የውርስ ሰርተፊኬት አንድ ሰው የራሱን ወራሽነት ለማስረዳት የሚወስደው ማስረጃ እንጂ ልሎች ወራሾች አለመኖራቸውን የሚያሳይ ሰነድ ስላለመሆኑ፣ እና በግራ ቀኙ የሟች ወራሾች መሆናቸው በማረጋገጥ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ከማስረጃነት በዘለለ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ በሚያዘው መሰረት ከልሎች ሰዎች ክርክር ተደርጎበት ውሳኔ ያገኘና በፍርድ ያለቀ መቃወሚያ የማይቀርብበት ተደርጎ ላወሰድ የማይገባ ስለመሆኑ፡ፍ/ህ/ቁ. 996/1/ እና እነ አቶ ክንፈ ሐጎስ /3ሰዎች/ እና ወ/ሮ ሃና ሐጎስ ጥቅምት ዓ.ም 69. በኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ ጋብቻ በፍቺም ሆነ በሞት ምክንያት ሲፈርስ ንብረት የሚጣራበት አግባብ በውል ወይም በስምምነት ተለይቶ ባልተቀመጠበት ሁኔታ የባልና ሚስት ሀብት የሚጣራው በቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 113 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት ስለመሆኑ፡ኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/95 በአዋጅ ወ/ሮ ቦንሲቱ ዱፍራ እና ወ/ሮ ታምሪ ረጋሳ XXXIX 83/96 እንደተሻሻለው አንቀጽ 93
No summary available.
ጥቅምት 22 ቀን 2010 ዓ/ም ዳኞች፡- ፀጋይ አስማማው አልማው ወል ሙስጠፋ አህመድ አብርሃ መሰለ ጰውሎስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ወ/ሮ ቦንሲቱ ዱፍራ - ተወካይ አቶ ዓለማየሁ ዱፍራ -ቀረቡ ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ታምሪ ረጋሳ - ተወካይ አቶ ጋረደ አርጋሳ ቀረቡ ።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
የክርክሩ ምክንያት ውርስ ይገባኛል የሚል ነው። የአሁኗ ተጠሪ በወላሶ ወረዳ ፍርድ ቤት ከሳሽ ሲሆኑ አመልካች ደግሞ 1ኛ ተከሳሽ ነበሩ። የክርክሩ መነሻ በአጭሩ የአሁኗ አመልካችና የሥር ሁለተኛ ተከሳሽ የነበሩት ብርቄ ዱፍራ የሟች ባለቤቴ ልጆች ሆነው ንብረትና ይዞታ ከውርስ በማያያዝ የሚስትነት ድርሻዬን ሳያካፍሉኝ ስለያዙ እንዲለቁልኝ የሚል ነው።
የአሁን አመልካች ከሥር ሁለተኛ ተከሳሽ ጋር በመሆን ያቀረቡት መልስ የቀረበው የጋብቻ ውል አባታችን የፈረመ አይደለም በማለት ተከራክረዋል። የወረዳ ፍርድ ቤት ግራ ቀኝ ክርክር አዳምጦ የሰው ማስረጃም ሰምቶ ከሳሽ የተከሳሾች ሟች አባት ሚስት ስለሆኑ የከሳሽን ድርሻ ይልቀቁላቸው በማለት ወስኖአል።
ይህንን ውሳኔ በመቃወም የሥር 1ኛ ተከሳሽ /የአሁኗ አመልካች /ይግባኝ ወስደው የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሳሽ ያቀረቡት የጋብቻ ውል በተከሳሽዋ በኩል የአባታችን ፊርማ አይደለም ተብሎ ተክዶ እያለ በሰነድ ምርመራ ላቦራቶሪ በኩል ሳይለይ የተሰጠው ውሳኔ ጉድለት አለው በማለት የሟች ውል ፊርማ የተካደው ተመርምሮ ውሳኔ እንዲሰጥ በማለት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሽሮ በነጥብ ተመልሷል።
የወላሶ ወረዳ ፍርድ ቤት የጋብቻ ውሉን ለኦሮሚያ ፖላስ ኮሚሽን ከላከ በኃላ የውሉ አርጂናል እንዲቀርብ በፖላስ በኩል በመጠየቁ የሥር ከሳሽ /የአሁኗ ተጠሪ/ አርጂናሉን /ዋናውን/ እንዲያቀርቡ ተጠይቀው ያለው ኮፒ መሆኑን በመግለጻቸው ከሳሽ ለማቅረብ ፍላጎት የልላቸው መሆኑን ተገንዝበን የቀረበው ክስ በማስረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ ከሳሽ /ተጠሪ/ የሟች ዱፍራ ሰርቤሳ ሚስት አይደለችም ብለን የቀረበውን ክስ ውድቅ አድርገናል፣ልላ ግንኙነት ካላቸው በንብረትና በይዞታ ጉዳይ ላይ ያሉዋቸውን መብት ከሳሽ ለማቅረብ ይህ ውሳኔ አያግድም በማለት ወስኗል።
ይህን ውሳኔ የአሁኗ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን የይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይግባኙን ተቀብሎ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኃላ ጋብቻን ማረጋገጥ የሚቻለው በጋብቻ ወረቀት ሲሆን የጋብቻ ወረቀት ማስረጃ በልለ ጊዜ ግን የጋብቻ ሁኔታ መኖሩን በማስረዳት ጋብቻ መኖርን ለማስረዳት እንደሚቻል የአሮሚያ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/95 በአዋጅ ቁጥር 83/96 እንደተሻሻለው አንቀጽ 93 /1/ ይደነግጋል። በይግባኝ ባይ /በአሁኗ ተጠሪ/ እና በተቃዋሚዎች አባት መካከል ጋብቻ መኖሩን ግራ ቀኝ ማስረጃዎች በሥር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር ቀርበው መስክረዋል። በልላ በኩል ሟች ለአሁኗ ተጠሪ ሚስቴ ነች ብለው ሲፈርሙላቸው ማየታቸውን በተጨማሪ ገልጸዋል። ስለሆነም በአሁኗ ተጠሪ እና በሟች ዱፍራ ሰርቤሳ መካከል ከ1998 ዓ/ም ጀምሮ ጋብቻ መኖሩ ስለተረጋገጠ የአሁኗ አመልካች ለተጠሪ የባለቤትነት ድርሻቸውን እንዲለቁላቸው በማለት የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔን በማሻር ወስኗል። የአሁኗ አመልካች ውሳኔውን በመቃወም ይግባኝ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ይግባኙን ተቀብሎ ካከራከረ በኃላ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አፅንቷል። በመቀጠልም የሰበር አቤቱታ ለክልሉ ሰበር ችሎት አቅርበው ተቀባይነትን ሳያገኝ ቀርቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ከከፍተኛ ፍርድ ቤት እስከ ክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት የተሰጡትን ውሳኔ ለማስቀየር ሲሆን አመልካች በሥር ፍርድ ቤቶች ተፈጽሞውብኛል ያሉዋቸውን ዝርዝር የቅሬታ ነጥቦችን አቅርበዋል።
የሰበር አቤቱታውን አጣሪው መርምሮ ተጠሪ ከሟች ጋር በጋራ ያፈሩት ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች በተመለከተ ግራ ቀኙ ባልተከራከሩበትና ምንም ማስረጃ ቀርቦ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ተጠሪ የሚስትነት ድርሻዋን እኩል ትካፈል ተብሎ የመወሰኑ አግባብነት መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ይቅረብ በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው በተወካያቸው በኩል በቀን 13/08/2009 ዓ/ም የተጻፈ መልስ የሰጡ ሲሆን የአመልካች ተወካይም በቀን 18/9/2009 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የነገሩ አመጣጥና የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸውን የሚመስል ሲሆን በውሳኔው ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል ወይስ አልተፈጸመም? የሚል ጭብጥ ተይዞ ጉዳዩ እንደሚከተለው ተመርምሯል። ከላይ እንደተገለጸው ክርክሩ አስቀድሞ እስከ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ክፍተኛ ፍርድ ቤት ድረስ ደርሶ የጋብቻ ውል ተጣርቶ እንዲወሰን የተመለሰ ሲሆን የወረዳ ፍርድ ቤትም የጋብቻ ውሉ ኮፒ ስለሆነ ኦርጂናሉ ካልቀረበ የኦሮሚያ ፖላስ ኮሚሽን ፊርማውን ለመመርመር ያለመቻሉን ገልጾ ተጠሪ ኦርጂናል ውል እስካላቀረቡ ድረስ ተጠሪ የሟች ዱፍራ ሰርቤሳ ሚስት አይደሉም ሲል ወስኗል። በዚህ ክርክር ላይ ትኩረት የተሰጠው ሚስትነት ክርክር ላይ እንጂ በንብረት ክርክር ላይ አይደለም። የንብረት ክርክር የሚደረገው የሚስትነት ሁኔታ መኖሩ ሲረጋገጥ እንጂ አስቀድሞ ላሆን አይችልም። የወረዳ ፍርድ ቤት ተጠሪ ሚስት አይደሉም የሚል ድምዳሜ ላይ የደረሰ በመሆኑ ስለ ንብረት ጉዳይ ያነሳውም ሆነ በውሳኔው ላይ ያሰፈረው ነገር የለም። የከፍተኛ ፍርድ ቤት ግን የተጠሪ ሚስትነት በሁኔታ ተረጋግጧል ካለ በኃላ ንብረትን በተመለከተ ውሳኔ አሳርፎበታል። ይህ አካሄድ ግራ ቀኙን ክርክር እና የክልሉን የቤተሰብ ህግ ድንጋጌን የተከተለ ነው ወይ? የሚለውን መመልከት ተገቢ ይሆናል።
የአሁን አመልካች ተጠሪ ሚስት ናቸው ቢባል እንኳን ተጠሪ ከአመልካች አባታቸው ጋር ያላፈሩት የአባታቸው ግል ንብረታቸው በመሆኑ ተጠሪ አይመለከታቸውም በማለት ያቀረብነው ክርክር በአግባቡ ሳይጣራ ለተጠሪ ንብረት ይገባቸዋል ተብሎ መወሰኑ ተገቢ አይደለም በማለት ይከራከራሉ። ከላይ እንደተገለጸው ይህ ክርክር በወረዳ ፍርድ ቤት የተነሳ ቢሆንም ከሚስትነት ክርክር ውጪ ንብረትን በተመለከተ ያልተጣራና ውሳኔ ያላረፈበት ነው። የኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/95 በአዋጅ ቁጥር 83/96 እንደተሻሻለው የባልና ሚስት ሀብት እንድት እንደሚጣራ በአንቀጽ 112 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ በግልጽ አስቀምጧል። በአንቀጽ 112 (1) መሰረት ባልና ሚስቱ የጋብቻቸው መፍረስ በንብረት በኩል የሚያስከትለውን ውጤት አስመልክተው በሚያደርጉት ስምምነት ወይም በጋብቻ ውላቸው መሰረት ሲሆን በንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት የተመለከተው የጋብቻ ውል ወይም ልላ ስምምነት የልለ ወይም በህግ ፊት የማይፀና ሆኖ የተገኘ እንደሆነ የባልና ሚስት ሀብት የሚጣራው በአንቀጽ 113 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት እንደሆነ የድንጋጌው ንዑስ አንቀጽ 2 በግልጽ ያመለክታል።
በያዝነው ጉዳዩ በተጠሪ እና በሟች ባለቤታቸው አቶ ዱፍራ ሰርቤሳ /በአመልካች አባት/ መካከል ንብረትን በተመለከተ በመካከላቸው የነበረው ጋብቻ በፍቺም ሆነ በሞት ምክንያት ሲፈርስ ንብረት የሚጣራበትን ሁኔታ በውል ወይም በስምምነት ለይተው ባላስቀመጡበት ሁኔታ አመልካች የሟች አባታችን የግል ንብረት ነው በማለት የሚከራከሩበት ንብረት ሳይጣራ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ተጠሪ የጠየቁት ንብረት ይገባቸዋል ሲል የወሰነው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
በመጨረሻም በግራ ቀኙ መካከል የተነሳውን የንብረት ይገባኛል ጥያቄ በተመለከተ ላጣራ የሚገባው በኦሮሚያ ክልል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/95 በአዋጅ ቁጥር 83/96 እንደተሻሻለው በአንቀጽ 113 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት ነው በማለት ይህ ችሎት ድምዳሜ ላይ ደርሷል።
በልላ በኩል አመልካች ከተጠሪ ሚስትነት ጋር አያይዘው ያነሱትን ቅሬታ ነጥብ በተመለከተ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተጠሪ የሚስትነት ሁኔታ በክልሉ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/95 በአዋጅ ቁጥር 83/96 እንደተሻሻለው አንቀጽ 93 /1/ መሰረት የጋብቻ ጽሁፍ ባይኖርም ተጠሪ በልላ አሳማኝ ማስረጃ ስላረጋገጡ ሚስት ናቸው ሲል የደረሰውን ድምዳሜ ይህ ችሎትም የሚስማማበት ነው።
በአጠቃላይ ከዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጀምሮ እስከ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ድረስ ያሉት ፍርድ ቤቶች ንብረትን በተመለከተ የሰጡት ውሳኔ የሚነቀፍ ሆኖ በማግኘታችን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው። ሲጠቃለልም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 35947 በቀን 24/6/2008 ዓ/ም፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ. 239363 በቀን 09/10/2008 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ እንዲሁም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችሎት አጣሪ በመ/ቁ. 249031 በቀን 15/3/2009 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሻሽሐል።
በተጠሪ እና በሟች ባለቤታቸው አቶ ዱፍራ ሰርቤሳ መካከል ጋብቻ ነበረ ተብሎ የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
ከላይ በፍርዱ ላይ በግልጽ እንደተገለጸው ክርክር የተነሳባቸው ንብረቶች በአግባቡ ሳይጣሩ የተጠሪ ሚስትነት ድርሻ ይገባቸዋል ተብሎ የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ተሸሯል።
ተጠሪ እና ባለቤታቸው ሟች አቶ ዱፍራ ሰርቤሳ በጋራ ያፈሩት ንብረቶች መኖር ያለመኖራቸውን፣ ለክርክር ምክንያት የሆኑትን ንብረቶች ማን እንዳፈራቸው? ከጋብቻ በፊት ወይም ከጋብቻ በኃላ የተፈሩ መሆን ያለመሆናቸውን እንዲሁም ተያያዥነት ያላቸውን ፍሬ ነገሮችን በክልሉ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/95 በአዋጅ ቁጥር 83/96 እንደተሻሻለው አንቀጽ 113 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት የወላሶ ወረዳ ፍርድ ቤት አጣርቶ እንዲወስን በፍትሓብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 343 /1/ መልሰናል።
የዚህን ችሎት ወጪና ኪሳራ የግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይድረሳቸው።
መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
ቅ/ሀ የሰበር መዝገብ መስከረም 22 ቀን 2ዐ10 ዓ.ም ዳኞች፦ አልማው ወል ሙስጠፋ አህመድ አብርሃ መሰለ ጳውሎስ ኦርሺሶ ሰናይት አድነው አመልካች:- ወ/ሮ መስከረም ጫካ- የቀረበ የለም ከተባለ በኋላ ቀረቡ ተጠሪዎች፦ 1.አቶ አክላሉ ሽፈራው -ከማረሚያ ቤት ቀረቡ 2.ወ/ሮ ካኦሬ ከተማ- የቀረበ የለም ከተባለ በኋላ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጠ ::
ጉዳዩ፦ የባልና ሚስት ፍቺን ተከትሎ የቀረበ የንብረት ክፍፍልን የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን በዚህ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካች በ1ኛተጠሪ ላይ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም በተጻፈ ያቀረቡት ክስ ከተጠሪ ጋር የነበረን ጋብቻ በፍቺ የፈረሰ ሲሆን ተጠሪ ደብድቦ ጉዳት ስላደረሰብኝ በማረሚያ ቤት የሚገኝ በመሆኑ የጋራ ንብረታችንን ልንካፈል ስላልቻልን በኮልፍ ቀራንዮ ክ/ከተማ 09 ቀበል የቤት ቁጥሩ አዲስ የሆነ ከጋብቻችን በፊት ለምልክት የሚሆን ጅምር ቤት የነበረው በጋብቻችን ወቅት ፈርሶ 4 ክፍል ሰርቪስ ቤት የሰራን ስለሆነ እና በጋራ ያፈራነው የቤት ቁሳቁስ ስላለን እንድንካፈል ይወሰንልኝ በተጨማሪም ተከሳሽ በጋብቻ ላይ ጋብቻ በመፈጸሙ ለጋብቻው መፍረስ ምክንያት ከመሆኑም በተጨማሪ ጋብቻው እንዲፈርስ በመጠየቄ ደብድቦ ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰብኝ ስለሆነ በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ ቁጥር 84 መሰረት የጉዳት ካሳ ብር 50,000.00 እንዲከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል።
የአሁን 1ኛ ተጠሪ የሆኑት የስር ተከሳሽ የሰጡት መልስ ከከሳሽ ጋር ጋብቻ ስንፈጽም የነበረን የጋብቻ ውል የጋራ ሀብታችንን የሚያስረዳልን ነው፤ የክርክሩን ቤት ከሳሽን ከማግባቴ በፊት የሰራሁት የግል ንብረቴ ነው፣ የካሳ ጥያቄውን በተመለከተ በማስረጃ ያልተደገፈ እና በምን ስልት እንደተሰላም ስለማይታወቅ ውድቅ ይደረግልኝ የሚል ሲሆን የአሁን 2ኛ ተጠሪ ባቀረቡት የጣልቃ ገብ ክርክር ከተከሳሽ ጋር በ1988 ዓ.ም ጋብቻ ፈጽመን በኦሮሚያ ክልል የነበረንን ቤት ሽጠን አሁን ክርክር የተነሳበትን ቤት በሰኔ ወር 2002 ዓ.ም ገዝተን ሳለ እኔ የተከሳሽን አባት ለማስታመም ገጠር በሄድኩበት ከሳሽ እና ተከሳሽ በዚህ ቤት አብረው የኖሩበት ቢሆንም ምንም አይነት መሻሻል ያልተደረገበት እና ቤቱንም እኔ እና ተከሳሽ በትዳር እያለን ያፈራነው ስለሆነ የቤቱ ግማሽ ድርሻ እንዳገኝ ይወሰንልኝ በማለት የጣልቃ ገብ ክርክራቸውን አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱም በግራ ቀኙ የቀረበውን ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ የቤቱ ቁሳቁስ ክርክር ያልቀረበበት ስለሆነ ከሳሽ እና ተከሳሽ እንዲካፈሉ ሲወስን የክርክሩን ቤት በተመለከተ ከሳሽ እና ተከሳሽ በባህላዊ ጋብቻ ሲጋቡ በሀብትሽ በሀብቴ በ80 ውል የተጋቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የጋብቻ ውል የቀረበ ስለሆነ፤ የክርክሩን ቤት ከሳሽ ከተከሳሽ ጋር ከመጋባታቸው በፊት ተከሳሽ እና ጣልቃ ገብ በትዳር እያሉ የገዙት መሆኑን እና ከሳሽ እና ተከሳሽ አብረው ሲኖሩበት ቤቱ ላይ የተለያየ እድሳት የተደረገበት መሆኑም ጭምር በምስክሮች ተረጋግጧል በማለት አትቶ ቤቱ የታደሰበትን ወጪ በተመለከተ ከሳሽ ከተከሳሽ ባለቤታቸው ጋር አብረው ሲኖሩ የተጠቀሙበት ግምት ቤቱ ከታደሰበት ወጪ የሚያንስ አይሆንም፤ ስለሆነም አለ የተባለው የእድሳት ወጪ የሚቻቻል ነው ብሎ ቤቱን በተመለከተ ግራ ቀኙ እንዲከፋፈሉ ውሳኔ ሰጥቷል። የካሳ ጥያቄውን በተመለከተ በዚህ መዝገብ የሚታየው የጋብቻ ፍቺ ውጤት በሆነው የጋራ እና የግል ንብረት ላይ በመሆኑ የካሳ ጉዳይ ባለመሆኑ ላወሰን አይገባም ተብሎ ታልፏል።
የአሁን አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፍደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታቸውን ቢያቀርቡም ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ የክርክሩን ቤት የእድሳት ወጪ በተመለከተ የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሳሽ እና ተከሳሽ በቤቱ ሲኖሩ ከተጠቀሙበት ጥቅም ጋር ይቻቻል በማለት የሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል ለቤቱ እድሳት እና ለማሻሻያ ስራው የወጣው ወጪ በባለሙያ ተገምቶ ግማሹን 1ኛ መልስ ሰጭ ለይግባኝ ባይ እንዲከፍሉ እንዲወሰን በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 343(1) መሰረት መልሶ ልኮለታል።
የአሁን አመልካች ለዚህ የፍደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር አቤቱታቸውን ያቀረቡት በነዚህ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱም የክርክሩ ቤት የኔ እና የ1ኛ ተጠሪ እንጂ 2ኛ ተጠሪን የሚመለከት ባልሆነበት ለ3 እንድንካፈል በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ እና ያቀረብኩትን የካሳ ጥያቄ የስር ፍርድ ቤቶች ሳይወስኑ ማለፋቸው መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የፈጸሙ ስለሆነ ላታረም ይገባል የሚል ነው።
የሰበር አጣሪው ችሎትም መዝገቡን መርምሮ ቅሬታው ለሰበር ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ የጽሁፍ መልስ እና የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል። የጉዳዩ አመጣጥ አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም በግራ ቀኙ የቀረበውን የሰበር አቤቱታ ግራ ቀኙ በስር ፍርድ ቤቶች ካቀረቡት ክርክር እና ማስረጃ አንጻር የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት መኖር ያለመኖሩን ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሰበር አጣሪው ችሎት ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረነዋል።
የአሁን አመልካች የሰበር አቤቱታ የክርክሩን ቤት በተመለከተ የኔ እና የ1ኛ ተጠሪ ነው በማለት የሚከራከሩ ሲሆን ቤቱ ግን የአሁን አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ጋብቻ ከመመስረታቸው በፊት የተሰራ መሆኑን በማመን አመልካች በሰጡት ቃል የተረጋገጠ ፍሬ ጉዳይ ነው። አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ይህንን ቤት በሀብትሽ በሀብቴ የባህላዊ የጋብቻ ውል የግራ ቀኙ የጋራ ሀብት እንዳደረጉት እና በጋብቻቸው ጊዜም በክርክሩ ቤት ላይ ተጨማሪ ስራ መስራታቸው እና አመልካች እና 1ኛ ተጠሪም ከመጋባታቸው በፊት 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በጋብቻ የነበሩ መሆናቸው በስር ፍርድ ቤቶች የፍሬ ነገር እና የማስረጃ ምዘና ተደርጎ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው።
በመሆኑም 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በጋብቻ በነበሩበት ጊዜ የተፈራ ንብረት መሆኑ በመረጋገጡ፣ በፍደራሉ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 62(1) መሰረት ባል እና ሚስት በጋብቻቸው ጊዜ የተፈራ ንብረት የ1ኛው ተጋቢ የግል ሀብት ነው እስካለተብለ ድረስ የጋራቸው እንደሆነ የሚገመት መሆኑን የሚደነግግ ሲሆን በተያዘው ጉዳይ ንብረቱ በተጠሪዎች ጋብቻ ጊዜ የተፈራ መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ የተጠሪዎች የጋራ ንብረት እንደሆነ በህጉ የሚገመት ሲሆን በ1ኛ ተጠሪ በኩል የክርክሩ ቤት የግል ንብረቴ ነው በማለት ተቃራኒ ክርክር ያልቀረበ ስለሆነ፣ አመልካችም በቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 42(1) ተጋቢዎች ንብረታቸውን በተመለከተ በጋብቻ ውል መወሰን እንደሚችሉ በተደነገገው መሰረት ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ባደረጉት የጋብቻ ውል መነሻነት እና ከጋብቻቸው በኃላ በቤቱ ላይ በሰሩት ተጨማሪ ስራ የቤቱ የጋራ ባለሀብትነትን ይመሰርታሉ።
በመሆኑም ግራ ቀኙ ተከራካሪዎች በክርክሩ ቤት ላይ የባለቤትነት መብት ያላቸው መሆኑ በፍሬ ነገርም ሆነ በህግ የተረጋገጠ ጉዳይ ሲሆን ክፍፍሉን በተመለከተ 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በነበራቸው ጋብቻ ላይ ህግ የሚከለክለውን በጋብቻ ላይ ጋብቻ በመፈጸም አመልካችን ያገቡ እና አመልካችም 1ኛ ተጠሪ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ትዳር እንዳላቸው ሳያውቁ ያገቧቸው እና 2ኛ ተጠሪም 1ኛ ተጠሪ ባለቤታቸው ልላ ትዳር መመስረታቸውን ሳያውቁ በላያቸው ላይ አመልካችን ያገቡባቸው ከመሆኑ አንጻር በስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተወስኖ በስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጸናው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በማግኘታችን የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ላሻሻል ይገባል ብለናል። ልላው እና በአመልካች የቀረበውን የጉዳት ካሳ ጥያቄን በተመለከተ የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ችሎቱ የባልና ሚስት ፍቺን ተከትሎ የሚመጣ የንብረት ክፍፍልን የሚመለከት በመሆኑ የጉዳት ካሳ ጥያቄውን በዚህ ችሎት መወሰን አይቻልም በማለት ሳይወስን ማለፉ እና የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ምንም ሳይወስን ማለፉ የጉዳት ካሳው ጥያቄ ከጋብቻ ፍቺው ጋር ተያይዞ የቀረበ እና ጉዳቱም የደረሰው ከፍቺው ጋር ተያይዞ መሆኑን አመልካች በስር ክርክራቸውም እያነሱት የቤተሰብ ህጉም ይህንኑ የካሳ ክፍያ ላወሰን እንደሚገባ ደንግጎት እያለ እና አመልካችም ይህንኑ የቤተሰብ ህግ ላይ የተደነገገውን ድንጋጌ ጠቅሰው አቅርበው እያለ የስር ፍርድ ቤቶች በክርክሩ ላይ ተገቢውን ሳይወስኑ የሰጡት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ስላገኘነው ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 19 ቀን 2ዐዐ8 ዓ.ም ተሰጥቶ በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 30 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሻሽሐል።
በአጠቃላይ የንብረት ክፍፍሉን በተመለከተ የክርክሩን ቤት ግምት 25 ፐርሰንት ለአሁን 1ኛ ተጠሪ ሆኖ የተቀረውን 75 ፐርሰንት አመልካች እና 2ኛ ተጠሪ እኩል ይካፈሉ ብለናል።
የጉዳት ካሳ ጥያቄውን በተመለከተ የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አከራክሮ እና በማስረጃ አጣርቶ የመሰለውን እንዲወስን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 343(1) መሰረት መልሰንለታል ይፃፍ።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ በየደረጃው ለሚገኙ የስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
No topics extracted.