በአፈፃፀም ሂደት ንብረቴ አላግባብ ተሸጠ ወይም መብቴ ተጎዳ የሚል ሰው ፤ አቤቱታውን አፈፃፀሙን ለያዘው ፍርድ ቤት ወይም አፈፃፀሙን የያዘው ፍርድ ቤት ስህተት የፈፀመ ነው በማለት በይግባኝ እንዲታረም ማድረግ እንጂ የአፈፃፀሙ መዝገብ ከተዘጋ እና አመታት ካለፉ በኃላ መብቴ ይከበረልኝ በማለት አዲስ ክስ ማቅረብ አቶ ጌታቸው ይርገቡስ እና እነ በላይ ናማጋ ( 3 ሰዎች) 131084 389 XLII ስለመሆኑ፤ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 404 እና 231(1) (ሀ) ልዩ ልዩ 394 76. በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2143(1) የተመለከተው የይርጋ ዘመን አላግባብ መበልፀግን አስመልክቶ በሚቀርቡ ክሶች ላይ ተፈፃሚነት የልለው ስለመሆኑ እና ተፈፃሚነት ላኖረው የሚገባው የአስር ዓመት የይርጋ ዘመን ስለመሆኑ፤ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2143(1)፤1845
No summary available.
መስከረም 22 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው በእውቀት በላይ እንዳሻው አዳነ ሃይሉ ነጋሽ እትመት አሰፋ አመልካች፡- ሙሉአለም ግዛው ወልድ -ጠበቃ መሀመድኑር አበደሰረም -ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1ኛ ዙፋን ዘለቀ - ተልማ አቻሜ -ቀረቡ 2ኛ መስፍን አስፋው 3ኛ አልማዝ አስፋው 4ኛ ቱቱ አስፋው ጠበቃ አማረ ጋሳ ቀረቡ 5ኛ ሶስና አስፋው መዝገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ ፍርድ ለማስፈፀም የተደረገው ሀራጅ የተመለከቱ ሲሆን የተጀመረው በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በፍርድ ባለመብት አቤቱታ አቅራቢነት ነው። በሥር ፍርድ ቤት የፍርድ ባለመሀብት ወ/ሮ አመለወርቅ ኢየሱስ ወራሽ ወ/ሮ ዙፋን ዘለቀ ሲሆኑ የፍርድ ባለዕዳዎች ደግሞ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ተጠሪዎች ናቸው። ለአፈፃፀም አቤቱታ መነሻ የሆነው ክርክር የተነሳበት ቤት በ15/05/07 ዓ/ም በተደረገ ሀራጅ ሽያጭ አቶ እንግዳወርቅ አታክልቲ ብር 22,500,000,00 ዋጋ በመስጠት አሸናፊ ቢሆኑም ገንዘቡን ገቢ ስላላደረጉ በድጋሚ ጨረታ እንዲወጣ መደረጉንና በዚሁ በ29/08/07 ዓ/ም በተደረገው ጨረታ ላይ ለቀደመው ጨረታ የተጫራቾች ብዛት በ16 ቀንሶ 5 ብቻ መቅረባቸውን እነዚህም ተጫራቾች እውነተኛና በቂ አለመሆናቸውን ገልፀው ጨረታው እንዲዛወር ሲጠይቁ በፅሁፍ ያቅርቡ ተብለው በመፃፍ ላይ እያሉ ከልላ የመ/ቤቱ ሰራተኛ ጋር በመነጋገር አሸናፊ ለሆኑ አቶ ሙሉአለም ግዛው በብር 10,350,000 ( አስር ሚላዮን ሶስት መቶ አምሳ ሺህ) እንዲሸጥ ተደርጓል።ሁለተኛ ጨረታ አካሄድ ላይ ቅሬታ አቅርቤ በፅሁፍ እያደረግኩ እያለ አጫራቹ ሃሳባቸው በመቀየር ሀራጁ በጥድፍያና በተነንኮል እንዲካሄድ ያደረጉ ስለሆነ ጨረታው ፈርሶ ልላ ጨረታ ይደረግልኝ በማለት ጠይቀዋል።የጨረታው አሸናፊ በበኩላቸው ጨረታውን ስርአቱን አሟልቶ የበለጠ ዋጋ አቅርቤ አሸናፊ ሆኛለሁ የማጭበርበር ተግባር አልተፈፀመም በማለት ተከራክረዋል ።
ፍርድ ቤቱ ግራቀኙ ካከራከረ እና ምስክሮች ከሰማ በኋላ የጨረታ ሽያጭ አካሄድ ስርአትን በጉልህ ሁኔታ በጣሰና ነፃ ውድድር ባልነበረበት ውጤትን ለመፍጠር በሚያስችል ሁኔታ የቀድሞ የተጫራቾች መግባባት በሚታይበት የተደረገ ሽያጭ ላፀና የሚገባ ባለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 445 መሰረት ጉድለት ያለበት ሽያጭ ስለሆነ በ29/08/07ዓ/ም የተደረገው አቶ ሙሉአለም ግዛው አሸናፊ የሆኑበት በአፈ/መ/ቁ.
16046 የተከናወነው ሀራጅ ላፈርስ ይገባል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ብይን ቅር ተሰኝተው ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢያቀርቡም ግራቀኙ አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ ቅሬታው ባለመቀበል ሰርዞታል። ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የሥር ፍርድ ቤቶች ብይንና ትዕዛዝ በመቃወም የቀረበ ነው። የአመልካች የሰበር ቅሬታ ዋና ትኩረት፡- በፍርድ አፈፃፀም የማይንቀሳቀስ ንብረት ጨረታ ሽያጭ የሚፈርሰው በጨረታ ስርአቱ ላይ ግዙፍ ጉድለት ወይም ትክክለኛ ያልሆነ ተግባር ወይም የማታለል ተግባር መኖሩ ከተረጋገጠ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ የጨረታው ሽያጭ እንዲፈርስ ያመለከቱት በጨረታው ጉዳት ደረሰብኝ ብለው ሳይሆን ቤቱ በ2ኛው ጨረታ ከተሰጠው ባነሰዋጋ የሚል በመሆኑ በህጉ አግባብ የተደረገው ጨረታ እንዲሰረዝ መደረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው የስር ፍረድቤቶች ውሳኔ ላሻር ይገባል በማለት አቅርበዋል። ጉዳዩ ለሰበር ይቅረብ በመባሉ ግራቀኙ የጽሑፍ ክርክር አድርጓአል።
ተጠሪዎች በበኩላቸው የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በአግባቡ መሆኑ በመዘርዘር የሥር ፍርድ ቤት ብይን ይሁን ትዕዛዝ ስሕተት የለውም ላጸና ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የአመልካች የመልስ መልስ የሰበር አቤቱታቸውን የሚያጠናክር ነው።
ከሥር የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ግራቀኙ በሰበር ችሎት ያደረጉት የጽሑፍ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ብይን እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማዛመድ ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ መርምረናል። ጉዳዩን እንደመረመርነውም በዚህ ችሎት ዕልባት የሚያስፈልገው ጭብጥ የሥር ፍርድ ቤቶች ጨረታው እንዲሰረዝ የሰጡት ብይን እና ትዕዛዝ በሕጉ አግባብ የተሰጠ ነው ወይስ አይደለም? የሚል ሆኖ አግኝቶታል።
ከሥር የክርክር ሂደት መረዳት የተቻለው ለክርክሩ መነሻ የሁነውን በጉለል ክፍለ ከተማ ቀበል 01/02 የቤት ቁጥር 750 የሆነውን ቤት በ15/05/07 ዓ/ም በተደረገ ሀራጅ ሽያጭ አቶ እንግዳወርቅ አታክልቲ ብር 22,500,000,00 ዋጋ በመስጠት አሸናፊ ቢሆኑም ገንዘቡን ገቢ ስላላደረጉ በድጋሚ ጨረታ እንዲወጣ መደረጉንና በዚሁ በ29/08/07 ዓ/ም በተደረገው ጨረታ ላይ ለቀደመው ጨረታ የተጫራቾች ብዛት መቀነሱ የጨረታው ተሳታፊዎችም እየተጠቃቀሱና እየተጠባበቁ ጨረታውን ማደረጋቸው በተደረገው የማጭበርበር ተግባር ምክንያት ቤቱ በመጀመሪያ ጨረታ ከተጠቀሰው ዋጋ ግማሽ በታች አሸናፊ መሆኑ በምስክሮች መረጋገጡ ከስር ፍርድ ቤቶች መዝገብ ለመረዳት ችለናል።
በመሰረቱ በሀራጅ በተሸጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የተፈጸመ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ወይም ማጭበርበር ወይም ማታለል ድርጊት ካለ አቤቱታ የሚቀርብበት ሥርዓት በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 445 ሥር ተደንግጓአል። በተያዘው ጉዳይ አመልካች በተደረገው ጨረታ ግዙፍ ጉድለት ወይም ትክክለኛ ያልሆነ ተግባር ወይም የማታለል ድርጊት መኖሩ አልተረጋገጠም በማለት አጥብቀው የሚከራከሩ ቢሆንም በሀራጅ አካሄድና ሽያጩ የተፈጸመበት ሥርዓት ጉድለት ወይም ትክክለኛ ያልሆነ ተግባር ወይም የማታለልና ማጭበርበር ድርጊት ስለመፈጸሙ በማስረጃ የተረጋገጠ ስለመሆኑ ድምዳሜ ላይ የደረሰና ይህ ምክንያት ደግሞ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 445 እንደተመለከተው ጨረታው ለማፍረስ በቂ ምክንያት በመሆኑ ሲታይ አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ የሕግ መሰረት ያለው ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ብይንና ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት አይደለም ብለናል።
በመሆኑም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ በ25/04/2008 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ፣ የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ20/03/2009 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ጸንቷል። ይፃፍ።
በዚህ ፍ/ቤት ጥር 23 ቀን 2009 ዓ.ም የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል ። ለሚመለከተው አካል ይፃፍ።
የዚህ ፍ/ቤት ክርክር ያስከተለው ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸው ይቻሉ ብለናል።
መዝገቡ ውሳኔ ያገኘ በመሆኑ ወደ መ/ቤት ይመለስ።
No specific laws extracted.
No topics extracted.