ጉዲት ወይም ወደፉት ሉደርስ የሚችል ጉዲት ስለመኖሩ ማረጋገጥ በሚቻልበት ጊዜ ይሆናል ፍርድ ቤቱም የስምምነቱ መሰረዝ የሚያስገኘው ጠቀሜታ በሚገባ ማጤንና መመዘን የሚጠበቅበት ስለመሆኑ የሕግ መንፈስና ይዘት ያሳያል በመሰረቱ ጉዱፈቻ በሕግ ጥበቃ የሚያስፈልገው በዋናነት የልጁን ጥቅም ለመጠበቅ ሲባል ነው።
የሕፃናትና ጥቅም ለመጠበቅ ሲባል የተለያዩ ስምምነቶች በዓለምና በአህጉር ደረጃ ተፈርመው በስራ ላይ /እየተተገበሩ/ ይገኛለ። ከስምምነቶች ውስጥም የሕጻናት መብቶች ኮንቬንሽንና የአፍሪካ ሕፃናት መብቶችና ደህንነት ቻርተር ተጠቃሾች ናቸው። ሐገራችን ኢትዮጵያም የሕጻናት መብቶች ኮንቬንሽንን ህዲር 29 ቀን 1984 ዓ.ም የአፍሪካ ሕጻናት መብቶችና ደህንነት ቻርተርን ደግሞ እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 02 ቀን 2002 አጽድቃለች።
ከእነዚህም በተጨማሪ የሕጻናትን መብትንና ደህንነትን በሚመለከት የፋዳራለ ሕገ-መንግሥት የተሻሻለው የፋዳራለ የቤተሰብ ሕግ እና ላልች ሕጏች በስራ ላይ ይገኛለ። በዓለም አቀፍም በአህጉርም ሆነ በአገር ደረጃ ያለት እነዚህ ሕጏች መሰታዊ መርሆዎችን ይዘዋል። በእነዚህ ሕጏች ከተካተቱት መሰረታዊ መርሆዎች አንደ ሕጻናትን በሚመለከቱ ጉዲዮች ለሕጻናት ጥቅምና ደህንነት (The Best interest of the child) ቅድሚያ መስጠት የሚለው መርህ ይገኝበታል።
የኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ-መንግሥት ኢትዮዽያ ያፀደቀቻቸውን የዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የአገሪቱ የሕግ አካል መሆናቸውን በአንቀጽ 9(4) ስር ከመደንገጉና በሕገ-መንግሥቱ በስፊት ሽፊን የተሰጣቸው መሰረታዊ የመብቶችና የነጻነቶች ድንጋጌዎች ሀገሪቱን ከተቀበለቻቸውና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሕግጋት ስምምነቶች ወይም ሰነድች መርሆዎች ጋር በተጣጣመ መንገድ መተርጏም ያለበት ስለመሆኑ ከማስቀመጡም በተጨማሪ የሕጻናትን ልዩ ችግር ከግምት ውስጥ ያስገቡ ንዐስ ድንጋጌዎች የያዘ አንቀጽ 36 ደንግጓል። የዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ ሁለት ሕፃናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች በሚወሰደበት ጊዜ ሁለ የመንግስታዊ ወይም የበጏ አድራጏት ተቋማት እንዱሁም ፍርድ ቤቶችንና አስተዲደር ባለስልጣናት ወይም የሕግ አውጪው አካላት የሕጻናትን ደህንነት በቀደምትነት መታሰብ ያለበት ስለመሆኑ አስገዲጅነት ባለው መልኩ ደንግጓል። ይህንኑ የሕገ-መንግሥቱ ድንጋጌ ለማስፈፀም የወጡ ፖሉሲዎች ወይም ሕጏችም መንፈሳቸው ሲታይ ለሕፃናት መብትና ደህንነት በተገቢው ሁኔታ የማስከበር ዓላማን ግንዛቤ ውስጥ ያስገቡ ናቸው ተብል ይታሰባል።
ጉዱፈቻ ሕፃናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች ተብለው በሕገ-መንግሥቱ ከተጠቀሱት ነገሮች አንደ መሆኑ የሚያከራክር ነጥብ ካለመሆኑም በላይ ሕገ- መንግሥቱ በአንቀጽ 36(5) ስር መንግሥት ለእጓለማውታን ልዩ ጥበቃ እንደሚያደርግላቸው በጉዱፈቻ የሚያድጉበትን ስርዓት የሚያመቻቹና የሚያስፊፈ እንዱሁም ደህንነታቸውንና ትምህርታቸውን የሚያራምደ ተቋሞች እንዱመሰርቱ እንደሚያበረታታ በግልጽ አስቀምጧል።
ከዚህ ሁለ መገንዘብ የሚቻለው የጉዱፈቻ ጉዲይ ከሕገ-መንግሥቱ ከተቀመጠው መርህ ኢትዮጵያ ካፀደቀቻቸው የሕፃናት መብት ኮንቬንሽን እንዱሁም ከተሻሻለው የፋዳራለ ቤተሰብ ሕግና ከላልች አግባብነት ካላቸው ሰነድች ይዘትና መንፈስ በጥንቃቄ መታየት ያለበት መሆኑን ነው። ይህ ችልት አግባብነት ያላቸውን ሕጏች በመመርመርም የሕፃናት መብትና ጥቅም ለማስከበር በቀደምትነት ላታይ የሚገባው መርህ የሕፃናት ጥቅምና ደህንነት (the best interest of the child) ስለመሆኑ በመ/፣35710 እና በላልች በርካታ መዛግብት አስገዲጅነት ያለውን ውሳኔ ሰጥቷል።
ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸው ሕጏች ይዘታቸው ከላይ የተመለከተውን የሚመስል ሲሆን ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች ሕፃን ቱለ ከተጠሪዎች ጋር የተደረገለት የጉዱፈቻ ውል እንዱፈርስ ጥያቄ ያቀረቡት ተጠሪዎች ሕፃኑን ላለመውሰድ በመግለጻቸውና በውሳኔያቸውም በመጽናታቸው ሕፃን ቱለ አመልካች በሚያስተዲድሩት ጊዜያዊ ማቆያ ውስጥ ለመቆየት ግድ ያለ መሆኑን ማቆያውም ለሕፃኑ ሕይወቱ የሚያስፈልጉትን ነገሮችን ያሟላ ባለመሆኑና ለላላ ወላጅ ለመስጠት ባለመቻለ በሕፃኑ የወደፉት እድገት የተጠሪዎች አድራጏት ከፍተኛ ጉዲት የሚያደርስ መሆኑን በመግለጽ ነው። የበታች ፍርድ ቤተች ተጠሪዎች ሕፃን ቱለን ላለመውሰድ በወሰደት ውሳኔ መጽናታቸውን አረጋጋጠው የአመልካችን ጥያቄ ሳይቀበለት የቀሩት ተጠሪዎች ሕፃኑን ካለመውሰድ የወሰኑት ውሳኔ ሕፃኑ አላስደሰተንም፣ ህጻኑን ለመውሰድ ፍላጏት አላሰደሩም፣ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 195(2) ስር የተመለከቱት ምክንያቶች አልተሟለም በሚል ምክንያት ሆኖ በልላ ምክንያት የተደገፈ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም በማለት ነው።
ከፍ ብለን እንደተመለከትነው በጉዱፈቻ አድራጊው ልጁን በዓለም አቀፍ የሕፃናት እና ሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን በሚፃረርና የልጁን ጥቅምና ደህንነት በሚጏዲ አኳኋን መያዙን ማረጋገጥ የሚያስችለ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ የጉዱፈቻ ስምምነቱ እንዱቀጥል ማድረግ የሚያስገኘው ፊይዲ ባለመኖሩ ጉዲዩን በሚመለከተው ማንኛውም አመልካች ጠያቂነት መሰረዝ እንደሚቻል በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 195 እና 196 ተደንግጓል። አንቀጽ 195(2) በተለይ ሲታይም ጉዱፈቻ አድራጊው በጉዱፈቻ የተቀበለውን ልጅ እንደልጅ ከማሳደግ ፊንታ በባርነት ወይም በባርነት በሚመስል ሁኔታ ወይም ከግብረ ገብ ውጪ በሆኑ ተግባሮች እንዱሰማራ በማድረግ መጠቀሚያ ያደረገው እንደሆነ ወይም በማናቸውም ላላ መንገድ የልጁን የወደፉት ሕይወት ክፈኛ በሚጎዲ አኳኋን የያዘው መሆኑን (ሰረዝ የተጨመረ) የተረዲ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ የጉዱፈቻ ስምምነቱን ለመሰረዝ እንደሚችል አስቀምጧል። በተያዘው ጉዲይም ሕጻን ቱለ ያለበት ሁኔታ ሲታይ እና ተጠሪዎች ሕፃኑን ለመውሰድ ፍቃደኛ ለመሆን ያለመቻላቸው እንዱሁም በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር የተጠሪዎች ወኪል ቀርበው “ልጁን አንደማንወስድ የጉዱፈቻ ውለ ከመጽደቁ በፉት የገለጽን በመሆኑ ልጁን ለመውሰድ አንገደድም የጉዱፈቻ ስምምነቱ ቢፈርስ አንቃወምም” በማለት መከራከራቸው ሲታይ በሕፃኑ የወደፉት ሕይወት ችግር አያስከትልም ብል ለመደምደም የሚያስችል አይደለም። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የቀረበውን ክርክር ከሕጉ መንፈስ ጋር ባግባቡ ሳያገናዝቡ የጉዱፈቻ ስምምነት ሉፈርስ አይገባም በማለት መወሰናቸው የሕፃኑን እድገት የሚጏዲ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል።
በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፈርድ ቤት በመ/ ሕዲር 05 ቀን 2001 እና ታህሳስ 04 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲት 12 ቀን 2001 ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪዎች ሕፃን ቱለን ለመውሰድ የካቲት 26 ቀን 2000 ዓ.ም ያደጉት እና መጋቢት 25 ቀን 2000 ዓ.ም በፍርድ ቤት የፀደቀ የጉዱፈቻ ስምምነት ውል ፈራሽ ነው ብለናል። ይህንኑ አውቀው ተገቢውን እንዱፈጽሙ ለስር ፍርድ ቤቶች ይፃፍ።
No topics extracted.