አንድ ቀድሞ በነበረ መመሪያ ዋጋ የወጣለትን ንብረት የተረከበ ወገን የንብረቱን መጥፋት ተከትሎ ክስ ሲመሰረት የንብረቱ ዋጋ በልላ አዲስ መመርያ የተሻሻለበት ሁኔታ መኖሩ ከተረጋገጠ ንብረቱ የጠፋበት ወገን የሰቆጣ ወረዳ ሚላሻ ጽ/ቤት እና ቄስ ሙሉጌታ ተፈራ XLV የሚሆነው አዲስ በወጣው መመርያ መሰረት በወጣው የዋጋ ተመን አግባብ ስለመሆኑ፣
No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 24 ቀን 2010 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተኽላት ይመስል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራው ፀሃይ መንክር አመልካች፡
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በመ/ ጥቅምት 21 ቀን 2009 ዓ.ም ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃወም ሲሆን ክርክሩ የጀመረው በጉድሩ ወረዳ ፍርድ ቤት የአሁን 1ኛ ተጠሪ በ2ኛ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ነው። የአሁን አመልካች በጣልቃ ገብነት ተከራክረዋል።
1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ይዘት፡- የ2ኛ ተጠሪ ባለቤት አቶ ታሪኩ ፊጤ 2ኛ ተጠሪን ዋስ አድርገው በ19/05/2002 ዓ.ም በተፃፈ ውል ብር 10,000.00 ተበድረው ገንዘቡን እስከ 30/05/2004 ዓ.ም ከፍሎ የማይጨርስ ከሆነ ብር 30,000.00 የሚያወጣውን በኮምቦልቻ ከተማ 01 ቀበል የሚገኝ ቤታቸውን እንድወስድ ተስማምተን ገንዘቡን በጊዜው ሳይመልሱልኝ በ2006 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፤ ስለሆነም 2ኛ ተጠሪ የቤቱን ስመሃብትነት ወደ ስሜ እንዲያዛውሩ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። 2ኛ ተጠሪ መልስ እንዲሰጡ ቢታዘዝም ለክሱ የሰጡት መልስ የለም።
በልላ በኩል የአሁን አመልካች ክርክር የተነሳበትን ቤት በ01/10/06 በተደረገ ውል በብር 30,000.00 2ኛ ተጠሪና ልጃቸው ወ/ሮ ጌጤ ጀቤሳ (በሥር 2ኛ ጣልቃ ገብ) ከሸጡልኝ በኋላ በጋራ ለኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ማመልከቻ አስገብተን እያለ በመካከላችን ያለው ውል ሳይፈርስ ከከሳሽ ጋር የሃሰት ውል አዘጋጅተው በዚህ ቤት ላይ እየተከራከሩ ስለሆነ ወደክርክሩ ገብቼ የባለንብረትነት መብቴን እንዳስከብር በማለት ጠይቀዋል።
ጣልቃ ገብ ወደክርክሩ እንዲገቡ ተፈቅዶ 2ኛ ተጠሪ ለጣልቃ ገቡ አቤቱታ በሰጡት መልስ በመካከላችን ውል የለም፤ ቤቱን አልሸጥኩም፤ ገንዘብም አልወሰድኩም በማለት ተከራክረዋል።
ጉዳዩን በቅድሚያ የተመለከተው የወረዳ ፍርድ ቤት የምስክሮችን ቃል እና የሰነድ ማስረጃዎችን ይዘት ከመረመረ እና የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር አጣርቶ እንዲያቀርብ ካደረገ በኋላ በሰጠው ውሳኔ ከሳሽ ያቀረበው የውል ሰነድ የግዥና ሽያጭ ውል መደረጉን የሚገልፅ አይደለም፤ የከሳሽ ምስክር ቤቱን በዕዳ ለዋስትና አስይዞታል ቢሉም በእዳ ለዋስትና መያዙን የሚያሳይ በከተማ አስተዳደሩ የተመዘገበ ነገር የለም፤ የማይንቀሳቀስ ንብረት በዕዳ ሲያዝ በጽሁፍ ሆኖ በማይንቀሳቀሰ ንብረት መዝገብ ላይ ካልተመዘገበ ውጤት አይኖረውም፤ በመሆኑም ከሳሽ ያቀረበው የዳኝነት ጥያቄ ውድቅ ላሆን ይገባል።
በልላ በኩል ተከሳሽ ከልጇ (በሥር 2ኛ ጣልቃ ገብ ሆነው የተከራከሩ ወ/ሮ ጌጤ ጀቤሳ) ጋር በመሆን ቤቱን ለአመልካች ሸጠው ስሙ እንዲዞር በከተማው አስተዳደር አስገብተው ከፍርድ ቤት የዕግድ ትዕዛዝ ስለተሰጠ ብቻ ስሙ ሳይዞር መቅረቱ ስለተረጋገጠ ተከሳሽ ቤቱን ለጣልቃ ገብ (የአሁን አመልካች) ላለቁ ይገባል በማለት ወስኗል።
ይህን ውሳኔ በመቃወም ተጠሪዎች ቅሬታቸውን በይግባኝ ለሆሮ ጉድሩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ክርክሩን ከሰማ በኋላ በሰጠው ውሳኔ የብድሩ መክፈያ ጊዜ ጥር 30/2004 ዓ.ም ካለፈ በኋላ የብድር ውል መሆኑ ቀርቶ ወደ ሽያጭ ውል የሚለወጥ በመሆኑ፤ 2ኛ ተጠሪ በ1ኛ ተጠሪ ለቀረበው ክስ መልስ ባይሰጡም ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ባቀረቡት ይግባኝ ቤቱን በህይወት ከልለው ባለቤታቸው ጋር በመሆን አስይዘው ብር 10,000.00 በመበደር እና በተባለው ቀን ካልመለሱ ቤቱን ለመልቀቅ መስማማታቸውን ገልፀዋል፤ የ1ኛ ተጠሪ ጥያቄም ቤቱ ለዕዳው ይዋል የሚል ነው፤ በልላ በኩል 2ኛ ተጠሪ ቤቱን ለአመልካች አልሸጥኩለትም ብለው እየተከራከሩ የሥር ፍርድ ቤት መያዣው አልተመዘገበም በሚል የከሳሽን (1ኛ ተጠሪን) ጥያቄ ውድቅ አድርጎ ቤቱ ለጣልቃ ገብ (ለአመልካች) እንዲለቀቅ መወሰኑ የህግ መሰረት የለውም በማለት ውሳኔውን ሽሮ ቤቱን 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ እንድትለቅ በማለት ወስኗል።
አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ችሎቶች ቅሬታቸውን ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የሰበር አቤቱታው ለዚህ ፍርድ ቤት የቀረበው ይህን በመቃወም ነው።
አመልካች ያቀረቡት የሰበር ማመልከቻ ተመርምሮ ለክርክር ምክንያት የሆነው በ1ኛ ተጠሪ ባለቤት ስም የሚታወቀውን ቤት 2ኛ ተጠሪ ለአመልካች በሽያጭ አስተላልፈው በገዥ (በአሁን አመልካች) ስም እንዲዛወር ለኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ማመልከታቸውን ስለማስገባታቸው አስተዳደሩ ለሥር ፍርድ ቤት ምላሽ የሰጠ መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የአሁን 2ኛ ተጠሪ ቤቱን ለአመልካች አልሸጥኩም ብላለች፤ ሟች ባለቤቴ ቤቱን ለ1ኛ ተጠሪ አስይዞ ብር 10,000.00 ተበድሮ ለመመለስ ባለመቻሉ ተጨማሪ ብር 20,000.00 ከ1ኛ ተጠሪ ተቀብለናል ፤ ቤቱ ለዕዳችን እንዲውል ለ1ኛ ተጠሪ ሰጥተናል በሚል ተከራክረዋል በማለት የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ የመሻሩን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ እና ተጠሪዎች መልስ እንዲሰጡበት ተደርጓል። በዚህ መሰረት ግራ ቀኙ የሥር ክርክራቸውን በማጠናከር በፅሁፍ ተለዋውጠዋል።
ከፍሲል ባጭሩ የገለጽነው የጉዳዩን አመጣጥ ሲሆን ተከራካሪዎቹ ወገኖች ካቀረቡት ክርክር እና የሥር ፍርድ ቤቶች ካረጋገጧቸው ፍሬ ነገሮች አንፃር በህጉ አግባብ የተቋቋመና መብትና ግድታ የሚፈጥር ሽያጭም ሆነ የመያዣ ውል መኖር አለመኖሩን እንዲሁም የሥር ፍርድ ቤቶች በየደረጃው ያሳለፉት ውሳኔ ህጉን መሰረት ያደረገ መሆን አለመሆኑን መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ባቀረቡት የጣልቃገብ አቤቱታ ክርክር የተነሳበትን ቤት በ01/10/06 በተደረገ ውል በብር 30,000.00 ከ2ኛ ተጠሪ እና ከልጃቸው ገዝተው ለኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ማመልከቻ አስገብተው እንደነበር በመግለጽ የሚከራከሩ ሲሆን 2ኛ ተጠሪ በበኩላቸው በመካከላችን ውል የለም፤ ቤቱን አልሸጥኩም፤ ገንዘብም አልወሰድኩም በማለት ተከራክረዋል። ተጠሪ ሽያጩን የካዱ በመሆኑ አመልካች እንደክርክራቸው የሽያጭ ውል መደረጉን ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል።
በመሰረቱ የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭ ውል ማስተላለፍ ጥንቃቄ እና ጥበቃ የሚሻ በመሆኑ የማይንቀሳቀስ ንብረት የሽያጭ ውል የሚደረግበት ስርዓት (ፎርም) የተለየና ጥብቅ መስፈርት የሚከተል መሆኑን ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1723 ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል።
በዚሁ ድንጋጌ መሰረት የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውሉ ሁለት መስፈርቶችን ማሟላት የሚጠበቅበት ሲሆን የመጀመሪያው ውሉ በጽሁፍ መሆኑ ሲሆን ሁለተኛው ውሉ በአዋዋይ ወይም በፍርድ ቤት መዝገብ ፊት መከናወን የሚኖርበት መሆኑ ነው።
ህጉ ይህ እንዲሆን የሚጠይቀው በተዋዋዮች መካከል በህግ ፊት የሚፀና ውል እንዲኖር ለማድረግ ነው። በዚህ ረገድ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ እና ልሎችም በርካታ መዛግብት አስገዳጅ ትርጉም ሰጥቷል።
በተያዘው ጉዳይ ከፍሲል እንደተመለከተው አመልካች ክርክር የተነሳበትን ቤት በውል የገዙ መሆኑን በማንሳት የሚከራከሩ ሲሆን 2ኛ ተጠሪ በበኩላቸው የሽያጭ ውል የለም በማለት ተከራክረዋል። አመልካች በግራ ቀኙ መካከል በህጉ መስፈርቶች መሰረት የሽያጭ ውል መደረጉን የሚያስረዳ ማስረጃ ማቅረባቸው አልተረጋገጠም። በልላ በኩል ተጠሪ በመንደር የተደረገ ስምምነት በመያዝ ከአመልካችና ከልጃቸው (የሥር 2ኛ ጣልቃ ገብ) ጋር በመሆን በከተማው አስተዳደር ማመልከቻ አስገብተው ከፍርድ ቤት የዕግድ ትዕዛዝ ስለተሰጠ ስሙ ሳይዞር ቀርቷል መባሉ በህጉ አግባብ የተቋቋመ ውል አለ እንዲባል በህጉ የተቀመጠውን መስፈርት የሚተካ አይሆንም። ስለሆነም በህጉ አግባብ የተቋቋመ የሽያጭ ውል በልለበት የስር ፍርድ ቤት በአመልካች እና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የሽያጭ ውል አለ በማለት ተጠሪ ለአመልካች ቤቱን ላለቁ ይገባል ሲል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል።
በልላ በኩል የሥር ከሳሽ (የአሁን 1ኛ ተጠሪ) ባቀረቡት ክስ የ2ኛ ተጠሪ ባለቤት አቶ ታሪኩ ፊጤ በ19/05/2002 ዓ.ም በተፃፈ የብድር ውል ብር 10,000.00 ተበድሮ ገንዘቡን እስከ 30/05/2004 ዓ.ም ከፍሎ የማይጨርስ ከሆነ ብር 30,000.00 የሚያወጣውን የተበዳሪ ቤት እንድወስድ ተስማምተናል፤ ገንዘቡን በጊዜው ሳይመልሱልኝ በ2006 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለዩ 2ኛ ተጠሪ መያዣ የተደረገውን የቤቱን ስመሃብት ወደ ስሜ እንዲያዛውሩ ይወሰንልኝ የሚል ይዘት ያለው ክስ አቅርበዋል።
የቀረበው የዳኝነት ጥያቄ 2ኛ ተጠሪ ስመሃብት እንዲያዛውሩ በፍርድ እንዲወሰን ቢሆንም ሥም የማዛወር ተግባር የአስተዳደር ሥራ በመሆኑ ተጠሪ ስመሃብቱን ወደ ስሜ እንዲያዛዉሩ ይወሰንልኝ በሚል ያቀረቡት አቤቱታ የክስ ምክንያት አለው ላባል የሚችል ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም። የ1ኛ ተጠሪ ክስ በመያዣ ውሉ መሰረት የቤቱን ስመሃብት አስተዳደሩ እንዲያዛውርላቸው 2ኛ ተጠሪ ተገቢውን ይፈፅሙልኝ በሚል የቀረበ ከሆነም 2ኛ ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት ለክሱ በቀጥታ የሰጡት መልስ ባለመኖሩና ልጃቸውም የመያዣውን ውል ሳይሆን የሽያጩን ውል በማመን ይከራከሩ ስለነበር በቅድሚያ በህጉ ፊት የሚፀና ውል መኖር አለመኖሩን መመርመር አስፈላጊ ይሆናል።
የማይንቀሣቀስ ንብረት መያዣ በማናቸውም አይነት ሰነድ ላይ የተመሰረተ ቢሆን ከተፃፈበት ቀን አንስቶ የማይንቀሳቀሰው ንብረት በሚገኝበት አገር ባለው በማይንቀሳቀስ ርስት መዝገብ ካልተፃፈ በቀር ማንኛውንም አይነት ውጤት እንደማያስገኝ የፍታብሕር ህግ ቁጥር 3052 ይደነግጋል። ከዚህም ልላ በፍ/ብ/ህ/ቁ 3060 እንደተደነገገው ዕዳው እንዲከፈል በተወሰነበት ጊዜ ሳይከፈል የቀረ እንደሆነ ገንዘብ ጠያቂው የመያዣ መብት ያገኘበትን የማይንቀሳቀስ ንብረት ይወስዳል የሚል ስምምነት ሁሉ ተቀባይነት እንደልለው ተመልክቷል። 1ኛ ተጠሪ ለሰጡት ብድር ቤቱን የፍታብሕር ህግ ቁጥር 3052 በሚደነግገው አግባብ መያዣ ስለማድረጋቸው የቀረበ ክርክርም ሆነ ማስረጃ የለም። ስለሆነም በህጉ አግባብ የተቋቋመ የመያዣ ውል አለ የሚባልበት ምክንያት አላገኘንም። በልላም በኩል የከፍተኛው ፍርድ ቤት 2ኛ ተጠሪ ለክሱ መልስ ባይሰጡም የብድር ዕዳው መኖሩን እና ቤቱም መያዣ መደረጉን በመግለፅ የይግባኝ ቅሬታ አቅርበው እንደነበር በውሳኔው አመላክቶ ቤቱን 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ እንዲለቁ በማለት ውሳኔ ቢሰጥም ውሳኔው በፍ/ብ/ህ/ቁ 3060 በግልፅ የተደነገገውን መሰረት ያደረገ ሆኖ አላገኘነውም። ስለሆነም ቤቱ ለ1ኛ ተጠሪ እንዲለቀቅ የተሰጠው ውሳኔ ህጉን የተከተለ ባለመሆኑ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው።
በአጠቃላይ የስር ፍርድ ቤት በአመልካች እና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የሽያጭ ውል አለ በማለት ተጠሪ ለአመልካች ቤቱን ላለቁ ይገባል ሲል የሰጠው ውሳኔ፤ እንዲሁም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የስም ይዛወርልኝ ጥያቄን አላግባብ ተቀብሎ በህጉ ተቀባይነት የልለውን ስምምነት መሰረት በማድረግ ውሳኔ ማሳለፉ እና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚና ሰበር ችሎቶች ይህን ሳያርሙ ማለፋቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
ውሣኔ
የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ08/07/2007 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ በ14/08/2007 ዓ.ም ያሳለፈው ትዕዛዝ እና የክልሉ ሰበር ችሎት በመ/ በ21/02/2009 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ይህ ውሳኔ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ከፈልን የሚሉትን ገንዘብ ለማስመለስ የሚያቀርቡት ክስ ቢኖር የሚከለክል አይሆንም ብለናል።
በዘህ ፍርድ ቤት ስለተደረገው ክርክር ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
ሰ/አ የሰበር መ/ቁ/ 136262 መስከረም 24 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች ፤ ብርሃኑ አመነዉ በዕዉቀት በላይ እንዳሻዉ አዳነ ሃይሉ ነጋሽ እትመት አሰፋ አመልካች ፤ የቤንሻንጉል ጉ/ክልል ዓቃቤ ህግ ተጠሪ ፤ መሀሪ ታደሰ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ፍርድ።
በዚህ መዝገብ የቀረበዉ ጉዳይ የወንጀል ክርክር የሚመለከት ነዉ ። አመልካች ተጠሪ ላይ የመሰረተዉ ክስ ይዘት የወ/ህግአንቀጽ 631/1/ለ ላይ የተደነገገዉን በመተላለፍ በ21/06/08 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ላይ እድሜዉ 8 ዓመት ከሆነዉ ግል ተበዳይ እያሱ ቦጋለ የተባለዉን ህጻን ልጅ ሰዉነታችንን እንታጠብ በሚል ሰበብ አታሎ ወደ ወንዝ ወስዶ የግብረሰዶም ፈጽሟል የሚል ሲሆን ተጠሪ ክዶ በመከሯከሩ ጉዳዩን በመጀመሪያ ዳኝነት የተመለከተዉ የፓዌ ወረዳ ፍ/ቤት በዓቃቤ ህግ ማስረጃ የተመሰከረና ተጠሪ በመከላከያ ማስተባበል አለመቻሉን አረጋግጦ በተከሰሰበት አንቀጽ የጥፋተኛነት ዉሳኔ ሰጥቶ ቅጣትን በተመለከተ የተጠሪ እድሜ 15 ዓመት መሆኑን በልላ በኩል የግል ተበዳይ እድሜ ከ13 ዓመት በታች ሆኖ ድርጊቱ የተፈጸመዉ በጫዋታ ዉስጥ መሆኑን ምክንያት በማድረግ በ15 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል ።
ተጠሪ በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝቶ ለመተከል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ፍ/ቤቱ ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ ተጠሪ ያስመዘገበዉ እድሜ 13 ሲሆን ፓዌ ሆስፒታል የተጠሪ እድሜ ከ14-16 መካከል የሚገመት መሆኑን በመግለጹ ላወሰድ የሚገባዉ እድሜ 14 ዓመት እንደሆነ እና ቅጣቱም ሲወሰን ስለህጻናት መብት ደህንነት በኢ.ፍ.ዲ.ሪ.ህገ መንግስትና በወ/ህጉ አንቀጽ 157 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች የተመለከተዉን መሰረት በማድረግ የተጠሪ እድሜ ከ9-15 እድሜ ክልል ዉስጥ ከመሆኑ አኳያ ላፈጸም የሚገባዉ የጥንቃቄ እርምጃ ብቻ ነዉ በማለት ተጠሪ እናቱ ዘንድ ሆኖ በፖላስ በኩል ክትትል እንዲደረግበት በወ/ህ/ አንቀጽ 159/2/ መሰረት ትዕዛዝ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝቶ ለክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት እና ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም ተቀባይነት አላገኘም ። ለዚህ ሰበር ችሎት አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ላይ ሲሆን የሰበር አቤቱታዉ ተመርምሮ ከፍተኛዉ ፍ/ቤት ተጠሪ ላይ የተላለፈዉን የጥፋተኛነት ዉሳኔ ተቀብሎ ቅጣትን በተመለከተ ለእናቱ በአደራ እንዲሰጥ የመወሰኑን አግባብነት በተመለከተ ከወ/ህ/ አንቀጽ 159 /2/ አንጻር ለመመርመር እንዲቻል ተጠሪ መልስ እንዲሰጥ ተደርጓል ።ተጠሪን በመወከል የመተከል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ተከላካይ ጠበቃ የሰጠዉ መልስ ባጭሩ በወ/ህጉ አንቀጽ 168/2/ መሰረት የቅጣቱ ጣሪያ 10 ዓመት ላይ እንዲወሰን ዓቃቤ ህግ የጠየቀዉ ተገቢ መሆኑን በልላ በኩል ተጠሪ አካለ መጠን ያልደረሰ አጥፊ በመሆኑና በአካባቢዉ የፀባይ ማረሚያ ባለመኖሩ ፀባዩን በቅርብ ለመከታተል ለእናቱ እንዲሰጥ መደረጉ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት ተከራክሯል ።
የጉዳዩ አመጣጥና የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ ባጭሩ የተገለጸ ሲሆን እኛም አቤቱታዉ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል የተያዘዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ አግባብነት ካለዉ ህግ ጋር በማገናዘብ መርምረናል ። መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘብነዉ ተጠሪ ጥፋተኛ የተባለዉ የወ/ህግ አንቀጽ 631/1/ለ ተላልፎ መገኘቱ ተረጋግጦ ነዉ ።በስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ ላይ ልዩነት የተፈጠረዉና እዚህ ሰበር ችሎት ድረስ ያከራከረዉ የቅጣት ዉሳኔ በተመለከተ ነዉ ።ተጠሪ ጥፋተኛ የተባለበት ድንጋጌ የሚያስቀጣዉ ከ15-25 ኣመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ነዉ ። ተጠሪ የወንጀል ድርጊቱን ሲፈጽም እድሜዉ 14 ኣመት ስለመሆኑ ማስረጃ የመመርመርና የማጣራት ስልጣን በህግ የተሰጠዉ የስር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት አረጋግጧል ። አቃቤ ህግ የተጠሪ እድሜ ከዚህ በላይ ስለመሆኑ አላረጋገጠም እነዚህን በስር ፍ/ቤቶች የተረጋገጡትን ፍሬነገሮች መሰረት በማድረግ ጉዳዩን መርምረናል።
ከላይ እንደተመለከተዉ ጉዳዩ ለሰበር የቀረበዉ ከወ/ህ/አንቀጽ 159/2/ አንጻር ለመመርመር ነዉ ። የዚህን ድንጋጌ ይዘት ከመመርመራችን በፊት አጠቃላይ ስለወጣት ጥፋተኞች በወ/ህጉ የተመለከተዉን መሰረታዊ መርህ ማየት ተገቢ ነዉ ።የወ/ህጉ አንቀጽ 52 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች እንደተመለከተዉ ህጻናትና ለአካለ መጠን ያልደረሱ ወጣት ወንጀል አድራጊዎች የወንጀል ሃላፊነትና የቅጣት ሁኔታ ለይቶ በጠቅላላዉ ክፍል አስቀምጧል ። ይኸዉም እድሜያቸዉ ዘጠኝ ዓመት ያልሞላቸዉ ህጻናት በወንጀል ድርጊት በሃላፊነት እንደማይጠየቁ ፤እድሜያቸዉ ከ9-15 ዓመት የሆናቸዉ ወጣት አጥፊዎች ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኙም ቅጣትና የጥንቃቄ እርምጃዎች እንደሚወሰዱባቸዉ ፤እድሜያቸዉ ከ15-18 ዓመት የሆኑት ወጣት አጥፊዎች የወንጀል ሃላፊነት እና መደበኛ ቅጣት እንደሚወሰንባቸዉ ነገር ግን የቅጣቱ መጠንና አተገባበሩ ላይ ከአዋቂ ሰዉ ልዩነት ያለዉ መሆኑን እንገነዘባለን ። ስለሆነም በወጣት አጥፊዎች ላይ የሚወሰነዉ ቅጣትና የጥንቃቄ እርምጃዎች በእነዚህ ድንጋጌዎች የተመለከተዉን መርህ የተከተለ እንዲሆን ህጉ ያስገድዳል ።
በተያዘዉ ጉዳይ ተጠሪ ድርጊቱን ሲፈጽም እድሜዉ 14 ኣመት መሆኑ በስር ፍ/ቤት የተረጋገጠ በመሆኑ ቅጣትን አስመልክቶ ተፈጻሚነት ያለዉ የወ/ህጉ አንቀጽ 53 መርህ እና ይህንኑ ተከትሎ በአንቀጽ 157-168 የተመለከተዉ ዝርዝር ሁኔታዎች ናቸዉ ።ከዚህ አንጻር የክልሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪ ላይ የተወሰነዉን የጥፋተኝነትና 15 ኣመት ጽኑ እስራት ቅጣት አጽንቶ አፈጻጸም በተመለከተ በወ/ህጉ አንቀጽ 159/2/ መሰርት በእናቱ ዘንድ ተገቢ ቁጥጥር እንዲደረግበት ትዕዛዝ መስጠቱ መነሻ ምክንያቱ በክልሉ ዉስጥ የወጣት ጥፋተኞች ፀባይ ማረሚያ ተቋም ባለመኖሩ ስለመሆኑ ተረጋግጧል ። በእኛም በኩል እንደተመለከትነዉ እድሜዉ ከ9-15 ኣመት የሆነ ወጣት ከባድ ወንጀል ፈጽሞ ቢገኝና የጥንቃቄ እርጃዎች ቢወሰንበት ይህ ላፈጸም የሚገባዉ በጠባይ ማረሚያ ተቋም መሆን እንደሚገባ የወ/ህ/አንቀጽ 168/1/ሀ ያስገነዝባል ። ከዚህ ባሻገር በተለየ ሁኔታ ወደ እስር ቤት የሚላከዉ ጥፋተኛዉ አደገኛና ሰላምን የሚያዉክ መሆኑ ሲረጋገጥ እንደሆነ ከአንቀጽ 168/1/ለ ይዘት መረዳት ይቻላል ።
ከዚህ አግባብ ተጠሪ የፈጸመዉ ድርጊት ከባድ ወንጀል ቢሆንም አደገኛና ሰላምን የሚያዉክ መሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ተጠሪ ለቤተሰብ ላሰጥ አይገባም በማለት ዓቃቤ ህግ ያቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት ያለዉ አይደለም ። በተመሳሳይ ሁኔታ ወጣት ጥፋተኛ ላይ የጥንቃቄ እርምጃዎች አፈጻጸም በተቻለ መጠን አጥፊዉን በማረም መልካም ዉጤት ላያስገኝ በሚያስችል አግባብ ላፈጸም እንደሚገባ ይህ ሰበር ችሎት በሰበር መ/ቁ/120332 ላይ ከሰጠዉ ፍርድ መገንዘብ ይቻላል ስለሆነም በክልሉ ዉስጥ ለወጣት ጥፋተኞች የሚያገለግል ጠባይ ማረሚያ ተቋም በልለበት ሁኔታ ፤ተጠሪ አደገኛ መሆኑም ባልተረጋገጠበትና በወላጅ እናቱ ቁጥጥር ስር ሆኖ የጠባዩ ሁኔታ ክትትል ቢደረግበት የተሻለ ዉጤት የማይመጣ መሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የስር ፍ/ቤት የሰጠዉ ትዕዛዝ የወ/ህጉ ስለወጣት ጥፋተኞች የደነገገዉን የጥንቃቄ እርምጃዎች ያገናዘበ ዉሳኔ ነዉ ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚያሰኝ ሆኖ አላገኘንም ።
ከዚህ ባሻገር ዓቃቤ ህግም ሆነ የተጠሪ ተከላካይ ጠበቃ ተጠሪ ላይ የተወሰነዉ ቅጣት በወ/ህጉ አንቀጽ 168/2/ መሰረት እንዲታረም ያቀረቡትን ጥያቄ አግባብነት ተመልክተናል በዚህ ድንጋጌ እንደተመለከተዉ ወጣት ጥፋተኛ የፈጸመዉ ወንጀል ከባድነትና ጥፋቱንም በፈጸመበት ጊዜ የነበረዉን የእድሜ ሁኔታ መሰረት በማድረግ ታስሮ የሚቆይበት ጊዜ ልክ ፍርድ ቤቱ እንደሚወስንና ጊዜዉም ከ1-10 ዓመት ላደርስ እንደሚችል ይደነግጋል ። በተያዘዉ ጉዳይ ተጠሪ ጥፋተኛ የተባለበት አንቀጽ 631/1/ለ የሚያስቀጣዉ ከ15-25 ዓመት ጽኑ እስራት በመሆኑ ወንጀሉ ከባድ ሲሆን ተጠሪ ወንጀሉን ሲፈጽም እድሜዉ 14 ኣመት መሆኑና ድርጊቱም የተፈጸመዉ በጫዋታ መካከል መሆኑ በስር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ፍሬነገር ነዉ ። የእስር ጊዜዉ ይህንን ፍሬነገርና ህጉን መሰረት አድርጎ መወሰን ሲገባ የስር ፍ/ቤቶች ተጠሪ ጥፋተኛ የተባለበትን ድንጋጌ ይዘት ብቻ መሰረት በማድረግ የ15 ኣመት እስራት መወሰናቸዉ ስህተት ስለሆነ ላታረም ይገባል ብለናል በዚሁ አግባብ ተጠሪ ላይ በስር ፍ/ ቤት የተወሰነዉ የ15 ዓመት እስራት ቅጣት በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁ/195/2/ለ/2 መሰረት በማሻሻል በ2 ዓመት እስር እንዲቀጣ ወስነናል ፡፤የእስራት አፈጻጸሙን በተመለከተ የመተከል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠዉ ትዕዛዝ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ ህግ ስህተት ባለመገኘቱ ጸንቷል ።
1ኛ.በፓዌ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ/09364 በ06/11/08 ዓ.ም በተጠሪ ላይ የተሰጠዉና እስከ ክልሉ ሰበር ችሎት የጸናዉ የጥፋተኛነት ዉሳኔ ጸንቷል ።
2ኛ.እስር ቅጣቱ በወ/መ/ህግ/ስ/ስ ቁ/195 /2/ለ/2 መሰረት ወደ 2 ኣመት ተሻሽሐል አፈጻጸሙን በተመለከተ የመተከል ዞን ከፍተኛ ፍ /ቤት በመ/ቁ/12794 በ15/02/09 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ ጸንቷል ።
No topics extracted.