በሁለት የህግ ሰውነት በተሰጣቸው አካላት መካከል የኢንቨስትመንት መሬት ያላግባብ ተይዞብኛል በሚል የሚነሳ ክርክርን በተመለከተ ክርክር ባስነሳው መሬት ላይ ግራ ቀኙ ያወጡት የኢንቨስትመንት ፈቃድ የፍድራል ከሆነ ጉዳያቸው ላታይ የሚችለው በፍድራል ፍርድ ቤቶች ሲሆን፣ ፈቃድ ያገኙት ግን በክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ ከሆነ በክልል ፍርድ ቤቶች የሚታይ ስለመሆኑ፤ እንዲሁም ከሁለቱ አንዱ ወገን የፍድራል ተመዝጋቢ ከሆነ ደግሞ ጉዳዩ ላታይ የሚገባው በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5/6 መሰረት በፍድራል ፍርድ ቤቶች ስለመሆኑ የፍደራል ኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 769/2004 ፣የኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 138/2000
No summary available.
ሚያዚያ 25 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- 1.ዓላ መሐመድ 2. ተኽላት ይመሰል 3. ተፈሪ ገብሩ 4. ቀነዓ ቂጣታ 5. ፀሐይ መንክር አመልካች........የሰቆጣ ወረዳ ሚላሻ ጽ/ቤት --- ዐ/ህግ አሳምር ጌጤ ቀርበዋል።
ተጠሪ..............ቄስ ሙሉጌታ ተረፈ ------ አልቀረቡም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር ጉዳይ የአንድ ክላሽ መሳሪያ እና ከመሰል 30 ጥይት ግምት ለማስከፈል የቀረበ ክስን መነሻ ያደረገ ክርክር ሲሆን፣ ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ላቀርብ የቻለዉ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.03-11989 የካቲት 16 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልን በማለት የአሁን አመልካች የቀረበዉን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ለመወሰን ነዉ።
የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ በሰቆጣ ወረዳ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች ከሳሽ፣የአሁን ተጠሪ ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ የነበረ ሲሆን፣ ከሳሽ ባቀረበዉ ክስ ተከሳሽ በሰቆጣ ወረዳ ቀበል 02 ነዋሪ ሲሆን በቀበልዉ ሚላሻ በኩል የማዕከል አስተባባሪ ኃይል አመራር ሆኖ ከሰቆጣ ወረዳ ሚላሻ ጽ/ቤት በሞድል 22 በ30/1/2007 ዓ.ም ወጪ አድርጎ የወሰደዉን የንምራ ቁጥር 8072 የሆነ ሰ/ከ/ክላሽ 1/አንድ/ ካዝና እና ከመሰል 30 ጥይት ጋር የወሰደ ስለሆነ ይህን የመንግስት የጦር መሣሪያ እንዲመልስ፣ ካልሆነ ግምቱን የክላሽ 30,000 /ሰላሳ ሺህ/ እና ጥይቱን 100*30=3,000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል እንዲወሰንልን በማለት ከሷል።
የሥር ተከሳሽ ባቀረበዉ መልስ በክሱ ላይ የተጠቀሰዉን ክላሽ ጠመንጃ በ30/1/2007 ዓ.ም በ6,000 /ስድስት ሺህ/ ብር ዋስትና በመፈጸም ማዉጣቴ አይካድም፣ ይሁን እንጂ በ20/8/2007 ዓ.ም ከሰቆጣ ከተማ 02 ቀበል ከቄስ ወልድ አያልዉ ቤት አድሬ መሳሪያዉ ጠፋኝ፣ ተከሳሽ በዚህ ምክንያት በወንጀል ተከስሼ የእስራት ቅጣት ተወስኖብኝ ስለምገኝ ድጋሚ ልከሰስ አይገባም፣ ተከሳሽ መጠየቅ ያለብኝ ወድጄ የፈረምኩት ብር 6,000 /ስድስት ሺህ/ ነዉ በማለት ተከራክሯል።
ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን በማየት በሰጠዉ ዉሳኔ ተከሳሽ ይህን መሳሪያ መዉሰዱን ስላልካደ ግምቱን መክፈል ያለበትም በአማራ ብ.ክ.መ. መስተዳድር መመሪያ በ30/7/2007 ዓ.ም ተሻሽሎ በወጣዉ የመሳሪያ ግምት ለክላሽ ዋጋ 30,000 /ሰላሳ ሺህ/ እና ለ30 ጥይት ብር 3,000 /ሶስት ሺህ/ በአጠቃላይ ብር 33,000 /ሰላሳ ሶስት ሺህ/ ተከሳሽ ላከፍል ይገባል በማለት ወስኗል።
የሥር ተከሳሽ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለዋግ ኽምራ ብሕረሰብ አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ይግባኙን ዉድቅ በማድረግ የሥር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።የሥር ከሳሽ በዚህ ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታዉን ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱ ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር በድምጽ ብልጫ በሰጠዉ ዉሳኔ የሥር ተከሳሽ ይህን ክላሽ መሳሪያ ሲረከብ በሥራ ላይ በነበረዉ መመሪያ ቁጥር 44/2001 አንቀጽ 17 /2/ መሰረት የክላሽ ዋጋ የተተመነዉ ብር 6,000 /ስድስት ሺህ/ እና የአንድ ጥይት ዋጋ ብር 10 የነበረ በመሆኑ በዚህ አግባብ ሲታይ የሥር ተከሳሽ የክላሽ መሳሪያ ዋጋ ብር 6,000 /ስድስት ሺህ/ እና የ30 ጥይት ዋጋ ብር 300 /ሶስት መቶ/ ለሥር ከሳሽ ላከፍል ይገባል በማለት የሥር ፍ/ቤቶችን ዉሳኔዎች በመሻር ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች በ15/7/2008 ዓ.ም የተጻፈ ሶስት ገጽ አቤቱታ አቅርቧል።
የአቤቱታዉም ይዘት በአጭሩ፡--ተጠሪ ያጠፋዉን የመንግስት የጦር መሣሪያ /ክላሽ/ ዋጋዉን መክፈል የሚገባዉ መሣሪያዉ ጠፋ ባለዉ ሚያዚያ 20 ቀን 2007 ዓ.ም በሥራ ላይ በነበረዉ የአማራ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት መጋቢት 25 ቀን 2007 ዓ.ም ባካሄደዉ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ስብሰባ በማሻሻል ባወጣዉ የመንግስት የጦር መሳሪያ ዋጋ ተመን መመሪያ መሰረት መሆን ሲገባዉ መሣሪያዉ ለተጠሪዉ ሲሰጥ የነበረዉን የመሳሪያ ግምት መሰረት በማድረግ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልን በማለት አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችሎት ይህን ጉዳይ በማየት ፣ተጠሪ የአከራካሪዉን የጦር መሳሪያ ግምት ላከፍለዉ የሚገባዉ መሳሪያዉን ሲረከብ በነበረዉ መመሪያ ቁጥር 44/2001 ነዉ ወይስ መጋቢት 25 ቀን 2007 ዓ.ም በተሻሻለዉ መመሪያ ላሆን ይገባዋል፣ የሚለዉን ነጥብ ለመመርመር ሲባል አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዲሰጥ ቢታዘዝም ለተጠሪ መጥሪያ ለማድረስ ተጠሪ በቀበልዉ እንደማይኖር ስለተረጋገጠ ምስክሮች ባሉበት ለሚስቱ መጥሪያ የተሰጠ መሆኑን አመልካች በአቤቱታ በማረጋገጡ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፏል።
በዚህ መዝገብ የተደረገዉ ክርክር ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት ይህን ክርክር ለሰበር አቤቱታዉ መነሻ ከሆነዉ ዉሳኔ እና አግባብነት ካላቸዉ የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዲሁም አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ የአሁን ተጠሪ ለክርክር መነሻ የሆነዉን የመንግስት የጦር መሳሪያ የሆነዉን በክሱ የተመለከተዉን ክላሽ ፈርሞ ከአመልካች ጽ/ቤት ከወሰደ በኋላ ሳይመልስ በመቅረቱ የአሁን አመልካች የዚህ መሳሪያ ከመሰል ጥይት ዋጋ ጋር እንዲከፈለዉ ባቀረበዉ ክስ ዳኝነት መጠየቁ መዝገቡ ያመለክታል። የአሁን ተጠሪ በሥር ፍ/ቤት ባቀረበዉ ክርክር መሳሪያዉን መዉሰዱን ሳይክድ በ20/8/2007 ዓ.ም የጠፋበት እንደሆነ በመግለጽ፣ የመሳሪያዉን ዋጋ መክፈል ከአለበት መሳሪያዉን በተረከበ ጊዜ በነበረዉ ዋጋ ተመን መሆኑን እንደሚገባ ገልጾ ተከራክሯል።
ከዚህ አንጻር ሲታይ የአሁን ተጠሪ ይህን መሳሪያ በተረከበበት ወቅት በ30/1/2007 ዓ.ም በሥራ ላይ የነበረዉ መመሪያ ቁጥር 44/2001 ሲሆን፣ በዚህ መመሪያ አንቀጽ 17 /2/ መሰረት የአንድ ክላሽ ዋጋ ብር 6,000 /ስድስት ሺህ/ እና የአንድ ጥይት ዋጋ ብር 10 /አስር/ መሆኑ ተደንግጓል። ነገር ግን የአማራ ብ/ክ/መ/ መስተዳድር ምክር ቤት መጋቢት 25 ቀን 2007 ዓ.ም ባካሄደዉ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ስብሰባ የመንግስት የጦር መሳሪያ ዋጋ ተመን በማሻሻል ባወጣዉ መመሪያ ቁጥር 11/4050 በ30/7/2007 ዓ.ም ተሻሽሎ በወጣዉ መሰረት የአንድ ክላሽ ዋጋ ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ/ እና የአንድ ጥይት ዋጋ ብር 100 እንዲሆን ተወስኗል። ይህ ከሆነ ከመጋቢት 25 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ የመንግስት የጦር መሳሪያ ዋጋ ተመን በተመለከተ ተፈጻሚነት ያለዉ መመሪያ መጋቢት 25 ቀን 2007 ዓ.ም ተሻሽሎ የወጣዉ መመሪያ እንጂ የቀድሞ መመሪያ ቁጥር 44/2001 ላሆን አይችልም። ይህ የተሻሻለ መመሪያ ከወጣ በኋላ የጦር መሳሪያ ዋጋ ተመን የተሻሻለ እና የተለወጠ በመሆኑ፣ በተጠሪ እጅ የነበረዉ ክላሽ ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ/ እና የአንድ ጥይት ዋጋ ብር 100 /መቶ/ ነዉ እንጂ በቀድሞ መመሪያ የተመለከተዉ ዋጋ ላሆን አይችልም። በተጠሪ እጅ የነበረዉ የክላሽ መሳሪያ ከመጋቢት 25 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ዋጋዉ የተለወጠ በመሆኑ ተጠሪዉ መሳሪያ በተረከብኩ ጊዜ በነበረዉ ተመን ልጠየቅ ይገባል በማለት በሥር ፍ/ቤት የቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት የለዉም።
ሲጠቃለል የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የአሁን ተጠሪ መሳሪያዉ ጠፍቷል ባለ ወቅት ሚያዚያ 20 ቀን 2007 ዓ.ም እና አመልካች ክስ ባቀረበዉ ጊዜ በሥራ ላይ ያለዉ መመሪያ በመሆኑ፣ ተፈጻሚነት እና አግባብነት ያለዉ መመሪያ ይኸዉ መመሪ ሆኖ ሳለ የቀድሞ መመሪያ ቁጥር 44/2001 መሰረት በማድረግ ተጠሪ የዚህ የክላሽ መሳሪያ ግምት ይክፈል በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.03-11989 የካቲት 16 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 /1/ መሰረት ተሽሯል።
የሰቆጣ ወረዳ ፍ/ቤት በመ.ቁ.0-05073 ሐምል 7 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና ይህን ዉሳኔ በማጽናት የዋግ ኽምራ ብሕረሰብ አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.01-02040 በ22/11/2007 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈጸመባቸዉ ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 /1/ መሰረት ጸንቷል።
የአሁን ተጠሪ መሳሪያዉ ጠፋብኝ ባለ ወቅት በሥራ ላይ ባለዉ የመንግስት የጦር መሳሪያ ዋጋ ተመን በተሻሻለዉ መመሪያ መሰረት የክላሽ ዋጋ ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ/ እና የአንድ ጥይት ዋጋ በብር 100 የ30 ጥይት 3,000 /ሶስት ሺህ/ በአጠቃላይ ብር 33,000 /ሰላሳ ሶስት ሺህ/ ብር ለአመልካች ይክፈል ብለናል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ ብለናል።
አመልካች በዚህ ችሎት የደረሰበት ወጪና ኪሳራ የራሱን ይቻል ብለናል።
ሩ/ለ
ታህሳስ 24 ቀን 2ዐ1ዐ ዓ.ም.
ዳኛች---- ተኽላት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራው ፀሐይ መንክር አመልካች----- ብዙአየሁ ሾኔ የቡና ተከል ልማት ኃ/የተ/የግ/ማህበር - ጠ/መኮንን በቀለ ተጠሪ------------ ቢ.ዲ.ኤፍ.ኤስ. ኢትዩጵያ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር- አቶ ንጉስ ሁነኛው ባለቤት ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዳይ የሁከት ይወገድልኝ ክስን መሰረት ያደረገ ሲሆን፣ክርክሩ የጀመረው በላሙ ኮሳ ወረዳ ፍ/ቤት ሆኖ ስር ከሣሽ የአሁን ተጠሪ ተከሣሽ ደግሞ አመልካች በመሆን ተከራክረው ተከሣሽ ሁከት እንዲያቆም የተሰጠው ፍርድ በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች በመፅናቱ ምክንያት የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው።
በስር ቀርቦ የነበረው ክስ እንደሚያመለክተው ከ2ዐዐዐ ዓ.ም.ጀምሮ የባለይዞታነት ማረጋገጫ ማስረጃ ያወጣሁበትን እና ልዩ ልዩ ተክሎችን ያለማሁበትን ይዞታዬን በ5ዐዐዐ ሄክታር ላይ የሚገኘውን ድንበሩ በክሱ ላይ የተገለፀው አዋሣኞች ያሉትን በምዕራብ በኩል ወደ ድንበሬ በመግባት መኖሪያ ቤቴን እና በ57 ሄክታር ላይ የሚገኘውን ቡና ግንቦት 2ዐዐ6 ዓ.ም. ድንበር አልፎ በመያዝ በምሥራቅ እና በደቡብ በኩል በማስፋፋት ይዞ የሚገኝ ስለሆነ ተከሣሽ ሁከት በመፍጠር ንብረቴን የያዘብኝ ስለሆነ ሁከት አቁሞ ይህንን ንብረቴን እንዲለቅልኝ እና የክሱን ወጪና ኪሣራ ጭምር እንዲከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት የአሁን ተጠሪ ክስ አቅርቧል።
ተከሣሽም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን ለክርክር መነሻ የሆነው መሬት ላይ ከሣሽ መብት የለውም፣ ምክንያቱም 57 ሄክታር መሬትን ጨምሮ 5ዐዐዐ ሄክታር መሬት በቀን 14/9/2ዐዐ6 ዓ.ም. በቁ DH/INV/J/883/06 ከኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በተፃፈ ደብዳቤ ከከሣሽ ላይ ተወስዶ ወደ መሬት ባንክ እንዲ ገባ ሆኗል ፣ ልላው ክሱ ከገጠር መሬት ጋር የተያያዘ በመሆኑ በፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት ቀደም ብሎ መሬቱ በሚገኝበት ቀበል መታየት ያለበት በመሆኑ በቀጥታ ለፍርድ ቤቱ መቅረቡን እቃወማለሁ ፣ ክስ የቀረበበት ይዞታ በየትኛው ቀበል እንደሚገኝም አልገለፀም በመሆኑም ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል የሚሉትን መቃሚያዎች ካቀረበ በኃላ የፍሬ ነገር መልሱን አቅርቧል። ይዘቱም የገፋሁት መሬት የለም፣ በአለው የመንግሥት መመሪያ መሰረት የኪራይ ውል ለ45 ዓመት ፈጽሜ በ12/6/2ዐዐ2 ዓ.ም. የተሰጠኝ ደብዳቤ በሕጋዊ መንገድ ከዞኑ ኢንቨስትመንት መስተዳድር የተሰጠኝ ስለመሆኑ ማስረጃ ያለኝ ስለሆነ ከሣሽ በመሬቱ ላይ መብት ስለልለው ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል ሲል አቅርቧል።
ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን በቃል ካከራከረ በኋላ የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃሚያ ውድቅ ማድረጉን፣ ፍሬ ጉዳዩን አስመልክቶም ግራ ቀኙን ካዳመጠ በኋላ የግራ ቀኙን ምስክሮች መስማቱን፣ በቀረበው ማስረጃም ከሣሽ ክርክር ከተነሳበት መሬት ውስጥ 57 ሄክታር መሬት እስከ ግንቦት ወር 2ዐዐ6 ዓ.ም.ይዞ እየተጠቀመበት የነበረ መሆኑን፣ ከ 2ዐዐ6 ዓ.ም. ግንቦት በኋላ ግን ተከሣሽ ይህንኑ መሬት ይዞ እየተጠቀመበት የሚገኝ መሆኑን ፍርድ ቤቱ መገንዘቡን፣ ተከሣሽ ግን ይዞታው የእኔ ነው ከማለት ውጭ ክርክር በተነሳበት መሬት ላይ ሁከት ስለመፍጠሩ እና ስላለመፍጠሩ የገለፀው ነገር አለመኖሩን፣ የተጠየቀው ዳኝነት የይዞታ ጥያቄ ሳይሆን የሁከት በመሆኑ ተከሣሽም ወደ ከሣሽ ይዞታ በመግባት አለቅም ማለቱ በምስክር የተረጋገጠ በመሆኑ ሁከት በመፍጠር በኃይል የያዘውን 57 ሄክታር የቡና መሬት እና የቆርቆሮ መኖሪያ ቤት ለከሣሽ ላለቅ ይገባል ሲል በመ/ቁ/ 12766 ታህሳስ 12 ቀን 2ዐዐ8 ዓ.ም. በዋለው ችሎት መወሰኑን የውሣኔው ግልባጭ ያመለክታል።
አመልካች ይግባኝ ብሎ ለጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም በመ/ቁ/ 34182 የካቲት 7 ቀን 2ዐዐ8 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ግራ ቀኙን አስቀርቦ እና ይግባኙን መርምሮ የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ የሚነቀፍ አይደለም በሚል አጽንቶታል። ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረበው የሰበር አቤቱታም አጣሪው ጉዳዩን ለሰበር ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙን ችሎቱ አስቀርቦና አቤቱታውን መርምሮ የስር ፍርድ ቤቶች ውሣኔ የተፈፀመበት መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት በመ/ቁ/ 24ዐ932 ጥቅምት ዐ7 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በማጽናት ወስኗል።
አመልካች በስር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለ በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ ሲል ጥቅምት 25 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም. የተፃፈ የሰበር አቤቱታ አቅርቧል።
አመልካች በአቤቱታው አጥብቆ ስህተት ናቸው በማለት የሚያነሳቸው ነጥቦች በአጭሩ፡የክልሉ ወረዳ ፍ/ቤት ጉዳዬን አከራክሮ ውሣኔ ለመስጠት የሥረ ነገር ሥልጣን የለውም፣ ምክንያቱም ጉዳዩን የመዳኘት ሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5/6/ መሰረት የተሰጣቸው የፍድራል ፍ/ቤቶች ናቸው በመሆኑም የበላይ ፍርድ ቤቶችም ይህን ስህተት ማረም ይጠበቅባቸው የነበረ በመሆኑ እንዲታረምልን፣ መደበኛ ፍርድ ቤቶች ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ተቀብለው ለማከራከር ሥልጣን የላቸውም፣ ምክንያቱም ጉዳዩ የኢንቨስትመንት መሬትን የተመለከተ በመሆኑ ያለአግባብ ተይዞብኛል የሚል ወገን በቅድሚያ መሬቱን ለፈቀደው ኢንቨስትመንት ቦርድ አቅርቦ ውሣኔ ሳያሰጥ በቀጥታ ለመደበኛ ፍርድ ቤት መቅረብ አይችልም። በመሆኑም አስተዳደራዊ ውሣኔ ያላገኘን ጉዳይ በቀጥታ የወረዳ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ ማከራከሩና ውሣኔ መስጠቱ ስህተት ነው ይባልልን፣ የጅማ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 43 መሰረት ወደ ክርክር እንዲገባ ጠይቀን መታለፉ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ላታረምልን ይገባል፣ አመልካች በተጠሪ ይዞታ ላይ ሁከት የፈጠረ ስለመሆኑ በአግባቡ አልተጣራም በሚል ሰፊ አቤቱታ አቅርቧል።
አቤቱታውን የመረመረው የሰበር አጣሪ ችሎት የቀረበውን አቤቱታ መርምሮ ክርክር የተነሳበት ይዞታ ለኢንቨስትመንት የተሰጠ ከመሆኑ አኳያ በቅድሚያ ለኢንቨስትመንት በቦርድ ቀርቦ እልባት ላያገኝ ይገባዋል በማለት የሰበር መ/ቁ. 4622ዐ ተጠቅሶ የቀረበው መቃወሚያ እና የጅማ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት በክርክሩ ጣልቃ እንዲገባ በአመልካች የቀረበው ጥያቄ በሥር ፍ/ቤቶች የመታለፉን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ለሰበር ይቅረብ በሚል በያዘው ጭብጥ መነሻነት መዝገቡ ላቀርብ ችሐል።
አቤቱታው እና የማስቀረቢያ ነጥቡ ለተጠሪ ደርሶት የመከላከያ መልሱን እንዲያቀርብ ከመጥሪያ ጋር የተላከለት በመሆኑ ጥር ዐ8 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም. የተፃፈ መልስ አቅርቧል።
ይዘቱም ከማስቀረቢያ ነጥቡ አኳያ በአጭሩ፡- አመልካች ጠቅሰው ያቀረቡት የሰበር ውሣኔ የላዝ አዋጅን መሰረት ያደረገ እንጂ የገጠር መሬትን የሚመለከት ባለመሆኑ አግባብ አይደለም፣ የተፈጠረ ሁከት እንዲወገድ የቀረበውን ክስ ለማየት ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት ብቻ ነው፣ ፍርድ ቤቱም ሁከት መፈጠር አለመፈጠሩን ጭብጥ በመያዝ አጣርቶ የሰጠው ውሣኔ በአግባቡ ነው፣ በዚህ ክርክር ሂደት ይዞታው በተጠሪ እጅ እንድት እንደገባ እንዲመረመርለት አመልካች ሲያቀርብ የነበረው መከራከሪያ ከሰበር መ/ቁ፤ 7ዐ8ዐ1 ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ መታለፉ በአግባቡ ነው፣ የሶስተኛ ወገንን ጣልቃ ገብነት አስመልክቶ ለቀረበው አቤቱታም የጅማ ዞን አስተዳደር በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባለት ጥያቄ አቅርበው ጉዳዩ በይግባኝ ደረጃ በጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቦ እና በመታየት ውድቅ አድርጎ ያለፈውን አመልካች ግን ጭራሽ ይሄ ጉዳይ እንዳልታየ አድርጎ ያቀረበው አቤቱታ ስህተት በመሆኑ ውድቅ ይደረግልን በሚል መልስ ከሰጠው በአጭሩ መዝግበናል። አመልካችም የቀድሞውን አቤቱታ በሚያጠናክር መልኩ የመልስ መልስ አቅርቦ ከመዝገብ ተያይዟል።
የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል እኛም የቀረበውን አቤቱታ መልስ እና የመልስ መልሱን ከስር ፍርድ ቤቶች ከሰጡት ውሣኔ እና ከጉዳዩ ጋር አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
እንደመረመርነውም በግራ ቀኙ መካከል እያከራከረ ያለው የኢንቨስትመንት መሬት መሆኑ ከላይ ተመልክተናል። የአሁን ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት አቅርቦት የነበረው ክስ ከላይ እንደተመለከትነው ይዞታን ገፍቶ በውስጡ ካለ የቆርቆሮ ቤት እና ተክሎች ጋር ይዞብኛል ሁከት ይወገድልኝ የሚል ሲሆን የስር ተከሣሽ /አመልካች / በፍሬ ጉዳይ ከመታየቱ በፊት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አለኝ በማለት በቅድሚያ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን በቀጥታ ተቀብሎ ለማከራከር ሥልጣን የለውም ጉዳዩ በገጠር መሬት ላይ የተነሳ ክርክር በመሆኑ በቅድሚያ መሬቱን ለፈቀደው አካል ቀርቦ መታየት ይገባዋል የሚል እና ልሎች መቃወሚያዎችን ጨምሮ ማቅረቡን ተመልክተናል።
አጣሪው ከያዘው ጭብጥ አኳያ ለፍርድ ቤቱ የቀረበውን ጉዳይ ስንመለከት አመልካች እና ተጠሪ ከመንግሥት በላዝ የኢንቨስትመንት መሬት በኪራይ የያዙ መሆኑን ነው።
የአሁን ተጠሪም በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ከያዝኩት የኢንቨስትመንት መሬት ላይ ተከሣሽ ገፍቶ 57 ሄክታር መሬት ይዞብኛል እንዲሁም በቦታው ላይ ያለ ቆርቆሮ በቆርቆሮ የተሰራ ቤት እና ተክሎችንም የያዘብኝ ስለሆነ ሁከት ፈጥሮብኛል የሚል ሲሆን ስር ተከሣሽ በበኩሉ ገፍቼ የያዝኩት መሬት የለም ከመንግሥት በህግ አግባብ የተሰጠኝ ነው በማለት በፍሬ ነገር መልሱ አቅርቧል። ወደ ፍሬ ነገር ክርክራቸው ከመገባቱ በፊት በቅድሚያ መታየት ያለበት የቀረበው ጉዳይ የሚገዛበትን ህግ መመልከት ተገቢ ሲሆን ክርክር ያስነሳው መሬት የሚገኘው በኦሮሚያ ክልል በመሆኑ የሚገዙበት ህግ ላሆን የሚችለው የኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 138/2ዐዐዐ ነው።
በዚህ አዋጅ ላይ ሁለት ኢንቨስተሮች / ግለሰቦች/ የይገባኛል ክርክር በሚያነሱበት ጊዜ ምን እንደሚሆን የደነገገው ነገር የለም። በፍድራል የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 769/2ዐዐ4 አንቀጽ 32 ማንኛውም ባለሀብት ከኢንቨስትመንቱ ጋር በተያያዘ ቅሬታ ካለው አግባብ ላለው የኢንቨስትመንት አካል አቤቱታ የማቅረብ መብት ይኖረዋል ይላል ይህ ማለት ግን ሁለት ኢንቨስተሮች የይገባኛል ክርክር በሚያነሱበት ጊዜ ጉዳያቸው የት እንደሚዳኝ የሚገልጽ ድንጋጌ አላስቀመጠም። በመሆኑም የአመልካች እና የተጠሪ ጉዳይ በተጠቀሱት ሁለት አዋጆች ላይ አለመግባባት ሲፈጠር ማን እንደሚዳኛቸው ያልተቀመጠ በመሆኑ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት መሄዱ የግድ ነው።
በልላ በኩል ደግሞ የኢንቨስትመንት ፈቃድ በክልልም በፍድራልም የሚሰጥ ሲሆን ክርክር ባስነሳው መሬት ላይ ግራ ቀኙ ያወጡት የኢንቨስትመንት ፈቃድ የፍድራል ከሆነ ጉዳያቸው ላታይ የሚችለው በፍድራል ፍርድ ቤቶች ሲሆን፣ ፈቃድ ያገኙት ግን በክልሉ ኢንቨስትመንት ቢሮ ከሆነ ደግሞ በክልል ፍርድ ቤቶች የሚታይ ይሆናል።
እንዲሁም ከሁለቱ አንዱ ወገን የፍድራል ተመዝጋቢ ከሆነ ደግሞ ጉዳዩ ላታይ የሚገባው በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5/6 መሰረት በፍድራል ፍርድ ቤቶች ይሆናል።
አመልካች እና ተጠሪ ኃላፊነቱ የተ/የግል ማህበር መሆናቸውን አሰያየማቸው የሚገልጽ ሲሆን የንግድ ማህበር እስከሆኑ ድረስ ተመዝጋቢነታቸው በፍድራል መንግስት መሆኑ ግልጽ ነው። በመሆኑም የተነሳው ክርክር በሁለት የህግ ሰውነት ባላቸው አካላት መሃከል በመሆኑ በፍድራልም ሆነ በክልሉ የኢንቨስትመንት አዋጅ ውስጥ በእንደዚህ አይነት አካላት መሃከል ግጭት /አለመግባባት /ሲፈጠር አለመግባባቱ የሚፈታበትን መንገድ በግልጽ ያልደነገገ በመሆኑ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት መሄዱ የግድ በመሆኑ በስር ፍርድ ቤት የቀረበው ክስ መቅረብ የነበረበት በፍድራል ፍርድ ቤት መሆኑ የግድ ሆኖ በህገ መንግሥቱ ለክልል ፍርድ ቤቶች የፍድራል ጉዳይን እንዲያዩ በተሰጠው ውክልና መሰረት ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክሱ መቅረብና መስተናገድ ሲገባው የክልሉ ወረዳ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን ሳይኖረው ተቀብሎ መወሰኑ እና የበላይ ፍርድ ቤቶችም የስር ፍርድ ቤት የፈፀመውን ስህተት ሳያርሙ ማለፋቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስለተገኘ ላታረም የሚገባው ነው ብለናል። በመሆኑም ተከታዩ ውሣኔ ተሰጥቷል።
ውሣኔ
የላሙ ኮሳ ወረዳ ፍ/ቤት በ18/4/2ዐዐ8 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የሰጠው ውሣኔ፣ የጅማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በ7/6/2ዐዐ8 ዓ.ም. በመ/ቁ/ 34182 ላይ የሰጠው ፍርድ እና የኦሮሚያ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/ 24ዐ932 ጥቅምት ዐ7 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ በመገኘቱ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ በህግ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክስ አቅርበው ውሣኔ ከማሰጠት የዚህ ፍርድ መሰጠት አያግዳቸውም።
በዚህ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ ላወጡት ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻሉ ብለናል።
የውሣኔው ትክክል ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይድረስ።
መዝገቡ ውሣኔ ስላገኘ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.