No summary available.
ህዲር 08 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- እነ ወ/ሮ ጽጌ ወልደመስቀል (6 ሰዎች) ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ስዩም ክፍላ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ የሰበር መዝገብ የቀረበው ክርክር በውርስ ህጉ ውስጥ የተመለከቱትን ይርጋ ድንጋጌዎችን አተረጓጎም እና አፈፃፀማቸውን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪ ጥቅምት 22 ቀን 1997 ዓ.ም አሻሽለው በአሁኑ አመልካቾች ላይ ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ ተጠሪና አመልካቾች የኮልኔል ክፍላ ደስታ ወራሾች ለመሆናቸው በአውራጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 1009/80 ህዲር 11 ቀን 1980 ዓ.ም ማረጋገጣቸውን፣ የአውራሻቸው ንብረት የሆነ በጉለላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 11 ቁጥሩ 228 የሆነ ቤት ከአመልካቾች ጋር በእኩልነት በመካፈል የደረሳቸው እንዲላቸው፣ ቤቱን አመልካቾች ተጠሪን አስወጥተው በመኖሪያነት እና እያከራዩ በመጠቀም ላይ እንደሚገኙ፣ የቤቱ ግምት ድርሻቸውም ብር 33,547.90 (ሰላሳ ሶስት ሺህ አምስት መቶ አርባ ሰባት ብር ከዘጠና ሳንቲም)፣ የኪራይ ደግሞ ብር 8118.75(ስምንት ሺህ አንድ መቶ አስራ ስምንት ብር ከሰባ አምስት ሳንቲም) እንደሚሆን ገልፀው አመልካቾች ገንዘቡን እንዱከፍሎቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። አመልካቾችም በተከሳሽነታቸው ቀርበው ክሱ የቀረበው አውራሻቸውን ከሞቱበት ከመስከረም 28 ቀን 1980 ዓ.ም በኋላ ታህሳስ 24 ቀን 1992 ዓ.ም በመሆኑ እና ይህንንም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000(1) ስር የተመለከተው የሶስት ዓመት የይርጋ ጊዜ ገደብ የሚያግደው ነው፣ የኪራይ ገንዘብ ጥያቄም ከዘጠኝ ዓመትና ከሰባት ወር በኋላ የቀረበ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(መ) መሰረት እንደተከፈለ የሚቆጠር ነው በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነጥቦችን አንስተው የተከራከሩ ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድም ተገቢነት አሎቸው ያሎቸውን ነጥቦችን በማንሳት ተከራክረዋል። የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ አመልካቾች ብር 7422.50 (ሰባት ሺህ አራት መቶ ሀያ ሁለት ብር ከሃምሳ ሳንቲም) እንዱከፍለ፣ ቤቱን በተመለከተም 1/2ኛው ለአንደኛ አመልካች ከተሰጣቸው በኋላ ላላው ቀሪውን 1/2ኛው ከተቻለ በአይነት፣ ካልተቻለ በስምምነት ወይም በሐራጅ ከተሸጠ በኋላ 1/6ኛው ለተጠሪ እንዱሰጥ ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካቾች ባለመስማማት ይገባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ይርጋን በተመለከተ የቀረበው ቅሬታ፤ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ጥያቄ የውርስ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ እንጂ የወራሽነት ጥያቄ ባለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/1/ መሰረት እንደማይታገድ፣ የኪራይ ገንዘብ ጥያቄም የተከራይና አከራይ ግንኙነት የላለ በመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2024/መ/ አግባብነት የላለው መሆኑን በመግለጽ የአመልካቾችን የይግባኝ ቅሬታ ውድቅ ካደረገ በኋላ ቤቱን በተመለከተ የስር ፍ/ቤት ያስቀመጠውን ክፍፍል በማሻሻል ተገቢ ነው ያለውን የክፍፍል መንገድ በመጥቀስ ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይርጋንና የቤቱን ክፍፍል አስመልክቶ የተሰጠውን ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካቾች ጠበቃ ሰኔ 15 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ አራት ገጽ የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ነው የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ለጉዲዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት ያለው ድንጋጌ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/1/ ሆኖ እያለ የይርጋ ክርክሩ መታለፈና ቤቱን በተመለከተ የተሰጠው የክፍፍል ጥያቄም የአንደኛዋን አመልካች ግማሽ ባለድርሻነት አለማገናዘቡ ተገቢነት የላለው ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል ተጠሪ ቀርበው ጥቅምት 4 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገጽ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። የመልሳቸው ይዘትም የይርጋ ክርክሩ የታለፈው ጥያቄው የውርስ ንብረት ክፍፍል በመሆኑ መሆኑንና የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000/1/ ድንጋጌ ተፈፃሚነቱ የወራሽነት ጥያቄን በሚመለከት ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አመልካቾች ህዲር 1 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነ ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ሲባል ከተያዘው የይርጋ ክርክር የመታለፈ አግባብነት አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ የሟች ወራሽነታቸውን ከአመልካቾች ጋር በአንድነት ህዲር 11 ቀን 1980 ዓ.ም በፍርድ ቤት ማስወሰናቸውን፣ አሁን እየተከራከሩ ያለት የውርስ ንብረት ድርሻቸውን አመልካቾች እንዱያካፍሎቸው መሆኑን ነው።
የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000 የወራሽነት ጥያቄ የማቅረቢያ የጊዜ ገደብ ነው። ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 996 እስከ 1002 ድረስ ከተደነገጉት ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻለውም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 999 ስር በተመለከተው መሰረት የሚቀርበው የወራሽነት ጥያቄ (Petition hereditists) በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 996 እና ተከታዬቹ ቁጥሮች ከተገለፀው የወራሽነት የምስክር ወረቀት ጋር የተያያዘ መሆኑን ነው። በመሆኑም የወራሽነት ጥያቄ አንድ ወራሽ በልላ በወራሽነት የውርስ ሐብት በያዘ ሰው ላይ ክስ ሲያቀርብ ተፈፃሚነት ባላቸው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000/1/ እና /2/ ድንጋጌዎች ስር በተመለከቱት ደንቦች መሰረት የሚገደብ ነው።
በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ የሟች ኮልኔል ክፍላ ደስታ ወራሽነታቸውን ህዲር 11 ቀን 1980 ዓ.ም ከላልች ወራሾች ጋር በመሆን በፍርድ ቤት ውሳኔ አረጋግጠው የክፍፍለ ጥያቄ በቀረበበት ቤት ውስጥ ከአመልካቾች ጋር ይኖሩ የነበረ መሆኑ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። ከዚህም የምንገነዘበው የሟቹ ወራሾች ተለይተው መታወቃቸውን ነው። የተጠሪ ጥያቄ ደግሞ የውርስ ክፍያ ነው። የውርስ ክፍያ ደግሞ ራሱን የቻለ የውርስ ህግ ሆኖ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1060 እስከ 1113 ድረስ ባለት ድንጋጌዎች ስር የተሸፈነ ጉዲይ ነው። የውርስ ክፍያ ጊዜን በተመለከተ የፍ/ብ/ሕጉ በአንቀጽ 1062 ስር የደነገገ ሲሆን የድንጋጌው ይዘትም ውርሱ በተጣራ ጊዜ በማናቸውም ጊዜ ቢሆን እያንዲንደ የጋራ ወራሾች ውርሱን እንከፊፈል ብለው ለመጠየቅ እንደሚችለ መደንገጉን የሚያሳይ ነው። በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1060 ድንጋጌ ስር ደግሞ የውርስ አከፊፈል እስካልተፈፀመ ድረስ ውርሱ በወራሾች መካከል ሳይነጣጠል እንደሚቆይ ተመልክቷል። በመሆኑም ተጠሪ የሟች ወራሽነታቸውን በሕጉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ አረጋግጠው ከቆዩ በኋላ የውርስ ንብረቱን የክፍፍል ጥያቄ ማቅረባቸው በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000/1/ እና /2/ ስር በተመለከተው የይርጋ ድንጋጌ የሚታገድ ሳይሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1062 ድንጋጌ መሰረት በማናቸውም ጊዜ የሚቀርብ በመሆኑ ፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የፈፀመው መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት አለ ለማለት አልተቻለም።
ላላው አመልካቾች አጥብቀው የሚከራከሩት በቤቱ ላይ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን የክፍፍል ሥነ-ሥርዓቱን በተመለከተ ነው። የውርስ አከፊፈል አሰራርን በተመለከተ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1082 እስከ 1096 ድረስ ባለት ድንጋጌዎች መሰረት መፈፀም ያለበት መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1083 ድንጋጌ በግልጽ ያሳያል። በዚህም መሰረት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ሲታይ በህጉ የተመለከተውን የውርስ አከፊፈል አሰራርንና በቤተሰብ ህጉም የተመለከቱትን አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎችን ያገናዘበ ነው ከሚባል በስተቀር የአንደኛ አመልካችን መብትም ሆነ የላልችን አመልካቾችን መብት ያጣበበ ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም። አመልካቾች ለተጠሪ የቤቱን ግምት ከፍለው ቤቱን በአይነት ለማስቀረት ከፈለጉም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1060/2/ የጋራ ወራሾች የሆኑ ሰዎች ባልተከፊፈለት የውርስ ንብረቶች ላይ ያላቸው መብት ስለ የጋራ ባለሐብትነት፣ ስለ ሪምና ስለ ላልች ግዙፍ መብቶች በሚለው የፍትሐብሕር ሕጉ አንቀጽ በተነገሩት ድንጋጌዎች መሰረት ይወሰናል በማለት ስለሚደነግግ በእነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት የቤቱን የገቢያ ዋጋ ለተጠሪ በመስጠት የቅድሚያ ግዥ መብት (Right of Recovery) ጥያቄ ከሚያነሱ በስተቀር ከወዱሁ ተጠሪ ቤቱን በሐራጅ እንዱሸጥ መጠየቅ አይችለም በማለት ሉቃወሙ የሚችለበት ጉዲይ አይደለም። በመሆኑም በዚህ ረገድ የቀረበው የአመልካቾች ቅሬታም ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። ሲጠቃለልም፤ ጉዲዩን በይግባኝ ተመልክቶ ውሳኔ ያሳረፈው ፍርድ ቤት የውርስ ህግ ድንጋጌዎችና አፈፃፀም ላይ የፈፀመው መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ስላልተገኘ ውሳኔው ሉፀና የሚገባ ነው በማለት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 15 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሚያዚያ 22 ቀን 2000 ዓ.ም ተሻሽል የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ሥ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.