አንድ የመንግስት ቤት ተከራይ የራሱ ቤት ካገኘ የመንግስት ቤትን በተከራይነት ይዞ መቀጠል አቶ ለማ ማሙዬ እና XLVII ስለመሆኑ፡መመሪያ ቁጥር 10/2006 አንቀፅ 15(2) በአዳማ ከተማ አስተዳደር ቀበል 12 ጽ/ቤት
No summary available.
የሰ/መ/ቁ/ - 137353 ጥር 22 ቀን 2010ዓ.ም ዳኞች፡- ዳኜ መላኩ ተኽላት ይመሰል ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- ወ/ሮ አዛለች አጎናፍር ጠበቃ ሚልኪያስ ቡልቻ ቀረቡ ተጠሪ፡- ገብርኤል አካባቢ ቀበል ጽ/ቤት ዐ/ሕግ አይናዲስ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ ያላግባብ የተያዘ ቤት ይለቀቅልኝ በሚል የቀረበዉን ዳኝነት መሰረት በማድረግ የተሰጠዉን ፍርድ በመቃወም የቀረበዉን የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነዉ። ክርክሩ የተጀመረዉ በሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
አመልካች በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘትም፤ በጎንደር ከተማ ገብርኤል አካባቢ ክ/ከተማ በ 735 ካ/ሜትር ቦታ ላይ ያላቸዉን ቤት ተጠሪ ያላግባብ በመያዝ ለግለሰቦች እያከራየ መሆኑን፣ ቤቱ በመንግስት ያልተወረሰ መሆኑን ገልጸዉ እንዲመለስላቸዉ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት የከንቲባ ጽ/ቤቱ ቤቱ እንዲመለስላቸዉ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም ተጠሪ ቤቱን ለማስረከብ ፍቃደኛ አለመሆኑን ጠቅሰዉ ተጠሪ ቤቱን እንዲያስረክባቸዉ ይወሰንላቸዉ ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸዉን የሚያሳይ ነዉ።
ተጠሪ ለቀረበበት ክስ በሰጠዉ መልስ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ያለዉ የፕራይቬታይዘሽን ኤጀንሲ በመሆኑ ክሱ ለፍርድ ቤቱ ላቀርብ እንደማይገባዉ እንዲሁም ክሱ በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ ገልፆ የመጀመሪያ መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን፣ ፍሬ ነገሩን በተመለከተ አመልካች በቤቱ ላይ መብት ያላቸዉ ስለመሆኑ ማስረጃ አለማቅረቡን እና ቤቱ የሚገኝበት ቦታ ስፋትም አመልካች እንደሚሉት 735 ካ/ሜ ሳይሆን 182 ካ/ሜትር መሆኑን እና ቤቱም የመንግስት እንጂ የአመልካች አለመሆኑን በመግለጽ የቀረበዉ ክስ ዉድቅ ሆኖ ይወሰንልኝ በማለት ተከራክሯል።
ጉዳዩ በመጀመሪያ የቀረበለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በዚህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ፤ ቤት ተወርሷል ወይስ አልተወረሰም የሚለዉን ጭብጥ በማስረጃ አጣርቶ የመወሰን ስልጣን የፕራይቬታይዘሽን ኤጀንሲ እንጂ የመደበኛ ፍርድ ቤት አለመሆኑን እንዲሁም አመልካች ከክሳቸዉ ጋር አያይዘዉ ያቀረቡት የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታም በ1965 ዓ.ም የተሰጠ በመሆኑ በቤቱ ላይ መብት ያላቸዉ መሆኑን አያሳይም በማለት የቀረበዉን ክስ ዉድቅ በማድረግ ወስኗል።
አመልካች ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ይግባኝም ተቀባይነት አላገኘም።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ሲሆን፣ አመልካች በቀን 26/08/09 ዓ.ም ተዘጋጅቶ በቀረበዉ 3 ገጽ የሰበር አቤቱታ በሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፀንቶ የተወሰነዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚሉባቸዉን ምክንያቶች በመዘርዘር ታርሞ ይወሰንላቸዉ ዘንድ ዳኝነት ጠይቀዋል። አቤቱታዉ ተመርምሮም ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለማየት ስልጣን የለዉም በሚል በስር ፍርድ ቤት የተሰጠዉን ዉሳኔ አግባብነት ግራ ቀኝ በተገኙበት ለማጣራት ሲባል መዝገቡ ለሰበር ያስቀርባል በመባሉ ተጠሪ ቀርቦ እንዲከራከር በተደረገለት ጥሪ መሰረት ቀርቦ ግራ ቀኝ ክርክራቸዉን በጽሑፍ ተለዋዉጠዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት በአጭሩ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችሎትም ለሰበር አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉን ዉሳኔ መዝገቡን ለማስቀረብ ከተያዘዉ ጭብጥ እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። ከግራ ቀኝ ክርክር ሂደት መገንዘብ የተቻለዉ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ላቀረቡት ክስ መሰረት ያደረጉት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት የግላቸዉ መሆኑን እና ተጠሪ ያላግባብ መያዙን ሲሆን፤ ተጠሪ በበኩሉ ቤቱ የአመልካች አለመሆኑን በመግለጽ የተከራከረ መሆኑን ነዉ። የስር የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን ክስ ዉድቅ ለማድረግ የቻለዉ በአንድ በኩል ቤቱ የተወረሰ መሆን አለመሆኑን በማስረጃ አጣርቶ ለመወሰን ፍርድ ቤት ስልጣን የለዉም በማለት በልላ በኩል አመልካች ያቀረቡት ማመልከቻ በቤቱ ላይ መብት ያላቸዉ መሆኑን የሚያሳይ አይደለም በማለት መሆኑን ተገንዝበናል። በመሰረቱ ፍርድ ቤት የቀረበለትን ጉዳይ ለማየት ስልጣን የልለዉ መሆኑን እንደተገነዘበ ይህኑን ጠቅሶ ወደ ፍሬ ነገር ክርክር ከመግባቱ በፊት ተቀባይነት የልለዉ መሆኑን ገልፆ የቀረበዉን የክስ አቤቱታ ከመመለስ አልፎ ፍሬ ነገርን በተመለከተ ዉሳኔ መስጠት እንደማይችል በፍ/ሥ/ሥርዓት ሕጉ አንቀጽ 231(1-2) ስር የተመለከተዉ ድንጋጌ ያስገነዝባል። ከዚህ አንፃር ሲታይ የስር ፍርድ ቤት በአንድ በኩል ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን የለዉም እያለ፣ በልላ በኩል ግን አመልካች በቤቱ ላይ መብት ያላቸዉ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ አላቀረቡም በማለት ፍሬ ነገሩን በተመለከተ የሰጠዉ ዉሳኔ ከፍ ሲል የተመለከተዉን የፍ/ሥ/ሥርዓት ህጉን ድንጋጌ ያላገናዘበ በመሆኑ ላታረም የሚገባዉ ሆኖ ተገኝቷል።
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ጉዳዩ ለመደበኛ ፍርድ ቤት የሚቀርብ አይደለም በማለት የሰጠዉን ዉሳኔ አግባብነት እንመልከት። በህግ ለልላ አካል በግልጽ እስካልተሰጠ ድረስ በፍርድ የሚያልቁ ጉዳዮችን አይቶ የመወሰን ስልጣን የፍርድ ቤቶች ስለመሆኑ በኢፍዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37 ስር ከተመለከተዉ ድንጋጌ መረዳት ይቻላል።
በመሆኑም ከስልጣን ጋር በተያያዘ ክርክር ሲኖር ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ያላቸዉ መሆን አለመሆኑን በመወሰን ረገድ ፍርድ ቤቶች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ጉዳይ የማየት ስልጣን በህግ ለልላ አካል የተሰጠ መሆኑ አለመሆኑን በአግባቡ የማረጋገጥ ግድታ እና ኃላፊነት ያለባቸዉ ሲሆን፤ ይህን አለማድረግ በዜጎች ፍትሕ የማግኘት መብት ላይ አሉታዊ ዉጤት ላያስከትል የሚችል መሆኑንም መገንዘቡ ተገቢ ነዉ።
የተያዘዉን ጉዳይ በተመለከተ የስር የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መደበኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለማየት ስልጣን የለዉም ሲል ለሰጠዉ ዉሳኔ በዋቢነት የጠቀሰዉ አዋጅ ቁጥር 110/87 እንዲሁም ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ የሰጠዉን ዉሳኔ ነዉ። በልላ በኩል አዋጅ ቁጥር 110/87 አንቀጽ 4(1) እና (2) መሰረት ከአዋጅ ዉጪ የተወሰዱ ንብረቶችን የባለቤትነት ሁኔታ የማጣራትና የመወሰን ስልጣን ለፕራይቬታይዘሽን ኤጄንሲ ይሰጣል፤ አዋጅ ቁጥር 572/2000 ከአዋጅ ዉጪ የተወሰዱ ንብረቶችን ለማስመለስ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ያላግባብ የተወረሱ የመንግስት ንብረቶችን እንደገና ለማስመለስ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን አይቶ የመወሰኑ ስልጣን የፕራይቬታይዜሽን ኤጄንሲ መሆኑን ይደነግጋል። ይሁንና ያላግባብ በከተማ አስተዳደር ወይም በቀበል የተያዘን ቤት ለማስመለስ የሚቀርብ የዳኝነት ጥያቄ ለየትኛዉ አካል እንደሚቀርብ በሁለቱም አዋጆች በግልጽ አልተደነገገም። ፍርድ ቤት በዋቢነት የጠቀሰዉ በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉ ዉሳኔ ሲታይ ከአዋጅ ዉጪ የተወረሱትን ቤቶች ለማስመለስ የሚቀርብ ዳኝነትን እንጂ የምርጫ ቤት ያላግባብ ተይዟል በሚል የቀረበዉን ክርክር መነሻ ያደረገ አይደለም። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት የጠቀሰዉ የሰበር ዉሳኔ ከአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2(1) አኳያ ለተያዘዉ ጉዳይ በዋቢነት ላጠቀስ የሚገባዉ አይደለም።
በአጠቃላይ በከተማ አስተዳደር ወይም በቀበል ያላግባብ የተያዘን የምርጫ ቤት ለማስመለስ የሚቀርበዉን ክስ የማየት ስልጣን በህግ ለልላ የመንግስት አካል ባልተሰጠበት ሁኔታ፣ እንዲሁም የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ የሰጠዉ ዉሳኔም ለተያዘዉ ጉዳይ አግባብነት የልለዉ ሆኖ እያለ፤
መደበኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለማየት ስልጣን የለዉም በሚል የደረሰበት ድምዳሜ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ይህንኑን በማጽናት የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ተወስኗል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/ 00562 በቀን 01/03/09 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት፣ የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 01-22362 በቀን 11/09/08 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት የሰጠዉን ፍርድ በማጽናት፣ የሰጠዉ ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገቡን እንደገና በማንቀሳቀስ ፍሬ ነገሩን በተመለከተ ግራ ቀኙን አከራክሮ ተገቢዉን ዉሳኔ ይሰጥበት ዘንድ መዝገቡ በፍ/ሥ/ሥ/ ህጉ አንቀጽ 341(1) መሰረት ተመልሶለታል።
በዚህ ችሎት በተደረገ ክርክር ምክንያት የወጣዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻሉ ብለናል።