በፍርድ ቤት ቀርቦ የፀደቀ ወይም ተቀባይነት ያገኘ የጉዲፈቻ ውልን መሰረት በማድረግ ወራሽነትን ያረጋገጠ ወገን የውርስ ንብረት ድርሻን ለማግኘት ያቀረበው ጥያቄ ቀድሞ በጉዲፈቻ ውል የፀደቀበት ውሳኔ መብቴ ተነካ በሚል ወገን በቀረበ መቃወሚያ መሰረት እንዲፈርስ እንዲሻር ባልተደረገበት የውርስ ድርሻ ክፍያ ጥያቄው ውድቅ ማድረግ ህግን መሰረት ያላደረገ በለጠ ነጋሽ እና እጅጋየሁ ላቀው XXXVII የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ ቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/1995 በአዋጅ ቁጥር 83/96 እንደተሻሻለ አንቀጽ
No summary available.
መስከረም 25 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- ፀጋይ አስማማው አልማው ወል ሙስጠፋ አህመድ አብርሃ መሰለ ጳውሎስ ኦርሺሶ አመልካች፡- አቶ በለጠ ነጋሽ-ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ እጅጋየሁ ላቀው-ጠበቃ ጎሳዬ ነጋሽ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዳዩ በመጀመሪያ የታየው በኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ሱሉልታ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች የህግ አሳዳጊዬ የሆኑት ወ/ሮ በለጤ ግዛው ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቷ ሟች አሳዳጊዬ በህይወት ዘመንዋ ያፈራችውን የግል ቤትዋን እና የገጠር እርሻ መሬት ከአሁንዋ ተጠሪ ከአሳዳጊዬ ልጅ ጋር እኩል እንድንካፈል እንዲውሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል።
ተጠሪም ለአቤቱታው በሰጡት መልስ የሟች ንብረትም ይሁን ይዞታ ሁሉም በስጦታ ውል አግኝቻለሁ፤አመልካችም በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ የጉዲፈቻ ውሉ ስላልፀደቀ የመውረስ መብት የለውም በማለት ተከራክረዋል። የስር ፍርድ ቤትም የተጠሪን መቃወሚያ በብይን ውድቅ በማድረግ የሟች ሀብትና የገጠር ይዞታ ከተጠሪ ጋር እኩል እንዲካፈሉ ሲል ወስኗል።
የአሁን ተጠሪ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም በፊንፊኔ ዙሪያ ለኦሮሚያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙ ክርክር ከሰማ በኋላ በሟችና በአመልካች መካከል በ1996 ዓ.ም የተደረገው የጉዲፈቻ ውል በኦሮሚያ ቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/1995 እና 83/1996 መሰረት እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ሰው የጉዲፈቻ ውል ሲደረግም ሆነ ፍርድ ቤት ሲያፀድቅ እድሜው 27 አመት እንደሆነ የውል ሰነድ ራሱ ያሳያል፤ ይህ ደግሞ ለህግ ተቃራኒ በመሆኑ አንድም መብት መስጠት አይችልም በማለት ፀድቋል የተባለው የጉዲፈቻ ውል ውድቅ በማድረግ አመልካች ከገጠር መሬት ይዞታ ውጭ ያለው የሟች ንብረት መውረስ አይችልም፤በልላ በኩል የገጠር መሬትን አስመልክቶ የሟች ቤተሰብ ከሆነ የመውረስ መብት ያለው ስለሆነ ይህ ደግሞ በማስረጃ ከተጣራ በኋላ እንዲወሰን ጉዳዩን ለወረዳ ፍርድ ቤት መልሶታል።
የአሁን አመልካች የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙ ክርክር ከሰማ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ስህተት ያለበት ሆኖ አልተገኘም በማለት በውሳኔ አጽንቶታል። በመቀጠል ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኘም።
የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። አመልካች የካቲት 8 ቀን 2009 ዓ.ም በፃፉት አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል የሚሉባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ በመደረጉ ተጠሪ መልስ እንዲሰጡበት በታዘዘው መሰረት ሚያዚያ 20 ቀን 2009 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። አመልካችም አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር መርምረናል። እንደመረመርነውም በዚህ ጉዳይ ወራሽነቱን ያረጋገጠበት መዝገብ ሳይሻር የውርስ ሀብት ለመጠየቅ ባስከፈተው መዝገብ ወራሽነት በስር ፍርድ ቤቶች ውድቅ በማድረግ መወሰናቸው በአግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝተናል።
ከመዝገቡ መገንዘብ የተቻለው ሟችና አመልካች በ1996 ዓ.ም የጉዲፈቻ ስምምነት ማድረጋቸው፤ስምምነቱም ለፍርድ ቤት ቀርቦ በመ/ቁ.498/96 ስምምነቱ ህጋዊ መሆኑን በማረጋገጥ ውሳኔ የተሰጠበት መሆኑን፤ይህ ውሳኔ መቃወሚያ ቀርቦበት ያልተሻረ መሆኑን ከክርክሩ ሂደትና ከስር መዝገብ ግልባጭ ተገንዝበናል። የአመልካች ጥያቄ የጉዲፈቻ ውሳኔ ስልጣን በተሰጠው ፍርድ ቤት የተወሰነ በውርስ አቤቱታ በተከፈተ መዝገብ እንደማስረጃ የቀረበውን ሰነድ መቃወም አትችልም፤የጉዲፈቻ ውሳኔ ስህተት ቢኖረው እንኳን በተወሰነበት መዝገብ ላይ መቃወሚያ ማቅረብ የምትችልበት እንጂ በዚሁ የውርስ ፋይል ላይ ማቅረብ የማይገባውን በመቀበል በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ ላታረም ይገባል የሚል ሲሆን ተጠሪ ደግሞ አመልካች በተሻረና ለጉዲፈቻነት በህግ በተቀመጠው ከ18 ዓመት እድሜ በላይ በ27 ዓመቱ የተደረገን የጉዲፈቻ ውል መነሻ በማድረግ ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት የልለው በመሆኑ ከክልሉ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እሰከ ክልሉ ሰበር ችሎት ድረስ የተሰጠውን የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ህግን መሰረት ያደረገ ስለሆነ ላፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል። እዚህ ላታይ የሚገባው ነጥብ የጉዲፈቻ ውል ውሳኔ ፀንቶ ባለበት ሁኔታና ሳይሻር በውርስ ንብረት ክፍፍል በተጠየቀበት በልላ መዝገብ የመታየቱ ጉዳይ ነው። የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ ቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/1995 በአዋጅ ቁጥር 83/96 እንደተሻሻለ አንቀጽ 202 መሰረት ከ18 ዓመት እድሜ በላይ የጉዲፈቻ ልጅ መሆን አንደማይችል ይደነግጋል፡ አመልካችም እድሜው 27 ዓመት የነበረ መሆኑ አከራካሪ አይደለም። ሟች ወ/ሮ በለጤ ግዛው አመልካችን የጉዲፈቻ ውል ለፍርድ ቤት ቀርቦ ተቀባይነት አግኝቷል። ፣.ይህ ውሳኔ መብቴን ይነካል የሚል ወገን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.41፤358 በክርክሩ ገብቶ መቃወም ወይም ውሳኔ ከተሰጠ በኋላም ቢሆን መቃወሚያ በማቅረብ መጀመሪያ የተሰጠው ውሳኔ እንዲሰረዝ ማድረግ እየተቻለ አመልካች ወራሽነቱን በማረጋገጥ የሟች ንብረት ድርሻውን በጠየቀበት መዝገብ ላይ የጉዲፈቻ ውል አስመልክቶ የተሰጠ ውሳኔ ላይ ህጋዊ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ በፍርድ ቤት የፀደቀ /የተሰጠ/ ውሳኔው ሳይሰረዝ የተሻረበት አግባብ ስነስርዓት ህጉን ያልተከተለ በመሆኑ ላታረም የሚገባ ሆኖ አግኝተነዋል።
ሲጠቃለል ስር ፍርድ ቤቶች በዚህ ጉዳይ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ ሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በሱሉልታ ወረዳ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 14 ቀን 2007 ዓ/ም ተሰጥቶ በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ህዳር 14 ቀን 2008 ዓ/ም በመሻር የሰጠው ውሳኔ በኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ የካቲት 3 ቀን 2008 ዓ/ም እና በኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ ህዳር 3 ቀን 2009 ዓ/ም በውሳኔ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽለዋል።
የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች የሟች ወ/ሮ በለጤ ግዛው የጉዲፈቻ ልጅ ስላልሆነ ላወርስ አይችልም በማለት የሰጡት የውሳኔ ክፍል በመሻር በሱሉልታ ወረዳ ጎርፎ ቀበል ውስጥ የሚገኝ መኖሪያ ቤት የመውረስ መብት ስላለው ከተጠሪ ጋር እኩል ላካፈሉ ይገባል ብለን ወስነናል።
የስር ፍርድ ቤቶች በገጠር እርሻ መሬት ይዞታ በተመለከተ የሱሉልታ ወረዳ ፍርድ ቤት የመ/ቁ.36014 የሆነውን በማንቀሳቀስ የገጠር መሬት አዋጅ በሚያዘው መሰረት የግራ ቀኙ ማስረጃ እንደገና በማጣራት ውሳኔ እንዲሰጥበት የተመለሰው የውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
No topics extracted.