No summary available.
ታህሣሥ 06 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- ወ/ሮ ዘነበች በያን - ተወካይ አለምነሽ ከበደ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ት ብርቅነሽ ከበደ - ቀረቡ
በዚህ መዝገብ የተያዘው ጉዲይ ልጅነት ማረጋገጥን የሚመለከት ነው። የአሁኑዋ ተጠሪ በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታ አባታቸው የ፶ አለቃ ከበደ በያን እና እናታቸው ወ/ሮ ብርሃኔ ኃ/ማሪያም ተጋብተው ሲኖሩ በ1964 ዓ.ም የተወለደ በመሆኑና አባታቸው ፶ አለቃ ከበደ በያን ከዚህ አለም በሞት ስለተለዩ የሟቹ ልጅ መሆናቸው ተረጋግጦ ማስረጃ እንዱሰጣቸው ጠይቀዋል። ተጠሪም ቀርበው ሟች የ፶ አለቃ ከበደ በያን እና ወ/ሮ ብርሃኔ ኃ/ማርያም ልጅ ያልወለደና ተጠሪ የወ/ሮ ብርሃኔ የክርስትና ልጅ መሆናቸውን ገልፀው ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም በግራ ቀኙ የቀረቡትን ምስክሮች ከሰማ በኋላ በተሻሻለው ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 156 መሰረት የሟች የ፶ አለቃ ከበደ በያን ልጅ ናቸው ሲል ወስኗል። አመልካች በውሳኔው ቅር በመሰኘት ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ ይግባኙን ባለመቀበል መዝገቡን ዘግቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካች በቅሬታቸው የ፶ አለቃ ከበደ በያን እና ወ/ሮ ብርሃኔ ኃ/ማርያም በጋብቻቸው ዘመን ልጅ ያልወለደና ወ/ሮ ብርሃኔም መሐን የነበሩ በመሆኑ የስር ፍ/ቤት ጉዲዩን በሚገባ ሳያጣራ ተጠሪ የሟች ልጅ ናቸው ሲል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት የሚል ነው። ችልቱም ተጠሪ የሟች ልጅ ናቸው ተብል የሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ የፁሁፍ ክርክር አቅርበዋል። ችልቱም መዝገቡን መርምሯል።
በስር ፍ/ቤት አቤቱታ የቀረበው ተጠሪ የሟች የ፶ አለቃ ከበደ በያን ልጅ ስለመሆናቸው እንዱረጋገጥ ነው። በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ልጅነትን ማስረዲት የሚቻለው የልደት ምስክር ወረቀት በማቅረብ ወይም የልደት ምስክር ወረቀት የላለ እንደሆነ የልጅነት ሁኔታ መኖሩን በማስረዲት እንደሆነ ከፍ ሲል የተጠቀሰው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 154 እና 155 ያመለክታለ። ከመዝገቡ ሂደት ለመረዲት እንደሚቻለው ተጠሪ ልጅነታቸውን ለማስረዲት የሞከሩት የልጅነት ሁኔታ መኖሩን በማረጋገጥ ነው። አንድ ሰው የልጅነት ሁኔታ አለው የሚባለው በማህበረሰቡ ዘንድ የእርሱ ልጅ ነው ተብል ሲገመት መሆኑን ከአንቀጽ 156 መረዲት ይቻላል። የልጅነት ሁኔታ መኖሩን ማስረዲት ከተቻለ ፍ/ቤት ልጅ ሲል የሕግ ግምት ሉወሰድ የሚችል መሆኑ አንቀጽ 157/1/ ያመለክታል።
ከአንቀፁ መረዲት እንደሚቻለው የልጅነት ሁኔታ መኖሩን ማረጋገጥ የመጨረሻ ማስረጃ (conclusive evidence) ሳይሆን የሕግ ግምት ብቻ ነው። ግምቱም ቢሆን አስገዲጅነት ያለው የሕግ ግምት አይደለም። ግምቱን የሚቃወም ወገን ማስረጃ በማቅረብ ግምቱን ማፍረስ እንደሚችል ንኡስ አንቀጽ 2 ይደነገጋል። በተያዘው ጉዲይ ከስር ፍ/ቤት ውሳኔ ግልባጭ እንደተረዲነው ሟች የተጠሪ ልጅ ለመሆናቸው የሰው ምስክሮች ያቀረቡ ሲሆን አመልካችም ቢሆኑ ተጠሪ ልጅ አለመሆናቸውን ለማስረዲት ተቃራኒ ማስረጃ አቅርበዋል። ነገር ግን የተጠሪ ምስክሮች ተጠሪ ሟች እና ወ/ሮ ብርሃኔ ባልና ሚስት በነበሩበት ጊዜ የተወለደና የአካባቢውም ህብረተሰብ ተጠሪን የሟች ልጅ አድርጏ የሚገምት መሆኑን ሲያስረደ የአመልካች ምስክሮች ይህንን የሕግ ግምት ማፍረስ አልተቻላቸውም። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት ተጠሪ የልጅነት ሁኔታ መኖርን ስላረጋገጡ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 156 መሰረት የ፶ አለቃ ከበደ በያን ልጅ ናቸው ሲል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለው ለማለት አልተቻለም።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 12503 ግንቦት 04 ቀን 2000 ዓ.ም ሰጠው ውሳኔ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 68578 ጥቅምት 13 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ፀንቷል፡
ተጠሪ የ፶ አለቃ ከበደ በያን ልጅ ናቸው ብለናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.