በግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰበት መኪና በወቅቱ ተጠግኖ ወደ ስራ ቢመለስ በአደጋው ምክንያት የተቋረጠን የገቢ መጠን ለመቀነስ ወይም ለማቅለል በቅን ልቦናና በማስተዋል የተደረገ እንቅስቃሴ ከልለ በደረሰ ጉዳት መጠን በሙሉ ካሳ ላጠየቅ ስላለመቻሉ፡በፍ/ብ/ህ/ቁ.2098 /1/፤2097(2) XXXIII
No summary available.
መስከረም 24 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ሙስጠፋ አህመድ አብርሃ መሰለ ጳውሎስ ኦርሺሶ ሰናይት አድነው አመልካቾች፡-
ተጠሪ፡- አቶ መላኩ መኬ ማዶ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው አመልካቾች የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልን በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዳዩ በመጀመሪያ የታየው በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ የሰልዳ ቁጥር ኮድ 03-79472 አ.አ ሚኒባስ መኪናቸው ጥቅምት 5 ቀን 2006 ዓ.ም በ1ኛ አመልካች ይሽከረከር የነበረውና በ2ኛ አመልካች እና በስር 3ኛ ተከሳሽ የሆነው ኖህ የደረቅ ጭነት አ.ማ ተመዝግቦ የሚገኘው የሰልዳ ቁጥር ኮድ 03-27047 ኢት የተሳቢ ቁጥር 03-03870 ኢት የሆነው መኪና ላይ የተጫነው ኮንቴይነር በመልስ ሰጪ መኪና ላይ ወድቆ ከባድ ጉዳት በማድረሱ የስር ከሳሽ መኪናው የደረሰበት ጉዳት ለማስገመት ያወጣውን ብር 5,500.00 (አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር) አደጋው የደረሰበት የሰልዳ ቁጥር 03-79472 አ.አ የሆነውን ላጠገን የማይችል በመሆኑ የመኪናው ከአደጋው በፊት የገበያ ዋጋው ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ጉዳት የደረሰበት መኪና የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ይህ መኪና በአማካይ በቀን ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) የሚያስገባ በመሆኑ ጉዳቱ ከደረሰበት ከጥቅምት 5 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ይህ ክስ እስከቀረበበት ሕዳር 10 ቀን 2006 ዓ.ም ድረስ ለ35 ቀናት ያጣውን ብር 10,500.00 (አስር ሺህ አምስት መቶ ብር)፤ ከህዳር 11 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ የስር ከሳሽ ያጣውን ጥቅም የቀን ገቢ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በዚህ ክስ ምክንያት የወጣውን ወጪ እንዲከፈላቸው እንዲወሰንላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል።
አመልካቾች ለቀረበው ክስ የሰጡት መልስ በተጠሪ መኪና ላይ ጉዳት መድረሱን አምነው 1ኛ አመልካች አደጋ የደረሰበት መኪና ጉዳት ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ጥገና ተደርጎለት ወደነበረበት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲመለስ እና ተጠሪ ያጣውን የእለት ገቢ እንዲያገኝ ተጠሪን ከአፍሪካ ኢንሹራንስ ጋር በማገናኘት መኪናው ከአደጋ በፊት ወደነበረበት እንዲመለስ የተለያዩ በመኪና ጥገና ላይ የተሰማሩ እና በአደጋ ገማች ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን በማወዳደር የአፍሪካ ኢንሹራንስ በ87,000.00 (ሰማንያ ሰባት ሺህ ብር) ላጠገን እንደሚችል ካረጋገጠ በኋላ መኪናው እንዲጠገን ተጠሪን ቢጠይቅም ፍቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ መኪናው በወቅቱ ሳይጠገን ቀርቷል። ስለሆነም ተጠሪ መኪናው ጠቅላላ የወደመ በማስመሰል ያቀረበው የመኪናው ጠቅላላ ዋጋ ተጠሪ መኪናው ተጠግኖ ወደነበረበት በመመለስ ያገኝ የነበረውን የእለት ገቢ በተጠሪ እምቢተኝነት በመቅረቱ ተጠያቂ አይደለንም፤ተጠሪ አደጋው የደረሰበት መኪና ተጠግኖ ወደነበረበት እንደሚመለስ በአፍሪካ ኢንሹራንስ ከተረጋገጠ በኋላ በልላ ድርጅት አስገምቻለሁ ይከፈለኝ በማለት ያቀረበው ብር 5,500.00 (አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር) ተጠሪ አለአግባብ ለመበልጸግ ላጠገን የሚችል መኪና አስቁሞ ያቀረበው ክስ በመሆኑ በክሱ ምክንያት ያወጣውን የዳኝነት፤የጠበቃ አበልና የተለያዩ ወጭዎችን የማንጠየቅ ስለሆነ ክሱ ውድቅ እንዲደረግልንና ከወጪ ኪሳራችን ጋር እንዲወሰንልን በማለት አፍሪካ ኢንሹራንስ ጣልቃ እንዲገባ ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱም የአፍሪካ ኢንሹራንስ ጣልቃ እንዲገባ ካደረገ በኋላ ግራ ቀኙ በማከራከርና የስር ከሳሽን ክስ በመስማት ጥር 8 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት አደጋ የደረሰበት መኪና ላጠገን እንደሚችል በመረጋገጡ ተሽከርካሪውን ለማስጠገን ብር 112,183.00 (አንድ መቶ አስራ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ሶስት ብር) የተገመተበትን ብር 5,500.00 (አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር) ተጠሪ ያጣውን የእለት ገቢ ከጥቅምት 10 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በየወሩ የአንድ ቀን ሰርቪስ ቀን በመቀነስ ብር 131,200.00 (አንድ መቶ ሰላሳ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር) ተጠሪ የወጪና ኪሳራ የመጠየቅ መብቱን በመጠበቅ ውሳኔ ሰጥቷል።
የአሁን አመልካቾች የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙ ክርክር ከሰማ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ስህተት ያለበት ሆኖ አልተገኘም በማለት በውሳኔ አጽንቶታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። አመልካቾች ነሐሴ 19 ቀን 2008 ዓ.ም በፃፉት አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል የሚሉባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ በመደረጉ ተጠሪዎቸ መልስ እንዲሰጡበት በታዘዘው መሰረት ጥር 23 ቀን 2009 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። አመልካቾችም አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር መርምረናል። እንደመረመርነውም የአመልካች ደንበኛ የሆነው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ ተሽከርካሪው አስፈላጊ ጥገና ተደርጎለት ከአደጋ በፊት ወደነበረበት እንዲመለስ ያደረገው ጥረት በተጠሪ እምቢተኝነት ምክንያት አለመሳካቱን ገልፀው እየተከራከሩ እያለ ይህ ሳይጣራ አመልካቾች የተቋረጠ ገቢ እንዲከፍሉ በስር ፍርድ ቤት የተወሰነው በአግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
ከመዝገቡ መገንዘብ የተቻለው አመልካቾች በተጠሪ መኪና ላይ ጉዳት መድረሱን አምነው 1ኛ አመልካች አደጋ የደረሰበት መኪና ጉዳት ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ጥገና ተደርጎለት ወደነበረበት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲመለስ እና ተጠሪ ያጣውን የእለት ገቢ እንዲያገኝ ተጠሪን ከአፍሪካ ኢንሹራንስ ጋር በማገኛኘት መኪናው ከአደጋ በፊት ወደነበረበት እንዲመለስ የተለያዩ በመኪና ጥገና ላይ የተሰማሩ እና በአደጋ ገማች ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን በማወዳደር የአፍሪካ ኢንሹራንስ በ87,000.00 (ሰማንያ ሰባት ሺህ ብር) ላጠገን እንደሚችል ካረጋገጠ በኋላ መኪናው እንዲጠገን ተጠሪን ቢጠይቅም ፍቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ መኪናው በወቅቱ ሳይጠገን ቀርቷል። ስለሆነም ተጠሪ መኪናው ተጠግኖ ወደነበረበት በመመለስ ያገኝ የነበረውን የእለት ገቢ በተጠሪ እምቢተኝነት በመቅረቱ ተጠያቂ አይደለንም በማለት ተከራክረዋል። ከዚህ በተጨማሪ በሥር ፍርድ ቤት በጣልቃገብነት ተከራካሪ የነበረው አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ ጉዳቱ እንደደረሰ መኪናው ተጠግኖ ወደነበረበት ለመመለስ ያደረገው ጥረት በተጠሪ ተቀባይነት እንዳላገኘ ገልፆ ተከራክሯል። ተጠሪ ይህንን የሚያስተባብል ክርክርና ማስረጃ ከሥርም ሆነ ከዚያ በኋላ በተደረገው ክርክር ያላቀረበ መሆኑን ተገንዝበናል። ተጠሪ ይህንን ገንዘብ በቅንነት በመቀበል ቀረብኝ የሚሉትን ገንዘብ ከአመልካቾች መጠየቅ የሚችሉበት እድል ነበራቸው። በተበዳይ ላይ ለደረሰ ጉዳት የሚከፈለው ካሣ ለቅን ልቦና ተቃራኒ በሆነ አኳኋን ላጠየቅ የማይገባ መሆኑ የፍታብሕር ህግ ቁጥር 2097 ንዑስ አንቀፅ 1 ይደነግጋል። ተጠሪ አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ ከአመልካች ጋር ያለውን የመድን ውል መሰረት በማድረግ እንዲቀበሉት የጠየቃቸውን ብር 87,000(ሰማንያ ሰባት ሺህ ብር) በቅንነት ቢቀበል ገቢ በመቋረጡ ምክንያት የደረሰባቸውን ኪሣራ ላያስቀሩት ወይም ላቀንሱት የሚችሉበት አቅም ይፈጥርላቸው ነበር። ልላ ሰው ኃላፊ በሆነበት ድርጊት ወይም አደጋ ጉዳት የደረሰበት ሰው ጉዳቱን ለማስቀረት ወይም የጉዳቱን መጠን ቀላል ለማድረግ ግድታና ኃላፊነት እንዳለበት የፍታብሕር ህግ ቁጥር 2097 ንዑስ አንቀፅ 2 ተበዳዩ በማስተዋል ቢሰራ ኖሮ የደረሰበትን ጉዳት ላያግደው ወይም ላያቀለው የሚችል ሲሆን በደረሰበት ጉዳት መጠን በሙሉ ካሣ ለመጠየቅ አይችልም በማለት በግልፅ ደንግጎታል። ተጠሪ በግጭቱ ጉዳት የደረሰበት መኪና በወቅቱ ተጠግኖ ወደ ስራ ቢመለስ በአደጋው ምክንያት ያቋረጠባቸውን የገቢ መጠን ለመቀነስ እየቻሉ ለማስጠገን እንቢተኛ ለመሆናቸው ምክንያት ኪሣራውን ለማስቀረት ወይም ላያቀሉት እንዳልቻሉ ለመገንዘብ ችለናል። በዚህ ምክንያት የተቋረጠው ገቢ መጠን መጨመር የተጠሪ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ.2098 /1/ መሰረት በከፊል ኃላፊነት አለበት ብለናል።
ሲጠቃለል ተጠሪ በመኪናው መውደም ምክንያት የተቋረጠባቸውን የገቢ መጠን ለመቀነስ ወይም ለማቅለል የፍታብሕር ህግ ቁጥር 2097 ንዑስ አንቀፅ 2 በሚደነግገው መሰረት በቅን ልቦናና በአስተዋይነት ያደረጉት እንቅስቃሴ የልለ መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ያልሰጡ በመሆኑ ውሳኔያቸው በከፊል መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበትና ላሻሻል የሚገባው ነው በማለት ወስነናል።
በፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 8 ቀን 2007 ዓ/ም ተሰጥቶ በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ግንቦት 22 ቀን 2008 ዓ/ም በውሳኔ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሻሐል።
በተጠሪ መኪና ላይ በደረሰው ጉዳት ምክንያት ለተቋረጠው ገቢ አመልካቾች ሙሉ ሐላፊነት የለባቸውም፤ተጠሪው ከፊል ሃላፊነት አለባቸው ብለናል።
የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ መኪናቸው ላይ በደረሰው ጉዳት ምክንያት ተጠሪ ለተቋረጠባቸው ገቢ ብር 131,400 (አንድ መቶ ሰላሳ አንድ ሺህ አራት መቶ ብር) አመልካቾች እንዲከፍሉ በማለት የሰጡትን ውሣኔ አሻሽለን አመልካቾች የተቋረጠ ገቢ ብር 65,700(ስልሳ አመስት ሺህ ሰባት መቶ ብር) 9% ወለድ ጋር የመክፈል ኃላፊነት አለባቸው ብለናል። ተሽከርካሪውን ለማስጠገን ብር 112,183.00 (አንድ መቶ አስራ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ሶስት ብር) 9% ወለድ ጋር እንዲከፍሉ ፤የተገመተበትን ብር 5,500.00 (አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር) አመልካቾች ለተጠሪ እንዲከፍሉ፤የስር ጣልቃ ገብ አፍሪካ ኢንሹራንስ ለተጠሪ ከሚከፈለው ገንዘብ ውስጥ ብር 90,781.30 (ዘጠና ሺህ ሰባት መቶ ሰማንያ አንድ ብር ከሰላሳ ሳንቲም) እንዲከፍል የተሰጠ ውሳኔ እንዲሁም ተጠሪ የወጪና ኪሳራ የመጠየቅ መብቱን በመጠበቅ የተሰጠ ውሳኔ ክፍል አልተነካም።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
No topics extracted.