No summary available.
ጥቅምት 24 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አርጋው አባቼ - ጠበቃ ደገፈ ምሶኔ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አስቴር አበጋዝ ወራሾች - እነ ወ/ሪት ንግስት አርጋው (ስድስት ሰዎች) መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ የጋብቻን በፍቺ መፍረስ ተከትል የተነሣውን የንብረት ክፍፍል ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የባልና ሚስት የጋራ ሐብት ነው ወይስ የባልየው የግል ንብረት? በሚል ክርክር ከተነሣባቸው ንብረቶች አንደ በአዱስ አበባ ከተማ በወረዲ 20 ቀበላ 45 ክልል ውስጥ የሚገኘው ቁጥር 629 የሆነው የመኖሪያ ቤት ነው። ፍ/ቤቱ ከሁለቱ ወገኖች የቀረበውን ክርክር ከሰማ በኋላ፣ ቤቱ ጋብቻው ከመመስረቱ በፉት አመልካች የሰራው የግል ሐብቱ ነው በማለት የወሰነ ሲሆን፣ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ግን ቤቱ የተሰራው ከጋብቻ በኋላ (በጋብቻው ወቅት) መሆኑን በማስረጃ አረጋግጫለሁ በማለት ቤቱ የባልና ሚስቱ የጋራ ሃብት ነው ብልአል። በመጨረሻ በይግባኝ ጉዲዩን ያየው የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤትም የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ጥር 15 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው አከራካሪው ቤት ከጋብቻ በፉት የነበረ ንብረት ስለመሆኑ በስር ፍ/ቤት የተደረገው ክርክር እያሳየ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ቤቱ የአመልካች የግል ንብረት አይደለም በማለት የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ ተመልክተናል።
ከላይ እንደተገለጸው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አከራካሪው ቤት የአመልካች የግል ሃብት ነው በማለት ቢወስንም፤ጉዲዩን በይግባኝ የሰማው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ግን አልተስማማም። የከፍተኛው ፍ/ቤት ቤቱ የተጋቢዎቹ የጋራ ሃብት ነው ለማለት የበቃው ቤቱ የተሰራው አመልካች እንደሚለው ከጋብቻ በፉት ሳይሆን፣ጋብቻው ከተመሰረተ በኋላ በ1966 እንደሆነ በከተማው አስተዲደር የሚገኘውን የቤቱን ማህደር አስቀርቤ አረጋግጫለሁ በማለት ነው። የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤትም ይህንኑ በማረጋገጥ ውሳኔውን አጽንቶአል። እንግዱህ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃም ሆነ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቶቹ ውሳኔ የተመሰረተው ተሰማ በተባለው ማስረጃ ላይ ነው። በማስረጃ አመዛዘን ረገድ የተሻለ መደምደሚያ የደረሰው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው ለማለት የሚያስችል የሕግ ምክንያትም የለም። ይልቁንም የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤት እንዱያይ ተጠይቆ ያላየውን (አላይም በማለት ያለፈውን) በአስተዲደር ክፍለ የሚገኘውን የቤቱን ማህደር አስቀርቦ የመረመረ በመሆኑ የተሻለ ስራ ሰርቶአል የሚባለው ይሄው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። ስለዚህም በዚህ ረገድ የተፈጸመ መሰረትዊ የሕግ ስህተት አለ ለማለት የሚያስችል ምክንያት አላገኘንም።
348/1/ መሰረት ፀንቶአል።
አከራካሪው ቤት የግል ሐብትህ ነው ይባልልኝ በማለት አመልካች ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት አለማግኘቱ በአግባቡ ነው ብለናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራቸውን ይቻቻለ።
የካቲት 16 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው የእግድ ትእዛዝ ተነስቶአል። ይፃፍ።
መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.