No summary available.
ጥቅምት 10 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሀይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካቾች፡- እነ ወ/ት ሰናይት ኃ/ማርያም - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አበበች ወርቁ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን ቀጥል የተመለከተውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ ጉዲይ በአመልካቾች አባት እና በተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ መፈረስን ተከትል የንብረት ክፍፍልን የሚመለከት ሲሆን ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት የውርስ አጣሪ ሰይሞ አጣሪውም ጉዲዩን ከተመለከተ በኋላ ለሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነውን የቤ.ቁ 084 ጨምሮ የባልና ሚስቱ የጋራ ሀብት ነው በማለት ሪፖርቱን ለፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት አቅርቦ ፍ/ቤቱም ይህንኑ ሪፖርት ተቀብል ማጽደቁን ተገንዝቦአል።
ከዚህ በኋላም የአሁን አመልካቾች የቤ.ቁ 084 የሆነው ቤት የሟች አባታችን የግል ንብረት ሆኖ ሳለ የባልና ሚስቱ የጋራ ንብረት ነው ተብል በውርስ አጣሪ የተደረሰበትን ሪፖርት የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ተቀብል ሪፖርቱን ማጽናቱ በአግባቡ አይደለም በማለት የይግባኝ ቅሬታቸውን ለፋዳራል ከ/ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱም በበኩለ ግራ ቀኙን አከራክሮ የውርስ አጣሪው ቤቱ የጋራ ነው ወደሚል ድምዲሜ የደረሰው የጋብቻ ውለን መሰረት በማድረግ ሲሆን ነገር ግን ውለ የጋራ ያደረገው የቤቱን ገቢ እንጂ ቤቱን እንዲልሆነ ከውለ በግልጽ መረዲት ይቻላል ካለ በኋላ የሥር ፍ/ቤትን ውሳኔ በመሻር ይሄው ቤት የአመልካቾች አባት የግል ሀብት ነው በማለት ውሳኔ መስጠቱን መዝገቡ ያስረዲል።
የአሁን ተጠሪም በከፍተኛው ፍ/ቤት ውሳኔ ቅሬታ አድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታ ለፋ/ጠ/ፍ/ቤት አቅርበው ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ይግባኝ ባይና የመ/ሰጭዎች አባት ሲጋቡ የቤ.ቁ 084 አስቀድሞ በሟች ተሰርቶ የነበረና ሁለት ክፍል ቤት ብቻ የነበረ ሲሆን ነገር ግን በጋብቻ ላይ እያለ ቤቱን በተደጋጋሚ ማደሳቸው ይህ ቤት እንዲይሸጥ በማሰብም ላላ ቤት ሸጠው ለዕዲ መክፈያነት በማዋል ቤቱ ከመሸጥ ስለማዲናቸው ቤቱም በፉት ከነበረው ሁለት ክፍል ላይ ተጨማሪ 9 ክፍል ሰርቪስ ቤቶችን በጋራ ስለመስራታቸውና አስቀድሞ ቤቱ የሚገኝበት ይዞታ 300 ሜ.ካሬ ብቻ የነበረ ሲሆን ነገር ግን በተጨማሪ ግንባታ ሲደረግ ይዞታውም ወደ 578 ካ.ሜትር ከፍ ስለማለቱ በክርክሩ የተረጋገጠ ስለሆነ በዚህ ሁኔታ ቤቱ የመ/ሰጪዎች አባት የግል ንብረት ነው መባለ በአግባቡ አይደለም በማለት በመሻር የባልና ሚስቱ የጋራ ሀብት ነው ሲል ውሳኔ ሰጥቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህም ችልት አቤቱታውን መርምሮ ለሰበር ላቀርብ ይገባል ብል ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን አከራክሯል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባው የጉዲዩ ጭብጥ ክርክር ያስነሳው ቤት የባልና ሚስቱ የጋራ ሀብት ነው? ወይንስ የባል የግል ንብረት? የሚለው ነው።
ከዚሁ ጭብጥ አኳያም ጉዲዩን መርምረናል።
ባልና ሚስት ጋብቻቸውን በሚፈጽሙበት ጊዜ በየግል የነበሯቸው ንብረቶች የግል ንብረቶቻቸው ሆነው እንደሚቀሩ በተሻሻለ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 57 ላይ ተመልክቷል። የአመልካቾች አባትና ተጠሪ ጋብቻቸውን በፈጸሙ ጊዜ የቤ.ቁ 084 በሟች የአመልካቾች አባት ስም ተመዝግቦ ሁለት ክፍል ቤት ብቻ እንደነበር የተረጋገጠ ሲሆን ይህ ፍሬ ነገርም ግራ ቀኙን አላከራከረም። ሆኖም ግን ግራ ቀኙ ሚያዝያ 13 ቀን 1966 ዓ.ም ያደረጉት የጋብቻ ውል ክርክር የተነሳበትን ቤትም ሆነ ላልች በባል ስም ተመዝግበው የሚገኙ ንብረቶችን የጋራ ለማድረግ እንደተስማሙ ከውለ አጠቃላይ ይዘት መገንዘብ የሚቻል ከመሆኑም በላይ በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ እንደተመለከተው ባልና ሚስቱ ጋብቻቸው ጸንቶ በቆየበት ጊዜ ቤቱን በተደጋጋሚ ማደሳቸው፣ በንግድ ምክንያት የመጣና በጋራ የሚፈለግባቸውን የግብር ክፍያ በተመለከተም ይሄው ቤት እንዲይሸጥ በማሰብ ላላ ንብረት ሸጠው የግብር ዕዲውን በመክፈል ቤቱን ማቆየታቸውና ቀድሞ የነበረውንም ይዞታ በማስፊፊት ላላ ተጨማሪ 9/ዘጠኝ/ ክፍል ሰርቪስ ቤቶች ስለመስራታቸው የተረጋገጠ እንደመሆኑ መጠን ይህም ቀድሞውንም ቢሆን በጋብቻ ውለ ቤቱን የጋራ ለማድረግ የነበራቸውን ሃሳብ የሚያጠናክር ነው።
ስለሆነም ግራ ቀኙ ባደረጉት የጋብቻ ውል አከራካሪው ቤት የጋራ እንዱሆን የተስማሙ ከመሆኑም ላላ ጋብቻው ጸንቶ በቆየ ጊዜም የቤቱ አገልግልት በመሰረታዊነት የተለወጠ ስለሆነ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የከፍተኛውን ፍ/ቤት ውሳኔ በመሻር ቤቱ የባልና ሚስቱ የጋራ ሀብት ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘነውም።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ ታህሳስ 27 ቀን 2001 ዓ.ም የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትን ውሳኔ በመሻር የሰጠው ፍርድ በአግባቡ ስለሆነ ጸንቷል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሳራ ይቻቻለ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.