No summary available.
ጥቅምት 10 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካቾች፡-
ለአቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ ልጅነትን ለማረጋገጥ በቀረበው ጥያቄ ላይ ተመስርቶ የተካሄደውን ክርክር የሚመለከት ነው። ከመዝገቡ እንዲየነው ተጠሪ ቀደም ሲል ለፍ/ቤት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት የሟች ደምሴ ፀጋዬ ልጅ መሆኑ ተረጋግጦ ተወስኖ ነበር። አመልካቾች ክርክሩ ውስጥ የገቡት ውሳኔውን በመቃወም እንዱሻርላቸው በመጠየቃቸው ነው። ተቃውሞአቸውም ተጠሪ የሟች ልጅ አይደለም የሚል ስለነበር፤
መቃወሚያው የቀረበለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪን በማስቀረብ የግራ ቀኝ ወገኖቹን ክርክር እና ማስረጃ ሰምቶአል። በመጨረሻም በተጠሪ በኩል የቀረበው የሰው እና የሰነድ ማስረጃ በእርግጥም የሟች ልጅ እንደሆነ አረጋግጦአል። ተቃዋሚዎች ይህን ማስረጃ ማስተባበል አልቻለም በማለት የቀድሞው ውሳኔውን አፅንቶአል። በዚህ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም በበኩለ ክርክሩን ከሰማ በኋላ ተጠሪ የሟች ልጅ ነው በማለት ወስኖአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካቾች ጥር 12 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈት ማመልከቻ በሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ተፈጽሞአል የሚለትን ስህተት በመግለጽ ውሳኔው ይሻርላቸው ዘንድ ጠይቀዋል። በበኩላችንም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው ተጠሪ የሟች ልጅ ነው በሚል የተሰጠው ውሳኔ ከተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 143 አንፃር ሲታይ አግባብነት ያለው ነው ወይስ የለውም? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው።
በመሆኑም በዚህ ረገድ የተሰማው የግራቀኝ ወገኖች ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
ከላይ እንደተገለጸው ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የሰማው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ግራቀኝ ወገኖችን ያከራከረው የልጅነት ጥያቄ በተመለከተ ማስረጃዎችን ሰምቶአል። በሰማው ማስረጃም ሟች (አባት ነው የተባለው ሰው) ተጠሪን እንደልጁ በማድረግ ሲንከባከብ እንደነበር፣ ትምህርት ቤት ወስድ እንዲስመዘገበው፣ ከቤተሰቦቹ ጋር በመቀላቀል ያኖረው እንደነበር ማረጋገጡን በውሳኔው ላይ አመልክቶአል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካቾች በተጠሪ በኩል የተሰማውን ማስረጃ ሉያስተባብለ እንዲልቻለ በትችቱ ገልጾአል። በመጨረሻም በማስረጃ ያረጋገጠው ፍሬ ነገር በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ (አዋጅ ቁ 213/92) አንቀጽ 143(ሰ) መሰረት አባትነትን ለማረጋገጥ በቂ ምክንያት እንደሆነ በመገንዘቡ ተጠሪ የሟች ልጅ ነው በማለት እንደወሰነ ተገንዝበናል።
አመልካቾችም ቢሆኑ እየተከራከሩ ያለት የሥር ፍ/ቤት አረጋግጫለሁ ያለውን ፍሬ ነገር አላረጋገጠም በማለት ሳይሆን፣ ተጠሪ ተወልጃለሁ የሚለው ከጋብቻ ውጪ በተፈጸመ የግብረስጋ ግንኙነት በመሆኑ ይህንኑ ግንኙነት በማያጠራጥር ሁኔታ ማስረዲት ሲገባው አላስረዲም በማለት እንደሆነ ከአጠቃላይ የክርክራቸው ይዘት ለመገንዘብ ችለናል።
የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 143 “በፍርድ ስለሚነገር አባትነት” በተመለከተ ዝርዝር ድንጋጌዎችን ይዞአል። እነዚህም ከንኡስ አንቀጽ(ሀ) እስከ (ሰ) ድረስ ያለት ሲሆኑ፣ አመልካቾች በመከራከሪያነት ያነሱት ነጥብ በንኡስ አንቀጽ (መ) በተመለከተው ድንጋጌ ላይ የተመሰረተ ነው። ይህ ድንጋጌ የልጁ እናትና አባት የተባለው ሰው በሕግ የታወቀ ግንኙነት ባይኖራቸውም፤ በሕግ በተመለከተው የእርግዝና ጊዜ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ በግብረሥጋ ግንኙነት አብረው የኖሩ መሆናቸው ከተረጋገጠ አባትነትን በፍርድ ውሳኔ ሉታወቅ እንደሚችል ስለሚያመለክት እንደላልቹ ድንጋጌዎች አንደኛው አባትነትን በፍርድ ውሳኔ የማወቂያ ዘዳ (ሁኔታ) ነው። ይህ ማለት ግን በዚህ ድንጋጌ የተመለከተው ሁኔታ ባለመረጋገጡ ብቻ አባትነትን በፍርድ ውሳኔ ማወቅ አይቻልም ማለት አይደለም። በተጠቀሰው አንቀጽ 143 መሰረት አባትነትን በፍርድ ውሳኔ ማወቅ የሚቻለው ከንኡስ አንቀጽ (ሀ) እስከ (ሰ) ካለት ድንጋጌዎች ውስጥ በአንደ የተመለተው ሁኔታ ሲሟላ ነው። በመሆኑም ቀጣይነት የግብረሥጋ ግንኙነት ስለመኖሩ ተጠሪ በማስረጃ አላረጋገጠም የሚለው የአመልካቾች ክርክር ተቀባይነት የለውም።
ስናጠቃልለው የሥር ፍ/ቤቶች ተጠሪን የሟች ልጅ በማለት በሰጡት ውሳኔ የተፈጸመ የሕግ ስህተት የለም ለማለት ችለናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ. ጥቅምት 1 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ህዲር 4 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348(1) መሰረት አፅንተናል።
ተጠሪ የሟች ልጅ ነው መባለ በአግባቡ ነው ብለናል።
ግራቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራቸውን ይቻቻለ።
መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.