No summary available.
የካቲት 9 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ አልማው ወላ አመልካች፡-
በዚህ መዝገብ የቀረበው የስጦታ ውልን የሚመለከት ጉዲይ ነው። በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ከሳሽ የነበሩት አመልካቾች ሲሆኑ በክሳቸውም ልጃቸው ተጠሪ እንዱጦሯቸውና እንዱንከባከቧቸው ግዳታ በማስገባት በየካ ክ/ከተማ ቀበላ 03/04 ክልል ውስጥ ቁጥር 1561 የሆነ ቤታቸውን በስጦታ የሰጧቸው ሲሆን የተጣለባቸውን ግዳታ ስላልተወጡ የስጦታ ውለ እንዱፈርስ ጠይቀዋል። ተጠሪ በመልሳቸው የስጦታ ይፍረስልን ጥያቄ በይርጋ ቀሪ ነው፣ቤቱ በስሜ ተዛውሯል፣በመሐከላችን ምንም አይነት የስጋ ዝምድና የለም፣የገባሁት ግዳታም የለም በነፃ ፈቃዲቸው ያደረጉት ውል ስለሆነ ሉፈረስ አይገባም በማለት ተከራክረዋል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ ተጠሪ በውለ ላይ አመልካቾችን ለመጦርና ለመቀለብ የገቡት ግዳታ ስለላለ ውለ ሉፈርስ አይገባም በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካቾች ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ ተጠሪዎችን ሳይጠራ መዝገቡን ዘግቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካቾች በቅሬታቸው ላይ ለተጠሪ ስጦታ የሰጡት ተጠሪዋ አመልካቾችን ለመጦርና ለመንከባከብ እንዱሁ ላላ ቤት ገዝታ ለመስጠት ግዳታ በመግባቷና ይህንን ግዳታ ባለመወጣቷ ውለ ሉፈርስ ይገባል ብለዋል። ችልቱም ተጠሪዋ አመልካቾችን ለመንከባከብና ለመጦር ግዳታ ስላልገቡ ውለ ሉፈረስ አይገባም የመባለን አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክራቸውን አቅርበዋል። ችልቱም መዝገቡን ከተያዘው ጭብጥ አኳያ እንደሚከተለው መርምሯል።
አመልካቾች ለስር ፍ/ቤት ክስ ያቀረቡት የስጦታ ውል እንዱፈርስላቸው ነው። ውለ እንዱፈርስ የጠየቁበት ምክንያት ተጠሪ አመልካቾችን ለመንከባከብና ለመጦር የገቡትን ግዳታ ባለመወጣታቸው መሆኑን ገልፀዋል። ተጠሪ ስጦታ የተሰጣቸው መሆኑን አምነው ነገር ግን በውለ ላይ የገቡት ምንም አይነት ግዳታ እንደላለ ተከራክረዋል። የስር ፍ/ቤትም የአመልካቾችን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው ተጠሪ አመልካቾችን ለመንከባከብና ለመጦር ግዳታ አልገቡም በሚል ነው። በመሆኑም ይህ ችልት ተጠሪ በስጦታ ውለ ላይ አመልካቾችን ለመርዲት ግዳታ የገቡ መሆኑን እና የስጦታ ውለ ሉፈርስ የሚገባበት የሕግ ምክንያት መኖር አለመኖሩን መመርመር ተገቢ ሆኖ አግኝቶታል። ለዚህ ይረዲው ዘንድ አመልካቾች ለተጠሪ ስጦታ ያደረጉበትን ውል ተመልክቷል። ጥር 12 ቀን 1991 ዓ.ም የተደረገው የስጦታ ውል በከፉል “ስጦታ ሰጪዎች ባልና ሚስት ስንሆን በአ/አበባ ከተማ በወረዲ 12 ቀበላ 11 የቤት ቁጥር አዱስ የካርታ የሆነውን ቤታችን ለወለድናት ልጃችን ወደፉትም ለምትጦረንና ለምትንከባከበን ጧሪ ቀባሪያችን ለሆነችው ልጃችን በፈለገችው አይነት እንድትጠቀምበት ይህንን ከላይ የተጠቀሰውን ቤታችንን በፍ/ሕ/ቁ. 2427 መሰረት በስጦታ የሰጠናት መሆናችንን በፊርማችን እናረጋግጣለን።” የሚል ነው።
ከዚህም የስጦታ ውል ይዘት “… ወደፉትም ለምትጦረንና ለምትንከባከበን ጧሪ ቀባሪያችን…” የሚለው ሐረግ አመልካቾች ለተጠሪዋ ስጦታ ያደረጉበት ምክንያት ተጠሪዋ ወደፉት እንድትንከባከባቸው እና እንድትጦራቸው መሆኑን ማየት የሚቻል ነው። በእርግጥ በኑዛዜው ላይ ተጠሪዋ አመልካቾችን የመንከባከብና የመጦር ግዳታ ገብታለች በሚል ግልጽ አማርኛ አልተቀመጠም። ነገር ግን ውል ሲተረጏም የቅንነትና የመተማመን ግንኙነትን መሰረት በማድረግና በቅን ልቦና ላሆን እንደሚገባው ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1732 መገንዘብ ይቻላል። በተያዘውም ጉዲይ አመልካቾች ቤታቸውን ለተጠሪ ሲሰጡ ወደፉት ከልጃቸው እርዲታና እንክብካቤ የሚያገኙ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ለመሆኑ የውለ ይዘት ያሳያል። በእርግጥ ተጠሪ ከአመልካቾች ጋር ምንም አይነት የስጋ ዝምድና የለኝም በማለት የሚከራከሩ ቢሆንም በስጦታ ውለ ላይ አመልካቾች የተጠሪ ወላጆች መሆናቸው ተጠቅሶ የተቀመጠውን ተጠሪዋም አምነው ስጦታውን መቀበላቸውን ከመዝገቡ ተመልክተናል።
በመሆኑም አመልካቾች ለተጠሪ ቤታቸውን የሰጡት ተጠሪ ልጃቸው በመሆናቸውና ወደፉትም እንድትንከባከባቸውና እንድትረዲቸው ግዳታ በማስገባት መሆኑን ችልቱ ተገንዝቧል።
እንግዱህ ተጠሪ አመልካቾችን ለመርዲትና ለመንከባከብ ግዳታ ገብተዋል ከተባለ ይህንን ግዳታቸውን ተወጥተዋል ወይ? የሚለው በመቀጠል ላታይ ይገባል።፡ አመልካቾች ተጠሪ ይህንን ግዳታ አልተወጡም በማለት ሲከራከሩ ተጠሪ ግዳታ አልገባሁም ከማለት በቀር አመልካቾችን እየረደና እየተንከባከቡ ስለመሆኑ ያቀረቡት ክርክር የለም። ለዚህም ለሰበር ችልት በሰጡት መልስ የሚከራከሩት አመልካቾች የጡረታ አበልና በኮንትራት እየተቀጠሩ ገቢ የሚያገኙና እርዲታ የማያሻቸው መሆኑን እንጂ በውለ መሰረት ግዳታቸውን ስለመወጣታቸው በማስተባበል ያቀረቡት ክርክር የለም። ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ በግልጽ ክድ ካልተከራከረ ወይም በመሸሽ መልስ ከሰጠ ክሱን እንዲመነ እንደሚቆጠር የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 235/2/ ያመለክታል። በመሆኑም ተጠሪ በውለ የተመለከተውን ግዳታቸውን ስላለመወጣቸው በአመልካቾች የተነገረውን በግልጽ ክደው ስላልተከራከሩ እዲመኑ ሉቆጠር ይገባል።
No topics extracted.
ስጦታ ገደብ ያለበት ወይም ግዳታ የተጣለበት ላሆን እንደሚችል በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2452/1/ ስር ተመልክቷል። ስጦታ ሰጪውም ተቀባዩ ግዳታውን ባለመፈፀሙ ምክንያት ስጦታው እንዱፈርስለት ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2464/1/ ያስገነዝባል። በተያዘው ጉዲይም ተጠሪ አመልካቾች ለመርዲትና ለመንከባከብ ግዳታ የገቡ በመሆኑና ግዳታቸው ባለመወጣታቸው አመልካቾች ውለ እንዱፈረስ ለመጠየቅ መብት አላቸው።
ተጠሪ የአመልካቾች የስጦታ ይፍረስልን ጥያቄ በይርጋ ይታገደል በማለት ተከራክረዋል። በእርግጥ በመንፈስ መጫን የተደረገ ስጦታ ስጦታው ከተደረገ ጊዜ አንስቶ በሁለት አመት ውስጥ ለዳኞች ካልቀረበ ዋጋ እንደላለው የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2441/1/ ያመለከታል። በተያዘው ጉዲይ አመልካቾች ውለን ሲያደርጉ የመንፈስ መጫን ነበር በማለት ይግለፁ እንጂ ስጦታው እንዱፈርስ በዋናነት የጠየቁት ተጠሪ በውለ መሰረት ግዳታቸውን እልተወጡም በሚል በመሆኑ ይህ የይርጋ ድንጋጌ አግባብነት የለውም። ስለሆነም ተጠሪዋ በስጦታ ውለ ላይ የተመለከተውን ግዳታቸውን ባለመወጣታቸው ውለ ሉፈርስ ይገባል። የውል መፍረስ ውጤቱም ተዋዋዮች ወደነበሩበት ቦታ መመለስ እንደሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1815 ስር ስለተመለከተ አመልካቾችና ተጠሪም በዚሁም መሰረት ውለ ከመደረጉ በፉት ወደነበሩበት ሁኔታ ሉመለሱ ይገባል። በአጠቃላይ ውለ እንዱፈርስ ሉወሰን ሲገባ የስር ፍ/ቤቶች ስጦታው ሉፈርስ አይገባም በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈጽመዋል።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 24359 መስከረም 8 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 72830 ኀዲር 5 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ተሽሯል።
ተጠሪ በስጦታ ውለ ላይ የተመለከተውን ግዳታቻውን ስላልተወጡ ስጦታው ፈራሽ ነው ብለናል።
የስጦታ ውለ በመፍረሱ ምክንያት ግራ ቀኙ ወደነበሩበት ሉመለሱ ስለሚገባ ተጠሪ ከአመልካቾች በስጦታ ያገኙትን ቤት ለአመልካቾች መልሰው ያስረክቡ ብለናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።