የአ/ብ//ክ/መ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሰራተኞች መተዳደሪያ ደንብ “በይግባኝ በቀረበለት ጉዳይ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል” በሚል ተገልጸው የሚገኙት ድንጋጌዎች በይግባኝ ደረጃ ቀርበው ለመታዬት የማይችሉ የመጨረሻ ውሳኔዎች መሆናቸውን አቶ ስለሽ ዋለልኝ እና የአ/ብ/ክ/መ. ሥ/ምግባርና ፀረ ሙስና ኮምሽን ዐ/ህግ
No summary available.
መሥከረም 22 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው በዕውቀት በላይ እንዳሻው አዳነ ሃይሉ ነጋሽ እትመት አሰፋ አመልካች፡- አቶ ወርቁ ታደሰ ጠበቃ ሱልጣን ሰይፍ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ጅራተ ኢልፈታ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የእርሻ መሬት ክርክርን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ሸዋ ዞን የባኮትቤ ወረዳ ፍ/ቤት ነው። ተጠሪ በአሁን አመልካች ላይ ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ አዋሳኙ በክሱ የተጠቀሰውን 0.25 ሕክታር መሬት ማረሚያ ቤት እያሉ በ2000 ዓ.ም አመልካች በሕገወጥ መንገድ ለከብቶች ግጦሽ የያዘባቸው መሆኑን በመግለጽ መሬቱን ለቀው እንዲያስረክቧቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
አመልካች በሰጡት መልስ የአከራካሪው መሬት ስፋት አንድ ሕክታር መሆኑን፤ከ1967 ዓ.ም ጀምሮ ለ42 ዓመታት ይዘው የሚጠቀሙበት እና ተጠሪ ተጠቅሞበት የማያውቅ በመሆኑ ይርጋ የሚያግደው መሆኑን በመግለጽ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በፍሬነገሩ ላይ በሰጡት መልስ መሬት በሚሰፈርበት ጊዜ ዳገታማ መሬት ነው ተብሎ ያልተሰፈረላቸው መሆኑን በመግለጽ የተጠሪ ክስ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ጉዳዩ በቀጥታ የቀረበለት ፍ/ቤት የወረዳውን መሬት አጠቃቀም እና አሥተዳደር ጽ/ቤት አከራካሪው መሬት የማን እንደሆነ እና በማን ሥም እንደተሰፈረ አጣርቶ እንዲገልጽ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ተጠቃሹ አካል ለፍ/ቤቱ በሰጠው ምላሽ አከራካሪው መሬት ለተጠሪ የተሰፈረ መሆኑ እና አመልካች ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከብቶችን እያሰማራበት ያለ መሆኑን በመግለጽ መልስ ሰጥቷል። የአመልካች ምስክሮች ለፍ/ቤቱ በሰጡት የምስክርነት ቃል የመሬት ኮሚቴ መሬት የአርሶ አደሩ ነው ተብሎ በተመራበት ዘመን አከራካሪውን መሬት ለአመልካች የሰጠው መሆኑን፤መሬቱ የግጦሽ መሆኑን እና አመልካች ከብቶች የሚያሰማራበት መሆኑን በመግለጽ መስክረዋል።
የተጠሪ ምስክሮች ለፍ/ቤቱ በሰጡት የምስክርነት ቃል አከራካሪው መሬት የተጠሪ መሆኑን እና አመልካች ለረጅም ጊዜ ከብቶችን ሲያሰማራበት የቆየ መሆኑን በመግለጽ መስክረዋል። ፍ/ቤቱም በግራቀኙ የቀረቡትን ማስረጃዎች እና በፍ/ቤቱ ትዕዛዝ የቀረበውን ማሥረጃ ከመረመረ በኋላ የቀረቡት ማሥረጃዎች አከራካሪው መሬት የተጠሪ መሆኑን ስለሚያረጋግጡ አመልካች መሬቱን ለተጠሪ ላያስረክብ ይገባል በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት በየደረጃው ላሉ የክልሉ ፍ/ቤቶች አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም አቤቱታቸው ተቀባይነት አላገኘም። የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- አመልካች ያቀረብኩት የይርጋ መቃወሚያ ታልፎ በፍሬጉዳይ ላይ የሰጠሁት አማራጭ መልስ ግንዛቤ ውስጥ ሳይገባ የበታች ፍ/ቤቶች አመልካች አከራካሪውን መሬት ለተጠሪ ላያስረክብ ይገባል በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል የሚል ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች አከራካሪውን መሬት ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ በሕገወጥ መንገድ መያዙ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ያቀረበው የይርጋ መቃወሚያ ታልፎ የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ በዚህ ችሎት እንዲታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል። ተጠሪ በሰጡት መልስ ተጠሪ እስከ 2000 ዓ.ም ድረስ በመሬቱ ስጠቀም እንደነበረ ተረጋግጧል፤አመልካች ከ1967 ዓ.ም ጀምሮ መሬቱን ይዣለሁ በማለት ያቀረበው ክርክር ሐሰት ስለሆነ አቤቱታው ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። እኛም እንዲጣራ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረነዋል። አመልካች አከራካሪውን መሬት ለረጅም ጊዜ ከብቶችን በማሰማራት የሚጠቀምበት መሆኑ በሥር ፍ/ቤት ቀርበው ከተሰሙት የግራቀኙ ምስክሮች አረጋግጠዋል። የወረዳውን መሬት አጠቃቀም እና አሥተዳደር ጽ/ቤት ለፍ/ቤቱ በሰጠው ምላሽም አመልካች ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ አከራካሪውን መሬት ከብቶችን በማሰማራት የሚጠቀምበት መሆኑን አረጋግጧል። በልላ በኩል አመልካች አከራካሪውን መሬት በሕገወጥ ውል መነሻነት የያዙት ስለመሆኑ በበታች ፍ/ቤቶች የተረጋገጠ ፍሬነገር የለም።
የኦሮሚያ የገጠር መሬት አጠቃቀም እና አሥተዳደር ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀጽ 32 አርሶአደሩ በመሬቱ ላይ ያለውን መብት ለማስጠበቅ በአሥራሁለት ዓመት የጊዜ ገደብ ውስጥ ካልጠየቀ መብቱ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን ይደነግጋል።
የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መ.፤79394 እና በልሎችም መዝገቦች ላይ ሕገወጥ የሆነውን ውል ውድቅ ለማድረግ በሕጉ የተመለከተው የይርጋ የጊዜ ገደብ መቃወሚያ ላሆን እንደማይችል በመግለጽ በየትኛውም እርከን ላይ ለሚገኙ ፍ/ቤቶች አስገዳጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
በተያዘው ጉዳይ አመልካች አከራካሪውን መሬት ከአሥራሁለት ዓመት በላይ ከብቶችን በማሰማራት የሚጠቀሙበት መሆኑ ፍሬነገርን የማጣራት እና ማሥረጃን የመመዘን ሥልጣን ባላቸው የበታች ፍ/ቤቶች የተረጋገጠ ፍሬነገር ነው። በልላ በኩል አመልካች አከራካሪውን መሬት ሕገወጥ በሆነ ውል መነሻነት የያዙት ስለመሆኑ በበታች ፍ/ቤቶች የተረጋገጠ ፍሬነገር የልለ በመሆኑ አመልካች መሬቱን ለረጅም ጊዜ የሚጠቀሙበት መሆኑን በመግለጽ የተጠሪ ክስ በይርጋ ይታገዳል በማለት ያቀረቡት የይርጋ መቃወሚያ ለጉዳዩ ተፈጻሚነት አለው። በመሆኑም ተጠሪ አመልካች መሬቱን እንዲለቅላቸው ያቀረቡት ክስ በክልሉ የገጠር መሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀጽ 32 በይርጋ የሚታገድ ነው። የበታች ፍ/ቤቶች አመልካች አከራካሪውን መሬት ከአሥራሁለት ዓመት በላይ ይዞ የሚጠቀምበት መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ የተጠሪን ክስ በይርጋ ውድቅ ማድረግ ሲገባቸው አመልካች መሬቱን ለተጠሪ ላያስረክብ ይገባል በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በኦሮሚያ ብሕራው ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ሸዋ ዞን የባኮትቤ ወረዳ ፍ/ቤት በመ. ሕዳር 08 ቀን 2009 ዓ.ም ተሰጥቶ፤በምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ. ሕዳር 13 ቀን 2009 ዓ.ም በትዕዛዝ፤በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ. ጥር 25 ቀን 2009 ዓ.ም በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ተሽሯል።
የተጠሪ ክስ በይርጋ የታገደ ነው ብለናል።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ።
-መዝገቡ ተዘግቷል።ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
የሰ/መ/ ቀን 25/7/2010 ዓ/ም ዳኞች አልማው ወል ሙስጠፋ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውሎስ ኦርሺሶ አመልካች- አቶ ስለሽ ዋለልኝ -አልቀረበም ተጠሪ- የአማራ ብ/ክ/መ. ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዐ/ህግ ስሜነህ ታደሰ ቀርቧል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዚህ ሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች ህዳር 25 ቀን 2010 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ ጥቅምት 9 ቀን 2010 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታውን በማቅረቡ ነው። ቅሬታውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የሚቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ላታይልኝ ይገባል የሚለውን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ በስር ውሳኔ ሰጪ አካላት የተሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ውሳኔ መሆኑ በደንብ ቁጥር 104/2004 ተመልክቶ እያለ በአማራ ብ/ክ/መ. ሕገ መንግስት በክልል ጉዳይ የበላይና የመጨረሻ ስልጣን ያለው መሆኑ በግልጽ ተቀምጦ እያለ የስረ ነገር ስልጣን የለኝም ማለቱ ስሀተት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው።
በስር ፍ/ቤት የነበረው ክርክር የጀመረው ከአማራ ብ/ክ/መ. የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የድስፒላን ኮሚቴ በሰጠው ውሳኔ ሲሆን ከሳሽ የአሁን ተጠሪ የአማራ ብ/ክ/መ.
የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የምርምርና የህግ ዳይሬክቶሬት ባቀረበው ክስ ተከሳሽ (የአሁን አመልካች) ለከፍተኛ ትምህርት በተላከበት ወቅት በልላ የመንግስት መ/ቤት ተቀጥሮ ከሁለት የመንግስት መስሪያ ቤት ደሞዝ በመውሰድ የማጭበርበር የድስፕላን ጥፋት ፈጽሟል የሚል ነው። ተከሳሽም ሁለት ቦታ እንዳልሰራ የሚከለክል ህግ የለም። የሰራሁት የኢኮኖሚ ችግር ስለገጠመኝ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ይሁንልኝ በሚል መልስ ሰጥተዋል። የኮሚሽኑ የድስፒላን ኮሚቴ አከራክሮ ተከሳሽ በኮሚሽኑ ደንብ ቁጥር 104/2004 አንቀጽ 72(19) ከተዘረዘሩት ጋር ተመሳሳይ ክብደት ያለው ልላ የዲስፕላን ጥፋት ፈጽሟል። በአንድ መንግስት ሁለት መ/ቤት ተቀጥሮ ከሁለት ቦታ ደሞዝ ማግኘት ህጋዊ አይደለም የተቀጠረው ዝውውር ሲፈፀም የተሰጣቸውን ክላራንስ በመጠቀም በመሆኑ ማጭበርበር ፈጽሟል። ለትምህርት ተልኮ በቋሚነት ተቀጥሮ ሙሉ ጊዜውን ተጠቅሞ ትምህርቱን ይከታተላል ማለትም አይቻልም። በመሆኑም ጥፋተኛ ነው ብለነዋል። ቅጣቱ በደንቡ ቁጥር 104/2004 እንቀጽ 72(19) የተከሰሰ ቢሆንም በደንቡ ቁጥር 104/2004 አንቀጽ 72(13) ማጭበርበር ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ስላገኘነው በደንብ ቁጥር 104/2004 አንቀጽ 71(ረ) መሰረት ከስራ ይሰናበት ሲሉ የውሳኔ ሃሳብ አቀረቡ። የበላይ ሃላፊውም የዲስፕላን ኮሚቴውን የውሳኔ ሃሳብ በማጽደቅ ከስራ እንዲሰናበት ወስኗል። ተከሳሽ የአሁን አመልካች ለኮሚሽነሩ ይግባኝ ቅሬታ አቅርቦ ኮሚሽነሩም ተከሳሽ የአሁን አመልካች ከስራ እንዲሰናበት የተሰጠውን ውሳኔ አጽንቷል።
ተከሳሽ የአሁን አመልካች ለአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ አቅርቦ በመ/ ጥቅምት 9 ቀን 2010 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ የጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሥረ ነገር ስልጣን በክልሉ ህገ መንግስት አንቀጽ 67(2ሐ) ማንኛውም የክልሉ ፍ/ቤቶች በመጨረሻ በሚሰጧቸው ጉዳዮች ላይ ብቻ ነው።
ሥልጣኑ ከተግባራዊነቱና የመንግስት ስልጣን ክፍፍል በተለይም ሕገ መንግስታዊ ትርጉምንም የመዳኘት ስልጣን ለፍ/ቤት ካለመስጠቱ አኳያ ከአስተዳደር አካሉ የሚነሱ ጉዳዮችን ሁሉ በሰበር የሚታይበት የህግ ስርዓት አለመዘርጋቱን የሚጠቁም ነው።
ይልቁንም የአስተዳደር አካላት ውሳኔ በፍ/ቤት የሚታረመው እንደ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 171/2002 ያሉ ህጎች በፍ/ቤት እንዲታዩ በግልጽ ሲደነግጉና ሲመራ ነው።
ከዚህ ውጪ በመርህ ሁሉም የአስተዳደር አካላት ውሳኔ በፍርድ ቤት ነው ለማለት የሚቻል አይደለም። በአዋጅ ቁጥር 223/07 አንቀጽ 17(2) አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ ለማስተናገድ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የስረ ነገር ስልጣን የለውም በማለት በአብላጫ ድምጽ ወስኗል።
የአሁን አመልካችም ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርበዋል። መዝገቡም ተመርምሮ በአማራ ብ/ክ/መ. የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተሰጠውን የዲስፕላን ውሳኔ በሰበር የማየት ስልጣን የለኝም በማለት የሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ከክልሉ ደንብ ቁጥር 104/04 አንቀጽ 75(3) እና ከኢፍዲሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(2/3) መሰረት መጣራት ያለበት በመሆኑ ቀርቧል። መልስና የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል። ተጠሪም ጥር 15 ቀን 2010 ዓ/ም በተጻፈ መልስ በአማራ ብ/ክ/መ. ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በደንብ ቁጥር 104/2004 አንቀጽ 75(3) መሰረት የኮሚሽኑ የበላይ ሃላፊ በይግባኝ በቀረበለት ጉዳይ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ እንደሚሆን የተደነገገ በመሆኑ እና የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ከደንብ ቁጥር 104/2004 አንቀጽ 67(2/3 ሐ/መ) መሰረት የሥረ ነገር ስልጣን የለኝም ማለቱ በአግባቡ ነው ሲል ተከራክረዋል።
አመልካችም ጥር 28 ቀን 2010 ዓ/ም በተጻፈ የመልስ መልስ አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል፣ እኛም የቀረበውን አቤቱታ፣ መልስ እና የመልስ መልሱን እንዲሁም የስር ፍርድ ቤት ውሣኔዎችን እና ከጉዳዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል። እንደመረመርነውም የስር የአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በፍርድ ቤት ከተሰጡ የመጨረሻ ውሳኔና መሰረታዊ የህግ ስህተት ካላባቸው ውሳኔ ውጪ በአስተዳደራው ውሳኔ ሰጪ አካላት የሚሰጡ ውሳኔዎችን ለማየት ሥልጣን የለኝም። የጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚው ችሎት ስልጣን በአማራ ብ/ክ/መ. ህገ መንግስት አንቀጽ 67(2ሐ) ድንጋጌ መሰረት ማንኛውም ክልላዊ ፍ/ቤት የመጨረሻ ውሳኔ በሰጡባቸው ጉዳዮች ላይ ብቻ በመሆኑ የአማራ ብ/ክ/መ. ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተሰጠውን የዲስፒላን ውሳኔ ለማየት ሥልጣን የለኝም ሲል መዝገቡን ዘግቶታል። ይሁንና የኢፍዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(2) የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በክልሉ ጉዳይ ላይ የበላይና የመጨረሻ የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል ሲል ደንግጓል።
አንቀጽ 80(3ለ) ደግሞ የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበትን በክልል ጉዳዮች የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ ለማረም በሰበር ችሎት ለማየት ሥልጣን ይኖረዋል ሲል ደንግጎ ይገኛል። እንዲሁም የኢፍዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 9(1) ሕገ መንግስቱ የሀገሪቱ የበላይ ሕግ እንደሆነና ማንኛውም ሕግ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከሕገ መንግስቱ ጋር መቃረን እንደልለበት ደንግጓል። የአማራ ብ/ክ/መ. ህገ መንግስት አንቀጽ 67(2ሐ) ድንጋጌ የኢፍዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3ለ) ጋር የሚቃረን አይደለም። ይሄውም የአማራ ብ/ክ/መ. ህገ መንግስት አንቀጽ 67(2ሐ) ድንጋጌ ማንኛውም ክልላዊ ፍ/ቤት የሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ሲኖርበት በሰበር ችሎት የማየት ስልጣን ይኖረዋል ሲል መደንገጉ የክልሉ ሰበር ሰሚው ችሎት በፍ/ቤቶች የተሰጡ የመጨረሻ ውሳኔ ብቻ እንደሆነ ትርጉም ላሰጠው የማይገባና በኢፍዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3/ለ) ድንጋጌ መሰረት በክልል ጉዳዮች የተሰጡ የመጨረሻ ውሳኔም ጭምር የማየት ስልጣን እንዳለው ላወሰድ የሚገባ ነው። እንዲሁም በተሻሻለው የአብክመ. የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሰራተኞች መተዳደሪያ ደንብ ቁጥር 104/2004 አንቀጽ 75(3) እና በልሎችም አዋጆች “በይግባኝ በቀረበለት ጉዳይ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል” በሚል ተገልጸው የሚገኙት ድንጋጌዎች በይግባኝ ደረጃ ቀርበው ለመታየት የማይችሉ የመጨረሻ ውሳኔዎች መሆናቸውን የሚገልጽ እንጂ በሰበር ሰሚው ችሎት መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለባቸውን ጉዳዮች ለማረም የሚቀርቡ ጉዳዮችን የሚጨምር አይደለም።
በኢፍድሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37(1) ስር እንደተመለከተው ማንኛውም ሰው በፍርድ ላወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለልላ በህግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብ እና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት እንዳለው ተደንግጓል።
በመሆኑም ህገ መንግስቱ ማንኛውም ሰው ጉዳዩ በፍርድ ላወሰን የሚገባው ጉዳይ ከሆነ ለፍ/ቤቶች አቅርበው ፍትህ የማግኘት መብት ሰጥቷቸዋል። በመሆኑም የአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በአስተዳደራዊ ውሳኔ ሰጪ አካላት የተሰጡ የዲስፕላን ውሳኔ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሥልጣን መሆኑ የክልሉ ሕገ መንግስት ያልከለከለውና የኢፍዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3/ለ) ሥልጣኑ እንዳለው ደንግጎ እያለ ጉዳዩ በተሻሻለው የአብክመ. የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሰራተኞች መተዳደሪያ ደንብ ቁጥር 104/2004 አንቀጽ 75(3) መሰረት ጉዳዩ በይግባኝ ደረጃ የመጨረሻ ውሳኔ ያገኝ ጉዳይ ሆኖ እያለና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለባቸውን ጉዳዮችን ተቀብሎ የማየት ስልጣን እያለው ሥልጣን የለኝም ሲል አቤቱታውን መዝጋቱ ከህጉ ድንጋጌ ትርጉም ውጪ የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል።
የአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ ጥቅምት 9 ቀን 2010 ዓ/ም በዋለው ችሎት በአብላጫ ድምጽ የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በአሁን አመልካች የቀረበለትን አቤቱታ የሰበር ሰሚው ችሎት ስልጣን በመሆኑ አከራክሮ ውሳኔ እንዲሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 343(1) መልስንለታል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.