No summary available.
ታህሣሥ 21 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- ወ/ሮ ዮዱት ኃይለ የህፃን ሄኖክ ዲንኤል ሞግዚትና አሳዲጊ ቀረበች።
ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የውርስ ንብረት ክፍፍልን መነሻ ያደረገ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲጀመር ከሣሽ የነበረችው አመልካች ስትሆን፣ፍ/ቤቱ ቀደም ሲል በሰጠው ትእዛዝ መሰረት በውርስ አጣሪ ተጣርቶ የቀረበውን የውርስ ክፍፍል የውሳኔ ሐሳብ በመቃወም ተከራክራለች የውርስ አጣሪው ባቀረበው የውሣኔ ሐሳብ ላይ ባቀረበችው የጽሐፍ አስተያየት በወረዲ 23 ቀበላ 10 ውስጥ የሚገኘው ቁጥር 1220 የሆነው ቤት ከሟች እማሆይ ምጽላል ተድላ ለወ/ሮ የሺንርኤ በስጦታ የተላለፈ ነው። ወ/ሮ የሺንርኤ የህፃን ሄኖክ አባትን (ዲንኤል አረጋይን) ጨምሮ አራት ወራሾች አለዋቸው። በመሆኑም የቤቱ ¼ኛ ድርሻ የህፃን ሄኖክ አባት ነው።
አጣሪው የወ/ሮ የሺንርኤ ወራሾች ስምንት(8) እንደሆኑ አድርጏ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም። የእማሆይ ምጽላል ተድላ 8(ስምንት) ልጆች በማከል ውርሱ እንዱከፊፈል በማለት የውሳኔ ሐሳብ ማቅረቡም ትክክል አይደለም የሚለትንና ላልች ነጥቦችንም በማከል እንደተከራከረች በመዝገቡ ተመልክቶአል።
በወቅቱ ተከሣሾች የነበሩት ተጠሪዎችም በበኩላቸው ባቀረቡት አስተያየት እማሆይ ምጽላል ተድላ ቤቱን ለወ/ሮ የሺንርኤ የሰጡት በሕይወት እስካለ ድረስ እንዱጠቀሙበት ብቻ ነው። ወ/ሮ የሺንርኤ ከሞቱ በኋላ ሐብቱ የሟች እማሆይ ምጽላል ተድላ ስለሚሆን የእማሆይ ምጽላል ተድላ ወራሾች ለሆንነው ለስምንታችን ይከፊፈላል።
ከስምንቱ የእማሆይ ምጽላል ተድላ ልጆች ውስጥ ሟች ወ/ሮ የሺንርኤ አንድዋ ስለመሆኑ የሚደርሳቸው ከቤቱ 1/8ኛ ነው። ይህ 1/8ኛ ደግሞ ለስምንቱ ልጆቻቸው (ለወ/የሺንርኤ ልጆች) ይከፊፈላል። ከእነዚህ ልጆች ውስጥ የህፃን ሄኖክ አባት አንደ ነው። በዚህ መሰረት ህፃን ሄኖክ የሚወርሰው የአባቱን ድርሻ ስለሆነ ሉያገኝ የሚችለው ከቤቱ 1/56ኛ ነው በማለት የውርስ አጣሪው ያቀረበው አማራጭ ሃሳብ እንደግፊለን በማለት ክርክራቸውን አሰምተዋል። በመጨረሻም ፍ/ቤቱ የተጠሪዎችን ክርክር እንዲለ በመቀበል የህፃን ሄኖክ ዲንኤል ድርሻ 1/56ኛ ነው በማለት ወስኖአል። ጉዲዩን በይግባኝ የሰማው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሳኔውን አጽንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ታህሣሥ 7 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈችው ማመልከቻ ያቀረበችውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው እማሆይ ምጽላል ተድላ መጋቢት 14 ቀን 1964 ዓ.ም ላደረጉት ስጦታ የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ትርጓሜ አግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ግራ ቀኝ ወገኖች በዚህ ረገድ ያሰሙት ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
እንደምንመለከተው ለቀረበው ክርክር አወሳሰን በዋንኛነት መሰረት የሆነው እማሆይ ምጽላል ተድላ ለልጃቸው ለወ/ሮ የሺንርኤ ያደረጉት የስጦታ ውል ነው። የስጦታ ውለ እማሆይ ምጽላል አከራካሪውን ቤት በወ/ሮ የሺ መሰጠታቸውን ያመለከታል። ይህ አከራካሪ አልሆነም። አከራካሪ የሆነው በስጦታው ውለ ወ/ሮ የሺ ያገኙት መብት የባለሃብትነት ነው ወይስ የመጠቀም ብቻ? የሚለው ነው። የሥር ፍ/ቤቶች “…. እስከ እድሜ ልኳ ድረስ ማንም ሰው እንዲይጠይቃት ሰጥቻታለሁ።” የሚለውን ሐረግ ነጥለው በመያዝ ወ/ሮ የሺ በስጦታ ውለ ያገኙት መብት ከባለሃብትነት በመለስ ያለው ነው የሚል ትርጓሜ ሰጥተዋል። በበኩላችን እንዲየነው ውለን በትክክል መተርጏም የሚቻለው አንድዋን ሐረግ ለይቶ በውጣት ሳይሆን፣አጠቃላይ ይዘቱን በማየት እንደሆነ ነው መገንዘብ የቻልነው። እማሆይ ምጽላል በስጦታ ውለ የገለጹት ቤቱ የተሰራው በወ/ሮ የሺንርኤ ቦታ ላይ መሆኑን፣ስመ ሐብቱ በእማሆይ ምጽላል ቢመዘገብም፤የሰሩት ግን ወ/ሮ የሺንርኤ እንደሆኑ ለወደፉቱ (የስጦታ ውለ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ) ወ/ሮ የሺንርኤ የቦታውን ካርታ በስማቸው አስነስተው አስከ እድሜ ልካቸው ድረስ ማንም ሰው ሳይጠይቃቸው የተሰጣቸው መሆኑን፣በአጠቃላይ እማሆይ ምጽላል ቤታቸውን ለልጃቸው (ለወ/ሮ የሺንርኤ) የሰጡዋቸው መሆኑን ነው። እነዚህ በስጦታ ውለ የተመለከቱት ፍሬ ነገሮች ተያይዘው ሲታዩ በትክክል የሚያረጋግጡት እማሆይ ምጽላል ቤታቸውን ለልጃቸው ያለምንም ገደብ ለመስጠት አስበው መነሳታቸው እና ይህን ሐሳባቸውም በውለ በቂ በሆነ ሁኔታ መግለፃቸውን ነው። ወ/ሮ የሺንርኤ የቦታውን ካርታ በስማቸው አስነስተው እንዱይዙ ተፈቀደላቸው ማለት ቤቱ በሃብትነት ተሰጥቶአቸዋል ከማለት ውጪ ሉተረጏም የሚችልበት አግባብ የለም በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች በስጦታ ውለ የሰጡት ትርጓሜ በእርግጥም በውለ የተገለጸውን የስጦታ አድራጊዋ ሐሳብና ፍላጏት መሰረት ያደረገ ሆኖ አላገኘነውም።
No topics extracted.
የስጦታ ውለ ከፍ ሲል በተመለተው ሁኔታ የሚተረጏም እስከ ሆነ ድረስ ቤቱ የወ/ሮ የሺንርኤ ሐብት ሆኖአል ማለት በመሆኑ የውርስ ማጣራቱ ሂደትም የኸው የወ/ሮ የሺንርኤ ውርስ የሚመለከት ነው የሚሆነው።
ውርሱን እንዱያጣራ የተሾመው ውርስ አጣሪ የወ/ሮ የሺንርኤ ልጆች 8(ስምንት) እንደሆኑ በማረጋገጥ ንብረቱ ለ8ቱ በማካፈል አመልካች ሞግዚት የሆነችለት ህፃን ሄኖክ ዲንኤል ድርሻ 1/8ኛ እንደሆነ በመግለጽ በአንድ በኩል ሲያቀርብ በልላ በኩል ደግሞ የእማሆይ ምጽላል 8 ልጆችም የውርሱ ተካፊይ እንደሆኑ በመቁጠር የህፃን ሄኖክ ድርሻ 1/56ኛ ነው የሚል ሁለተኛ አማራጭ አቅርቦአል። በግልጽ እንደሚታየው የሁለተኛው አማራጭ መነሻ ቤቱ የእማሆይ ምጽላል ሐብት ነው የሚለው ነው። ይህ የሆነው ግን የስጦታ ውለን በተሳሳተ ሁኔታ በመተርጏም በመሆኑ ተቀባይነት ያለው አይደለም። በመሆኑም የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሁለተኛውን አማራጭ በመቀበል የውርስ ክፍፍለ እንዱከናወን መወሰኑ ትክክል አይደለም። በልላ በኩል ግን የወ/ሮ የሺንርኤ ልጆች (ወራሾች) 8 (ስምንት) መሆናቸው በውርስ አጣሪው የተረጋገጠ በመሆኑ ውርሱ የሚከፊፈለው ለስምንቱ ወራሾች እንጂ አመልካች እንደምትለው ለህፃን ሄኖክ አባት እና ለሦስቱ ተጠሪዎች ብቻ አይደለም። በዚህ ስላትም የውርስ አጣሪው ባቀረበው ሪፖርት አንደኛው አማራጭ መሰረት የህፃን ሄኖክ ዲንኤል ድርሻ ከቤቱ 1/8ኛ (አንድ ስምንተኛ) ይሆናል። ሲጠቃለል የስር ፍ/ቤቶች ለስጦታ ውለ የሰጡት ትርጓሚ የተሳሳተ በመሆኑ ታርሞ የውርስ ክፍፍለ መደረግ ያለበት ቤቱ የሟች ወ/ሮ የሺንርኤ ሐብት እንደሆነ በመቁጠር ነው ብለናል።