ወጣት ጥፋተኞችን የተመለከቱ የጥንቃቄ እርምጃዎች አፈጻጸም በተቻለ መጠን አጥፊውን በማረም መልካም ውጤት ላያስገኝ በሚያስችል አግባብ መሆን የሚገባው ስለመሆኑ፣ ለወጣት ጥፋተኞች የሚያገለግል የጠባይ ማረሚያ ተቋም በልለበት ፣ በወላጅ ቁጥጥር ስር ሆኖ የሚደረግ የባህሪ ሁኔታ ክትትል የተሻለ ውጤት እንደማይመጣ እና የጥፋተኛው አደገኛነት በተገቢው አግባብ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ቅጣቱ በአዋቂዎች እስር ቤት እንዲፈፀም የሚሰጥ ውሳኔ ተገቢነት የልለው ስለመሆኑ፡የወንጀል ህግ አንቀጽ 168/2
No summary available.
የሰ/መ/ቁ/ - 136245 ቀን - 23/05/2010 ዳኞች፡- ዳኜ መላኩ ተኽላት ይመሰል ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- በደል ቢራ አ/ማህበር ነ/ፈጅ ወንድወሰን ክፍሉ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ገብረመዲህን ገ/ሕይወት አልቀሩቡም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ክርክሩ የተጀመረዉ በ ኢሉአባቦር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበዉ ክስ ይዘትም በአጭሩ፤ ከአመልካች ጋር ባደረጉት ቢራ የማከፋፈል ዉል መሰረት ተጠሪ 1 እና 716,1487 የሆኑትን ቼኮች አስይዞ ባዶ ጠርሙሶችን በመዉሰድ ሲሰራ የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ብር 1,036,840.00 ጥሬ ገንዘብ አስይዞ አመልካችም በቼኮቹ ምትክ ብሩን ተቀብሎ ሁለቱን ቼኮች መልሶ የሰጠዉ መሆኑን፣ ይህ በእንዲህ እንዳለ ተጠሪ ስራዉን አቋርጦ የተረከባቸዉን ጠርሙሶች ለአመልካች የመለሰ ሲሆን፣ አመልካች በማስያዣነት ከወሰደዉ ገንዘብ ዉስጥ ብር 783,840.00 የከፈለዉ ሲሆን ቀሪዉን 253,000.00 ብር ግን ተጠሪ ገንዘቡን ገቢ አላደረገም በሚል የከለከለዉ በመሆኑ ይሄዉ ገንዘብ ከ14/11/2006 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ 15 ወለድ ጋር እንዲከፈለዉ ይወሰንለት ዘንድ ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነዉ።
አመልካች ለቀረበበት ክስ በሰጠዉ መልስ፤ ተጠሪ በብር 1,036,840.00 ለሚገመት የገንዘብ መጠን ሁለት ቼኮችን አስይዞ ጠርሙሶቹን ከወሰደ በኋላ 7 ለሆነ ቼክ በጥሬ ገንዘብ ገቢ ያደረገ ሲሆን፣ 1 ለሆነዉ ቼክ ብር 253,000.00 ገንዘቡን ገቢ ሳያደርግ በስህተት ገቢ እንደተደረገ ተቆጥሮ ሁለቱም ቼኮች የተመለሱለት መሆኑን ጠቅሶ ተጠሪ ገንዘቡን ገቢ ያደረገ መሆኑን የሚያሳይ ደረሰኝ ማቅረብ ያለበት መሆኑን ጠቅሶ ክሱ ዉድቅ ሆኖ ይወሰንለት ዘንድ ዳኝነት ጠይቋል።
ጉዳዩ በመጀመሪያ የቀረበለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በዚህ መልኩ ግራ ቀኝ ያቀረቡትን ክርክር ከሰማ በኋላ፤ ተጠሪ የሚጠበቅበትን ገንዘብ 0.00 በመክፈሉ ምክንያት ቀደም ሲል አስይዞ የነበረዉ ሁለቱ ቼኮች ከምስጋና ጋር የተመለሱለት መሆኑን፣ አመልካች ገንዘቡ ገቢ መደረጉን ገልፆ ሁለቱን ቼኮች ለተጠሪ መመለሱ የሚያሳይ የሰነድ ማስረጃ መቅረቡን እና ይህም ማስረጃ በፍ/ሕጉ አንቀጽ 2020 መሰረት በቂ መሆኑን ጠቅሶ አመልካች ለተጠሪ በክሱ የተመለከተዉን ብር 253,000.00 ከ14/11/2004 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር ለተጠሪ እንዲከፍል ሲል ወስኗል።
ተጠሪ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በበኩሉ ተጠሪ ገንዘቡን ካስያዘ በኋላ ቼኩን መልሶ ላወስድ የቻለበት አግባብ ዋስትና እንጂ ዕዳን የማይመለከት በመሆኑ በፍትሐብሕር ሕጉ ከአንቀጽ 2018-2025 ያሉት ድንጋጌዎች ለጉዳዩ ተፈጻሚነት የልላቸዉ መሆኑን፣ በልላ በኩል አመልካች ለተጠሪ በፃፈዉ ደብዳቤ በቼክ የተመለከተዉ ገንዘብ ሳይከፈል በስህተት እንደተከፈለ ተቆጥሮ ለተጠሪ የተመለሰለት መሆኑን እና ተጠሪ ደረሰኝ ካቀረበ በድጋሚ የሚታይለት መሆኑን የገለጸለት መሆኑን እና በርግጥም ተጠሪ ከፍሎ ቢሆን ኖሮ በባንክ እስቴትመንት ላይ ላገኝ እንደሚችል በመግለጽ የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ በመሻር አመልካች ለክርክሩ ምክንያት የሆነዉን ገንዘብ ለተጠሪ ላከፍል አይገባም ሲል ወስኗል። ተጠሪ ይህን ዉሳኔ ባለመቀበል ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን፣ ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት በበኩሉ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰጠዉን ዉሳኔ በመሻር በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ የነበረዉን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ሲሆን፣ አመልካች በቀን 03/05/09 ዓ.ም ተዘጋጅቶ በጠበቃዉ አማካይነት ያቀረበዉ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ ብር 253,000.00 ገቢ ሳያደርጉ ቼኩ በስህተት የተመለሰላቸዉ መሆኑ እና በአመልካች ሲኒየር አካዉንታንት የተጠሪ አካዉንት ተፈትሾ ተጠሪ ገንዘቡ ገቢ አለመደረጉ ተረጋግጦ እያለ አመልካች ገንዘቡን እንዲከፍል የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆኑን በመግለጽ ታርሞ ይወሰንለት ዘንድ ዳኝነት ጠይቋል።
አቤቱታዉ ተመርምሮ ያስቀርባል በመባሉም ተጠሪ ቀርቦ ግራ ቀኝ እንዲከራከሩ በተደረገለት ጥሪ መሰረት ቀርቦ ግራ ቀኝ ክርክራቸዉን በጽሑፍ ተለዋዉጠዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት በአጭሩ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችሎትም ለሰበር አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉን ዉሳኔ ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። መዝገቡን እንደመረመርነዉ ተጠሪ ለብር 1,036,840.00 ቼክ አስይዞ ጠርሙሶቹን መዉሰዱን፣ ከዚህ ዉስጥ አመልካች ለተጠሪ .00 የከፈለዉ በመሆኑ ላይ ግራ ቀኝ ክርክር የላቸዉም። ተጠሪ ለጠርሙስ መያዣ በሰጣቸዉ ሁለት ቼኮች ላይ የተመለከተዉን ብር 1,036,840.00 በጥሬ ገንዘብ ለአመልካች መክፈሉን ገልፆ አመልካች ቼኮቹን ስመልስ ለተጠሪ በፃፈዉ ደብዳቤ ያረጋገጠ ስለመሆኑም ተገንዝበናል፤
አመልካችም ይህን አምኗል። አመልካች ለተጠሪ ላመልስ ከሚገባዉ ገንዘብ ብር 253,000.00 ላለመክፈል በዋናነት የሚከራከረዉ ይህ ገንዘብ ገቢ ሳይሆን ገቢ እንደተደረገ ተደርጎ በደብዳቤዉ የተገለጸ እና ቼኩም በስህተት የተመለሰ መሆኑን፣ በስህተት የተከፈለ ስለመሆኑም በልላ ጊዜ በተፃፈ ደብዳቤ ለተጠሪ መግለጹን ነዉ። በልላ በኩል ገንዘብ የተከፈለ መሆኑን የሚገልጽ ሰነድ ወይም ደብዳቤ ሰነዱን ባዘጋጀዉ ወይም ደብዳቤዉን በፃፈዉ ሰዉ ላይ ማስረጃ እንደሚሆን በፍትሐብሕር ሕጉ አንቀጽ 2018(1) ስር ከተደነገገዉ መገንዘብ ይቻላል። ህጉ ይህን ድንጋጌ በዚህ መልኩ ሲያስቀምጥም አንድ ሰዉ ገንዘብ መከፈሉን በተመለከተ የሚሰጠዉ የሰነድ ማስረጃ ወይም ደብዳቤ በርግጥም ገንዘቡ መከፈሉን አረጋግጦ ነዉ በሚል ሃሳብ እንደሆነ ይታመናል።
አመልካች ቼኩ ለተጠሪ የተመለሰዉ እንዲሁም ደብዳቤዉም የተፃፈዉ ተጠሪ ገንዘቡን ገቢ ሳያደርግ መሆኑን እና ይህም ስህተት መሆኑን በኋላ ለተጠሪ በፃፈዉ ደብዳቤ የገለጸለት መሆኑን በመግለጽ ይከራከራል፤ ይሁንና በስር ፍርድ ቤት በሰጠዉ መልስ ተጠሪ ገንዘቡን ገቢ አድርጎ ከሆነ ይህን የሚያሳይ ደረሰኝ ማቅረብ እንደሚገባዉ በመግለጽ ተከራክሯል። አመልካች ቼኩ የተመለሰዉ በስህተት መሆኑን ገልፆ ለተጠሪ በፃፈዉ ደብዳቤም ተጠሪ ገንዘቡን ገቢ ማድረጉን የሚያሳይ ደረሰኝ ካቀረበ በድጋሚ ላያጣራ እንደሚችል አመልክቷል። ይህ በአጠቃላይ የሚያሳየዉ አመልካች ገንዘቡን ገቢ ሳያደርግ ገቢ እንዳደረገ ተቆጥሮ ቼኩ የተመለሰለት በስህተት መሆኑን ገልፆ ለተጠሪ የፃፈዉ ደብዳቤም ተጠሪ ገንዘቡን ገቢ ማድረግ አለማድረጉን አመልካች እራሱ እርግጠኛ ባልሆነበት ሁኔታ መሆኑን ነዉ። በመሆኑም አመልካች ቼኩ ለተጠሪ የተመለሰለት በስህተት መሆኑን በመግለጽ አመልካች በኋላ ላይ የፃፈዉ ደብዳቤ ቀደም ሲል ገንዘቡ ገቢ መደረጉን አረጋግጦ ቼኩን ከምስጋና ጭምር ለተጠሪ በመመለስ የሰጠዉን ማረጋገጫ ላያስተባብል የሚችል አይደለም።
ከዚህ ሁሉ አንፃር ሲታይ የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኢሉአባቦር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ በማጽናት የሰጠዉ ፍርድ የግራ ቀኝ ክርክር እና የቀረበዉን ማስረጃ መሰረት ያደረገ ነዉ ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም ተከታዩ ተወስኗል።
የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/ 127837 በቀን 14/03/09 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/207712 ላይ የሰጠዉን ዉሳኔ ሽሮ የኢሉአባቦራ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/24452 ላይ የሰጠዉን ዉሳኔ በማጽናት የሰጠዉ ፍርድ በፍ/ሥ/ሥ/ ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችሎት በተደረገ ክርክር ምክንያት የወጣዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻሉ ብለናል።
No topics extracted.