No summary available.
ጥቅምት 05 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- አቶ ብሩክ ኃ/እየሱስ - ጠበቃ ዘውደ ወራሣ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ፊናዬ አበበ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የባልና ሚስት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በደቡብ ብሓር ብሄረሰቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት በወናጏ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት በዚሁ ፍርድ ቤት አመልካች የነበሩት የአሁኗ ተጠሪ ከአሁኑ አመልካች ጋር የመሰረቱት ጋብቻ እንዱፈርስላቸው፣የጋብቻ ውጤት የሆነው ንብረትም ክፍፍለ እንዱፈጸም የንብረቱን ዓይነትና ግምቱን ዘርዝረው ዲኝነት ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማና ከመረመረ በኋላ ጋብቻው እንዱፈርስ አድርጏ ንብረቱን በተመለከተም ተገቢ ነው ያለውን ውሣኔ ሰጥቷል። ውሣኔውም እስከ ክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ጸንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው የስር ፍርድ ቤቶች በዱላ ከተማ ቀበላ 02 ውስጥ የሚታወቅ ዋና መኖሪያ ቤት የባልና ሚስት የጋራ መሆናቸው ስለተረጋገጠ ከስድስት ሰርቪስ ቤቶች ጋር ፍቺ ከተሰጠበት ጀምሮ የተገኘ ጥቅም እና ቤቶቹ ተሽጠው እንዱከፊፈለ በማለት በሰጡት ውሣኔ ክፍል ነው።
የአመልካች ጠበቃ ሰኔ 12 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት ሦስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት መተዲደሪያችን ሆኖ ስለመዋዋላችን በ25/11/1987 ዓ.ም በተፃፈ የጋብቻ ውል ተገልጾ እያለና ተጠሪም ክስ ሲመሰርቱ የግል ሐብቴ ነው እሷን አይመለከታትም ብል የተዋዋለው ሐይለ ቃል ባለመኖሩ ቤቱ የጋራ ነው የሚል ዲኝነት ጠይቀው እያለ ከጋብቻ በፉት የተፈራውን ንብረት የባልና ሚስት የጋራ ነው በማለት መወሰኑ የደቡብ ብሓር ቤሓረሰቦችን ብሓራዊ ክልልላዊ መንግስት የቤተሰብ ሕግን አንቀጽ 66 ድንጋጌና የተዋዋይ ወገኖችን ሐሳብና ፍላጏት ያላገናዘበ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመ ነው ተብል ሉሻር ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያስገነዝብ ነው። አቤቱታው ተመርምሮ በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት ተጠሪ ቀርበው ሐምል 17 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መልሳቸውን አቅርበዋል አመልካች በበኩላቸው መስከረም 11 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚገባ መልኩ መርምሮታል እንደመረመረውም በዱላ ከተማ ቀበላ 02 የሚታወቅ ዋና መኖሪያ ቤት ከ6/ስድስት/ ሰርቪስ ቤቶች ጋር ፍቺ ከተሰጠበት እለት ጀምሮ ጥቅምና ቤቶቹ የባልና ሚስት የጋራ ሐብት ናቸው፤ ተብል መወሰኑ በአግባቡ መሆን ያለመሆኑን በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ንብረት አመልካችና ተጠሪ ጋብቻ ከመመስረታቸው በፉት የተሰራ መሆኑን በ25/11/1987 በተደረገው የጋብቻ ውል ቤቱን መተዲደሪያቸው በማድረግ መስማማታቸውን ነው።
በመሰረቱ ባልና ሚስት ጋብቻቸውን በሚፈጽሙበት ጊዜ በየግል የነበሯቸው ንብረቶች ወይም ከጋብቻ በኋላ በውርስ ወይም በስጦታ በየግላቸው የሚያገኟቸው ንብረቶች በጋብቻ ዘመንም የግል ሆነው ይቀራለ። ይሁን እንጂ ይህ ሁኔታ በሕጉ ጥበቃ የሚደረግለት ንብረቶቹ በጋብቻ ውል የጋራ እንዱሆኑ ስምምነት ከላለ ብቻ ነው።
በተያዘው ጉዲይ አከራካሪ የሆነውን የጋብቻ ውለ በሕግ ፉት ያለው ተፈፃሚነት ሣይሆን በጋብቻ ውለ የተገለፀው “መተዲደሪያችን” የሚለው ቃል ቤቱ የጋራ ስለመሆኑ ባልና ሚስት መስማማታቸውን ያሳያል ወይስ አያሳይም? የሚለው ነጥብ ነው። አመልካችና ተጠሪ አደረግን የሚለት የጋብቻ ውል መተዲደሪያችን ብል ከሚገልፃቸው ንብረቶች ውስጥ ከአከራካሪው ቤት በተጨማሪ የአመልካች ደመወዝና ብር 10,000.00(አስር ሺህ) ጥሬ ገንዘብ ይገኙበታል። እነዚህ ንብረቶች ለማንኛውም የቤተሰቡ ወጪ የሚውለ መሆኑ ይታመናል።
አመልካችና ተጠሪ ይህንኑ ጥሬ ገንዘብና ቤቱን እየተጠቀሙ ለአስራ አንድ ዓመታትም አንድ ላይ ኖረዋል።
እንግዱህ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች እነዚህ ከሆኑና የጋብቻ ውለ ይዘት ትርጉም አከራካሪ ከሆነ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1731 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎችን የግራ ቀኙ ፍላጏት ምን እንደነበር መመርመር የግድ ይሎል።
No topics extracted.
በመሰረቱ በውል ውስጥ የተጠቀሱት ቃላትና ድንጋጌዎች ግልጽ ባልሆኑ ጊዜ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1732፣1735- 1738 ድረስ ባለት ድንጋጌዎች ስር በሰፈሩት ደንቦች መሰረት መተርጏም የተፈቀደ ነው። በዚህም መሰረት ለተያዘው ጉዲይ አግባብነት ያላቸው ደንቦች በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1734 እና 1736 ሲሆኑ ተዋዋዮች ውላቸውን ከመዋዋላቸው አስቀድሞ ወይም ከተዋዋለ በኋላ የነበሩበትን ሁኔታዎች፣የፈጸሙትን ተግባር በማመዛዘንና ሐሣባቸውን ምን እንደነበር ለማወቅ መሞከር እና የውልችን ቃልች አንደን ከአንደ ጋር እያዛመደ በመመልከት ለውለ ጉዲይ አግባብ ያለውን ትርጉም መስጠት ተገቢ ስለመሆኑ ተጠቃሽ ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ። በያዝነው ጉዲይ አመልካችና ተጠሪ በ25/11/1987 ዓ.ም አደረግን የሚለት የጋብቻ ውል መተዲደሪያችን ብል ከሚገልፃቸው ንብረቶች ውስጥ ከአከራካሪው ቤት በተጨማሪ የአመልካች ደመወዝና ብር 10,000(አስር ሺህ) ጥሬ ገንዘብ ይገኙበታል። እንደሁም ይህንኑ ጥሬ ገንዘብና ቤቱን እየተጠቀሙ ለአስራ አንድ ዓመታትም አንድ ላይ ኖረዋል።
በመሆኑም አመልካችና ተጠሪ የጋብቻ ውለን በተዋዋለበትና ከተዋዋለ በኋላ የነበሩበት ሁኔታ እና ጥሬ ገንዘቡንም ለመተዲደሪያቸው አድርገው የተዋዋለ መሆናቸው መተዲደሪያ የሚለውን ቃል በጋብቻ ውለ የተጠቀሙበት አከራካሪውን ቤት የጋራ ከማድረግ ፍላጏት ነው ከሚባል በስተቀር ላላ ትርጉም ሉሰጠው የሚገባው ሆኖ አልተገኘም። ከፍቺ በኋላ በቤቱ የተገኘ ጥቅምም ከጋራ ንብረት የተገኘ መሆኑ አስከተረጋገጠ ድረስ ተጠሪ የማያገኙበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች በጉዲይ ላይ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
348/1/ መሰረት ጸንቷል።