የፍ/ብ/ስ/ስ/ቁ. 41፣358 67. በውርስ የተላለፈን የመንግስት ንግድ ቤት የማከራየት መብትን ከወራሾች መካከል አንዱ ያለ ከተማ አስተዳደሩ እውቅና ያከራየ እንደሆነ ፤ የተከራይነት መብት የሚቌረጠው ያከራየው ወራሽን በተመለከተ ብቻ እንጂ ልሎች እሱ በሞግዚትነት የሚያስተዳድራቸው ወራሾች የመከራየት መብታቸው የሚቀጥል ስለመሆኑና ፤አከራዩ ሞግዚታቸው ባከራያቸው ወገኖች ላይ በንግድ ቤት የኪራይ ውል መነሻነት ክስ ለማቅረብ የሚያበቃ መብትና ጥቅም ያላቸው ስለመሆኑ፡- XXXVIII
No summary available.
ታህሳስ 26 ቀን 2ዐ1ዐ ዓ.ም.
ዳኞች--- ዳኜ መላኩ ተኽላት ይመስል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- 1ኛ አቶ መዚድ ተስፋዬ አህመድ 2ኛ አቶ መርዙቅ ተስፋዬ አህመድ ጠ/ወልደሰስላሴ ብርቱ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዘይነባ ለካ ሱሩር ጠ/መሀዲ ሁሴን ቀረበ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዳይ የጀመረው በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን በስር ከሣሽ አመልካቾች ሆነው ተከሣሽ ተጠሪ በመሆን በኪራይ ውል መነሻነት ተከራክረዋል።
በስር ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረው ክስ የሚያመለክተው በቂ/ክ/ከ/ወረዳ 18 ቁጥሩ ዐ63/መ/ ተመዝግቦ የሚያታወቀውን የፋብሪካ ውጤቶች የህንጻ መሳሪያ ንግድ ድርጅት የከሣሾች እህት ከሆነችው ወ/ሮ አሰለፈች ተስፋዩ በወር ብር 5,ዐዐዐ/አምስት ሺ ብር/ ከሚያዝያ ዐ3/2ዐዐ3 ጀምሮ ተከሣሾች መከራየታቸውን ሆኖም ከሚያዝያ ዐ3/2ዐዐ4 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥቅምት ዐ2/2ዐዐ5 ዓ.ም.ድረስ የአንድ ዓመት ኪራይ ብር 6ዐዐዐዐ.ዐዐ /ስድሣ ሺ ብር/ አልከፈሉም። በተጨማሪም ጥቅምት ዐ3ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም.እስከ ጥር 23/2ዐዐ5 ዓ.ም. ድረስ ያለውንም ኪራይ ብር 18,333.33 አልከፈሉም። ተከሣሽ እንዲከፍሉ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ለመክፈል ፈቃደኛ አይደሉም ስለሆነም በድምሩ 78,333.33 / ሰባ ስምንት ሺ ሶስት መቶ ሰላሳ ሶስት ብር ከሰላሳ ሶስት ሣንቲም/ ከወለድ ጋር እንዲከፍሉ ይወሰንልን በማለት ጠይቀዋል።
ተከሣሽ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ከጥቅምት ዐ3/2ዐዐ4 ጀምሮ ያለውን የኪራይ ገንዘብ እንዲከፈላቸው የጠየቁ ሲሆን ክሱን ያቀረቡት 6 ወር ካለፈው በኋላ በመሆኑ በይርጋ ይታገዳል። የንግድ ቤቱ የከተማው አስተዳደር ንብረት ስለሆነ መቅረብ ያለበት በከተማ አስተዳደሩ ፍርድ ቤት ነው፣ ከሣሾች ቤት አላከራዩንም ያከራዩን እህታቸው በመሆናቸው ቤቱ ለአሁን ተከሣሽ ይገባል በማለት አስተዳደሩ የወሰነው በአግባቡ በሚል እንጂ የኪራይ ውል አለ ብሎ አልወሰነም ስለሆነም የኪራይ ገንዘብ ለመጠየቅ የሚያስችል ውል ስለልላቸው ክሱን ለማቅረብ መብትና ጥቅም የላቸውም በማለት ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ግራ ቀኙን በቃል አከራክሯል። ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን ያለው መሆኑን ከወሰነ በኋላ ቀሪውን መቃወሚያ አስመልክቶ ተከሣሽ ኪራዩን የተከራየሁት ከከሣሾች እህት ወ/ሮ አሰለፈች እንጂ ከከሣሾች አይደለም በሚል የተከራከሩ ሲሆን የኪራይ ውሉ ላይ ወ/ሮ አሰለፈች በስሜ ተመዝግቦ የሚገኘውን የንግድ ድርጅት ለተከሣሽ አከራይቻለሁ የሚል ተገልጿል እንጂ ከሣሾችን በመጨመር ወይም ሞግዚትና አስተዳዳሪ መሆናቸውን በመግለጽ የተፈፀመ ባለመሆኑ ከሣሾች ይህን ውል መሰረት በማድረግ ክስ ያቀረቡት የመክሰስ መብት ሳይኖራቸው ነው በማለት በብይን መዝገቡን መዝጋቱን የመ/ቁ/ 22834 የካቲት 18 ቀን 2ዐዐ8 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የተሰጠው የብይን ግልባጭ ያሣያል።
አመልካቾች ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢሉም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 177126 ሐምል 26 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ይግባኝ ቅሬታውን በትዕዛዝ ውድቅ ማድረጉን ተመልክተናል።
አመልካቾች በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ ሲሉ ጥቅምት 21 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም.
የተፃፈ የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል። ይዘቱም በአጭሩ ፡- አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት የኪራይ ገንዘብን አስመልክቶ ባቀረቡት ክስ ላይ መብትና ጥቅም ያላቸው መሆኑን፣ ምክንያቱም የንግድ ቤቱ የተከራይነት መብት የመጣው ከአመልካቾች ወላጆች ከአቶ ተስፋዩ አህመድ ናጂ እና ከወ/ሮ በላይነሽ ምሩሪ እንደሆነ የኪራይ ውሉ በማስረጃነት ቀርቧል።
የወራሽነት ማስረጃንም አቅርበዋል፣ የአውራሻቸውን መብት እና ግድታ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 826/2/ መሰረት ለወራሾች ተላልፏል። አመልካቾች አካለ መጠን ባላደረሱበት ጊዜ እህታቸው ወ/ሮ አሰለፈች ተስፋዩ አካለመጠን ላላደረሱት ልጆች ሞግዚት ለመሆናቸው ሐምል 3ዐ ቀን 1995 ዓ.ም. በመ/ቁ/ 19ዐ4/95 የተሰጠ ውሣኔን በማቅረብ ተረጋግጧል። ወ/ሮ አሰለፈች በውርስ የመጣውን ክርክር ያስነሳውን የንግድ ድርጅት ከቂ/ክ/ከ/ወ/8 ጋር ሲዋዋሉ እነ አሰለፈች ተስፋዩ በማለት የተከራዩ መሆኑን ማስረጃ ቀርቧል። ተጠሪ ወራሽና ሞግዚት ከሆኑት ከወ/ሮ አሰለፈች ተስፋዩ በተከራዩት የንግድ ቤት ላይ መብትና ጥቅም ያላቸው ስለመሆኑ በአ.አ.ከተማ የመ/ደ/ፍ/ቤት ቂ/ክ/ከ/ ምድብ ችሎት በመ/ቁ/ ዐ7615 እና በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ሁለት መዛግብት ተጣምረው በተሰጠው ፍርድ ቁጥሩ ዐ63/መ/ ያሁን አመልካቾች ወላጆች አቶ ተስፋዩ አህመድና ወ/ሮ በላይነሽ ምሩሪ በጋብቻ እያሉ ለንግድ አገልግሎት በጋራ ተከራይተውት የነበረ መሆኑን የይግባኝ ባይ ወላጆች ሲሞቱ የተከራይነቱ መብት በሕይወት ላሉት ልጆቻቸው የተላለፈ መሆኑን፣ አመልካቾች አቅመ አዳም ባለመድረሳቸው እነ አሰለፈች ተስፋዩ በሚል እህታቸው ያደረጉት የኪራይ ውል ልሎችንም የሚጭምር በመሆኑ መብት ያላቸው መሆኑን ስለሚያሳይ ስር ፍርድ ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ተብሎ እንዲታረምላቸው በጠበቃቸው አማካይነት የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል።
አቤቱታውን የመረመረው የሰበር አጣሪ ችሎትም አቤቱታው ለሰበር ያስቀርባል በሚል ጭብጥ ይዞ በመላኩ መዝገቡ ለችሎት ቀርቧል። አቤቱታው ከማስቀረቢያ ነጥቡ ጋር ለተጠሪ ደርሷቸው መልስ እንዲያቀርቡ ከመጥሪያ ጋር የተላከላቸው ሲሆን ሚያዝያ 12 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም. የተፃፈ መልስ አቅርበው ተያይዟል። ይዘቱም ከማስቀረቢያ ነጥቡ አኳያ ብቻ እንደተመለከትነው ፡- በወ/ሮ አሰለፈች በስሟ ላደረገችው የኪራይ ውል አመልካች እንድት ከእኔ ጋር የቤት ኪራይ ውል አለኝ በማለት እንደሚችል ያላስረዳና ላያስረዳም ስለማይችል የሰበር ችሎቱ ውሣኔውም ቢሆን ቤቱ ለአመልካች ይገባል ከማለት በቀር በእኔ እና በአመልካች መካከል ውል ማቋቋም ስለማይችል የአመልካችን ክስ በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ውድቅ መደረጉ አግባብ ነው በማለት አቅርበዋል።
አመልካቾች የመልስ መልስ አቅርበው ከመዝገብ ተያይዟል።
የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል እኛም የቀረበው አቤቱታ አጠቃላይ ክርክር እና አግባብነት ያለውን የህግ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ መርምረናል።
እንደመረመርነውም አመልካቾች በስር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ የኪራይ ገንዘብ ይከፈለን የሚል ሲሆን ተጠሪ ደግሞ የኪራይ ውል ማድረጋቸውን ገልፀው ነገር ግን ከአመልካቾች ጋር ሣይሆን ከእህታቸው ጋር የተዋዋልኩ እና ውሉም እነሱን ስለማይገልጽ ክስ የማቅረብ መብት የላቸውም ተብሎ ውድቅ እንዲሆንላቸው ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱም በተከሣሽ ላይ ክስ ለማቅረብ መብትና ጥቅም የላችሁም በማለት በብይን ክሱን ውድቅ አድርጐታል። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ማጽናቱን ተመልክተናል።
የአመልካቾች ጥያቄ በአጣሪው ከተያዘው ጭብጥ አኳያ ስንመለከተው ክርክር የተነሳበት የንግድ ድርጅት ከአመልካቾች ወላጆች መብቱ በውርስ የተላለፈላቸው ሲሆን በጊዜው ህጋዊ ተግባር ለመፈፀም አመልካቾች አቅመ አዳም ያልደረሱ በመሆኑ ወራሽነታቸውን ካረጋገጡ በኋላ በእህታቸው ወ/ሮ አሰለፈች ተስፋዩ አማካይነት ከአስተዳደሩ ጋር የኪራይ ውል በንግድ ቤቱ ላይ “እነ ወ/ሮ አሰለፈች ተስፋዩ” በሚል የተዋዋሉ በመሆኑ ተረጋግጧል።
ወ/ሮ አሰለፈች የአመልካቾች ሞግዚት እና ወራሽም መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን በዚህ ክርክር ባስነሳው የንግድ ቤት ላይ ያላቸው መብት ከልሎች ወራሾች ጋር እኩል ሲሆን ለልላ ሰው ንብረቱን በሚያከራዩበት ጊዜ ይህንን የሞግዚትነት ሥልጣን ተላብሰው እንጂ በራሳቸው ሙሉ ስልጣን ላሆን አይችልም። ምክንያቱም ግለሰቧ በዛ የንግድ ቤት ላይ ከልሎች ወራሾች ጋር እኩል ድርሻ ያላቸው በመሆኑ ነው።
በዚህ ክርክር ባስነሳው የንግድ ቤት ላይ በስር ፍርድ ቤት በልላ መዝገብ ክርክር ተደርጐበት እስከ ፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ደርሶ የነበረ እና በሰ/መ/ቁ/ 84ዐ37 በሆነው መዝገብ ላይ ግንቦት 19/2ዐዐ5 ዓ.ም. ውሣኔ ተሰጥቶበታል።
በዚህ የሰበር መዝገብ ላይ ፍርድ ቤቱ ለክርክሩ በሰጠው ማጠቃለያ ውሣኔ የንግድ ቤቱን የአመልካቾች ሞግዚት ለልላ 3ኛ ወገን አሳልፈው ያከራዩት መሆኑን እና በመመሪያውም ያለአስተዳደሩ እውቅና አሳልፈው ማከራየታቸው የተከራይነት መብቱን ወደ ተከራየው ሰው የሚያዛውር በመሆኑ ወ/ሮ አሰለፈች ይህንን በውርስ ለወራሾች የተላለፈላቸውን ንግድ ቤት ያለአስተዳደሩ እውቅና ማከራየታቸው በራሳቸው በኩል ያለውን የተከራይነት መብት የሚያቋርጥባቸው እንጂ የልሎች በሞግዚትነት የሚያስተዳድሯቸውን ወራሾች መብት የሚነካ መሆን እንደልለበት በመግለጽ ፣ በሰበር መዝገቡ ላይ አመልካች በዚህ በያዝነው መዝገብ ደግሞ ተጠሪ የሆኑት ግለሰብ በመመሪያው መሰረት ንግድ ቤቱን ከአስተዳደሩ በቀጥታ በራሷ ስም ለመከራየት እንደመብት ጥያቄ ለማቅረብ የማያስችላት ሁኔታ አይኖርም ስለሆነም አስተዳደሩ የልሎች ወራሾችን የተከራይነት መብት ላያስቀጥል በሚያስችል መልኩ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱ በአግባቡ ነው በማለት በስር የከተማው ሰበር ሰሚ ችሎት ማጽናቱን የውሣኔው ግልባጭ ያሳያል።
ከዚህ የምንረዳው ወ/ሮ አሰለፈች በስማቸው በሞግዚትነት የሚያስተዳድሯቸው ወራሾችን ንብረት ለተጠሪ አከራይተው እንኳን ቢሆን የተከራይ አከራይ መመሪያ ወ/ሮ አሰለፈችን ከሚመለከት በስተቀር ልሎች ወራሾችን የሚመለከት እንደማይሆን እና ከአስተዳደሩ ጋር ልሎች ወራሾች የመከራየት መብታቸው የሚቀጥል መሆኑን ነው። ምክንያቱም ወ/ሮ አሰለፈች ያከራዩት ንብረት በግላቸው መብት ያገኙበት ሣይሆን የልሎችንም የሚጭምር በመሆኑ ተቀባይነት አይኖረውም።
በዚህ ረገድ አመልካቾች በውርስ ባገኙት መብት መነሻነት የኪራይ ገንዘብ ተጠሪ እንዲከፍሉ የጠየቁ በመሆኑ ክርክር ባስነሳው የንግድ ቤት የኪራይ ውል መነሻነት ክስ በተጠሪ ላይ ለማቅረብ የሚያበቃ መብትና ጥቅም ያላቸው በመሆኑ መብትና ጥቅም የላችሁም በማለት የስር ፍርድ ቤት በብይን መዝገቡን መዝጋቱ እና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ይህንን ስህተት ሳያርም ማጽናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ በመገኘቱ ላሻር የሚገባው ነው ብለን ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
አመልካቾች ክስ ለማቅረብ መብትና ጥቅም አላቸው ብለናል።
የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በብይን የዘጋውን መ/ቁ/ 22834 በማንቀሳቀስ አመልካቾች ያልተከፈለን የኪራይ ገንዘብ ተጠሪ ላከፍሉን ይገባል በማለት ያቀረቡትን ክስ ከተጠሪ ጋር በሞግዚትነታቸው መነሻነት የኪራይ ውል የፈፀሙትን ወ/ሮ አሰለፈች ተስፋዩን በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 41 መሰረት ወደ ክርክር እንዲገቡ በመጥራት በፍሬ ነገር ላይ በማከራከር ላወሰን የሚገባው በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 341/1/ መሰረት አከራክሮ ተገቢ ነው ያለውን እንዲወስን መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት በግራ ቀኙ የወጣ ወጪ ካለ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
የውሣኔው ትክክል ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይድረስ።
መዝገቡ ውሣኔ ስላገኘ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.