የመንግስት ተቋማት ሰራተኞቻቸውን የመቆጣጠር እና የመከታተል ግድታቸውን ሳይፈጽሙ ቀርተው በተገልጋዮች ላይ ጉዳት በደረሰ ጊዜ ጉዳዩ አይመለከተንም በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የልለው ስለመሆኑ፡የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2126 (2) እና 2127 (1)
No summary available.
የሰበር መዝገብ ሕዳር 28 ቀን 2010 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ሙስጠፋ አህመድ አብርሃ መሰለ ጳውሎስ ኦርሺሶ ሰናይት አድነው አመልካች፡- በደሴ ከተማ የአራዳ ክፍለ ከተማ ገቢዎቸ ጽ/ቤት -ዓ/ሕግ ሙላት መሐመድ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1.ወ/ሮ ዘይነባ ሰይድ -የቀረበ የለም 2.አቶ ቴዎድሮስ ፍቅሩ---የጽሁፍ መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፏል።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል።
ጉዳዩ አለአግባብ የተከፈለ ነው የተባለን ገንዘብ ለማስመለስ ከቀረበ ክስ ጋር ተያይዞ የተነሳ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን አመልካች አቤቱታውን ለዚህ ችሎት ያቀረበው በደሴ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ08/11/2007 ዓ.ም.የተሰጠውን ውሳኔ አሻሽሎ አመልካችን ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ለክሱ በአንድነትና በነጠላ ኃላፊ በማድረግ የደቡበ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ13/03/2008 ዓ.ም.የሰጠው እና በአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 01-03707 በ28/11/2008 ዓ.ም. በፍርድ፣እንዲሁም በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 03-15588 በ05/05/2009 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል በማለት ነው።
1ኛ ተጠሪ በወረዳው ፍርድ ቤት ክስ ያቀረቡት በደሴ ከተማ በአራዳ ክፍለ ከተማ በቁጥር A-462 የተመዘገበ ቤት ከወ/ሮ ዘሀቡ ሁሴን ገዝተው ውሉን 1ኛ ተከሳሽ ለነበረው የአሁኑ አመልካች ሲያቀርቡ ቤቱ በባለሙያ በብር 276,644.50 በመገመቱ ለስም መዛወሪያ መክፈል የሚገባቸው ብር 13,832.20 ሆኖ ሳለ የአመልካች ሰራተኛ የሆነው የስር 2ኛ ተከሳሽ /የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ/ በማታለል በሆነው ደረሰኝ ላይ ብር 23,832.20 ጽፎ በመቀበል በፊደል ግን ብር 13,832.20 በሚል ሞልቶ የሰጣቸው መሆኑን እና በዚሁ አግባብ የስም ዝውውሩ የተፈጸመ መሆኑን ገልጸው አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ያለአግባብ የተቀበሉትን ገንዘብ ብር 10,000 በአንድነትና በነጠላ እንዲከፍሐቸው በመጠየቅ ነው።2ኛ ተጠሪ ስላልቀረቡ ጉዳዩ የተሰማው በልሉበት ሲሆን የአሁኑ አመልካች በበኩሉ ቀርቦ 2ኛ ተጠሪ በፈጸሙት ድርጊት በዲሲፕላን ከስራ የተሰናበቱ መሆኑን እና ገንዘቡ ለ2ኛ ተጠሪ የግል ጥቅም የዋለ እንጂ ለአመልካች ገቢ ያልተደረገ መሆኑን ገልጾ በአመልካቹ ላይ የቀረበው ክስ ውድቅ እንዲደረግ ተከራክሯል።ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ ድርጊቱ የተፈጸመው በሰራተኛው ጥፋት በመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2126 (3) እና 2127 መሰረት አመልካች ኃላፊነት የለበትም በማለት የተጠየቀውን ገንዘብ 2ኛ ተጠሪ ብቻ እንዲከፍሉ ውሳኔ ሰጥቷል።የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህንን ውሳኔ አሻሽሎ አመልካችን ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ለክሱ በአንድነትና በነጠላ ኃላፊ ለማድረግ የቻለው 2ኛ ተጠሪ ድርጊቱን የፈጸመው ስራውን በማከናወን ሂደት ውስጥ በመሆኑ አመልካች በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2126 (2) መሰረት ኃላፊነት አለበት በሚል ምክንያት ሲሆን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በበኩሉ ተጨማሪ ማጣራት ካደረገ በኃላ ይህንን ውሳኔ ላያጸና የቻለው የክፍለ ከተማው የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዋና የስራ ሂደት በ02/06/2007 ዓ.ም.
ለመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዋና ስራ ሂደቱ በፃፈው ደብዳቤ ለስም መዛወሪያ በ1ኛ ተጠሪ ስም ብር 23,832.20 ገቢ እንደተደረገ ያረጋገጠ ስለመሆኑ በተደረገው ተጨማሪ ማጣራት በመረጋገጡ አመልካቹ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2126 (2) መሰረት ኃላፊነት አለበት መባሉ የሚነቀፍ አይደለም በማለት ነው።
በክልሉ ሰበር ችሎት በትዕዛዝ የጸናው ይኸው ውሳኔ ሲሆን አመልካች ለዚህ ችሎት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በአንድነትና በነጠላ ኃላፊ የመደረጉን አግባብነት ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2126 (2) እና 2127 (1) እንዲሁም በመዝገብ ከተሰጠው የሰበር ገዥ ውሳኔ አንጻር ተጠሪዎቹ ባሉበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ የ2ኛ ተጠሪ መልስ የመስጠት መብት ታልፎ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ነጥብ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት አመልካች አጥብቆ የሚከራከረው እና ጉዳዩም ለሰበር ክርክር ያስቀርባል የተባለው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2126 (2) እና 2127 (1) እንዲሁም በመዝገብ የተሰጠውን አስገዳጅ የሕግ ትርጉም መሰረት በማድረግ ነው።ተጠቃሹ ገዥ ውሳኔ የመንግስት ሰራተኞች ናቸው የተባሉት ግለሰቦች ወደ ጉዳዩ ገብተው እንዲከራከሩ ከተደረገ በኃላ ኃላፊነቱ የመንግስት ነው ወይስ የሰራተኞቹ ነው? ወይስ የሁለቱም ወገኖች ነው? የሚሉ ነጥቦች ተለይተው ውሳኔ እንዲያርፍባቸው በነጥብ የተመለሰን ጉዳይ የሚመለከት ነው።በተጠቃሹ መዝገብ የመንግስት ተቋም ከነበረው አመልካች የቀረበው ክርክር ይዘትም የአመልካች ድርጅት ሰራተኞች ዕቃ አቅራቢ ከነበረው ተዋዋይ ወገን ጋር በመተባበር ለፈጸሙት ተግባር መንግስት ኃላፊ ላሆን አይገባውም የሚል ይዘት ያለው መሆኑን በውሳኔው ላይ የሰፈረው የክርክሩ ይዘት ያመለክታል።በተያዘው ጉዳይ 1ኛ ተጠሪ የማይገባቸውን ክፍያ የፈጸሙት ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በመመሳጠር እና አመልካችን ለመጉዳት በማሰብ ስለመሆኑ በአመልካቹ በኩል የቀረበ ክርክር እና ማስረጃ ስለመኖሩ የመዝገቡ ግልባጭ የሚጠቁመው ነገር የለም።በሰበር ደረጃም በዚህ ረገድ የቀረበ ክርክር የለም።ከዚህም በተጨማሪ በተያዘው ጉዳይ ተፈጸመ በተባለው ድርጊት ጉዳቱ የደረሰው በ1ኛ ተጠሪ ላይ እንጂ በመንግስት ላይ አይደለም።በመሆኑም በሁለቱ ጉዳዮች ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር መለያየት አንጻር ገዥ ውሳኔው ለተያዘው ጉዳይ ተፈጻሚነት የሚኖረው አይደለም።በልላ በኩል የክፍለ ከተማው የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዋና የስራ ሂደት በ02/06/2007 ዓ.ም. ለመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዋና ስራ ሂደቱ በፃፈው ደብዳቤ ለስም መዛወሪያ በ1ኛ ተጠሪ ስም ብር 23,832.20 ገቢ እንደተደረገ ያረጋገጠ ስለመሆኑ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በፍርዱ ላይ አስፍሯል። አመልካች ይህ ደብዳቤ ላጻፍ የቻለው 2ኛ ተጠሪ በሰጡት መረጃ መነሻ ነው የሚል ይዘት ያለው ክርክር ያቀረበ ቢሆንም በመሰረቱ የመንግስት ተቋማት ሰራተኞቻቸውን የመቆጣጠር እና የመከታተል ግድታ ያለባቸው መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም።ይህን ሳይፈጽሙ ቀርተው በተገልጋዮች ላይ ጉዳት በደረሰ ጊዜ ጉዳዩ አይመለከተንም በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት ላሰጠው የሚገባ አይደለም።አመልካች ከገንዘብ ጋር በተያያዘ የስራ መደብ ላይ ይሰሩ የነበሩት 2ኛ ተጠሪ ዋስ ለሚፈጽሙት ጥፋት ዋስ እንዲኖራቸው ማድረግ ይገባው ነበር በማለት 1ኛ ተጠሪ በሰበር መልሳቸው ላቀረቡት ክርክርም አመልካቹ በመልስ መልሱ ላይ የሰጠው ግልጽ ማስተባበያ የለም።በመሰረቱ ላከፍል የማይገባውን ነገር የከፈለ ሰው እንዲመለስለት የመጠየቅ መብት ያለው ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2164 ስር ተመልክቷል። አመልካቹ ገንዘቡን የሚከፍል ከሆነም ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በሕጉ አግባብ መስርቶት የነበረውን የቅጥር ግንኙነት መሰረት አድርጎ በመጨረሻ ከ2ኛ ተጠሪ ማስተካት የሚችል ከመሆኑ በቀር ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በአንድነትና በነጠላ ኃላፊ መሆን አይገባኝም በማለት የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት ላሰጠው የሚገባ ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ ፍሬ ነገርን የማጣራት እና ማስረጃ የመመዘን ጉዳይን የሚመለከት ነው ከሚባል በቀር መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቶአል።
የተሰጠውን ውሳኔ አሻሽሎ አመልካችን ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ለክሱ በአንድነትና በነጠላ ኃላፊ በማድረግ የደቡበ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ13/03/2008 ዓ.ም. የሰጠው እና በአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 01-03707 በ28/11/2008 ዓ.ም.
በፍርድ፣ እንዲሁም በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 03-15588 በ05/05/2009 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ፀንቷል።
ይጻፍ።
የውሳኔው ቅጂ ለስር ፍርድ ቤቶች ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቶአል።
No topics extracted.