No summary available.
ጥቅምት 10 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- ተስፊዬ ሞላ - ቀረበ ተጠሪዎች፡-
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ብይን በማጽናት ሐምል 24 ቀን 2000 ዓ.ም በመ/ቁ. 35810 በሰጠው ውሳኔ ላይ ነው። ጉዲዩ የውርስ ሃብት ክፍፍልን መነሻ ያደረገ ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ ሲጀመር ከካሽ የነበረው አመልካች ነው ከመዝገቡ እንደሚታየው አመልካች በተጠሪዎች ላይ ክስ የመሰረተው በውር አጣሪ ተጣረቶ ከቀረበው የውርስ ሃብት ላይ ድርሻዬን ያካፍለኝ በማለት ነው። ተጠሪዎችም ለቀረበው ክስ መልስ የሰጡ ሲሆን፣1ኛ ተጠሪ ክሱን አልተቃወመም። ከሣሽ ድርሻውን ይውሰድ ብልአል። ተጠሪዎች ግን ክሱ በይርጋ ቀሪ ስለሆነ ሉሰረዝ ይገባል በማለት ተከራክረዋል። በመጨረሻም ፍ/ቤቱ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል የሚለውን መቃወሚያ በመቀበል ክሱን በመሰረዝ ብይን ሰጥቶአል። በዚህ ብይን ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤትም ብይኑ ጉድለት የለበትም በማለት የይግባኙን ሰርዞአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ነሐሴ 30 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው ተጠሪዎች ያነሱት የይርጋ መቃወሚያ ቀደም ሲል ውርሱ ሲጣራ በነበረበት ወቅት እልባት አግኝቶ እያለ እንደገና ተነስቶ ተቀባይነት የማግኘቱን አግባብነት ለመመረመር ነው። በመሆኑም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው ተመልክተናል።
የክርክሩ አመጣጥ እንደሚያሳየው ጉዲዩን በሚመለከት ሁለት መዝገቦች ተከፍተዋል። የመጀመሪያው መዝገብ ውርስ እንዱጣራ የቀረበውን ጥያቄ የተስተናገደበት ሲሆን፣ሁለተኛው ደግሞ ውርሱ ተጣርቶ በውርስ አጣሪው የቀረበውን ሪፖርት መሰረት በማድረግ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ የቀረበበት ነው። ላላው ከክርክሩ ሂደት የተገነዘብነው የውርስ ይጣራ ጥያቄ የቀረበው በአመልካቹ ሲሆን፣በዚህን ጊዜም የይርጋ መቃወሚያ ቀርቦ እንደነበር እና ጉዲዩን ያየው ፍ/ቤት ግን መቃወሚያውን ውድቅ በማድረግ ውርሱ እንዱጣራ ትእዛዝ ሰጥቶ በዚሁ መሰረት መፈጸሙን ነው። አመልካች የይርጋው መቃወሚያ ሁለት ጊዜ ነው የታየው የሚል የመከራከሪያ ነጥብ ያነሳውም ይህን መሰረት በማድረግ ነው።
እንደምንመለከተው ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ያቀረቡት የይርጋ መቃወሚያ ቀደም ሲል ተነስቶ ውድቅ የተደረገ ስለመሆኑ አከራካሪ አልሆነም። የውርስ ማጣራት ሂደቱ ተጠናቆ አጣሪው ሪፖርቱን ከፍ/ቤት ያቀረበው ጥር 29 ቀን 1999 ዓ.ም ሆኖ አመልካች የንብረት ክፍፍል ጥያቄ(ክስ) ያቀረበው ደግሞ መጋቢት 3 ቀን 1999 ዓ.ም እንደሆነ የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠው ብይን ላይ ተመልክቶአል። ይህም ማለት አመልካች ክሱን የመሰረተው ክፍያውን ካወቀ አንድ ዓመት ከማለፈ በፉት በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1080 በተመለከተው ድንጋጌ መሰረት ጥያቄው በይርጋ ቀሪ አልሆነበትም። ሲጠቃለል አውራሹ ከሞቱበት ቀን አንስቶ የታሰበው የይርጋ ጊዜ የውርስ ይጣራልኝ ክስ በቀረበ ጊዜ ተነስቶ ውድቅ በመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5 አንፃር ሲታይ በድጋሚ የሚቀርብበት የሕግ ምክንያት የላለ ስለሆነና የውርስ አጣሪው ባቀረበው ሪፖርት መሰረት የቀረበው የንብረት ልካፈል ጥያቄም በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1080/3/ የተደነገገው የአንድ ዓመት የጊዜ ወሰን ከማለፈ በፉት የቀረበ በመሆኑ ጥያቄው/ክሱ/ በይርጋ ቀሪ ነው በሚል በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 53613 ጥር 26 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ብይን እና የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 35810 ሐምል 24 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
No topics extracted.
አመልካች ያቀረበው የንብረት ልካፈል ክስ በይርጋ ቀሪ አልሆነም በማለት ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክሩን ክሱ በቀረበበት መዝገብ እንዱቀጥል በማድረግ ግራ ቀኝ ወገኖች በጉዲዩ ሥረ-ነገር ላይ የሚያቀርቡትን ክርክር ከሰማ በኋላ የመሰለውን ውሳኔ ይስጥ በማለት ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 341/1/ መሰረት ይመለስለት ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሳቸው ይቻለ። መዝገቡ ይመለስ።