No summary available.
ጥር 5 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ አልማው ወሉ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡-
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የውርስ ጥያቄን የሚመለከት ነው። አመልካwች ለምዕራባዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡት መቃወሚያ የእህታቸው ልጅ አቶ ሣምሶን ተስፊይ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የሟቹ ወራሾች ተጠሪ ብቻ ሣይሆኑ አመልካwችም መሆናቸውን ተጠሪ ግን ለብቻቸው ውርስ አጣርተው በፍ/ቤት ማፀደቃቸውን ገልፀው ይኸው ሪፖርትና ሪፖርቱን መሰረት ተደርጎ ለተጠሪ የተሰጣቸው የወራሽነት ምስክር ወረቀት እንዱሰረዝ ጠይቀዋል። በተጨማሪም በሟች ስም የተመዘገበው ቤት ከእናት ወገን የመጣ በመሆኑ ሉወርሱ የሚገባቸው አመልካwች ብቻ መሆናቸው የሟች ገንዘብን በተመለከተ ከተጠሪ ጋር እኩል ሉካፈለ እንደሚገባና በዚሁ መሰረት የወራሽነት ምስክር ወረቀት እንዱሰጣቸው ጠይቀዋል። ተጠሪም ለቀረበው መቃወሚያ በሰጡት መልስ ክርክር የተነሣበት ቤት የተሰራበትን ቦታ ወ/ሮ አመዘነች ከማዘጋጃ ቤት ተመርተው ለልጃቸው ለወ/ሮ አበበች ሐጎስ በስጦታ ሰጥተዋቸው ወ/ሮ አበበች ቤት እንደሰሩበት አመልካwች ቦታው የእናታችን ነው በሚል ክስ አቅርበው ተጠሪ ልጃቸውን ወክለው ተከሪክረው ቦታው የወ/ሮ አበበች ነው ተብል መወሰኑን ቦታው በምሪት የተገኘ እንጂ በውርስ የተላለፈ ርስት ባለመሆኑ የቤተሰብ ንብረት ነው ልባል እንደማይቻል ገልፀው ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ርስት የሚለው ቃል መሬት የግለሰብ እያለ መሸጥ መለወጥ በሚቻልበት ጊዜ የመጣ ሆኖ በአንድ ወገን ዘር ሐረግ የመጣ ቅርስ መሰረት በማድረግ ነው በተያዘው ጉዲይ የሟች እናት ቦታውን በስጦታ ካገኙ በኋላ ንብረት ያሰፈሩበት ስለሆነ የአንድ ወገን ዘር ሐረግ ነው ልባል አይችልም፣ የሟች የአቶ ሳምሶን ተስፊይ ብቸኛ ወራሽ ተጠሪ ብቻ ናቸው የሟቹ እናት ሟችን ሣይወርሱ ስለሞቱ አመልካwች እህታቸውን ተክተው ሉወርሱ አይችለም በማለት የአመልካwች ክስ ውድቅ አድርጓል። በዚህ ውሣኔ ላይ አመልካwች ለትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤትና ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርበው አቤቱታቸው ውድቅ ተደርጎባቸዋል። የአሁኑ ሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። አመልካwች በአቤቱታቸው ወ/ሮ አመዘነች ለሟች እናት በስጦታ የሰጡት ቤት የነበረበት ቦታ ነው ስለሆነ ከእናት ወገን የተገኘ ንብረት ለእናት ወገን ላሰጥ ይገባል፣ ቤቱን የሰሩት የሟች እናት ናቸው ቢባል እንኳን እህታቸውን ተክተው ሉወርሱ ስለሚችለ ውርሱ ለተጠሪ ብቻ መተላለፈ ስህተት ነው የሚል ነው። ችልቱም የሟች ገንዘብ በሙለ ተጠሪ እንዱወርሱ እና ከእናት ወገን የመጣ የማይንቀሣቀስ ንብረት /ቤት/ ለሟች አባት ይገባል በሚል የሰጠው ውሣኔ አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ የጽሐፍ ክርክራቸውን አቅርቧል። ችልቱም መዝገቡን መርምሯል።
ከፍ ሲል እንደተመለከተው ተጠሪ የልጃቸውን ውርስ አጣርተው በፍ/ቤት በማፀደቃቸው አመልካwች ተቀዋሚ ሆነው ቀርበዋል። አመልካwች መቃወሚያ ያቀረቡት የሟች አቶ ሳምሶን ተስፊይ እናት የአመልካwች እህት በመሆናቸው የሟችን ውርስ እህታቸውን በመተካት የመውረስ መብት ያላቸው መሆኑን ምክንያት በማድረግ ነው። በመሆኑም ስለ ተተኪ ወራሽነት በፍ/ሕጉ ውስጥ የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ማየት ተገቢ ይሆናል።
በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 842/3/ ስር እንደተመለከተው የሟች ልጆች የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች ሲሆኑ ልጆች ቀድመው ከሞቱና ወደታች የሚቆጠር ተወላጅ ትተው ከሆነ ተወላጆቹ ወላጆቻቸውን ተክተው ሟችን እንደሚወርሱ ያመለክታል። ሟች ልጆች የላለት ከሆነ እናትና አባት ሁለተኛ ደረጃ ወራሾች እንደሚሆኑና አባት ወይም እናት ቀድመው ከሞቱም የእነሱን ፊንታ ልጆቻቸው ወይም ወደታች የሚቆጠሩ ተወላጆች እነሱን ተክተው እንደሚወርሱ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 843/ 844/2 ተመልክቷል። በአባት ወይም በእናት በኩል ወደታች የሚቆጠር ከላለ ውርሱ በሙለ ለላላው መስመር ላለ ወራሽ እንደሚተላለፍ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 844/3 ያመለክታል። ከፍ ሲለ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች የተተኪ ወራሽነት የተፈፃሚነት ወሰን ወደታች በሚቆጠሩ ተወላጆች እንጂ ወደ ጎን በሚቆጠር ዝምድና እንዲልሆነ መገንዘብ ይቻላል። በተያዘው ጉዲይ አመልካwች የሟች እናት ወደታች የሚቆጠሩ ተወላጆች ሣይሆኑ ወደጎን የሚቆጠሩ ዘመድች ወይም እህቶች ናቸው። በመሆኑም ከጅምሩም ቢሆን የሟችን እናት ተክተው ወራሽ ለመሆን የሚያስችላቸው መብት አልነበራቸውም። የሟች እናት ትተው የሄደት ወደታች የሚቆጠሩ ተወላጆች ስለላላቸው ውርሱ ሉተላለፍ የሚችለው ለላላኛው መስመር ወራሽ በዚህ ጉዲይ ለሟች ወላጅ አባት ነው። በመሆኑም አመልካwች እህታቸውን ተክተው መውረስ ስለማይችለ ቀድሞውንም ቢሆን ተቃውሞ ለማቅረብ የሚያስችላቸው መብት አልነበራቸውም። በዚህም ምክንያት የሟች እናት የተረከቡት ባድ ቦታ ሣይሆን ቤት የተሰራበት ቦታ ነው የሚለው ክርክርም ሆነ የሟችን ገንዘብ ለመካፈል ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም።
No topics extracted.
በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች የሟች አቶ ሳምሶን ተስፊይ ውርስ በሙለ ለተጠሪ ሉተላለፍ ይገባል በማለት በሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈጽመዋል ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩ ውሣኔ ተሰጥቷል።
ው ሣ ኔ
የምዕራባዊ ዞን ማዕከላዊ ፍ/ቤት የመዝገብ ቁጥር ባልተጠቀሰ ጥር 21 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 737ዐ መጋቢት 11 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ እና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 3ዐ799 ግንቦት 27 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ፀንቷል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸው ይቻለ