No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 21 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ልጅነት ይታወቅልኝ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተጠሪ ሞግዚትና አስተዲዲሪ መጋቢት 13 ቀን 1997 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ ሕፃን ሐናን ከአቶ ታዱዮስ ሐረገወርቅ የወለድኳት ስለሆነ ሕፃን ሐና የአቶ ታዱዮስ ልጅ መሆኗ በፍርድ ውሳኔ ይታወቅልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀው ፍርድ ቤቱም የአሁኑ አመልካቾች በላለበት የተጠሪን ምስክሮችን በመስማት የተሻሻለውን የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀፅ 143(መ)”ን” መሰረት በማድረግ ሕጻን ሐና የአቶ ታዱዮስ ሐረገወርቅ ልጅ ናት በማለት ግንቦት 22 ቀን 1997 ዓ.ም ውሳኔ ሰጥቷል።
ከዚህም በኋላ የአሁኑ አመልካቾች ውሳኔው መብታችንን የሚነካ ነው በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 358 መሰረት መቃወሚያ አቅርበዋል። ለመቃወሚያው መሰረት ያደረጓቸው ነጥቦችም ለውሳኔ መሰረት የሆነው የልደት ምስክር ወረቀት የወጣው አቶ ታዱዮስ ሐረገወርቅ ህዲር 06 ቀን 1997 ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ ጥር 18 ቀን 1997 ዓ.ም ነው፣ የጥምቀት ምስክር ወረቀቱም አቶ ታዱዮስ ሐረገወርቅ ያልፈረሙበት ነው፣ የተሰሙት ምስክሮችም ለውሳኔው መሰረት የሆነው ድንጋጌ የሚጠይቀውን መመዘኛ በሚገባ አላስረደም የሚለ ናቸው። የአሁኗ ተጠሪም በአመልካቾች መቃወሚያ ላይ መልስ ሲሰጡ በጉዲዩ ላይ የቀረቡት የጽሐፍ ማስረጃዎች የወጡበት ሁኔታ በአሰራር ደረጃ የተለመደ በመሆኑ ማስረጃዎች በሕግ ፉት ተቀባይነት ያላቸው መሆኑንና ሟች ታዱዮስ ሐረገወርቅም ሕፃን ሐናን እንደአባት ሆነው ሲንከባከቧት የነበረ መሆኑ በምስክሮች ባግባቡ መመስከሩን ገልፀው መቃወሚያው ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል። የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ ሕፃን ሐና የሟች ታዱዮስ ሐረገወርቅ ልጅ ስለመሆኗ ልጅነት በፍርድ ከሚታወቅባቸው መንገድች መካከል በአንደ አልተረጋገጠም በማለት ቀደም ሲል የሰጠውን ውሳኔ ሰርዞታል።
በዚህ ውሳኔ የአሁኗ ተጠሪ ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ እና የተጠሪ ምስክሮችን በድጋሚ ከተሰሙ በኋላ ሟች ታዱዮስ ሐረገወርቅ ከሕፃን ሐና ወላጅ እናት ጋር ቀጣይነት ባለው ግንኙነት ውስጥ እንደነበሩ፣ ሕፃኗን እንደ አባት በመሆን ያሳድጓት እንደነበር መረጋገጡን እና የልደት ምስክር ወረቀትም ማስረጃውን በሰጠው አካል እስካልተሰረዘ ድረስ ተቀባይነት እንዲለው በመግለፅ ሟቹ የአቶ ታዱዮስ ሐረገወርቅ የህፃኗ አባት መሆናቸው በልደት ምስክር ወረቀትና በምስክሮች ቃል ተረጋግጧል ጠበቃ ፊንታሁን አባተ ቀረቡ በማለት በስር ፍርድ ቤት በመ/ ሰኔ 10 ቀን 1999 ዓ.ም የተሰጠውን ውሳኔ ሽሮታል። ከዚህም በኋላ የአሁኑ አመልካቾች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካቾች ጠበቃ ጥር 06 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሦስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቀርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ የልደት ምስክር ወረቀቱ አቶ ታዱዮስ ሐረገወርቅ ከሞቱ በኋላ የወጣ መሆኑ እየታወቀ እና የተጠሪ ምስክሮች ቃልም የሕፃኗ እናት እና አባት የተባለው ሰው በሕግ በተመለከተው የእርግዝና ጊዜ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ በግብረ ስጋ ግንኙነት አብረው የነበሩ ስለመሆኑ ሕጉ በሚጠይቀው መመዘኛ የመሰከሩ ስለመሆኑ የማያረጋግጥ ሆኖ እያለ ፍርድ ቤቱ በሕጉ የተቀመጠውን ጥብቅ መመዘኛ በማለፍ ሟች የሕፃን ሐና አባት ናቸው ብል የወሰነው ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ሕፃን ሐና የሟች ታዱዮስ ሐረገወርቅ ልጅ ናት በሚል የተሰጠው የልጅነት ምስክር ወረቀት ሟች ከሞቱ በኋላ የተሰጠ ነው እየተባለ የስር ፍርድ ቤት ይህንን የልጅነት ምስክር ወረቀት ብቻ መሰረት አድርጎ ሟች የሕፃኗ አባት ናቸው በማለት የሰጠው ውሳኔ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎ ተጠሪ ሐምል 08 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገፅ ማመልከቻ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢነት ያለው መሆኑን ያሳያለ ያሎቸውን ምክንያቶችን በመዘርዘር መልሳቸውን ሰጥተዋል። የአመልካቾች ጠበቃም ነሐሴ 20 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ አንድ ገፅ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ቀርቦ ላታይ ይገባዋል ሲባል ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አከራካሪው የልደት ምስክር ወረቀት ለተጠሪ የተሰጠው አቶ ታዱዮስ ሐረገወርቅ ሕዲር 06 ቀን 1997 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ ጥር 18 ቀን 1997 ዓ.ም መሆኑን፣ ይህንኑ የልደት ምስክር ወረቀት የሰጠው አካልም ሥልጣን ያለው ሆኖ ማስረጃውን ያልሰረዘው መሆኑን፣ ተጠሪ ከዚህ የሰነድ ማስረጃ በተጨማሪ በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ማስረጃ የሰው ምስክሮችን የሚጨምር መሆኑን የስር ፍ/ቤት በጉዲዩ ላይ ውሳኔ የሰጠው የሰነድ እና የሰው ምስክሮች ቃል በመመዘን መሆኑን ነው። የስር ፍርድ ቤት የደረሰበት ድምዲሜም ሟች ታዱዮስ ሐረገወርቅ የህፃን ሐና አባት መሆናቸው በልደት ምስክር ወረቀትና በምስክሮች ቃል ተረጋግጧል የሚል ስለመሆኑም የውሳኔው ግልባጭ በግልፅ የሚያሳይ መሆኑንም ተገንዝበናል።
ልጅነት ደግሞ በቀዲሚነት በልጅነት የምስክር ወረቀት የሚረጋገጥ ሲሆን የልጅነት ምስክር ወረቀት ከላለ ደግሞ የልጅነት ሁኔታ መኖሩን በማሳየት እንደሚረጋገጥ፣ የልጅነት ሁኔታ የላለ ከሆነ ሲሆንም ተወላጅነትን በምስክሮች ወይም ማናቸውንም ዓይነት ማስረጃ በማቅረብ ማስረዲት እንደሚቻል የተሻሻለው የቤተሰብ ሕጉ እንደቅደም ተከተለ በአንቀፅ 156፣ 168፣ 158፣ እና 169 ስር ደንግጓል። አመልካቾች አጥብቀው የሚከራከሩት ደግሞ የልደት ምስክር ወረቀት ለተጠሪ የተሰጠበት ጊዜ ሟች ታዱዮስ ሐረገወርቅ ከሞቱ በኋላ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት ነው። ይሁን እንጂ የልደት ምስክር ወረቀት አባት ነው የተባለው ሰው ከሞተ በኋላ የተሰጠ ሆኖ ሲገኝ ዋጋ የለውም የሚል የሕግ ድንጋጌ የላለ ሲሆን የስር ፍርድ ቤትም ማስረጃው በተገቢው አካል እስካልተሰረዘ ድረስ ዋጋ አለው በማለት ከተጠሪ የሰው ምስክሮች ቃል ጋር አዛምድ በመመዘን ክብደት መስጠቱ በማስረጃ አቀባበል ላይ የተፈፀመ ስህተት ስለመኖሩ የሚያሳይ አይደለም። ይልቁንም የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሲታይ መሰረት ያደረገው ማስረጃ ምዘናን ነው። የማስረጃ ምዘና ጉዲይ ደግሞ የሰበር ችልት ስልጣንና ኃላፉነት አለመሆኑን ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 80(3/ሀ) እና ከአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 10 እና 22 ድንጋጌዎች ይዘት የምንገነዘበው ነጥብ ነው። በመሆኑም በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት ስላልተቻለ ሉፀና የሚገባ ሆኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 10 ቀን 2001 ዓ.ም በተሰጥቶ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር ታህሳስ 01 ቀን 2001 ዓ.ም በትዕዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
ሕፃን ሐና የሟች ታዱዮስ ሐረገወርቅ ልጅ ናት ተብል መወሰኑ ባግባቡ ነው ብለናል።
ለክርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.