በአዋጅ ቁ 515/1999 መሰረት በህመም ምክንያት ለ8 ወራት ፍቃድ ላሰጠው የሚገባ ሰራተኛ የ8 ወር ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት በህመም ምክንያት ወደ ስራ ለመመለስ ያልቻለ እንደሆነ የስራ ውሉ ላቋረጥ የሚገባ ስለመሆኑ፣ አዋጅ/ቁ 515/1999 አንቀጽ 79/1ለ፤/አንቀጽ 42/2/፣/3/ እና/5/
No summary available.
የሰ.መ.
ቀን 12/7/2010 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወል ሙስጠፋ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውሎስ አርሺሶ አመልካች- ሚሮና ኢንዳስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማ - ጠበቃ ታደሰ ገመቹ ቀርቧል ተጠሪ- ጫልቱ ዓለሙ፣ መሰረት አበራ፣ ብርቱካን ነገዎ እና አልማዝ አበበ - ቀርበዋል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዚህ ሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች ሚሮና ኢንዳስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማ ታህሳስ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ ታህሳስ 2 ቀን 2010 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታውን በማቅረቡ ነው። ቅሬታውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የሚቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ላታይልኝ ይገባል የሚለውን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ የስር ፍ/ቤት ከሳሾችና ተከሳሽ የተስማማንበት የምርት መጠን ከሳሾች መስራት አንደሚችሉና ልሎችም ሰራተኞች እየሰሩ ስለመሆኑ ተረጋግጦ ሳለ ተጠሪዎች ለመስራት እምቢተኛ በመሆናቸው የተሰናበቱ መሆኑ ስንብቱ ህጋዊ ሆኖ ሳለ ህገወጥ ስንብት ነው ሲል መወሰኑ ስህተት ነው። የስር ፍ/ቤት በከሳሾች ያልቀረበውን ክርክር ራሳቸው በማንሳት የሰጡት ውሳኔ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.182 ድንጋጌ ውጪ ነው። ከሳሾች እንዲሰሩ የተፈለገው ምርት መጠን በ3 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ብቻ የሚሰሩት ሆኖ እያለ ከአቅማቸው በላይ ነው ተብሎ ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቀ. 377/96 አንቀጽ 61(1) ውጪ መወሰኑ አለአግባብ በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው።
በስር ፍ/ቤት የነበረው ክርክር ከሳሽ የአሁን ተጠሪዎች ጫልቱ ዓለሙ፣ መሰረት አበራ፣ ብርቱካን ነገዎ እና አልማዝ አበበ በኦሮሚያ ብ/ክ/መ. የበረክ ወረደ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ተከሳሽ (የአሁን አመልካች) ሚሮና ኢንዳስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከሳሾች ካለጥፋታችን ጥር 29 ቀን 2009 ዓ/ም ከዚህ በፊት ሰርተን የማናውቀውን ከአቅማችን በላይ እንድንሰራ ሲነገረን ከአቅማችን በላይ ነው ስላልን ከስራ ያሰናበተን በመሆኑ ላከፈለን የሚገቡ ክፍያዎችን ይከፈለን ሲሉ ክስ መስርተዋል። ተከሳሽም ከሳሾች ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቀ. 377/96 አንቀጽ 27(1ረ) መሰረት ስራ ለመስራት ችሎታ እያላቸው የስራው ውጤት በብዛትና በጥራት ላይ ከተስማማነው በታች በመስራታቸው ካለማስጠንቀቅያ ተሰናብተዋል። ከሳሾች እንደ ድርጅቱ እቅድ የቦልጋም ምርት 8 ዙር ከሬሜላ 11 ዙር እንዲያመርቱ ተስማምተን ሲሰሩ ቆይተው በኋላ አንሰራም በማለታቸው ካለማስጠንቀቅያ መሰናበታቸው ህጋዊ ስንብት በመሆኑ ክሳቸው ውድቅ ይሁንልኝ በሚል መልስ ሰጥተዋል። የስር በኦሮሚያ ብ/ክ/መ. የበረክ ወረደ ፍ/ቤት አራት መዝገቦች የመ/ በአንድ በማጣመር የመረመረ መሆኑን ገልጾ በመ/ ላይ ሰኔ 8 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ ተከሳሽ ከሳሾች ቦልጋም 8 ዙር ከረሜላ 11 ዙር ሲያመርቱ ቆይተው አንሰራም በማለታቸው ምርት ቀንሶብናል ቢልም ከ2000 ዓ/ም እስከ 2006 ዓ/ም ባሉት ጊዜያት ከ4 እስከ 7 ዙር ምርት ስያመርቱ እንደነበር የተረጋገጠ እንጂ ምርት እየቀነሰ የመጣ አይደለም። ተከሳሽ ምርት ለመጨመር ከፈለገ ማሽንና ሰራተኛ በመጨመር እንጂ ባለው ሰራተኛ ከአቅም በላይ በማሰራት አይደለም።
ተከሳሽ ከሳሾችን ከአቅማችን በላይ ነው ስላሉ ብቻ ሳያረጋግጥ ከስራ ማሰናበቱ ህገወጥ ነው። ለከሳሾች ላከፍል ይገባል ያለውን በማስላት እንዲከፈላቸው ወስኗል። ከሳሽ የአሁን አመልካች ለፊንፊኔ ዙርያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርቦ የፊንፊኔ ዙርያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ አከራክሮ መስከረም 25 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ አሰሪው ማምረት ያለበት ምርት ኮታ ማውጣት፣ ለማምረት የሚያግዙ ዘመናዊ መሳሪያዎችን ማመቻቸት ብቻ ሳይሆን ከሚፈለገው ምርት ጥራትና መጠን በታች የሚሰራ ሰው ካለ የተለያዩ ስልጠና በመስጠት ምርታማነት መጨመር እያለበት ልሎች ቡድን ስላመረቱ ብቻ ከሳሾችም ማምረት አለባቸው በሚል ከከሳሾች የቀረበውን ሀሳብ ባለመቀበል ከሳሾችን ከስራ ማሰናበቱ ህገወጥ የስራ ስንብት ነው መባሉ ባግባቡ ሲሆን ከሳሾች ሁሉም የጡረታ ዋስትና ተጠቃሚ መሆናቸው ተረጋግጦና ከሳሾችም ያልካዱ ሆኖ እያለ የአገልግሎት ክፍያ እንዲከፈላቸው መወሰኑ ስህተት ነው ሲል የስር ፍ/ቤት ውሳኔን በማሻሻል ክፍያውን አስተካክሎ ወስኗል። ተከሳሽ የአሁን አመልካች ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታውን አቅርቦ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ አከራክሮ ታህሳስ 2 ቀን 2010 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ ከሳሾች ተከሳሽ እንደሚለው 8 ዙር ቦልጋም እና 11 ዙር ከረሜላ ሰርተው እንደማያውቁ እየተከራከሩ ሲሆን በስር ፍ/ቤትም የተሰሙት የግራ ቀኙ ምስክሮች ይህንኑ ገልጸዋል። በመሆኑም ተከሳሽ ከሳሾችን ከአቅማቸው በታች ሰርተዋል በማለት ከስራ ማሰናበቱ ማስረጃ ያልተደገፈና የህግ ድጋፍ የልለው ነው። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት አይደለም ሲል የስር ፍ/ቤት ውሳኔ በማጽናት ወስኗል።
የአሁን አመልካችም ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርበዋል። መዝገቡም ተመርምሮ ተጠሪዎች በመደበኛ የስራ ሰዓታቸው ምርቱን በማሳደግ እንዲሰሩ በአመልካች የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ከአቅማችን በላይ ነው በማለት ለመስራት ፍቃደኛ አለመሆናቸው በተረጋገጠበት ሁኔታ የስር ፍ/ቤት ስንብቱ ህገ ወጥ ነው በማለት የወሰኑበት አግባብ ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቀ. 377/96 አንቀጽ 13(2) እና 27(1) አንጻር ለመመርመር ሲባል ቀርቧል። መልስና የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል። ተጠሪዎች ጥር 4 ቀን 2010 ዓ/ም በተጻፈ መልስ የስር ፍ/ቤት ያቀረብነውን ክስ በማስረጃ አጣርቶ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቀ. 377/96 መሰረት ተተርጉሞ የሰጠው ውሳኔ በመሆኑ ስህተት ያለበት አይደለም የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ይጽናልን ሲሉ ተከራክረዋል።
አመልካችም ጥር 24 ቀን 2010 ዓ/ም በተጻፈ የመልስ መልስ አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል፣ እኛም የቀረበውን አቤቱታ፣ መልስ እና የመልስ መልሱን እንዲሁም የስር ፍርድ ቤት ውሣኔዎችን እና ከጉዳዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል። እንደመረመርነውም በስር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች ተጠሪዎች እንዲሰሩ የሚፈልገውን 8 ዙር ቦልጋም እና 11 ዙር ከረሜላ መጠንና ጥራት ምርት ካሁን በፊት ተጠሪዎች አምርተው እንደማያውቁ እንድያውም የምርት መጠኑን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻሻሉ የመጡ መሆኑ ተረጋግጧል። የአሁን አመልካች ተጠሪዎች ይህን 8 ዙር ቦልጋም እና 11 ዙር ከረሜላ መጠንና ጥራት ምርት ማምረት ስለመቻላቸው በማስረጃ አላረጋገጠም። ሰራተኞች በሙሉ እውቀታቸውና ብቃታቸው ሰርተውም እኩል የምርት ጥራትና መጠን ያመርታሉ ተብሎ አይታሰብም። አንደኛው ሰራተኛ ባመረተው ምርት መጠንና ጥራት መነሻነት ልላውን ከአቅም በታች ሰርቷል ለማለት በቂ መሰፈርት አይሆንም ። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪዎች ከአቅማቸው በታች መስራታቸው ባለማረጋገጡና ባላቸው እውቀትና ብቃት እያመረቱ ካለው ምርት በላይ እንዲያመርቱ በመጠየቃቸው እንዲያመርቱ የተጠየቁትን ምርት ለማምረት የሚቸገሩ መሆኑን በማሳወቃቸው የአሁን አመልካች ከስራ ያሰናበታቸው መሆኑ ህገወጥ የስራ ስንብት እንደሆነ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኝም።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ ታህሳስ 2 ቀን 2010 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ።
ታህሳስ 17 ቀን 2010 ዓ/ም በዋለው ችሎት የበረህ ወረዳ ፍ/ቤት የአፈጻጸም መ/ የተሰጠው እግድ ተነስቷል። ይጻፍ።
የስር ፍ/ቤት እንዲያውቁት የዚህ ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ ይድረሳቸው ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.