የባንኮችን መልካም ስም፣ የአገልግሎት ብቃት፤ ታማኝነት እና የሥራ እንቅስቃሴን ልሎች ሰዎች እንዲጠራጠሩ የሚያደርግ ተግባር መፈጸም የፍትሐብሄር ተጠያቂነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ. 2109 የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2102 XXXII
No summary available.
መስከረም 30 ቀን 2010 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወል ሙስጠፋ አህመድ አብርሃ መሰለ ጳውሎስ ኦርሺሶ ሰናይት አድነው አመልካች፡- የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን -ዓቃቤ አቶ ዐቢይ ተሃድሶ ቀረቡ ተጠሪ፡- የዳሽን ባንክ አክሲዮን ማኅበር -ነ/ፈጅ አቶ አስራት አድማሱ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ ያለው ፍርድ ተሰጥቷል።
የክርክሩ ምክንያት የካሳ ጉዳይን የሚመለከት ነው። የአሁኑ ተጠሪ በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበረ ሲሆን የክሱም ይዘት፡- ተከሳሽ /የአሁኑ አመልካች/ አውጥቶ ለነበረው የግንባታ ሥራ ጨረታ አፈጻጸም ተጫራቹ ለሚያስይዘው የዋስትና ገንዘብ አመልካች በጻፈው ደብዳቤ ከዳሽን ባንክ የሚቀርብ ማንኛውም ዓይነት ዋስትና ተቀባይነት የለውም በማለት መግለጹ እና ይህንንም ለተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ማሳወቁ የተጠሪን መልካም ስም ያጠፋ በመሆኑና ባንኩም የደንበኝነት ቅድሚያ ክፍያ እንዲሁም የመልካም ሥራ አፈጻጸም ፈጽሞ ቢሆን ኖሮ ላያገኝ ይችል የነበረውን ብር 417,117.71 /አራት መቶ አስራ ሰባት ሺህ አንድ መቶ አስራ ሰባት ብር ከሰባ አንድ ሳንቲም/ እንዲከፍልና ለፈጸመው ህገ ወጥ ድርጊት ማስተባበያ እንዲሰጥ በማለት ዳኝነት ጠይቋል።
የአሁኑ አመልካች /የሥር ተከሳሽ/ የተጠሪን /የከሳሽን/ ስም አንስተን ሳይሆን ለህንፃው ተቋራጭ የቅበላ ደብዳቤ በገለጽንበት ወቅት ዋስትናን ማስያዝ በተመለከተ ከዳሽን ባንክ ጋር ካለን የፍርድ ቤት ክርክር አንጻር የማንቀበል መሆኑን ከመግለጽ ውጪ የከሳሽን ስም አላጠፋንም፣ ስም ሳይጠፋ መልካም ስሜ ጠፍቷል በማለት ያቀረበው ክስ በመሆኑ መብትና ጥቅም የለውም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ካቀረበ በኃላ በአማራጭ በሰጠው መልስ ከባንኩ ጋር ፍርድ ቤት ክርክር ስላለን ኮንትራክተሩ ጨረታ በማሸነፉ የአሸናፊነቱን የሚገልጽ ዝርዝር ደብዳቤ ላይ ከዳሽን ባንክ የሚቀርብ የመልካም ሥራ ዋስትናን በተመለከተ የማንቀበል መሆኑን ገልጸናል። በግልባጭ እንዲያውቁት የተደረጉትም መ/ቤቶች ቢሆኑ ካለን የሥራ ግንኙነት በብድር የተገኘ ገንዘብ በመሆኑ ስለጨረታ አሸናፊ እንዲያውቁት የተጻፈ ደብዳቤ ከመሆኑ ባሻገር የስም ማጥፋት ተግባር ያልፈጸምን ስለሆነ ክሱ ውድቅ እንዲደረግልን በማለት ተከራክሯል።
ክርክሩን የሰማው የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዳዩን መርምሮ የሥር ተከሳሽን / የአሁኑን አመልካችን/ ጥፋተኛ በማድረግ ከሳሽ /ተጠሪ/ የጠየቀውን ብር 417,117.71 /አራት መቶ አስራ ሰባት ሺህ አንድ መቶ አስራ ሰባት ብር ከሰባ አንድ ሳንቲም/ 9% ከሚታሰብ ወለድ ጋር እንዲከፍል እና ወጪና ኪሳራ ዝርዝር የማቅረብ መብቱን በመጠበቅ ውሳኔ ሰጥቷል።
ይህን ውሳኔ ቅር በመሰኘት የአሁኑ አመልካች ይግባኝ ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የከፍተኛ ፍርድ ቤቱም ይግባኙን ሰርዟል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን ውሳኔ እንዲሁም የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ለማስለወጥ ሲሆን አመልካች በሥር ፍርድ ቤቶች ተፈጽሞብኛል ያላቸውን ዝርዝር የቅሬታ ነጥቦችን አቅርቧል። አጣሪው የሰበር አቤቱታውን መርምሮ ቀደም ሲል ከተጠሪ ባንክ ጋር ክስ ስለነበረን ጉዳዩም በፍርድ ቤት እየታየ ባለበት ሁኔታ ከዳሽን ባንክ የሚቀርበውን ዋስትና አንቀበልም ማለቱ ስም ማጥፋት ነው የተባለበት አግባብነት መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ይቅረብ ሲል አዟል።
ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ ሚያዚያ 12 ቀን 2009 ዓ/ም የተጻፈ መልስ አቅርቦ የተከራከረ ሲሆን አመልካቹም በቀን 26/09/2009 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
የነገሩ አመጣጥና የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን የሚመስል ሲሆን በሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል ወይስ አልተፈጸመም? የሚል ጭብጥ ተይዞ ጉዳዩ ተመርምሯል። ግራ ቀኙን እያከራከረ ባለው ደብዳቤ ላይ የአሁኑ አመልካች “የቅበላ ደብዳቤ” በሚል ርዕስ ሥር “ማሳሰቢያ” በማለት ከተጠሪ ባንክ ማንኛውንም ዓይነት ዋስትና አንቀበልም በማለት ስለመጻፉ በሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ሰፍሮ ይገኛል። ይህ የተጻፈው መልእክት የተጠሪን መልካም ስም ያጠፋ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ላታይ ይገባል።
ደብዳቤው የባንኩን የሥራ እንቅስቃሴን ልሎች ሰዎች እንዲጠራጠሩ የሚያደርግ እንደሆነ መረዳት ይቻላል። ማንኛውም ምክንያታዊ ሰው ከደብዳቤው ላረዳ የሚችለው ባንኩ በሥራው፣በሙያውና በሚሰጠው አገልግሎት ብቃት እና ታማኝነት እንደልለው ነው። አመልካች የባንኩን ዋስትና የማይቀበልበትን ምክንያት አብራርቶ ቢጽፍ ኖሮ ምክንያቱ ግልጽ ላሆንና የሚያነቡም ሰዎች ላረዱ ይችሉ ነበር። ነገር ግን ደብዳቤው በጥቅሉ የባንኩን ዋስትና አንቀበልም በማለቱ ለተለያየ ጥርጣሬ የሚጋብዝ፣ ከባንኩ ጋር ደንበኝነት ለመፍጠር የሚፈልጉ ቢኖሩ እንኳን ባንኩን እንዲጠራጠሩ የሚደርግ፣ የተጠሪ ድርጅት ሥራ እንዲቀዘቅዝና የተቋቋመለትን ዓላማ እንዳይወጣ መሰናክል የሚፈጥር እንደሆነ ለመገንዘብ ያስችላል። ደብዳቤው ለተጠሪ ብቻ ተጽፎ የቀረ ሳይሆን ለተለያዩ አካላት ግልባጭ የተደረገ ነው። ይህ ደብዳቤ የደረሳቸው አካላት ከባንኩ ጋር የውል ግንኙነት ለማድረግ ቢፈልጉ የተላለፈው መልእክት ከፍተኛ ጥያቄን የሚፈጥርባቸው እንደሆነ መገመት ይቻላል። አመልካች ይህን ደብዳቤ ሲጽፍ ግልባጭ ያደረገው ከአመልካች ጋር የሥራ ግንኙነት ያላቸው አካላት በመሆናቸው ነው በማለት ቢከራከርም በተጠሪ ላይ የሚያስከትለውን ውጤት በአግባቡ ማጤን ሲገባው ሳያጤን የጻፈው ደብዳቤ በመሆኑ በዚህ አኳኋን ላስተባበል የሚችል ሆኖ አላገኘነውም።
ከዚህ በተጨማሪ አመልካች ደብዳቤውን የጻፈው ከተጠሪ ጋር በፍርድ ቤት ክርክር ስላለ ነው ይበል እንጂ ከፍ ብሎ እንደተገለጸው የተጻፈው ደብዳቤ ይህንን አይገልጽም። ይህን በተመለከተ ተጠሪ ለዚህ ችሎት በሰጠው መልስ በአመልካች እና ጣና ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር መካከል በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር አመልካች የውል ጥሰት ፈጽሟል በሚል ባቀረበው ክስ በአመልካች ስም ተጠሪ ዘንድ ያለው የዋስትና ገንዘብ እንዳይከፈል እግድ እንዲሰጥለት ባንኩን 2ኛ ተከሳሽ አድርጎ ያቀረበ ክስ መሆኑን፣ ጉዳዩን ሲያይ የነበረው ፍርድ ቤት ክስ ከመስማቱ እና ክርክር ከመደረጉ በፊት በባንኩ ዘንድ ያለን ገንዘብ ለማሳገድ ካስፈለገ የእግድ አቤቱታ ከማቅረብ በቀር ባንኩን ተከሳሽ አድርጎ ማቅረቡ የሥነ ሥርዓት ግድፈት ነው በሚል ከክሱ ከኪሳራ ጋር አሰናብቶናል በማለት ተከራክሯል። የአሁኑ አመልካች ይህንን መከራከሪያ በመልስ መልሱ በአግባቡ አላስተባበለም። ይህ በሆነበት ሁኔታ ከተጠሪ ጋር ክርክር ስለነበረን የጻፍኩት ደብዳቤ ነው በማለት አመልካች የሚያቀርበው ማስተባበያ ተገቢ አይደለም።
በመሰረቱ የባንክ ሥራ ከፋይናንስ እንቅስቃሴ እና ለደንበኞቹ ከሚሰጠው አገልግሎት ጋር እጅጉን የተቆራኘ በመሆኑ በሥራ አፈጻጸሙ ላይ ያለው መልካም ስም የህልውናው መሰረት ነው። ህጉም ለዚህ መልካም ስም ጥበቃ ያደርጋል። ይህን መልካም ስም የሚያጎድፍ ተግባር መፈጸም ተጠያቂነትን ያስከትላል። ይህም በፍትሓብሕር ህግ ቁጥር 2109 ላይ በግልጽ ተደንግጓል። በተያዘው ጉዳይ ከላይ በግልጽ እንደተመለከተው አመልካች የጻፈው ደብዳቤ የተጠሪን መልካም ስም የሚነካ ነው። የሥር ፍርድ ቤት ይህን ተመልክቶ አመልካችን ኃላፊ ማድረጉ ተገቢ ነው።
በልላ በኩል ካሳን በተመለከተ ተጠሪም በዚህ ደብዳቤ ምክንያት የደንበኝነት ቅድሚያ ክፍያ እንዲሁም የመልካም ሥራ አፈጻጸም ፈጽሞ ቢሆን ኖሮ ላያገኝ ይችል የነበረውን ብር 417,117.71 /አራት መቶ አስራ ሰባት ሺህ አንድ መቶ አስራ ሰባት ብር ከሰባ አንድ ሳንቲም/ እንዳጣ ገልጾ አመልካቸ እንዲከፍል ዳኝነት ጠይቋል። የሥር ፍርድ ቤቶችም ተጠሪ የጠየቀውን ብር አመልካች እንዲከፍል ውሳኔ ሰጥቷል። ነገር ግን በአመልካች ላይ የደረሰውን ትክክለኛ ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ ለይቶ ለማወቅ የማያስችል በሆነበት ሁኔታ የሥር ፍርድ ቤት የተጠየቀውን ብር እንዳለ አመልካች ለተጠሪ እንዲከፍል መወሰኑ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። ካሳው በፍትሓብሕር ህግ ቁጥር 2102 መሰረት ላወሰን የሚገባው በርትዕ ነው። የሥር ፍርድ ቤት ጉዳዩን በዚህ መልክ አይቶ ያለመወሰኑ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ካሳው ላሰላ የሚገባው በርትዕ ነው ብለናል። በመሆኑም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
1.የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ. 227957 በቀን 02/02/09 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ እንዲሁም የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ.180632 በቀን 04/05/2009 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍትሓብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 348 /1/ መሰረት ተሻሽሐል።
2.አመልካች ለተጠሪ በፍትሓብሕር ህግ ቁጥር 2102 መሰረት በርትዕ ብር 50,000.00 /አምሳ ሺህ ብር/ ካሳ ላከፍል ይገባል ተብሎ ተወስኗል።
የዚህ ችሎት ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ ይቻሉ።
3.የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይድረሳቸው።
መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡:
No topics extracted.