በሀራጅ አካሄድና ሽያጭ ስርዓት ተገቢ ያልሆነ ድርጊት፣ ማጭበርበር ወይም ማታለል መኖሩ በማስረጃ ከተረጋገጠ ጨረታውን ለማፍረስ በቂ ምክንያት ስለመሆኑ፣ የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 445
No summary available.
የሰበር መዝገብ ህዳር 29 ቀን 2010 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዳኜ መላኩ ብርሃኑ አመነው እንዳሻው አዳነ ሃይሉ ነጋሽ እትመት አሰፋ አመልካች፡- የኢ/ገ/ጉ/ባለስልጣን ተጠሪ፡- ሻንዶንግ ሃይወይ ኢንጂነሪንግ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ለዚህ ሰበር የቀረበው ጉዳይ በአሁኑ አመልካች ተወስኖ የተሰጣቸው የግብር መጠን ላይ ቅር በመሰኘት ተጠሪ ለፍድራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ያቀረቡትን ጥያቄ መነሻ ያደረገ ክርክር ነው። ተጠሪ ለግብር ይግባኝ ሰሚው ጉባኤ ያቀረቡት ቅሬታ ይዘት፡በሱር ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ተቋራጭነት በሚገነባው የሚል ጭፍራ አለወሃ የመንገድ ስራ ማሻሻል 2ኛ ፕሮጀክት በንኡስ ስራ ተቋራጭነት በሰሩበት ጊዜ ዋናው የስራ ተቋራጭ ለመንገድ ግንባታ አገልግሎት የሚውል ግብአት እያቀረበ ስራው ከተሰራ በኋላ በውሉ መሰረት ከንኡስ ስራ ተቋራጭ ገንዘብ እየተቀነሰ የተከፈለ በመሆኑ እንዲሁም የባንክ አገልግሎት ክፍያ በዋናው ስራ ተቋራጭ የተከፈለ ቢሆንም ከንኡስ ስራ ተቋራጭ እንዲቀነስ የውል ስምምነት ባደረጉት መሰረት የተከፈለ በመሆኑ የአሁኑ ተጠሪ ግብር እንዲከፍል የተጠየቀበት ገቢ ለማግኘት ያወጡት ውጭ ሆኖ ላያዝ ሲገባ ይህ ሳይያዝ የተወሰነ ግብር በመሆኑ ፍትሃዊ አይደለም በማለት ውሳኔው ተገቢ አለመሆኑን ጠቅሰው አመልካች አላግባብ የጠየቃቸውን ክፍያ ጉባኤው ውድቅ እንዲያደርግላቸው ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የፍድራሉ የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በጉዳዩ ላይ አመልካች መልስ እንዲሰጥ ካደረገ በኋላ በግራ ቀኙ መካከል የቀረበው ክርክርና ማስረጃ በመመርመር በሰጠው ውሳኔ በተጠሪ በኩል የጥሬ እቃ ክፍያ በሱር ኮንስትራክሽን ተቀንሶ ለመቅረቱ የክፍያ ሰርትፊኬት የቀረበ በመሆኑ እንዲሁም በተጠሪ እና በሱር ኮንስትራክሽን መካከል በተደረገው የውል ስምምነት ለባንክ አገልግሎት የሚከፈል ክፍያ በይግባኝ ባይ የሚሸፈን በመሆኑና ገንዘቡ በሱር ኮንስትራክሽን ስም መከፈሉን የባንክ አሰራር ስለሆነ የግብአት ዋጋና የባንክ አገልግሎት ክፍያ ወጭ ዋና ስራ ተቋራጭ በሆነው በሱር ኮንስትራክሽን በወጭ አለመያዙ ተረጋግጦ ለአሁኑ ይግባኝ ባይ በወጭ ተይዞለት ግብሩ እንደገና ላሰላ እንደሚገባ ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ቅሬታ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙ አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ በግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የተሰጠውን ውሳኔ በመሻር ለግንባታ እቃ አቅርቦት ወጣ የተባለው ብር 34,371,218.06 እና ለባንክ አገልግሎት ክፍያ ወጣ የተባለው ብር 564,480.00 ለተጠሪ በወጪነት ላያዝ አይገባም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። የአሁኑ ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ቅሬታ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ በመሻር የፍድራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የተሰጠውን ውሳኔ በማፅናት ውሳኔ ሰጥቷል። አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚሁ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በሰበር ችሎት ላታይ ይገባዋል በመባሉ ተጠሪ ቀርበው የጽሁፍ ክርክራቸው ተለዋውጠዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው።ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ህጎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል።እንደመረመርነው በዚህ ችሎት ምላሽ ማግኘት የሚገባው ነጥብም ተጠሪ በወጪነት እንዲያዝለት ያቀረበው ደረሰኝ በልላ አካል የተመዘገበ በሆነበት ሁኔታ ወጪ ለማረጋገጥ በልላ አካል የተመዘገበ ደረሰኝ ተቀባይነት ያለው መሆን አለመሆኑ ከግብር አዋጁ መርህ አንፃር በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ ሆኖ አግኝተነዋል። ከክርክሩ ሂደት ለመረዳት እንደቻልነው ተጠሪ እንዲከፍል የተጠየቀውን የንግድ ትርፍ ግብርና የተጨማሪ እሴት ታክስ የ2011 እ.ኤ.አ. የግብር ዘመን መሆኑ ተጠሪ በዚሁ የግብር ዘመን ወጪ ማድረጉን በመግለፅ ያቀረበውን የሲሚንቶ፣የነዳጅ፤ልሎች የግንባታ እቃ ወጪዎች ብር 34,371,218.06 (ሰላሳ አራት ሚላዮን ሶስት መቶ ሰባ አንድ ሺህ ሁለት መቶ አስራ ስምንት ከስድስት ሳንቲም) እና ለባንክ አገልግሎት የተፈፀመን ክፍያ ወጪ ብር 564,480 (አምስት መቶ ስልሳ አራት ሺህ አራት መቶ ሰማንያ ብር) በወጪነት እንዲያዝለት ጠይቆ አመልካች ውድቅ በማድረጉ መነሻ ያደረገ ክርክር ነው ።
ግብር ከፋዩ ወጪዎችን ማረጋገጥ እስከቻለ ድረስ ለንግድ ስራው ዋስትና ለመስጠትና እንቅስቃሴውን ለማስቀጠል የተደረጉ ወጪዎች ተቀናሽ እንደሚደረግ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 20 ስር ተደንግጓል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ግብር ከፋዩ ወጪውን ለማስረዳት ማረጋገጫ ማቅረብ እንዳለበት አከራካሪ ጉዳይ አይደለም። አሁን በያዝነው ጉዳይ ተጠሪ በወጪነት እንዲያዝለት እየጠየቀ ያለው በ2011 እ.ኤ.አ. የግብር ዘመን ወጪ አድርጌያለሁ በማለት፤ ማድረጉን ያረጋግጥልኛል በማለት ያቀረበውን የሲሚንቶ፣የነዳጅ፤ልሎች የግንባታ እቃ ወጪዎች ብር 34,371,218.06 (ሰላሳ አራት ሚላዮን ሶስት መቶ ሰባ አንድ ሺህ ሁለት መቶ አስራ ስምንት ከስድስት ሳንቲም) እና ለባንክ አገልግሎት የተፈፀመን ክፍያ ወጪ ብር 564,480 (አምስት መቶ ስልሳ አራት ሺህ አራት መቶ ሰማንያ ብር) አጠቃላይ በተጠሪ ስም ወጪ ተደርገው የቀረቡ ሳይሆን ዋና ተቋራጭ በሆነው በሱር ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ወጪ የተደረገ ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ ነው።
የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 20 ስር እንደተደነገገው ወጪ አውጥቻለሁ የሚል አካል ወጪውን ማስረዳት የሚችለው በሚያቀርበው ህጋዊና ተቀባይነት ያለው ደረሰኝ መሆን እንዳለበት ከድንጋጌው ይዘትና መንፈስ የምንረዳው ጉዳይ ነው። በልላ በኩል የግዢ ደረሰኝ ማለት የሻጭና የገዢ ሙሉ ስም፣ የግብር ከፋዩ መለያ ቁጥር፣ተከታታይ ደረሰኝ ቁጥር፣የተሸጠው እቃ ወይም አገልግሎት አይነትና የታክሱ መጠን፣የሽያጩ ወይም ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ዋጋ መያዝ ያለበት ስለመሆኑ ከተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀፅ 22(2) እና ደረሰኝ አያያዝና አጠቃቀም መመረያ ቁጥር 28/2001 አንቀፅ 4(1) ጣምራ ንባብ መረዳት ይቻላል።ስለሆነም ግብር ከፋዩ ለንግድ ስራው ያወጣውን ወጪ ማረጋገጥ አለበት ሲባል ይህንን ለማረጋገጥ የሚቀርበው ህጋዊ ደረሰኝ ደግሞ ወጪ አውጥቻለሁ በሚለው አካል ስም መሆን እንዳለበት ከተጠቀሰው ድንጋጌ እና ከማስረጃ መርህ አንፃር ተቀባይነት ያለው ነው። ስለሆነም በሱር ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስም ወጪ የተደረገ የሲሚንቶ፣የነዳጅ፤ልሎች የግንባታ እቃ ወጪዎች እንዲሁም ለባንክ አገልግሎት ክፍያ ተጠሪ ገቢ ለማግኘት ያወጡት ወጭ ሆኖ ላያዝ ይገባል በማለት የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ከገቢ ግብር አዋጅ ድንጋጌ ውጪ ስለሆነ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው ብለናል። በመሆኑም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የካቲት 10 ቀን 2009 ዓ/ም የኢ.ፍ.ድ.ሪ. የፍድራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የተሰጠው ውሳኔ በማፅናት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ተሽሯል።
የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ. ሰኔ 01 ቀን 2009 ዓ/ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ እና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
No topics extracted.