የድሬድዋ ከተማ ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 416/96 134681 ሳዲቅ አብዱሪህማን ጥቅምት 21 431 XLVI መሰረት የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን ለማስፈፀም ሲባል ከይዞታ ባለቤትነት፣ ከፈቃድ አሰጣጥ እና ከቦታ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የሚነሱ ክርክሮችን ከማየት ባለፈ በእርሻ መሬት ባለይዞታነት ይገባኛል ጥያቄን መሰረት ያደረገ ክርክርን ለማስተናገድ የስረ ነገር ስልጣን የልለው ስለመሆኑ፡የአ/ቁ 416/1996 አንቀፅ 31(1) (ሰዎች) እና የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ቀን 2010 ዓ/ም 84. በከተማ አስተዳደር ወይም በቀበል ያላግባብ የተያዘን የምርጫ ቤት ለማስመለስ የሚቀርብን ክስ የማየት ስልጣን በህግ ለልላ የመንግስት አካል ባልተሰጠበት ሁኔታ መደበኛ ፍርድ ቤቶች የማየት ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ፡ኢ.ፊ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 37
No summary available.
ጥቅምት 21 ቀን 2010 ዓ/ም ዳኞች፡- ፀጋዬ አስማማው አልማው ወል ሙስጠፋ አህመድ አብርሃ መሰለ ጰውሎስ ኦርሺሶ አመልካቾች፡-
የክርክሩ ምክንያት ያለአግባብ የተወሰደ የካሳ ገንዘብ ይመለስ የሚል ነው። ክሱ የቀረበው ለድሬዳዋ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ ሲሆን አመልካቾች ደግሞ ተከሳሾች ነበሩ። የክሱ ይዘትም፡- የአሁኑ አመልካቾች እና የዚህ ሰበር ተካፋይ ያልነበሩት የሥር 3ኛ ተከሳሽን ጨምሮ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ የልላቸውን ንብረት ወይም ይዞታ በማስመዝገብ የልላ ሰው የሆነውን ይዞታ የእኛ ነው በማለት ትርፍ ገንዘብ ብር 131,797.73 /አንድ መቶ ሰላሳ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ዘጠና ሰባት ብር ከሰባ ሶስት ሳንቲም/ እንዲመልሱ እንዲወሰንልን የሚል ነው።
የሥር ተከሳሾች መጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና በፍሬ ነገሩ ላይም ተገቢ ነው ያሉትን ክርክር አቅርበዋል። ጉዳዩን የተመለከተው የድሬዳዋ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን ክርክር እና የምስክሮችን ቃል እንዲሁም የሰነድ ማስረጃዎችን መርምሮ የሥር ተከሳሾች ካላቸው ይዞታ መሬት ትርፍ መሬት በማስመዝገብ የወሰዱትን በክሱ ላይ የተጠቀሰውን ብር 131,797.73 /አንድ መቶ ሰላሳ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ዘጠና ሰባት ብር ከሰባ ሶስት ሳንቲም/ ተመላሽ አንዲያደርጉ ሲል ውሳኔ ሰጥቷል።
ይህን ውሳኔ በመቃወም የአሁኑ አመልካቾች ይግባኝ ለድሬዳዋ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርበው ተቀባይነትን ሳያገኝ ቀርቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የከተማ አስተዳደሩ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ እንዲሁም የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ ለማስለወጥ ሲሆን ይዘቱም፡- የድሬዳዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የፍትሓብሕር ዳኘነትን በሚመለከት በቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/1996 አንቀጽ 33 ሥር ከተደነገገው ውጪ በተከራካሪ ወገኖች መካከል የሚነሱ የፍትሓብሕር ክርክሮችን፣ የይዞታና ያልተገባ ጥቅም ተወስዷል በሚል የሚቀርቡ ክርክሮች ሰምቶ ማስረጃ ተቀብሎ የመወሰን የሥረ ነገር ሥልጣን ሳይኖራቸው የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲሻርልን የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም አከራካሪ የሆነው የይዞታ ባለቤትነት ጥያቄው የሚታየው በፍድራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ወይም የከተማው ሰበር ሰሚ ማየት ሲገባው ለከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረበበትንና የተያዘበትን አግባብነት ለማጣራት ተብሎ ለሰበር ሰሚ ችሎት እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርቦም የግራ ቀኙ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
የነገሩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሯል።
ከክርክሩ እንደተገነዘብነው የሥር 1ኛ- 3ኛ ያሉት ተከሳሾች በቀድሞ ልኬት መሰረት 4.6647 ሄክታር ሲሆን የወሰዱት የመፈናቀያ ካሳ ብር 183,664.50 /አንድ መቶ ሰማኒያ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ አራት ብር ከሃምሳ ሳንቲም/ ተሰርቶ ክፍያ የተፈጸመ ሲሆን በድጋሚ ጂ.ፒ.ኤስ መለኪያ መሥሪያ መሰረት የተለካው የመሬት መጠን 3.271 ሄክታር የመፈናቀያ ካሳ ክፍያ ብር 128,789.97 /አንድ መቶ ሃያ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ብር ከዘጠና ሰባት ሳንቲም/ መከፈል ሲገባ በልላቸው መሬት መጠን 1.304 ሄክታር በማስመዝገብ ብር 54,874.53 /አምሳ አራት ሺህ ስምንት መቶ ሰባ አራት ብር ከሃምሳ ሶስት ሳንቲም/ ትርፍ ገንዘብ ወስደዋል፣ የሥር 4ኛ ተከሳሽ /የአሁኑ 3ኛ አመልካች/ የሆኑት ደግሞ በቀድሞ ልኬት መሰረት 5.4570 ሄክታር ሲሆን የመፈናቀያ ካሳ ብር 190,995.00 /አንድ መቶ ዘጠና ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አምስት ብር/ ተሰርቶ ክፍያ የተፈጸመ ሲሆን በአዲስ መልክ ሲለካ 3.2592 ሄክታር መሬት ሆኖ የመፈናቀያ ካሳ ግምቱ ብር 114,072. /አንድ መቶ አስራ አራት ሺህ ሰባ ሁለት ብር/ መክፈል ሲገባ በልላቸው መሬት መጠን 2.1978 ሄክታር በትርፍነት በማስመዝገብ ብር 76,923.00 /ሰባ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ሶስት ብር/ ትርፍ ክፍያ ተፈጽሞላቸዋል የሚል ነው። የሥር ፍርድ ቤትም ጉዳዩን ተመልክቶ የሥር ከሳሽ /የአሁኑ ተጠሪ/ እንዲመለስ የጠየቀውን ገንዘብ የሥር ተከሳሾች /የአሁኑ አመልካቾች/ እንዲመልሱ ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህ ጉዳይ በዋናነት ላታይ የሚገባው የሥር ፍርድ ቤት የቀረበውን ጉዳይ አይቶ ለመወሰን የሥረ ነገር ሥልጣን አለው ወይስ የለውም? የሚል ነው። አንድ ፍርድ ቤት አንድን ጉዳይ አይቶ ለመወሰን በመጀመሪያ ደረጃ የሥረ ነገር ሥልጣን ላኖረው ይገባል። የአሁኑ ተጠሪ ሥልጣንን በተመለከተ የአሁኖቹ አመልካቾች የራሳቸው ያልሆነን የልላ ግለሰብን ይዞታ ጨምረው በማስለካት ከመንግሥት ተጨማሪ የካሳ ክፍያ የወሰዱ በመሆኑ ምክንያት የማይገባቸውንና የማይመለከታቸውን ስለወሰዱ እንዲመልሱ የቀረበ ክስ በመሆኑ በድሬዳዋ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/1996 አንቀጽ 31 (1) እንደተመለከተው የከተማውን ማስተር ፕላን አፈጻጸም የሚመለከት የይዞታ ባለቤትነት፣ ፍቃድ አሰጣጥ ወይም ይዞታ አጠቃቀምን በተመለከተ የሚነሱ ክሶችን የማየት ሥልጣን የከተማው ፍርድ ቤት ስለሆነ ክስ መስርተን ውሳኔ ማሰጠታችን እንዲሁም የካሳው ጉዳይም ከይዞታው ጋር የሚገናኝ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤትም ሥልጣኑን መሰረት በማድረግ የሰጠው ውሳኔ አግባብ ስለሆነ የህግ ስህተት ስለልለ የአመልካቾች አቤቱታ ውድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክሯል። ለዚህ ሥልጣን ጉዳይ ዋና መሰረት ተደርጎ የተነሳውን የድሬዳዋ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ 416/1996 አንቀጽ 31 /1/ መመልከት ለክርክሩ ህጋዊ እልባት ለመስጠት ያስችላል።
የድሬዳዋ አስተዳር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/1996 አንቀጽ 31 (1) ድንጋጌ እንደሚከተለው ይነበባል።
ይህ ድንጋጌ በግልጽ እንደሚያመለክተው የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን ለማስፈጸም ሲባል ከይዞታ ባለቤትነት፣ ከፍቃድ አሰጣጥ እና ከቦታ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የሚነሱ ክርክሮችን የከተማው ፍርድ ቤት ለማየት እንዲችል በህግ አውጪው የተሰጠ ሥልጣን ነው። ነገር ግን ከያዝነው ጉዳይ ወይም የክርክር ዓይነት ጋር ተያይዞ የተሰጠ የዳኝነት ሥልጣን አይደለም።
በመሰረቱ አሁን እያከራከረ ያለው ጉዳይ በአዋጁ አንቀጽ 31 /1/ ላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ ሳይሆን አመልካቾች የራሳቸው የእርሻ ይዞታ መሬት ያልሆነ ወይም የይዞታው ባለቤት ያልሆኑበትን የልላ ሰው እርሻ መሬት ይዞታ በትርፍ አስለክተው የማይገባቸውን ገንዘብ ወስደዋል የሚል ይዘት ያለው ነው። በዚህ መሰረት ክርክሩ በተከራካሪ ወገኖች መካከል የተነሳ የእርሻ መሬት ባለይዞታነት ይገባኛል ጥያቄን መሰረት በማድረግ የተነሳ በመሆኑና ባለይዞታው ማን እንደሆነ አከራክሮ በመለየት በትርፍ መሬት ይዞታ ተሰጥቶ የነበረው ትርፍ የካሳ ገንዘብ እንዲመለስ የሚለውን የፍትሓብሕር ክርክር የመዳኘት የሥረ ነገር ሥልጣን በድሬዳዋ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/1996 አንቀጽ 31 /1/ መሰረት ለከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የተሰጠ ሥልጣን ባለመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
በመጨረሻም የሥረ ነገሩን ለመስማት ፍርድ ቤቱ ሥልጣን የልለው በሆነ ጊዜ ስለሚፈጸም ሥነ ሥርዓት የፍትሓብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 9 በግልጽ ያስቀመጠውን ድንጋጌ የሥር ፍርድ ቤቶች ባለማጤን ጉዳዩን ለማየት የሥረ ነገር ሥልጣን የላቸውም ተብሎ የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያለአግባብ በማለፍ ወደ ፍሬ ነገር ክርክር በመግባት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል፡
የድሬዳዋ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.01913 ግንቦት 3 ቀን 2009 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ በቀን 19/3/2009 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍትሓብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሽሯል።
ለዚህ የሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነውን ጉዳይ የሥር ፍርድ ቤቶች አይተው ለመወሰን የሥረ ነገር ሥልጣን የላቸውም ተብሎ ተወስኗል።
የዚህን ችሎት ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
በቀን 12/04/2009 ዓ/ም የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ለሚመለከተው አካል ይጻፍ።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይላክላቸው።
መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.