No summary available.
ጥቅምት 10 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ዘውዳ ወ/ጊዮርጊስ - ጠበቃ ፈጠነ ከበደ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ት ኤልሳቤጥ ኪዲኔ - ቀረበች **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ አባትነት ይረጋገጥልኝ ጥያቄን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን አመልካች የነበሩት የአሁኗ ተጠሪ ናቸው። የአቤቱታቸው ይዘትም፤ወላጅ እናቴ ወ/ሮ ቻይና ከበደ ከሟች ፉታውራሪ ኪዲኔ ኃይላ ጋር ከጋብቻ ውጪ ባደረጉት ነዋሪ የሆነ ግንኙነት በ1971 ዓ.ም የተወለድኩ፣እኔ በተፀነስኩበት ጊዜ ሟችና እናቴ በአንድ ግቢ፤ በአንድ ቤት ውስጥ ይኖሩ የነበረ ሲሆን ሟች በሕይወት እያለ በወር ብር 200.00(ሁለት መቶ) በወላጅ እናቴ አማካኝነት ቀለብ ይከፍለ ነበር፣ስለዚህ ከሟች ፉታውራሪ ኪዲኔ ኃይላ መወልዳ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 125/1/ መሰረት ተረጋግጦ ማስረጃ ይሰጠኝ በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው። የአሁኗ አመልካችም በጣልቃ ገብነት ወደ ክርክሩ ገብተው ተጠሪ አባትነት እንዱታወቅ ያቀረቡት ክስ የተሟላ ስላልሆነና የተጠሪ እናት ወ/ሮ ቻይና ከበደ ከሟች ፉታውራሪ ኪዲኔ ኃይላ ጋር በሕግ የታወቀ ግንኙነት እንደነበራቸው ያስወሰኑበትን ማስረጃ ስላላቀረቡ አቤቱታቸው የክስ ምክንያት የለውም የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድም ተጠሪ መቼ ቀንና ወር እንደተወለደ ስላልጠቀሱ፣ሟች ከተጠሪ እናት ጋር ለአንድም ጊዜ አብረው ኖረው ስለማያውቁ፣ሟች ከተጠሪ እናት በየትኛው ግቢ መቼ እንደኖሩ ስላልተገለፀና ለተጠሪ እናት በወር ሁለት መቶ ብር ቀለብ መክፈል አባት ለልጁ በሕግ ማድረግ የሚገባውን እንክብካቤ መመዘኛዎችን ስለማያሟላና ቀለብም ቆርጠውላቸው ስለማያውቁ፣የተጠሪ ምስክሮች በምን ጭብጥ ላይ ቃላቸውን እንደሚሰጡ በአቤቱታቸው ስላልጠቀሰ፣እስከሞቱበት ጊዜ ድረስ በሟችና በተጠሪ መካከል የአባትነት እና የልጅት ግንኙነት ሁኔታ ስላልነበረ አቤቱታው ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ተጠሪ እንደክሳቸው አቀራረብ ሟች ፉታውራሪ ኪዲኔ ኃይላና እናታቸው ቻይና ከበደ ተጠሪ የተወለደበትንና የተፀነሱበትን ጊዜ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 125/1/ እና 106/2/ ድንጋጌዎች መሰረት አላስረደም፣የምስክሮች ቃልም እርስ በራሱ የሚጋጭ ነው በማለት የተጠየቀውን ዲኝነት ውድቅ አድርጓል። በዚህ ውሣኔ ተጠሪ ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ በምስክሮች ቃል ተከሰተ የተባለው ልዩነት ጊዜን ብቻ የሚመለከት መሆኑን ይህ ልዩነት ከአጠቃላይ የምስክሮች ቃል ይዘት ጋር ተዛምድ ላታይ እንደሚገባ በመጥቀስ በተጠሪ ምስክሮች ቃል ፍሬነገር ላይ ቅራኔ ሳይኖርና ምስክርነቱ የተሰጠበት ጊዜ እርዝማኔ ግምት ውስጥ መግባት እንደአለበት በመግለጽ የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ በመሻር የተሻሻለውን የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 106/1/ እና 125/1/”ን” ጠቅሶ ተጠሪ የሟች ፉታውራሪ ኪዲኔ ኃይላ ልጅ ናት ሲል ወስኗል። በዚህ ውሣኔ የአሁኗ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ጠበቃ መጋቢት 21 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት 4(አራት) ገጽ የሰበር አቤቱታ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከቱት ፍርድ ቤቶች በሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል ትእዛዝ ተሰጥቶ ተጠሪ ቀርበው ሐምል 16 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ 4/አራት/ ገጽ ማመልከቻ መልሣቸውን አቅርበዋል። አመልካችም የመልስ መልሣቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም ተጠሪ የሟች ፉታውራሪ ኪዲኔ ኃይላ ልጅ ናት ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የተጠሪ ክስ መሰረት ያደረገው ሟች ፉታውራሪ ኪዲኔ ኃይላ እና ወ/ሮ ቻይና ከበደ ጋብቻ ሳይፈጸም እንደባልና ሚስት አንድ ላይ ሲኖሩ ተፀንሰው የተወለደ መሆኑንና ሟች ፉታውራሪ ኪዲኔ ኃይላ ለተጠሪ በወር ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) ቀለብ ይሰጡ የነበረ መሆኑን ሆኖ ይህንኑ ለማስረዲትም የሰው ምስክሮችን አቅርበው ያሰሙ መሆኑን ነው። ጉዲዩን በተመለከቱት ፍርድ ቤቶች የተመዘገበው የተጠሪ ምስክሮችን ቃል ይዘት፡-1ኛ ምስክር የአመልካች እናት ሲሆኑ ከሟች ፉታውራሪ ኪዲኔ ኃይላ ጋር ከ1971 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ዓመት በቤታቻው ውስጥ አብረው ሲኖሩ ተጠሪን ሦስት ወር እርጉዝ ሆነው ሟች ቤት ተከራይተው ከቤታቸው እንደአስወጡ፣በወር ብር 200.00 ይረዶቸው እንደነበርና የቤት ኪራይም ይከፍለላቸው የነበረ መሆኑን፣ገንዘቡን ሕይወታቸው እስከአለፈ ጊዜ ድረስ መስጠታቸውን፣በሟች ቤት በኪራይ በሱማላ ጦርነት ጊዜ ከውጪ ዜጋ ጋር ይኖሩ የነበረ መሆኑንና ሟች ልጅ ውለጂልኝ፣ቤት ተከራይቼ አስቀምጥሻለሁ ያሎቸው መሆኑን፣ተጠሪን ዓመተምህረቱን በማያስታውሱት በየካቲት ወር የውጪ ዜጋው ከሄደ ከሁለት ዓመታት በኋላ ከሟች መውለዲቸውንና የባልና ሚስት ፊርማ ግን ያልነበራቸው መሆኑን መመስከራቸውን፣2ኛ ምስክር በበኩላቸው ወ/ሮ ቻይና ከ1969 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1980 ዓ.ም ድረስ በሰገነት ሆቴል ውስጥ ከፉታውራሪ ኪዲኔ ጋር ሲወጡ ሲገቡ አያለሁ፣ልጅ ግን አልወለደም በማለት መመስከራቸውን፣3ኛ ምስክር ደግሞ ፉታውራሪ ኪዲኔ እና ወ/ሮ ቻይና በ1970 ዓ.ም ሰገነት ሆቴል ውስጥ አብረው ይኖሩ እንደነበረ፣ወ/ሮ ቻይና ከበደ ወሩን በማያስታውሱት በ1970 ዓ.ም የሦስት ወር ቅሪት ነኝ ብለው የነገሯቸው መሆኑን፣ሟችና ወ/ሮ ቻይና ከበደ እንደ ባልና ሚስት መኖራቸውን እንደሚያውቁ፣በ1970 ዓ.ም መጨረሻ ወደ አዱስ አበባ በመሄዲቸው ልጅ መውለደን ግን አላውቅም በማለት መመስከራቸውንና 4ኛ ምስክርም በ1973 ዓ.ም ወ/ሮ ቻይና ቤት ተከራይተው ይኖሩ ነበር፣ሟች በሕይወት እስካለ ድረስ ለረጅም ጊዜ ለተጠሪ ቀለብ እያለ በየወሩ ሲሰጡ የነበረ መሆኑን እንደሚያውቁ በመግለጽ መመስከራቸውን የሚያሣይ መሆኑን ነው።
በተሻሻለው የፋዳራል የቤተሰብ ሕግ አባትነት የሚታወቅባቸው መንገድች፣ በእናትየዋና በአንድ ወንድ መካከል በሕግ የታወቀ ግንኙነት መኖሩን በማረጋገጥ፣አባትየው ልጁን ልጄ ነው ሲል በመቀበለ ምክንያት ወይም በፍርድ በሚሰጥ ውሣኔ እንዱታወቅ ሲደረግ የሚለት ሦስት መንገድች ናቸው።
አባትነት በሕግ ግምት የሚታወቅበት መንገድ በተዘዋዋሪ የጋብቻ መኖሩን ወይም ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት አብሮ መኖርን በማስረዲት የሚረጋገጥ ነው። በዚህ ረገድ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ይዘትና አቀራረፃቸው ወንድየውና ሴትየዋ በሕግ በታወቀው ግንኙነት መኖራቸውና መኖር የጀመሩበት ጊዜ ከግምት ሉገባና በተገቢው መንገድ ሉረጋገጥ እንደሚገባው ያስገነዝባለ። በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 126 መሰረት ልጅ በሚፀነስበት ወይም በሚወለድበት ጊዜ በልጅ እናትና በአንድ ወንድ መካከል በሕግ የታወቀ ግንኙነት መኖሩ ከተረጋገጠ ወንድየው የልጁ አባት ነው የሚል የሕግ ግምት እንደሚወሰድ ተመልክቷል። በዚህ የሕጉ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው በልጁ እናትና በወንድየው መካከል በሕግ የታወቀ ግንኙነት እንዲለ ወይም የተወለደው በሕግ የታወቀው ግንኙነት ፀንቶ ባለበት መሆኑን ማሣየት የግድ የሚል መሆኑን ነው። በቤተሰብ ሕጉ “በሕግ የታወቀ ግንኙነት” የሚባለ ግንኙነቶች ጋብቻ አንደ ስለመሆኑ አንቀጽ 1/1/ እና /2/ ድንጋጌዎች የሚያሣዩ ሲሆን የኢ.ፋ.ዳ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 35/2/ ድንጋጌ ይዘትም ይህንኑ ያስረዲል። ላላው በሕግ የታወቀ ግንኙነት የሚባለው ጋብቻ ሣይፈጸም እንደባልና ሚስት አብሮ መኖር ስለመሆኑም የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 98 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች የሚያስገነዝቡት ነው። በመሆኑም የሕግ ግምት ተጠቃሚ የሚሆነው ልጅ በጋብቻ ወይም ጋብቻ ሣይፈጸም እንደባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ በሕጉ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ የተጸነሰ ወይም የተወለደ ልጅ ነው። በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 128/1/ አንድ ልጅ ጋብቻው ከተፈጸመ ከ180 ቀናት በኋላ ወይም ጋብቻው በፈረሰ በ300 ቀናት ውስጥ የተወለደ እንደሆነ ልጁ በጋብቻው ውስጥ እንደተፀነሰ ንኡስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ ለዚሁ ተቃራኒ የሆነ ማስረጃ ተቀባይነት እንደማይኖረው አስገዲጅነት ባለው መልኩ አስቀምጧል። እንዱሁም የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 130/2/ ድንጋጌ አንቀጽ 128 ድንጋጌ ሥር የተመለከተው ሕጋዊ ግምት በጋብቻ ተሳስረው በሚገኙ ተጋቢዎች ብቻ ሳይሆን ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት አብረው በሚኖሩ ወንድና ሴት ላይም ተፈፃሚ መሆናቸውን ያስገነዝባል።
እንግዱህ ሕጉ እነዚህን ሁኔታዎች ካስቀመጠ በጉዲዩ ላይ የሚቀርበው ማስረጃም በተገቢው መንገድ በጥንድች መካከል የነበረውን ግንኙነት ዓይቱንና የጽንሱ ጊዜ እንዱሁም የልደት ጊዜው ማረጋገጥ ይጠበቅበታል።
በተያዘው ጉዲይ የተጠሪ ምስክሮች ቃል የተጠሪ እናትና ሟች ፉታውራሪ ኪዲኔ ኃይላ የነበራቸውን የግንኙነት ዓይነት በተመለከተ የተጋቡ ሰዎችን ሁኔታ ሲያሳዩ እንደነበርና ቤተሰቦቻቸውም ሆነ ማህበረሰቡ እንደተጋቡ ሰዎች የሚኖሩ ናቸው ብለው ይገምቷቸው እንደነበር የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ የተጠሪ እናትና ሟች አብረው ይኖሩ ነበር የተባለውን ጊዜ እና ተጠሪ ተወለደ የተባለውን ጊዜ በተመለከተ ልዩነት ባለበት ሁኔታ መመስከራቸውን ከመዝገቡ ግልባጭ ተመልክተናል። ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይኸው ፍሬ ነገር ስለመኖሩ ግንዛቤ ለተጠሪ ምስክሮች ቃል ክብደት ሰጥቷል። ይሁን እንጂ ይኸው የፍርድ ቤቱ አካሄድ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 128፣130፣106 እና 125 ድንጋጌዎች ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች አፈፃፀም ተግባራዊነቱን ሉያሣይ የሚችል ነው። በመሆኑም የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪ እናትና በሟች ፉታውራሪ ኪዲኔ ኃይለ መካከል በህጉ አግባብ የተፈጸመ ጋብቻ ሣይኖር እንደባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት ለመኖሩ ተጠሪ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 125/1/፣128፣130 እና 106/2/ አንፃር ያላስረደና ያቀረቧቸው ምስክሮች ቃልም እርስ በእራሱ የሚጋጭ መሆኑን ገልጾ የደረሰበትን ድምዲሜ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሻረው ሕጋዊ በሆነ ምክንያት ሆኖ አልተገኘም። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም በከፍተኛው ፍርድ ቤት የተፈጸመውን ስህተት ማረም ሲገባው ውሣኔውን ማጽናቱ ባግባቡ ሆኖ አልተገኘም።
በዚህም መሰረት ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከቱት ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉሻር የሚገባው ነው።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ኀዲር 09 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋደራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ መጋቢት 08 ቀን 2001 ዓ.ም በትእዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 15572 የካቲት 18 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
ተጠሪ የሟች ፉታውራሪ ኪዲኔ ኃይላ ልጅ አይደለም ብለናል።
ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.