No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 27 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ሀይለራጉኤል ደበላ - ጠበቃ ገመቹ ሮሮ ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የቤት ይለቀቅልኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካች ጥር 13 ቀን 1999 ዓ.ም በተጠሪዎች ላይ በመሰረቱት ክስ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ የአመልካች አባት የነበሩት ሟች አቶ ደበላ ልቡ ከወ/ሮ ክብነሽ ጎንደል ጋር ጋብቻ ከማድረጋቸው በፉት የነበሯቸውንና ቁጥራቸው 1056/1057 የሆኑት የግል ቤቶች መስከረም 19 ቀን 1956 ዓ.ም ባደረጉት ኑዛዜ ወ/ሮ ክብነሽ በሕይወት እስከአለ ድረስ እንዱኖሩ እና እንዱጠቀሙበት ከሞቱ በኋላ ወደ ወራሾች እንዱተላለፍ በማለት መናዘዛቸውን፣ ኑዛዜውም በፍ/ቤት መፅደቁም፣ ኑዛዜው ወ/ሮ ክብነሽ ቤቱን ከፈለጉ እንዱሸጡ፣ እንዱለውጡ የሚል ቢሆንም በውርስ እንዱያስተላልፈ የሚያዝ ሆኖ እያለ ለዘመድቻቸው ማውረሳቸውን ገልፀው ተጠሪዎች ያላግባብ የያዙትን ቤት ለቀው እንዱያስረክቧቸው፣ ተጠሪዎች ለተጠቀሙበት የቤት ኪራይ አመልካች የመጠየቅ መብታቸው ተጠብቆ እንዱወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የአሁኑ ተጠሪዎችም በተከሳሽነት ቀርበው በሰጡት መልስ ሟች ወ/ሮ ክብነሽ በሟች አቶ ደበላ ልቡ ኑዛዜ መሰረት ንብረቱን ወደራሳቸው በማዞር የግል ንብረት በማድረግ ሲጠቀሙበት የቆዩ በመሆኑና ክሱም ኑዛዜው ከተፈፀመ በኋላ የቀረበ በመሆኑ እንዱሁም ኑዛዜውን ለመቃወም የሚቀርብ ክስን ስርዓት ተከትል ያልቀረበ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም የሚለ ነጥቦችን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት አንስተው የተከራከሩ ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድም ሟች አቶ ደበላ ባደረጉት ኑዛዜ ወ/ሮ ክብነሽ ቤቱን ለመሸጥ፣ ለመለወጥ እንዱችለ ስልጣን የሚሰጥ በመሆኑ ወ/ሮ ክብነሽ ንብረቱን ለላላ የማስተላለፍ መብት አላቸው ንብረቱንም በስማቸው አዙረው ሲጠቀሙበት ቆይተው ግንቦት 27 ቀን 1996 ዓ.ም በውልና ማስረጃ በተደረገ ኑዛዜ ለተጠሪዎች የሰጧቸው በመሆኑ የአመልካች ክስ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጀ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የተጠሪዎችን ክርክር ውድቅ አድርጎ ሟች አቶ ደበላ ልቡ መስከረም 19 ቀን 1956 ዓ.ም አደረጉ የተባለው ኑዛዜ ሟች ወ/ሮ ክብነሽ ጎንደል በኑዛዜ ንብረቱን ለማስተላለፍ ሥልጣን የሚሰጥ አይደለም፣ የሟች ደበላ ልቡ ኑዛዜ ከወ/ሮ ክብነሽ ጎንደል ሞት በኋላ ተፈፃሚነት አለው በሚል ምክንያት ተጠሪዎች አከራካሪውን ቤት ለአመልካች እንዱያስረክቡ የቤት ኪራይ በተመለከተ ከቤቱ ጋር ክስ መቅረብ የነበረበት ስለሆነ የአመልካች ወደፉት የመክሰስ መብት ሉጠበቅ አይገባም ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ተጠሪዎች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ፍርድ ቤቱም ጉዲዩን ከአከራካሪው ኑዛዜ ይዘት ጋር በማገናዘብ መርምሮ በኑዛዜው ላይ ሟች አቶ ደበላ ልቡ ወ/ሮ ክብነሽ ሕይወቷ እስካለ ድረስ በከፉል ወይም በሙለ ለመሸጥ በፈለገች ጊዜ ልትሸጥና ልትለውጥ ትችላለች፣ ለመሸጥ ጠበቃ ባርናባስ ደስታ ቀረቡ በፈለገች ጊዜ ወራሾቿ ወይም ወራሾቼ እርሷ ፈቅዲ ካልሰጠቻቸው ሉቃወሟት አይችለም በሚል ያስቀመጡ ስለሆነና ይህ የተናዛዡ ሀሳብ የሚያስገነዝበው ደግሞ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ንብረት ሟች ወ/ሮ ክብነሽ ካልፈቀደ በቀር ቤቱን ለፈለጉት ሰው ቢሰጡ ከኑዛዜው መልዕክት ውጪ እንዲደረጉ የሚያስቆጥር አይደለም በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሽሮታል። በዚህ ውሳኔ የአሁኑ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
አመልካች ሐምል 13 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገፅ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ሟች አቶ ደበላ ልቡ ባደረጉት ኑዛዜ ሟች ወ/ሮ ክብነሽ ጎንደል ንብረቱን ለመሸጥ፣ ለመለወጥ ትችላለች ተብል የተቀመጠው ሐረግ በኑዛዜ ለላላ ሰው መሥጠትን ያጠቃልላል ተብል የተተረጎመው ሟች ወ/ሮ ክብነሽ ንብረቱን ለራሳቸው ጥቅም ብቻ ለመሸጥ፣ ለመለወጥ ይችላለ የሚል ግልፅ የሆነ ቃል እንጂ ለላላ ሰው ጥቅም ንብረቱን እንዱለውጡ ወይም እንዱሸጡ የሚል መልዕክት የላለው ግልፅ ቃል ሆኖ እያለ ይህንኑ ግልፅ ቃል በሚጻረር መልኩ መተርጎሙ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም ይገባዋል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ሟች አቶ ደበላ ልቡ ያደረጉት ኑዛዜ ወ/ሮ ክብነሽ ንብረቱን ሉሸጡ፣ ሉለውጡ እንጂ እርሳቸው በኑዛዜ እንዱያስተላልፈ የሚያስችላቸው እንደሆነ ተደርጎ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎ የግራ ቀኙ የቃል ክርክር መስከረም 26 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት ተሰምቷል።
No topics extracted.
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ላቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አከራካሪው ንብረት የሟች አቶ ደበላ ልቡ የግል ንብረት መሆኑን ተጠሪዎች አለመካዲቸውን፣ ሟች ወ/ሮ ክብነሽ ጎንደል የሟች አቶ ደበላ ልቡ ሚስት የነበሩ መሆኑን፣ አቶ ደበላ ልቡ ለወ/ሮ ክብነሽ ጎንደል መስከረም 19 ቀን 1956 ዓ.ም የተደረገ ኑዛዜ የተውላቸው መሆኑን፣ ይህንኑ ኑዛዜም በከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 1553/59፣ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ደግሞ በመ/ቁጥር 70/62 ማስፀደቃቸውን፣ ሟች ወ/ሮ ክብነሽ ጎንደል ግንቦት 27 ቀን 1996 ዓ.ም ውል እና ማስረጃ ክፍል ባደረጉት ኑዛዜ ደግሞ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ንብረት ለሁለተኛ ተጠሪ፣ ለወ/ት ትዕግስት ፈለገ፣ ለወ/ት ኩላገር ፈለገ፣ ለወ/ት ወለላ ፈለገ፣ ለወ/ት ሙላቷ ፈለገ እና ለሕፃን ዮሴፍ እንዲሳ ፈለገ የተናዘዙላቸው መሆኑን ነው። አከራካሪው ነጥብ ሟች አቶ ደበላ ልቡ በተውት ኑዛዜ ሟች ወ/ሮ ክብነሽ ጎንደል ንብረቱን ከፍጻሜ ሕይወታቸው በኋላ በኑዛዜ ለላላ ሰው የማስተላለፍ መብት/ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል ወይስ አልተሰጣቸውም? የሚለው ነጥብ ነው። ለጉዲዩ እልባት መስጠት ይቻል ዘንድም ሟች አቶ ደበላ ልቡ መስከረም 19 ቀን 1956 ዓ.ም ባደረጉት ኑዛዜ ቃል አግባብነት ያለውን ክፍል ተመልክተናል። ይኸው የኑዛዜ ክፍል “ የሰጠኋትን ቤት ከነቦታው ሕይወቷ እስካለ ድረስ በከፉል ወይም በሙለ ለመሸጥ በፈለገች ጊዜ ልትሸጥ ልትለውጥ ትችላለች፣ ለመሸጥ በፈለገች ጊዜ ወራሾቿ ወይም ወራሾቼ እርሷ ፈቅዲ ካልሰጠቻቸው ሉቃወሟት አይችለም፣ ….. ከዚህ በላይ እንደተጻፈው ቃል የሰጠኋትን ሀብትና ንብረት ለውጣ እራሷ የምትጦርበት ሲሆን ከርሷ የተረፈ ቢኖር ግን ውርሱ ለልጇ አርያና ለልጅ ልጇ ለኃይለራጉኤል መሆኑ ብቻ ሳይሆን ከቀሪው ሀብቴ ጋር አንድ ላይ ተደባልቆ ከኔ በተወለደት ማለት ከሙለነሽ ላይ ለወለድኳቸው ልጆች ብቻ ከክብነሽ የማደጎ ልጆቿ ጋር እንደየድርሻቸው ሉከፊፈለ ይችላለ …..” በሚል የተቀመጠ ነው።
በመሰረቱ ኑዛዜ ሉተረጎም የሚገባው ቃላቶቹ እና መልእክቱ ግልፅ ሳይሆን ሲቀር ነው። በልላ አገላለፅ ኑዛዜው ግልፅ ቃላቶችንና መልዕክትን የያዘ ከሆነ ትርጓሜ መስጠት አያስፈልግም። ይህንን መሰረታዊ መርህን መከተል ያለብን መሆኑን ደግሞ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 910(2) ድንጋጌ በግልፅ ያስገነዝባል። በመሆኑም የኑዛዜው ቃል መተርጎም ያለበት ስለኑዛዜው መልእክት ጥርጣሬ በሚፈጥርበት ጊዜ አሻሚ ወይም ግልፅ ያልሆነ እንደሆነ ብቻ ነው። ይህን ደንብ ተፈጻሚ የሚሆንበትን መንገድም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 910(1)፣ 911፣ 925 እና ላልች ድንጋጌዎች ያሳዩናል። ስለሆነም የኑዛዜው ቃላት ግልፅ የሆኑ እንደሆነ የተናዛዡ እውነተኛ፣ ትክክለኛ ፈቃድ የትኛው ነው ብል ትርጓሜ መስጠትና ከኑዛዜው ቃል መራቅ የማይፈቀድ ስለመሆኑ ከላይ የተጠቀሱት የውርስ ሕግ ድንጋጌዎች ያሳያለ።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም የሟች አቶ ደበላ ልቡ ኑዛዜ ሟች ወ/ሮ ክብነሽ ጎንደል በሕይወት እስካለ ድረስ ለመሸጥ፣ ለመለወጥ የሚያስችላቸው እንጂ ከራሳቸው ጥቅም ውጪ ለላላ ሰው በኑዛዜ እንዱያስተላልፈ የሚያስችላቸው አለመሆኑን ከላይ የተገለፀው የኑዛዜ ክፍል ያሳያል። በመሆኑም ይኸው የኑዛዜ ክፍል የሟች ፍላጎትና መልዕክት ግልፅ የሚያደርገው ሆኖ እያለ የከፍተኛ ፍርድ ቤት የኑዛዜውን አንድን ክፍል ብቻ ነጥል ትርጉም የሰጠው ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 910(1) እና (2) ድንጋጌዎች ስር የተመለከተውን የኑዛዜ አተረጓጎም መርህን ባላገናዘበ መልኩ ሆኖ አግኝተናል። በዚህ ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 29 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ሚያዚያ 21 ቀን 2001 ዓ.ም በትዕዛዝ የጸናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/