No summary available.
ጥቅምት 12 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካቾች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት መስከረም 13 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ስለጠየቁ ነው። የክርክሩ መሰረታዊ መነሻ የአሁን ተጠሪ ሟች አቶ ዘውዳ በሱፈቃድ ወላጅ እናቱን ወ/ሮ አድማስወርቅ ጥላሁንን አግብተው ሲኖሩ የተወለደ በመሆኑ የሟች አቶ ዘውዳ በሱፈቃድ ልጅና ወራሽ መሆኑ በፍርድ እንዱረጋገጥለት ያቀረበውን አቤቱታና ማስረጃ በመመርመር ተጠሪ የሟች ዘውዳ በሱፈቃድ ልጅና ወራሽ ነው በማለት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ነው። የሥር ፍርድ ቤት ይህንን ውሣኔ ከሰጠ በኋላ የአሁን አመልካቾች በተቃዋሚነት ቀርበው ሟች አቶ ዘውዳ በእሱፈቃድ 1940 ዓ.ም ለትምህርት ወደ አሜሪካ ሄደው ለሰባት ዓመታት እዚያው የቆዩ ስለሆነ 1945 ተጠሪን ሉወስደ አይችለም። ከዚህ በተጨማሪ ሟች ዘውዳ በእሱፈቃድ ከሁለተኛ፣ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪ ውጭ ላላ ልጅ የላላቸው መሆኑን ጥር 18 ቀን 1990 ዓ.ም ኑዛዜ ያደረጉ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ አቶ ኤፍሬም ዘውዳ (ተጠሪ) የሟች ልጅ ነው በማለት የሰጠውን ውሣኔ እንዱያነሣልን በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩላቸው የአመልካቾች ፍርደን ለመቃወም ያቀረቡት ማመልከቻ ደርሷቸው አቶ ዘውዳ በእሱፈቃድ 1944 ዓ.ም ተመልሰው በመምጣት ወ/ሮ አድማስወርቅ ሚስታቸውን ጠይቀው ተመልሰዋል። እኔም ተረግዤ ተወልጃለሁ። የመቃወም አመልካቾች የእኔ ወላጅ እናት ወ/ሮ አድማስወርቅ ጥላሁንና አቶ ዘውዳ በእሱፈቃድ በባልና ሚስትነት ተጋብተው አልኖሩም ብለው ባልተቃወሙበት ሁኔታ የሟች ልጅ ልጅ መሆኔ ህግ ግምት የሚያዝበትን ጉዲይ በምስክር ለማፍረስ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል። ፍርድ ቤቱም የአመልካቾችንና የተጠሪን ማስረጃ ከሰማ በኋላ የተጠሪ ማስረጃ ሚዛን የሚደፊና ተዓማኒነት ያለው የአመልካቾች ማስረጃ ተዓማኒነት አጠራጣሪ መሆኑን በመግለፅ ቀደም ሲል የሰጠሁትን ውሣኔ የሚነሳበት ምክንያት የለም በማለት የአመልካቾችን መቃወሚያ ውድቅ አድርጎታል። አመልካቾች ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኙን ሰርዞታል።
አመልካቾች ተጠሪ አቶ ዘውዳ በሱፈቃድ አሜሪካን አገር ለትምህርት ሄደው ባለበት ተወለድኩ ያለ በመሆናቸውና በመጀመሪያ እኔ ከተወለድኩ በኋላ ለትምህርት ሄደ ያለ ሲሆን በኋላ በእረፍት መጥተው ነው የተረገዝኩት በማለት ያቀረቡት ክርክር የሥር ፍርድ ቤት ተቀብል መወሰኑ ተገቢ ባለመሆኑ አቶ ዘውዳ በሱፈቃድ ተጠሪን ለማሣደግ ያደረጉት ተሣትፍ የላለ በመሆኑና ተጠሪም ይህንን ያላስረዲ በመሆኑ ከሁለም በላይ አቶ ዘውዳ በሱፈቃድ ባደረጉት ኑዛዜ ከሁለተኛ ሶስተኛ እና አራተኛ አመልካቾች ውጭ ልጅ የላላቸው መሆኑን ያደረጉት ኑዛዜ በቂና አሳማኝ ማስረጃ ሆኖ እያለ ተጠሪ የሟች አቶ ዘውዳ በሱፈቃድ ልጅ ነው ተብል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልን በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩላቸው እኔ የተወለድኩት በወላጅ እናቴና በሟች ዘውዳ በሱፈቃድ መካከል ህጋዊ ጋብቻ ባለበት ጊዜ ውስጥ በመሆኑ የሟች ልጅ መሆኔ የተሻሻለው የፋዳራል የቤተሰብ ህግ የተረጋገጠ ነው። አመልካቾች ይህንን የህግ ግምት ለማስተባበል በተሻሻለው የፋዳራል የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 144 የተደነገጉትን ሁኔታዎች ማስረዲት ይጠበቅባቸዋል። ኑዛዜ የእኔን ልጅነት ለማሰረዝ የሚችል አይደለም የዚህ አይነት ይዘት የለውም በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካቾች የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካቾች ለሥር ፍርድ ቤት ባቀረቡት የፍርድ መቃወሚያም ሆነ በሰበር አቤቱታቸው የተጠሪ ወላጅ እናት ወ/ሮ አድማስወርቅ ጥላሁን ከሟች አቶ ዘውዳ በሱፈቃድ ጋር የጋብቻ ግንኙነት አልነበራቸውም። ተጠሪ የተወለደው የሁለቱ ጋብቻ ከፈረሰ በኋላ ነው የሚል መቃወሚያ አላቀረቡም።
አመልካቾች ተጠሪ የተወለደው አቶ ዘውዳ በሱፈቃድ ለትምህርት አሜሪካ ሄደው ባለበት ጊዜ ነው በማለት አጥብቀው የሚያቀርቡትን ክርክር አግባብነት ካለው የህግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ መርምረናል። በአንድ ወንድና አንዱት ሴት መካከል ጋብቻ ፀንቶ ባለበት ጊዜ የተወለደ ልጅ አባቱ ነው የሚባለው ባልዬው እንደሆነ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 126 ይደነግጋል። ከዚህ አንፃር ተጠሪ የተወለደው በእናቱ ወ/ሮ አድማስወርቅ ጥላሁንና በአቶ ዘውዳ በሱፈቃድ መካከል የነበረው ጋብቻ ፀንቶ ባለበት ጊዜ መሆኑ ያልተካደ በመሆኑ የተጠሪ አባት አቶ ዘውዳ በሱፈቃድ መሆናቸውን ህጉ ግምት የያዘበት ጉዲይ ነው።
ተጠሪ በህግ ግምት የአቶ ዘውዳ በሱፈቃድ ልጅ መሆኑን ከማስረዲቱም በላይ አቶ ዘውዳ በሱፈቃድ ባለቤታቸውን ሉጠይቁ ለእረፍት በመጡበት ጊዜ የተረገዘ መሆኑን የአቶ ዘውዳ በሱፈቃድ የቅርብ ዘመድች በምስክርነት በማቅረብ አስረድተዋል። ይኸ በመሆኑ ተጠሪ የአቶ ዘውዳ በሱፈቃድ ልጅ አለመሆኑን ማስረዲት የሚቻለው በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 144 መሰረት ሳይሆን በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 167 መሰረት የመካድ ክስ በማቅረብና በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 168 እስከ አንቀፅ 173 ከተዘረዘሩት አንደኛውን ለማስረዲት የሚችል በቂ ማስረጃ በማቅረብ ነው። ከዚህ በተጨማሪ የመካድ ክስ ለማቅረብ የሚችለው አባት ነህ ተብል በህግ ግምት የተሰጠው እሱ የሞተ እንደሆነ ተወላጆቹ እና ላልች ዘመድቹ በቅደም ተከተል እንደሆነ የቤተሰብ ህጉ ደንግጓል።
አንደኛ አመልካች ዘውዳ እሱባለው ሚስትና የሁለተኛ፣ ሶስተኛና አራተኛ አመልካቾች እናት ብትሆንም በዚህ ጉዲይ ተጠሪ ላይ የመካድ ክስ የማቅረብ መብትና ችልታ የላትም። ሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪዎች ያቀረቡት መቃወሚያና መቃወሚያቸውን ለማስረዲት ያቀረቡት ማስረጃ ታዓማኒነት የላለው መሆኑና የተጠሪ ማስረጃ ሚዛን የሚደፊ መሆኑ ፍሬጉዲይ የመመዘን ስልጣን ያላቸው የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተስማምተውበታል። ሟች አቶ ዘውዳ በሱፈቃድ አደረጉት የተባለው ኑዛዜም ተጠሪ የሟች ልጅ ላለመሆኑ ብቃት ያለው ማስረጃ ተደርጎ እንዱወሰድ የሚያስገድድ ህግ የላለ በመሆኑ በዚህ በኩል የበታች ፍርድ ቤቶች የህግ ስህተት ፈፅመዋል የሚል መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ ሆኖ አላገኘነውም። በአጠቃላይ የአመልካቾች ተጠሪ የሟች ዘውዳ በሱፈቃድ ልጅ አይደለም የሚለውን ክርክራቸውን የቤተሰብ ህጉ በሚደነግገው መሰረት በበቂ ሁኔታ አላስረደም በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ህጉን መሰረት ያደረገና ስህተት የላለበት ሆኖ ስላገኘነው በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 348 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት አፅንተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
አመልካቾችና ተጠሪ በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ለየራሳቸው ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሙለ ድምፅ ተሰጠ።
No topics extracted.