ሰራተኞች በሙሉ እውቀታቸውና ብቃታቸው ሰርተው እኩል የምርት ጥራትና መጠን ያመርታሉ ተብሎ የማይገመት ስለመሆኑና የአንደኛው ሰራተኛ ያመረተው ምርት መጠንና ጥራት ብቻ ለልላው ሰራተኛ ከአቅም በታች ሰርቷል ለማለት በቂ መሰፈርት ሆኖ ላወሰድ የማይገባ ስለመሆኑ፡- 150947 ሚሮና ኢንዳስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማ እና እነ ጫልቱ ዓለሙ (4 ሰዎች) መጋቢት12 ቀን 2010 ዓ/ም XXIX የንግድ ህግ 268 52. በአክሲዮን ዝውውር ማመልከቻ ሰነድ ላይ የአክስዮን ማህበሩ ማህተም ማረፉ አልያም ዝውውሩ ፀድቋል ወይም ተመዝግቧል የሚል ምልክት መደረጉ ብቻውን በንግድ ህግ ስር በአዛዥ ሁኔታ የተቀመጠውን በባለአክሲዮኖች መዝገብ የመመዝገብ ግድታን የማይተካ ወይም ቀሪ የማያደርግ ስለመሆኑ የንግድ ህግ 331 (1) እና 341 (2) XXX ሲረጋገጥ ስለመሆኑ፣ የማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድም .ሆነ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ አንድ ማህብር ከተቋቋመ ጀምሮ ተደርጎ አያውቅም በሚል ምክንያት ብቻ አንድ ማህበር እንዲፈርስ ላወሰን የማይገባ ስለመሆኑና በንግድ ህጉ መሰረት እንደበቂ ምክንያት ላወሰድ የማይችል ስለመሆኑ፣ የንግድ ህግ 217 እና 218፣ 495/1/ እና /3/
No summary available.
መጋቢት 12 ቀን 2010 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወል ሙስጠፋ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውሎስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ወ/ሮ መዋዕል ትኩዕ መርሻ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ነገረፈጅ ፍቨን ቢኒያም።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዳዩ ከአክሲዮን ሽያጭ ጋር የተያያዘ ነው። ክርክሩ የጀመረው በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ነው። የአሁን አመልካች /የሥር ከሳሽ/ ሰኔ 3 ቀን 2007 ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት የክስ አቤቱታ ለተከሳሽ ማኅበር /ለአሁን ተጠሪ/ አክሲዮን የመግዛት ፍላጎት እንዳላቸው አሳውቀው ተከሳሹም አክሲዮኖቹን ለመሸጥ የሚፈልግ አለ መጥተው መግዛት ይችላሉ በማለት ባደረገላቸው ጥሪ መሰረት ጥር 12 ቀን 2006 ዓ/ም የማኅበሩ አባል ከሆኑት ከአቶ ሰባጋዲስ ስዩም 3949 አክሲዮኖችን በመግዛት ብር 120,904.80 /አንድ መቶ ሃያ ሺህ ዘጠኝ መቶ አራት ብር ከሰማኒያ ሳንቲም/ መክፈላቸውን፣ አቶ ሰባጋዲስ ስዩም እና ከሳሽ /የአሁን አመልካች/ ተከሳሽ /የአሁን ተጠሪ/ ባዘጋጀው የማዘዋወሪያ የውል ሰነድ ላይ ተፈራርመው ተከሳሽም በራሱ ማኅተም በማጽደቅ ዝውውሩን መመዝገቡን ገልጸው ተከሳሽ ማኅበር በ2006 ዓ/ም ለእያንዳንዱ ባለአክሲዮን ያከፋፈለውን ትርፍ ጨምሮ ሰርተፊኬት ላይ አስፍሮ እንዲሰጣቸው በቃልም ሆነ በጽሁፍ ቢጠይቁም ይህንን ለመፈጸም ፈቃደኛ ስላልሆነ ተከሳሽ በአክሲዮን ማዘዋወሪያ የውል ሰነድ ላይ በራሱ ማኅተም ያጸደቀው የአክሲዮን ሽያጭ ከገዙዋቸው ግለሰብ በማስተላለፍ ወይም ከሚሸጣቸው አክሲዮኖች ላይ በመቀነስ መዝግቦ ሰርተፊኬት እንዲሰጣቸው ወይም አክሲዮኑን ለመግዛት ያወጡትን ገንዘብ ማግኘት ከነበረባቸው ትርፍ ክፍያ ጋር ብር 173,022.22 /አንድ መቶ ሰባ ሶስት ሺህ ሃያ ሁለት ብር ከሃያ ሁለት ሳንቲም/ ከነወለዱ እንዲከፍላቸው፣ ወጪና ኪሳራን እንዲተካ እንዲወሰንላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል።
የአሁን ተጠሪ /የሥር ተከሳሽ/ ሰኔ 25 ቀን 2007 ዓ/ም በተጻፈ መልስ ከሳሽ ያቀረቡት ማስረጃ የአክሲዮን ማስተላለፊያ ጥያቄ የሚቀርብበት ማመልከቻ ነው፣ ተከሳሽ ማኅበር የአክሲዮን ዝውውሩን አልመዘገበም፣ ለከሳሽም የሰጠው ማረጋገጫ የለም፣ ተከሳሽ ማኅበር በህጉ መሰረት ለመመዝገብ እና ለጠቅላላ ጉባዔ ለማቅረብ ሲያጣራ የሻጩ አክሲዮኖች ከሳሽ አክሲዮኖቹን ከመግዛታቸው በፊት በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የታገደ በመሆኑ ዝውውሩ ላፈጸም አልቻለም። በመሆኑም ከሳሽ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክሯል።
ጉዳዩን የተመለከተው የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 1ኛ/ ተከሳሽ ማኅበር ለከሳሽ ለ3949 አክሲዮኖች የአክሲዮን ሰርቲፊኬት ለከሳሽ ላሰጥ ይገባል ወይስ አይገባም? 2ኛ/ የአክሲዮን ሰርተፊኬቱን የመስጠት ኃላፊነት የለበትም የሚባል ቢሆን ከሳሽ የጠየቁትን ክፍያ ተከሳሽ የመክፈል ኃላፊነት አለበት ወይስ የለበትም? የሚሉትን ጭብጦች በመያዝ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃዎችን መርምሯል። የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ ጥር 12 ቀን 2006 ዓ/ም የተደረገው የአክሲዮኖች ዝውውር ወይም ማስተላለፊያ ማመልከቻ ሰነድ ነው። በዚህ ሰነድ (መ) እና (ሰ) ሥር ዝውውሩን ያፀደቀው አካል ዝውውሩን ተቀብሎ የመዘገበው ሰው ስም እና ፊርማ ያረፈ፣ የተከሳሽ ማኅበር ማኅተም ያረፈበት ቢሆንም ይህ ሰነድ ግን በንግድ ህግ ቁጥር 331 /1/ እና 341 /2/ ሥር በአዛዥ ሁኔታ የተቀመጠውን በባለአክሲዮኖች መዝገብ የመመዝገብ ግድታን የሚተካ ወይም ቀሪ የሚያደርግ አይደለም፡፤ በማመልከቻ ሰነዱ ላይ ዝውውሩ ፀድቋል ወይም ተመዝግቧል መባሉ ብቻውን ተከሳሽ በባለአክሲዮኖች መዝገብ ከሳሽን በመመዝገብ ባለአክሲዮን አድርጓል የሚያስብል አይደለም። እነዚህ ተሸጡ የተባሉት አክሲዮኖችም ከሽያጭ ውሉ በፊት እንዳይሸጡ የእግድ ትዕዛዝ ከተሰጠባቸው ተከሳሽ ይህን ሁኔታ በመተላለፍ በአክሲዮኖች መዝገብ ዝውውሩን መመዝገብ ግድታ አለበት ላባል አይችልም፡፤ ከሳሽ በባለአክሲዮኖች መዝገብ ካልተመዘገቡ ደግሞ ተከሳሽ የአክሲዮን ሰርተፊኬት እንዲሰጥ የሚገደድበት ሁኔታ የልለ በመሆኑ ተከሳሽ የራሱን አክሲዮኖች ለመሸጥ ባልተስማማበት ሁኔታም ልላ አክሲዮን በምትኩ እንዲሰጥ የሚጠየቅበትም ሆነ የሚገደድበት አግባብ የልለ በመሆኑ ከሳሽ በዚህ ረገድ ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም በማለት ወስኗል።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ ከሳሽ አክሲዮኖቹን ለመግዛት ገንዘቡን የከፈሉት ለአቶ ሰባጋዲስ ስዩም ሲሆን እነዚህ ክፍያ የተፈጸመባቸው አክሲዮኖች የእግድ ትዕዛዝ ያለባቸው በመሆኑ ዝውውሩ ላፈጸም አልቻለም፣ ይህ ከሆነ ደግሞ ክፍያውን እንዲከፍል መጠየቅ የሚቻለው ክፍያውን የወሰደውን አካል እንጂ ተከሳሽ ባለአክሲዮኑ በህጉ በተሰጠው መብት መሰረት አክሲዮኖችን ለመሸጥ በመጠየቁ ሁኔታዎቹን ስላመቻቸ ብቻ ክፍያውን ባልተቀበለበት ሁኔታ የልላውን ሰው ኃላፊነት የሚወስድበት አግባብ የለም፣ ከዚህ በተጨማሪ የትርፍ ክፍያ ተከሳሽ የመክፈል ኃላፊነት ያለበት ባለአክሲዮን መሆኑ ለተረጋገጠ ሰው እንጂ እንዲሁም የመክፈል ኃላፊነት የልለበት በመሆኑ እንዲከፍል ላጠይቅ አይችልም። በመሆኑም ከሳሽ የጠየቁትን ክፍያ ተከሳሽ የመክፈል ኃላፊነት የልለበት በመሆኑ ላከፍል አይገባም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
የአሁን አመልካች ውሳኔውን በመቃወም ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይግባኙን ተቀብሎ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኃላ በፍትሓብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 348 /1/ መሰረት የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ውሳኔውን ለማስለወጥ ሲሆን አመልካች በሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈጽሞብኛል ያሉዋቸውን ቅሬታ ነጥቦችን ዘርዝረው አቅርበዋል።
የሰበር አቤቱታውን አጣሪው መርምሮ በዚህ ጉዳይ አከራካሪዎች አክሲዮኖች ለአመልካች ላሸጡ የቻሉት ተጠሪ ባደረገው ጥሪ መነሻ ከመሆኑ አንጻር የሥር ፍርድ ቤቶች አክሲዮኖቹ እገዳ የነበረባቸው ናቸው በማለት ተጠሪን ከኃላፊነት ነፃ ማድረጋቸው መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ይቅረብ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ነሐሴ 1 ቀን 2009 ዓ/ም የተጻፈ ዝርዝር መልስ አቅርቦ የተከራከረ ሲሆን የአመልካች ጠበቃም ጥቅምት 13 ቀን 2010 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የነገሩ አመጣጥና የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን የሚመስል ሲሆን 1ኛ/ አመልካች ለገዙባቸው አክሲዮኖች ተጠሪ ሰርተፊኬት ላሰጥ ይገባል ወይስ አይገባም?
2ኛ/ ሰርቲፊኬት ላሰጥ አይገባም የሚባል ከሆነ አመልካች የከፈሉትን ገንዘብ ከነወለዱ ተጠሪ ላመልስ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚሉ ጭብጦች ተይዘው ጉዳዩ እንደሚከተለው ተመርምሯል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ አመልካች ተጠሪ ባደረገው ጥሪ መሰረት የአቶ ስባጋዲስ ስዩም አክሲዮን ድርሻ መግዛታቸውን ሲከራከሩ ተጠሪ ደግሞ በግለሰቦች የተያዙ የአክሲዮን ድርሻዎችን በተመለከተ ባለአክሲዮኖች መሸጥ በሚፈልጉበት በራሳቸው የሚያመጡትን የገዢ ማመልከቻ ተቀብሎ እና መርምሮ ለአጽዳቂ አካል ከማስተላለፍ ውጪ ገዢ እና ሻጭ የማገናኘትም ሆነ የማደራደር ሥራ እንደማይሰራ፣ ብሕራዊ ባንክ የሰነዶችና ማረጋገጫ ጽ/ቤት የሚያጣራውን የምዝገባ ሥርዓት ተጠሪ ባንክ በውክልና እንዲሰራ በመመሪያ በሰጠው የውክልና ሥልጣን መሰረት ተጠሪ ባንክም አቶ ስባጋዲስ ስዩም ከተባሉት የባንክ ባለአክሲዮን እና የአሁን አመልካች ተስማምተው በተጠሪ ጽ/ቤት በመቅረብ የአክሲዮን ዝውውር ማመልከቻ ቅጽ ሞልተው ለተጠሪ ባንክ ሲያቀርቡ የተቀበለ መሆኑን ገልጾ ተከራክሯል። ይህንን መከራከሪያ ብሕራዊ ባንክ ለባንኮች ታኅሳስ 20 ቀን 2001 ዓ/ም በቁጥር ሱዳ/ባሱመ/382/08 ካስተላለፈው መመሪያ አንጻር ተመልክተናል።
በዚህ መመሪያ በግልጽ እንደተቀመጠው የተጠሪ የሥራ ድርሻ የሰነዶች ማረጋገጫ ጽ/ቤት የሚያከናውነውን የማጣራት ሥራ በውክልና ማከናወን ነው። በመመሪያው የአክሲዮን ዝውውርን በተመለከተ በቁጥር 3 ሥር ከንዑስ ቁጥር 3.1.እስከ ንዑስ ቁጥር 3.6 የተቀመጠው ማናቸውም የአክሲዮን ዝውውር ማመልከቻዎች ለተጠሪ ባንክ በሚቀርቡበት ወቅት በተለይም በተራ ቁጥር 3.2 ላይ እንደተገለጸው የአክሲዮን ማኅበራቱ የአክሲዮን ዝውውር ጥያቄውን ተቀብለው በንግድ መዝገብ ላይ ከመመዝገባቸው እና ለ3ኛ ወገን ከማሳወቃቸው በፊት ማጣራት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎችን ማጣራት እና ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያለባቸው መሆኑን ነው።
በተያዘው ጉዳይ በአሁን አመልካች እና በአቶ ስባጋዲስ ስዩም መካከል ጥር 12 ቀን 2006 ዓ/ም የአክሲዮን ዝውውር ማመልከቻ ተፈርሞ ለአሁን ተጠሪ ባንክ ሲቀርብለት ሰነዱን ፈርሞ እና ማኅተም አድርጎ መቀበሉን ተጠሪ አይክድም። ተያይዞ ከቀረበልን የውሳኔ ግልባጭ እንደተመለከትነው የቀረበውን የአክሲዮን ዝውውር ማመልከቻን መሰረት በማድረግ ባንኩ ማጣሪያ ሲያደርግ የአክሲዮን ዝውውር እንዲደረግ የቀረበው የአቶ ስባጋዲስ ስዩም የአክሲዮን ድርሻ በ2004 ዓ/ም ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በተሰጠ እግድ ትዕዛዝ የታገደ መሆኑን ነው። የአሁን ተጠሪም ይህንን ለአመልካች ያሳወቀ መሆኑን ገልጾ ተከራክሯል። ይህንን የአሁን አመልካችም ክደው አልተከራከሩም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአክሲዮን ባለቤትነት የማጽደቅ ሥልጣን የጠቅላላ ጉባኤው እንጂ የተጠሪ ባንክ እንዳልሆነ በህግ የተደነገገ ነው። የአክሲዮን ባለቤትነት የሚመዘገበውም በጠቅላላ ጉባኤው ከፀደቀ በኃላ ነው። በዚህ ረገድ የተፈጸመ ስለመሆኑም አመልካች ያቀረቡት ማስረጃ የለም። የአመልካች መከራከሪያ መሰረት የሚያደርገው የአክሲዮን ዝውውር ማመልከቻውን ተጠሪ ተቀብሎ በራሱ ፊርማና ማኅተም አረጋግጧል የሚል ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የተነሳውን ክርክር በተመለከተ በሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ በግልጽ እንደሰፈረው አመልካችና አቶ ስባጋዲስ ሥዩም ተፈራርመው ያቀረቡት የአክሲዮን ዝውውር ማመልከቻ የተጠሪ ባንክ አክሲዮን ማህበር ማኅተም ያረፈበት ቢሆንም ይህ ሰነድ ግን በንግድ ህግ ቁጥር 331 /1/ እና 341 /2/ ሥር በአዛዥ ሁኔታ የተቀመጠውን በባለአክሲዮኖች መዝገብ የመመዝገብ ግድታን የሚተካ ወይም ቀሪ የሚያደርግ አይደለም፡፤ በአክሲዮን ዝውውር ማመልከቻ ሰነዱ ላይ ዝውውሩ ፀድቋል ወይም ተመዝግቧል መባሉ ብቻውን ተጠሪ በባለአክሲዮኖች መዝገብ አመልካችን በመመዝገብ ባለአክሲዮን አድርጓል የሚያስብል አይደለም። ስለሆነም ተጠሪ ለአመልካች የአክሲዮን ባለቤትነት ሰርተፊኬት ለመስጠት የሚገደድበት ህጋዊ ሁኔታ የለም በማለት በሥር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ ከላይ በአንደኛው ጭብጥ በዝርዝር እንደተገለጸው በተጠሪ አክሲዮን ማኅበር ውስጥ ባለድርሻ የሆኑት አቶ ስባጋዲስ ስዩም እና አመልካች ተፈራርመው ያቀረቡትን የአክሲዮን ዝውውር ማመልከቻን ተጠሪ ሲያጣራ ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በተጻፈው እግድ ምክንያት አክሲዮኑ ለልላ ሶስተኛ ወገን ላተላለፍ የማይችል በመሆኑ የማጣራት ሂደቱን ባለማለፉ ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ ባልተወሰነበትና ባልፀደቀበት፣ በንግድ ህጉ መሰረት ምዝገባ ባልተደረገበት እንዲሁም ክርክር የቀረበበት ገንዘብ ለተጠሪ ባንክ ስለመሰጠቱ ወይም ገቢ ስለመደረጉ ማረጋገጫ ባልቀረበበት አመልካች የጠየቁትን ክፍያ ተጠሪ የመክፈል ኃላፊነት የልለበት በመሆኑ ላከፍል አይገባም በማለት የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የወሰነውን ውሳኔ ስንመለከተው የሚነቀፍበት ምክንያት የልለው ሆኖ አግኝተነዋል።
ሲጠቃለልም የሥር ፍርድ ቤቶች ከላይ በዝርዝር የተገለጹትን መሰረታዊ ነገሮችን በአግባቡ በማጤን የሰጡት ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ባለመኖሩ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በኮ/መ/ቁ.228396 በ13/4/2008 ዓ/ም እንዲሁም የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ.176245 ጥር 1 ቀን 2009 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ በፍትሓብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ 348 /1/ መሰረት ፀንቷል።
ተጠሪ ለአመልካች የአክሲዮን ምስክር ወረቀት ላሰጥ አይገባም፤ አመልካች የጠየቁትን ክፍያ ተጠሪ ላከፍል አይገባም ተብሎ በተሰጠው ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም ተብሎ ተወስኗል።
የዚህን ችሎት ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይድረሳቸው።
መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.