የጉዳት ካሳ ጥያቄ ከጋብቻ ፍቺ ጋር ተያይዞ የቀረበ በሆነበት እና ጉዳቱም የደረሰው ከፍቺው ጋር ተያያዞ መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ ጥያቄው የባልና ሚስት ፍቺን ተከትሎ ከሚነሳ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ጋር በአንድ ላይ ላስተናገድ አይችልም በሚል የሚሰጥ ውሳኔ ተገቢነት የልለው ስለመሆኑ፡የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 84 135902 ወ/ሮ መስከረም ጫካእና አቶ አክላሉ ሽፈራው (2 ሰዎች) መስከረም 22 ቀን 2ዐ10 ዓ.ም ግብር 367 71. ከቀረጥ ነጻ መብትን በመጠቀም ወደ ሀገር የገባን እቃ ለመሸጥ ወይም ወደ ልላ ለማስተላለፍ ከተፈለገ ቀድሞ ቀረጡን በመክፈል ነጻ ማድረግ የሚገባ ስለመሆኑ፡አዋጅ/ቁ 859/2006 አንቀጽ 30(1) XL
No summary available.
ጥር 23 ቀን 2ዐ1ዐ ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዳኜ መላኩ ተኽላት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ /ዶ/ር/ ቀነዓ ቂጣታ ፀሐይ መንክር አመልካች----- 1ኛ አቶ ብሩክ ገ/ሥላሴ ቀረቡ 2ኛ አቶ ገ/ህይወት በርሄ አልቀረቡም ተጠሪ----------- አቶ ዳዊት ተሰማ ቡታ አልቀረቡም መዝገቡ ተመርምር ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
በመኪና ሽያጭ ውል መነሻነት የታጣ ጥቅም ላከፈለኝ ይገባል በሚል በአሁን አመልካቾች ከሣሽነት በተጠሪ ተከሣሽነት በስር የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀረበው ክስ የተሰጠው ውሣኔ በፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ በመሻሩ መነሻነት የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የሰጠው ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በሚል የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው።
በስር ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረው ክስ እንደሚያስረዳው በአመልካቾች እና በተጠሪ መካከል የመኪና ሽያጭ ውል ተፈጽሞ የነበረ ሲሆን፣ የሰ.ቁ. ዐ3-ዐ2-5ዐ764 ኢት የሆነውን ትራክተር የጭነት ተሽከርካሪን ለንግድ ሥራ አገልግሎት የሚውል በብር 1,7ዐዐ,ዐዐዐ.ዐዐ/ አንድ ሚላዩን ሰባት መቶ ሺ ብር/ በ19/ዐ4/2ዐዐ6 ዓ.ም. በተፃፈ ውል ሽያጭ መፈፀማቸውን እና ከዚህ ገንዘብ ላይ ብር 5ዐዐ,000.ዐዐ/ አምስት መቶ ሺ ብር/ ወዲያው ከፍለው መኪናውን መረከባቸውን፣ ቀሪ ገንዘቡን ስመ ንብረቱ ሲዛወር ላከፍሉ መስማማታቸውን፣ መኪናው ከውጭ ሲገባ ቀረጥ ያልተከፈለበት በመሆኑ ለሥራ ሳይሰማራ መቆየቱን ገልፀው በ27/2/2ዐዐ7 ዓ.ም. የተፃፈ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን፣ ሆኖም ቀድመው አድርገውት የነበረውን ውል በመተው በ9/7/2ዐዐ7 ዓ.ም. ልላ ውል መስማማታቸውን፣ የውሉም ይዘት ተሽከርካሪው ከተገዛበት ዋጋ ውስጥ አሁንም በውሉ ዕለት 85ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ ወዲያውኑ ከፍለው ከሣሽ ከዳሽን ባንክ ተሽከርካሪውን በዋስትና አስይዘው የተበደረውን ገንዘብ 500,ዐዐዐ.ዐዐ ዕዳ ነፃ አድርገው ብር 14ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ በቼክ 3 በሆነ በቀን ዐ9/ዐ7/2ዐዐ8 የተፃፈ ከአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ እንዲወስድ የሰጡት መሆኑን ገልፀዋል።
የቀረጥ ገቢ ዕዳ ብር 2ዐዐ,ዐዐዐ.ዐዐ መሆኑን ተከሣሽ የነገሯዋቸው በመሆኑ ከሽያጭ ገንዘቡ ላይ እንዲቆርጡ መስማማታቸውን፣ ሆኖም ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሲጠይቁ 2ዐዐ,ዐዐዐ.ዐዐ ሣይሆን ብር 489,ዐዐዐ.ዐዐ /አራት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሺ ብር/ መሆኑ መገለፁን፣ በመሆኑም ብር 132,ዐዐዐ.ዐዐ/ አንድ መቶ ሰላሳ ሁለት ሺ ብር/ ከተስማሙት ልዩነት የፈጠረ በመሆኑ ይህንን ገንዘብ ከፍለው ስም እንዲያዛውሩ ቢጠይቋቸው ላፈጽሙላቸው ያልቻሉ በመሆኑ በመኪናው ተጠቅመው ላያገኙ የሚገባቸውን ጥቅም ያሳጧቸው በመሆኑ፣ ተሽከርካሪው በቀን ብር 6,ዐዐዐ.ዐዐ፣ በወር 18ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ የሚያስገባ በመሆኑ ገቢው በ8 ወር ተባዝቶ ብር 1,44ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ/ አንድ ሚላዩን አራት መቶ አርባ ሺ ብር/ ያጣነውን ገቢ እና ውሉን በማፍረሱ ምክንያት 2ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ/ ሃያ ሺ ብር/ መቀጮ ጨምረው በድምሩ ብር 1,49ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ/ አንድ ሚላዩን አራት መቶ ዘጠና ሺ ብር/ እንዲከፍሉ እንዲወሰንላቸው ክስ ማቅረባቸውን ተመልክተናል።
ተከሣሽም ባቀረቡት መልስ መኪናውን የሸጥኩት ከቀረጥ ነፃ ለኢቨስትመንት ያስገባሁት መሆኑን ነግሬ የቀረጡን ላከፍሉ ተስማምተን ነው። እንድረዳቸው ጠይቀውኝ ልላ ውል ተዋውለናል። ከመኪናው ዋጋ ላይ ብር 21ዐ,ዐዐዐ.00/ ሁለት መቶ አስር ሺ ብር/ ቀንሼላቸው ተዋውለናል። ስለሆነም ክሱ ተገቢ አይደለም። የታጣውን ጥቅም መጠን በተመለከተም ተሽከርካሪው ከ9/7/2ዐዐ7 ዓ.ም. እረፍት እና ሰርቪስ ሳያስፈልግ እና ዕቃ ለመጫን እና ለማውረድ የሚቆምባቸው ቀናቶች ሳይታሰቡ በቀጣይነት የቀን ገቢ ብር 6,ዐዐዐ.ዐዐ ይገኛል በማለት የጠየቁት ገቢ እና በውሉ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ግድታ ያልተወጡት ከሣሾች ሆነው እያለ ውሉ ባለመፈፀሙ ምክንያት የጠየቁት ቅጣት ብር 2ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ የሕግ መሰረት ስለልለው ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን በቃል ማከራከሩን እና የቀን ገቢውን ለማወቅም ተመሳሳይ ሥራ ከሚሰሩ ድርጅቶች በመጠየቅ እና በማስቀረብ ተከሣሽም አስተያየት እንዲሰጡበት በማድረግ መዝገቡን መመርመሩን፣ ከተደረገው ክርክር እና ከቀረበው ማስረጃ በመነሳትም ለደረሰው ጉዳት ተከሣሽ ኃላፊ መሆኑን እና ጉዳቱም መካስ ያለበት በመሆኑ ከሣሾች ያጡትን ገቢ በቀረበው ማስረጃ መሰረት በማስላት እና ከተጠየቀው በመቀነስ ብር 132,ዐዐዐ.ዐዐ/ አንድ ሚላዩን ሶስት መቶ ሃያ ሺ ብር / የ8 ወር ገቢ ተከሣሽ እንዲከፍል መወሰኑን ወደፊት ስም እስኪዛወር ድረስ የሚታሰብ መሆኑን በመግልጽ መወሰኑን የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 226982 ሰኔ 28 ቀን 2ዐዐ8 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የተሰጠው የውሣኔ ግልባጭ ያሳያል።
የስር ተከሣሽ/ ተጠሪ/ ይግባኝ ብለው ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን አስቀርቦ እና ጉዳዩን መርምሮ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው ውል በሕግ በተከለከለ ነገር ላይ የተፈፀመ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 1678/ለ/ እና 1716/1/ መሰረት ህጋዊ ውጤት የሚያስከትል ባለመሆኑ በውሉ የተመከተው ግድታ በአግባቡ አልተፈፀመም በሚል ምክንያት ይ/ባይ በውሉ መሰረት ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት ፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 231/1/ሀ/ መሰረት የክስ ምክንያት የልለው መሆኑን ገልዖ ነገር ግን ውሉ ፈርሶ ግራ ቀኙ ወደነበሩበት ለመመለስ የሚያቀርቡትን ክስ የውሣኔው ግልባጭ የማያግድ መሆኑን በመግለጽ እና የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ በመሻር መዝገቡን መዝጋቱን የመ/ቁ/ 131429 ጥር 25 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የሰጠው ውሣኔ ግልባጭ ያመለክታል።
ይህን የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሣኔ በመቃወም እና በውሣኔው ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል በማለት አመልካቾች የካቲት ዐ5 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም. የተፃፈ የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል። ይዘቱም በአጭሩ፡- ሙሉ የክርክሩን ይዘት በመግለጽ ላታረም ይገባዋል ሲሉ ያቀረቡት የህግ ስህተት የሚያመለክተው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2ዐዐ6 አንቀጽ 13ዐ ቀረጥ ሳይከፈልበት ወደ ሀገር ለኢንቨስትመንት የገባ ዕቃ ላሸጥ ላለወጥ ወይም ለ3ኛ ወገን መተላለፍ እንደሚችል ይደነግጋል። መተላለፍ የሚችልበትን አግባብ ደግሞ ዕቃው ሲሸጥ ያለበትን ቀረጥ በመክፈል እንደሆነ ደንግጓል።
በአመልካቾች እና በተጠሪ መሃከል የተደረገው ውል ደግሞ ውል የተደረገበት ተሽከርካሪ ላይ ያለው ቀረጥ ብር 21ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ ብቻ ነው ወክላችሁኝ ቀረጡን ክፈሉ ብለው ከሽያጩ ብር ላይ ቆርጠን ተክተናቸው ልንከፍል ስንንቀሳቀስ ዕዳው ከተጠቀሰው በላይ 13ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ ጨምሮ ተገኝቷል። አከራካሪ ጭብጥ የነበረው በውሉ ላይ ከተገለጸው በላይ የሆነው የቀረጥ ብር ማን ይክፈል ቀረጡ ባለመከፈሉ ተሽከርካሪው በመቆሙ የታጣ ገቢ መክፈል የማን ግድታ ነው የሚል ነው። አዋጁ የሚያስቀምጠው ከቀረጥ ነፃ የገባን ዕቃ መሸጥ ከተፈለገ ቀረጡን ቅድሚያ ከፍሎ ነፃ ማድረግ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የሰጠው ትርጉም የተሳሳተ ነው እንዲባልልን የሚሉ እና ሰፊ የይታረምልን ጥያቄን አንስተዋል።
አቤቱታውን የመረመረው የሰበር አጣሪ ችሎትም በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የሽያጭ ውል በህግ የተለከለከ ነው በሚል የከሳሾች/አመልካቾች/ የስር ክስ ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ላመረመር ይገባል በማለት በማስቀረቡ ላቀርብ ችሐል። በዚሁ መሰረት የቀረበው አቤቱታ እና የማስቀረቢያ ነጥቡ ለተጠሪ እንዲደርስ እና የመከላከያ መልስ እንደያቀርቡ ከመጥሪያ ጋር የተላከላቸው ሲሆን ተጠሪም ሚያዝያ 16 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም. የተፃፈ መልስ ያቀረቡ ሲሆን አመልካችም የመልስ መልስ አቅርበው ተያይዟል።
የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል እኛም የቀረበውን አቤቱታ አጠቃላይ ጉዳዩን አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
እንደመረመርነውም በግራ ቀኙ መካከል ሁለት ጊዜ የሽያጭ ውል ክርክር ባስነሳው ተሽከርካሪ ላይ የተፈፀመ መሆኑ ያለማከራከሩን እና የመጀመሪያውን ውል ሁለተኛው ውል መተካቱን አመልካቾችም መኪና ከተጠሪ ተረክበውም ሙሉ ገንዘብ ባይሆንም ክፍያ መፈፀማቸውን ፣ የተሸጠው መኪና ግን ለኢንቨስትመንት የገባና ቀረጥ ያልተከፈለበት የነበረ መሆኑ አላከራከራቸውም።ነገር ግን መታየት የሚገባው በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የመኪና ሽያጭ ውል ውል ለማድረግ በተፈቀደ ነገር ላይ የተደረገ ነው ወይንስ አይደለም የሚለውን ሲሆን፣ ይህን አስመልክቶ ከተነሳው ክርክር ጋር አግባብነት ያለው ድንጋጌ አዋጅ ቁጥር 859/2ዐዐ6 አንቀጽ 3ዐ/1/ እንደሚደነግገው ከቀረጥ ነፃ የገባን ተሽከርካሪ መሸጥን የሚከለክል ባይሆንም ነገር ግን መሸጥ ከተፈለገ ቀረጡን ከፍሎ ነፃ ካደረገ በኋላ መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ሲሆን በግራ ቀኙ መካከል ግን የሽያጭ ውሉ የተደረገው ቀረጥ ሳይከፈልበት በፊት ውሉ የተደረገ እና ቀረጥ ያልተከፈለበት መሆኑ ሲረጋገጥ ደግሞ የቀድሞውን የሽያጭ ውል በልላ ውል በመተካት ቀረጥ እንዲከፈልበት የተዋዋሉ መሆኑን የሚያሳይ መሆኑን ከክርክሩ መረዳት ይቻላል።
የህጉ አላማ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው ወደ አገር የሚገቡ ንብረቶች አንድን አላማ ለማሳካት ሲባል እንጂ እንደተፈለገ ላሸጡ ላለወጡ ወይም ለ3ኛ ወገን እንደማንኛውም ንብረት ላተላለፉ የማይችሉ መሆናቸውን በማሰብ ሲሆን ይህን ለመቆጣጠር እና መንግሥትም ይህ ቀረጥ ሳይከፈልበት ወደ አገር የገባ ዕቃ ለታሰበለት አላማ ሳይውል ሲቀር በቀረጥ ነፃ መብት የሚጠቀመው ሰው ፣ወይንም የህግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት በዛ ንብረት ላይ ያለውን የቀረጥ ነፃ መብት በመጠቀም ለልላ እንዳያስተላልፍ ላቆጣጠርበት እና ቀረጡን ማስከፈልና ገቢውን መሰብሰብ ተገቢ መሆኑን በመረዳት ከማንኛውም ዝውውር በፊት ቀረጡ እንዲከፈል አስገዳጅ ሁኔታን ማስቀመጡን እንረዳለን።
ከዚህ ይህ ድንጋጌ ከተቀረፀበት አላማ አንፃር ስንመለከተው ከቀረጥ ነፃ መብትን በመጠቀም ወደ አገር የገባን ዕቃ ወደ ልላ ማስተላለፍ ከተፈለገ ቀድሞ ቀረጡን በመክፈል ነፃ ማድረግን የሚጠይቅ በመሆኑ ይህ ሳይደረግ ወደልላ ማስተላለፍ ግን በራሱ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ጥብቅ ክልከላ የተደረገበት መሆኑን ከድንጋጌው መረዳት የሚቻል በመሆኑ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የመኪና ሽያጭ ውል በህግ ክልከላ በተደረገበት ነገር ላይ የተፀመ ነው በማለት የቀረበውን ክርክር የስር የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ ማድረጉ የሚነቀፍ እና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት የሚያበቃ ሕጋዊ ምክንያት ባለመገኘቱ ላፀና የሚገባው ነው ብለን ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ውሣኔ
በዋለው ችሎት የሰጠው ውሣኔ የተፈፀመበት መሰረታዊ የህግ ስህተት የልለበት ሆኖ በመገኘቱ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በግራ ቀኙ በዚህ ፍርድ ቤት የወጣ ወጪ ካለ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
የውሣኔው ትክክል ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይድረስ።
መዝገቱ ውሣኔ ስላገኘ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.