ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ተፈጽሟል የሚል ክስ ለፍደራል የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የዳኝነት ችሎት ማቅረብና አስተዳደራዊ እርምጃና ቅጣት እንዲጣል የማድረግ ስልጣን ያለው የባለስልጣኑ ዓቃቤ ህግ ምስኪ ኢንዱስትሪዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ቤካስ ኬሚካልስ ሀ/የተ/የግ/ማህበር XLIII አዋጅ ቁ. 813/2006 አንቀጽ 37/1
No summary available.
የሰ/መ/ቁ/ - 131084 ቀን - 25/04/2010 ዳኞች፡- ተኽላት ይመስል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- አቶ ጌታቸዉ ይርገቡስ - አልቀረቡም ተጠሪዎች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
ጉዳዩ የተጀመረዉ በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች በተጠሪዎች ላይ ያቀረበዉን ክስ መነሻ ያደረገ ነዉ። የአመልካች ክስ ይዘትም በአጭሩ፤
ወ/ሮ መቅደስ አበበ የፍርድ ባለ መብት በመሆን ባቀረቡት የአፈፃፀም ክስ ምክንያት ቁጥሩ 150 የሆነዉ ቤት በዕዳዉ ምክንያት እንዲሸጥ በተወሰነዉ መሰረት ተሸጦ ገንዘቡ ገቢ ከተደረገ በኋላ፣ ቁጥራቸዉ 149 እና 151 የሆኑ ቤቶች ቁጥሩ 150 ከሆነዉ ቤት ጋር የተያያዙ ቢሆኑም የተለያዩ መሆናቸዉን እያወቁ ወይም ማወቅ ሲገባቸዉ ተጠሪዎች ተመሳጥረዉ የቤ/ቁ/ 149 እና 151 የሆኑትን ቤቶች 3ኛ ተጠሪ እንዲረከብ ያደረጉ በመሆኑ ቤቶቹን ከዳቦ ማሽን ጭምር ተጠሪዎች እንዲያስረክቡኝ ይወሰንልኝ የሚል ነዉ።
ተጠሪዎች በስር ፍርድ ቤት ቀርበዉ መልስ እንዲሰጡ የተደረገ ሲሆን፣ 1ኛ ተጠሪ ባለመቅረቡ ጉዳዩ በልለበት እንዲታይ ተደርጓል። 2ኛ ተጠሪ ፍርድን የማስፈጸም ኃላፊነት የተሰጠዉ እና የፍድራል ፍርድ ቤቶች አካል እንጂ እራሱን የቻለ የህግ ሰዉነት የተሰጠዉ ተቋም አለመሆኑን ገልፆ ላከሰስ እንደማይገባዉ የተከራከረ ሲሆን፤
3ኛ ተጠሪ በበኩሉ ቁጥሩ 150 የሆነዉን ቤት ተረክቦ የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ አወጥቶበት ለ8 ዓመታት በእጁ አድርጎ የነበረ መሆኑን፣ አመልካች ቁጥሩ 151 የሆነዉ ቤት የግል ቤቱ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ያላቀረበ መሆኑን በመጥቀስ ክሱ ዉድቅ ሆኖ እንዲወሰንለት በማለት መከራከሩን መዝገቡ ያሳያል።
ጉዳዩ በመጀመሪያ የቀረበለት የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም በዚህ መልኩ በግራ ቀኝ የቀረበዉን ክርክር ከሰማ በኋላ፤ 1ኛ ተጠሪ ዳኛ ሆነዉ ጉዳዩን ሲያዩ በነበረበት ወቅት ለፈጸሙት ተግባር በፍትሐብሕር ሕጉ አንቀጽ 2138(ሐ) መሰረት ክስ ላቀርብባቸዉ የማይገባ መሆኑን፣ 2ኛ ተጠሪም ፍርድ ለማስፈጸም በፍድራል ፍርድ ቤቶች ስር የተደራጀ አካል እንጂ እራሱን የቻለ የህግ ሰዉነት ያለዉ ባለመሆኑ ላከሰስ አይገባም በማለት በሁለቱ ላይ የቀረበዉን ክስ ዉድቅ ያደረገ ሲሆን፤ ቁጥሩ 150 የሆነዉ ቤት ቁጥሩ 151 ከሆነዉ ቤት በተናጥል የሚገኝ መሆኑ እና ይዞታዉ የማን እንደሆነ የሚያሳይ የሰነድ ማረጋገጫ ማስረጃ አለማግኘቱን ገልፆ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የይዞታ አስተዳደር እና የሽግግር ጊዜ አገልግሎት የላከለትን ደብዳቤ መነሻ በማድረግ አመልካች በቤቱ ላይ መብት ያለዉ መሆኑን አላረጋገጠም በሚል ምክንያት 3ኛ ተጠሪን በተመለከተ የቀረበዉንም ክስ ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። አመልካች ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበዉ ይግባኝም ተቀባይነት አላገኘም።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ሲሆን፣ አመልካች በቀን 28/11/08 ዓ.ም ተዘጋጅቶ በቀረበዉ የሰበር አቤቱታ፤ በፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ፀንቶ የተወሰነዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚልባቸዉን ምክንያቶች በመዘርዘር ታርሞ ይወሰንለት ዘንድ ዳኝነት ጠይቋል። አቤቱታዉ ተመርምሮ ያስቀርባል በመባሉም ተጠሪዎች እንዲቀርቡ በተደረገላቸዉ ጥሪ መሰረት 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ቀርበዉ ግራ ቀኝ ክርክራቸዉን በጽሑፍ ተለዋዉጠዋል። 1ኛ ተጠሪ ባለመቅረቡ በልለበት እንዲታይ ተደርጓል።
የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት በአጭሩ ከፍ ሲል የተመለከተዉን የሚመስል ሲሆን፣ ይህ ችሎትም ለአቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉን ዉሳኔ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም አመልካች ተጠሪዎችን አንድ ላይ አጣምሮ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ክስ ለማቅረብ መሰረት ያደረገዉ ከወ/ሮ መቅደስ አበበ ጋር በነበራቸዉ ክርክር የፍርድ ባለ ዕዳ በመሆን በቀረበባቸዉ የአፈፃፀም ክስ 1ኛ ተጠሪ በወቅቱ ዳኛ በመሆን በአፈፃፀም መዝገብ ላይ በሰጠዉ ትዕዛዝ፣ 2ኛ ተጠሪ ፍርዱን በማስፈጸም ሂደት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት 3ኛ ተጠሪ እንዲረከብ በማድረጉ እና 3ኛ ተጠሪ ደግሞ በመጀመሪያ በአፈፃፀም እንዲሸጥ ሳይወሰን ቁጥራቸዉ 149 እና 151 የሆኑትን ቤቶች መረከቡ ስለመሆኑ ከክርክሩ ሂደት ለመገንዘብ ተችሐል። ይህም የሚያሳየዉ አመልካች መብቴ ተጥሷል በሚል ላቀረበዉ ክስ ምክንያቱ ከፍርድ አፈፃፀም ጋር በተያያዘ በተጠሪዎች የተፈጸመ ተግባር መሆኑን ነዉ። ይህ ከሆነ አመልካች ያቀረቡት ክስ ከመነሻዉም ተቀባይነት ያለዉ መሆን አለመሆኑ የዚህን ችሎት ምላሽ የሚሻ ጭብጥ ይሆናል።
በመሰረቱ በልላ ሰዉ በተፈጸመ ድርጊት ምክንያት መብቱ የተጣሰበት ሰዉ መብቱን ለማስከበር አቤቱታዉን ስልጣን ላለዉ አካል የማቅረብ መብት ያለዉ ሲሆን፤
የሚቀርበዉም አቤቱታ የጉዳዩን ዓይነትና መሰረታዊ ባህርይ መሰረት በማድረግ በህግ የተዘረጋዉን ስርዓት ተከትሎ መሆን እንደሚገባዉ እሙን ነዉ። ወደ ተያዘዉ ጉዳይ ስንመለስ፣ ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ፣ አመልካች ክሱን ለማቅረብ በምክንያትነት የጠቀሰዉ በፍርድ አፈፃፀም ሂደት በተጠሪዎች በተፈጸሙት ተግባራት ምክንያት መብቱ መጎዳቱን ነዉ። ለተያዘዉ ጭብጥ እልባት ለመስጠት ይቻል ዘንድም በአፈፃፀም ምክንያት የፍርድ ባለዕዳ ንብረት የሚያዝበትን እና የሚሸጥበትን ስርዓት በተመለከተ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕጉ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በቅድሚያ ማየቱ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል።
ፍርድን ለማስፈጸም ሲባል ንብረት ስለሚያዝበት፣ ስለሚሸጥበት ስርዓት እና ዉጤቱ በፍትሐብሕር ሥ/ሥርዓት ሕጉ ከአንቀጽ 404 ጀምሮ ባሉት ድንጋጌዎች ተመልክቷል።
ከድንጋጌዎቹ አጠቃላይ ይዘት መረዳት የሚቻለዉም፤ ሂደቱ የሚመራዉ የአፈፃፀም መዝገቡን በያዘ ፍርድ ቤት ሲሆን ፍርድ ቤቱም በአፈፃፀም ምክንያት ንብረት የሚሸጥበትን ሁኔታ እና ስርዓቱን በመከታተል እና እንደየአግባብነታቸዉ በስነ ስርዓት ሕጉ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት ሂደቱን በመምራት የፍርድ ባለዕዳ፣ የፍርድ ባለ መብትን እና የገዥዉን መብቶች ባገናዘበ መልኩ የሽያጩ ሂደት መከናወኑን የማረጋገጥ ግድታ ያለበት መሆኑን ነዉ። ይህ ሂደትም የተሸጠዉ ንብረት በርግጥም እንዲሸጥ የተወሰነ ንብረት መሆን አለመሆኑ፣ ሂደቱ በህጉ የተመለከቱትን ስርዓቶች የተከተለ መሆን አለመሆኑ፤ ከሂደቱ ጋር በተያያዘ ከፍርድ ባለ መብት፣ ከፍርድ ባለ ዕዳ፣ ከገዥዉ እንዲሁም ከንብረቱ ጋር በተያያዘ መብት ወይም ጥቅም አለኝ ከሚል 3ኛ ወገን የሚቀርበዉን ተቃዉሞ መርምሮ ዉሳኔ መስጠትን ሁሉ የሚያካትት ስለመሆኑ ከድንጋጌዎቹ አጠቃላይ ይዘት እና መንፈስ የምንገነዘበዉ ጉዳይ ነዉ።
በእርግጥ ከሽያጭ ሂደት ጋር በተያያዘ በፍርድ ቤቱ ወይም በፍርድ አስፈፃሚዉ አካል በሚፈጸም ስህተት/ጥፋት ምክንያት የፍርድ ባለ መብት ወይም የፍርድ ባለ ዕዳ እንዲሁም የገዥዉ መብት ላጎዳ የሚችልበት ሁኔታ ላፈጠር እንደሚችል ይታወቃል።
ይሁንና እነዚህ ስህተቶች የሚቃኑት በስነ ስርዓት ህጉ መሰረት አፈፃፀሙን በያዘዉ ፍርድ ቤት በመሆኑ፣ ሽያጩ በሚደረግበት ሂደት ወይም ከዉጤቱ ጋር በተያያዘ ስህተት (ጥፋት) በመፈጸሙ ምክንያት መብቴ ተጎድቷል የሚል ወገን የሚኖረዉ የህግ መፍትሕ ይህ እንዲስተካከልለት ጥያቄዉን አፈፃፀሙን ለያዘዉ ፍርድ ቤት ማቅረብ ነዉ።
በመሆኑም አፈፃፀሙን የያዘዉ ፍርድ ቤት በዕዳ ምክንያት እንዲሸጥ ከተወሰነዉ ቁጥሩ 150 ከሆነዉ ቤት ልላ አመልካች ለክርክሩ መነሻ ያደረጋቸዉ ሁለቱ ቤቶች ያላግባብ እንዲሸጡ በፍርድ ቤቱ ልላ ትዕዛዝ መሰጠቱ ወይም ከተሸጠዉ ንብረት ዉጪ ልላ ተጨምሮበት 3ኛ ተጠሪ ያላግባብ እንዲረከብ ተደርጎ ከሆነ እና በዚህ ምክንያት መብቱ የተነካ መሆኑን ካመነበት አፈፃፀሙን ለያዘዉ ፍርድ ቤት አቤቱታዉን ማቅረብ አላያም አፈፃፀሙን በያዘዉ ፍርድ ቤት የተፈጸመዉ ስህተት እንዲታረም ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦ መብቱን ማስከበር ነበረበት። ይሁንና ይህን ሳያደርግ የአፈፃፀም
ለማስከበር በአዲስ መልክ ያቀረበዉ ክስ ሥነ ሥርዓታዊ ባለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ህጉ አንቀጽ 231(1-ሀ) መሰረት ተቀባይነት ያለዉ አይደለም። በመሆኑም የአመልካችን ክስ ዉድቅ በማድረግ በስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በከፍተኛ ፍርድ ቤት በትዕዛዝ የፀናዉ ዉሳኔ ከዉጤት አንፃር ሲታይ የሚነቀፍ ሆኖ ስላልተገኘ ተከታዩ ተወስኗል።
የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/174646 በቀን 01/09/08 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት፣ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 45369 ላይ የሰጠዉን ዉሳኔ በማጽናት፣ የሰጠዉ ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችሎት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻሉ ብለናል።
No topics extracted.