No summary available.
የሰ/መ/ቁ/ 41857 ጥቅምት 24 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አሕመድ ሐሴን - ጠበቃ ማርቆስ ወ/ሰንበት ቀረበ ተጠሪዎች፡-
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ የውርስ ሃብት ክፍፍልን መሰረት ያደረገ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ ከሣሽ የነበረችው የአሁንዋ አንደኛ ተጠሪ ናት። ክስ የመሰረተችው በአሁኑ አመልካች፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ተጠሪዎች ላይ ነው። በክስዋም ሞግዚት የሆነችለት የኋላእሸት ሙለጌታ የተባለውን ልጅ የውርስ መብት ለማስከበር ክሱን እንደመሰረተች ገልጻ ያለሞግዚት አድራጊዋ ስምምነት ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ከአመልካች ጋር ያደረጉት የቤት ሺያጭ ውል እንዱፈርስ እና የቤቱ 1/3ኛ ለሞግዚት አድራጊዋ እንዱሰጥ ይወሰንላት ዘንድ ጠይቃለች።
ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ለክሱ በሰጡት መልስ የቤቱ ግማሽ የላላ ሰው መሆኑን በአንድ በኩል ሲገለጹ፤ በልላ በኩል ደግሞ ቀሪውን (የቤቱን ግማሽ) ለሦስቱ ተከፊፍል ከሣሽ ሞግዚት የሆነችለት ልጅ ድርሻውን 1/3ኛ ሉወስድ ይችላል ብለዋል። አመልካች ግን ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል የሚል መቃወሚያ ከማቅረቡም በላይ፤ ቤቱን የገዛው ስመሃብቱ ለሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ከዞረ በኋላ እንደሆነና ከውለ በኋላም ስመሃብቱ ለሱ መዛወሩን በመግለጽ ተከራክሮአል። ክሱን ያስተናገደው ፍ/ቤትም የሁለን ወገኖች ክርክር ከሰማ በኋላ፣ በአመልካች፣ በሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል ፈርሶአል።
የቤቱ ግማሽ ከተቻለ በአይነት፣ ካልተቻለ ተሽጦ 1/3ኛ ለከሣሽ ሞግዚት አድራጊ ይሰጥ በማለት ወስኖአል።
በልላ በኩል ደግሞ አመልካች ውሳኔውን በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ በዚህ ደረጃም ክርክሩ ተሰምቶአል። በመጨረሻም ፍ/ቤቱ ውለ ይፈርሳል የሚለውን የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ ሲያፀና ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች በቤት ሺያጭ ውል ስም የወሰደት ብር 100,000(መቶ ሺህ ብር) ግን ከነወለደ ለአመልካች ይመልሱ በማለት ወስኖአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ህዲር 25 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው የቤት ሺያጭ ውለ እንዱፈርስ መደረጉ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው።
ከሥር ጀምሮ በተደረገው ክርክር እንደተመለከተው ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት አንደኛ ተጠሪ ሞግዚት ለሆነችለት ልጅ እና ለሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች በውርስ የተሰጠ ሃብት ነው። በልላ በኩል ደግሞ ውርሱ ከመከፊፈለ በፉት ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ለአመልካች ሽጠውታል። የአንደኛ ተጠሪ ክርክር የተመሰረተውም የ3ቱም የጋራ የሆነው ንብረት ለመሸጥ የሁለም የጋራ ባለሃብቶች ስምምነት ሉኖር ይገባል በሚለው ላይ ነው። በእርግጥም የጋራ የሆነውን ንብረት ለመሸጥ፣ ለማስተላለፍ ወይም በዋስትና ለማስያዝ ወይም የተመደበበትን አገልግልት ለመለወጥ የጋራ ባለንብረቶቹ ሁለ ስምምነት አስፈላጊ እንደሆነ በፍ/ብ/ሕግ ቁ 1266 የተደነገገ ሲሆን፣ የውርስ ሃብትም አካፊፈለ እስኪፈጸም ድረስ በወራሾቹ መካከል ውርሱ ሳይነጣጠል እንደሚቆይ በፍ/ብ/ሕግ ቁ 1060(1) ተመልክቶአል።
ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ቤቱን ለአመልካች የሸጡት ስመሃብቱን በራሳቸው ካዛወሩ በኋላ ነው። ይህ ማለት ደግሞ የሺያጭ ውለ ከመደረጉ ወይም ቤቱን ለአመልካች ከማስተላለፊቸው በፉት ከሚመለከተው የአስተዲደር ክፍል የባለቤትነት የምስክር ወረቀት በስማቸው አግኝተው ነበር ማለት ነው። በፍ/ብ/ሕግ ቁ 1195(1) እንደተመለከተው የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብትነትን በማወቅ በአስተዲደር ክፍል የባለሃብትነት የምስክር ወረቀት በተሰጠ ጊዜ የምስክር ወረቀቱን ያገኘው ሰው የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ባለሃብት ሆኖ ይቆጠራል። እንግዱህ በያዝነው ጉዲይ በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠውን ሁኔታ ከሕጉ ጋር አገናዝበን ስንመለከተው ቤቱ ያልተከፊፈለ የውርስ ሃብት መሆኑ ቀርቶ የሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች የግል ሃብት እንደሆነ እንደሚቆጠር ነው መገንዘብ የሚቻለው። ከሁለ በላይ ደግሞ አመልካች ቤቱን የገዛው የሽያጮቹን የባለሃብትነት የምስክር ወረቀት በማየት ሲሆን፣ ይህን በመከተልም ቤቱ በራሱ ስም አዙሮ የባለቤትነት የምስክር ወረቀት ያገኘበት በመሆኑ በአመልካቹ እና በሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል የሚፈርስበት በሕግ የሚደገፍ ምክንያት የለም።
No topics extracted.
ላላው ቀጥለን የተመለከትነው አንደኛ ተጠሪ ሞግዚት የሆነችለት ልጅ ድርሻ እንዳት ይታያል? የሚለው ነው። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በውለ መፍረስ በመስማማቱ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች በቤት ሽያጭ ስም የተቀበለት ገንዘብ ለአመልካች እንዱመልሱ ወስኖአል። ይህ ከሆነ ደግሞ አንደኛ ተጠሪ ሞግዚት የሆነችለት ልጅም ከላልቹ ወራሾች ጋር በመሆን ከቤቱ ድርሻውን ሉያገኝ ስለሚችል ችግር አይኖርም። በዚህ ሰበር ችልት እምነት ግን ውለ ሉፈርስ ስለማይገባ ቤቱ በወራሾቹ መካከል ይከፊፈል የሚል አካሄድ አይኖርም። ወራሾቹ ሉከፊፈለ የሚችለት ከቤቱ ሽያጭ የተገኘውን ገንዘብ ነው። ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ቤቱን የእነሱ ሃብት ብቻ እንደሆነ አድርገው ቢሸጡትም፤ በመጨረሻ የታመነው ግን የ3ቱም ወራሾች ሃብት መሆኑ ስለሆነ ከዚህ ሃብት የተገኘው የሺያጭ ገንዘብም የ3ቱ ወራሾች ነው ማለት ነው። በመሆኑም አንደኛ ተጠሪ ሞግዚት የሆነችለት ልጅ የተለየ ሥነ-ሥርዓት መከተል ሳያስፈልገው ከቤቱ ሽያጭ ከተገኘው ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ድርሻውን 1/3ኛ (አንድ ሦስተኛ) የማግኘት መብት አለው። በዚህ መሰረትም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ. ግንቦት 28 ቀን 99 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ጥቅምት 26 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 348(1) መሰረት ተሻሽለዋል።
በአመልካች እና በሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል አይፈርስም ብለናል።
አንደኛ ተጠሪ ሞግዚት የሆነችለት ልጅ ከቤቱ ሽያጭ ከተገኘው ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ድርሻውን 1/3 (አንድ ሦስተኛ) ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ይስጡት ብለናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራቸውን ይቻቻለ።
በዚህ ሰበር ችልት ውሳኔ መሰረት ይፈጸም ዘንድ ለሥር ፍ/ቤቶች ይጻፍ። መዝገቡ ይመለስ።